ማህበረ ቅዱሳንና የተሐድሶ ነገር ለተስፋ የተሰጠ መልስ አዲሱ ተስፋዬ መንግሰቱ ለደጀ ሰላም
ቅዳሜ ጃንዋሪ ስምንት ተስፋ የተባሉ ደራሲ አቦጊዳ እና ኢትዮጲያን ሪቪው በተባሉ ድረ ገፆች ላይ “ማህበረ ቅዱሳንና የ ኢትዮጲያ ቤ/ክ ተሐድሶ ያስፈልጋታል የሚሉ ተሐድሶዎች” በሚል ርዕስ እጅግ አስቂኝ ፅሁፍ አውጥተዋል። ተስፋ እንደተለመደው እውነቱን ሀሰት፣ውሸቱን ደግሞ እውነት እያሉ ስለ ማህበረ ቅዱሳንና ተሐድሶ አዲስ ታሪክ እየደረሱ ናቸው።በዚሁ ፅሁፋቸው የቻሉትን ያህል ማህበረ ቅዱሳንን ጥላሼት ከቀቡ በሁዋላ፣ ስለ ተሐድሶም “ምሁርነትና ደግነት” ለማሳመን ብዙ ዳክረዋል።
ለመሆኑ ተሃድሶዎች እነማን ናቸው? እውነት ተስፋ እንደሚሉን ይሆኑን? ግጭታቸውስ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ነውን? ዋነው አላማቸውስ ምንድነው?
እነሆ ለተስፋ ና ለመሰሎቻቸው።
ተሐድሶዎች እነማን ናቸው ? እምነታቸውስ ምንድነው ?
በመሰረቱ “ተሀድሶዎች ማናቸው? “ ብሎ ለሚጠይቅ ሰው ትክክለኛ መልሱ አንድ ነው ። ይሄውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ወደ ሉተር ካምፕ ለመቀየር በቤተ ክርስትያንን ውስጥ ገብተው ቤተክርስትያንን የሚያውኩ የጥፋት( የኑፋቄ) መልእክተኞች ናቸው።የሚያምኑት እምነትም ከፕሮቴስታንት ዶክትሪን ጋር ምንም ለውጥ እንደሌለው ዋፒዲያ የተባለው ድረ ገጽ እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል።
“According to its followers, the Ethiopian Orthodox Tehadeso Church (Amharic የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተሃድሶ ቤተክርስትያን) …Since most of its members were former traditional Orthodox, some believe this reformed form of Orthodox will mend relationships between Orthodox Christians and P’ent’ay Christians in Ethiopia… Yet their beliefs resemble that of the different Ethiopian P’ent’ay churches, the Pentecostal and evangelical churches found in the country.”
ይህ የተሃድሶ እንቅስቃሴ የተጠነሰሰውም ሆነ የሚመራው በተለያየ ግዜ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን በመዳፋችው ለማስገባት ሲጥሩ በነበሩ በውጭ ሚሲዮናውያን ነው። Brian L.Fargher የተባለው ሚሲዮናዊ “origins of new church movement in Southern Ethiopia” በተባለው መፅሀፉ ላይ አፄ ሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግሰት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የነበሩ ሚሲዮናውአንን ሀሳብ ይህን ይመስል እንደነበረ ይነግረናል
“Expatriate missions recognized that the potential for two pronged ministry existed in Ethiopia. The Challenge of Abyssinia is double one: to give the Christian message to the non Christian Abyssinian and to revive the Abyssinian church. ..Others felt that movement of reform existed and these should be strengthened….missionaries spoke of strengthening movements of reform among the orthodox …”
ተሀድሶ በዘመነ አጤ ሃይለስላሴ
ብቻቸውን ይህን ሴራ ለማከናወን እንደማይችሉ የተረዱት ሚሲዮናውያኑም አላማቸውን ለማስፈጸምም ኢትዮጵያውያንን ማጥመድ ጀመሩ።ዴቪድ ስቶክ የተባለ ሚሲዮናዊ ሰባኪ መምህር ስብሀት ለአብን አባብሎ አባብሎ ቀለበቱ ውስጥ አስገባቸው። ስዊድናዊያን ሚሲዮኖችም ዘመንፈስ ቅዱስ አብርሃ የተባሉ አነስተኛ የቤተ ክህነት እውቀት አላቸውን ሰው በመቅረብ ማተባቸውን አስበጠሱ።በነኚህም ሰዎች አማካኝነት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ማደስ የሚል ስውር አላማቸውን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ ።
በመካነ ኢየሱስ ቤ/ን አባል የሆኑትና የመሰረት ስብሀት ለአብን የህይወት ታሪክ የጻፉት ዶክትር ድርሻዬ መንበሩ መሰረት ለሰሩት ክህደት እንዲህ ሲሉ አሞግሰዋቸዋል።
“On January 14, 1996, Aleqa Meseret died. He is considered a great reformer of the EOC after Abba Estifanos of the 15th century who was persecuted and killed by Aºe Zära Yaqob (1434-1468) in Debre Berhan”
መሰረት ስብሐት ስብሀት ለአብ ጮራ የተባለውን የኑፋቄ መጽሐፍ የሚያሳትመው ማህበረ በኩርም መስራች ነበሩ።
He was the founder of an association called Mahbere Bekure (Association of the First-Born) which has an ongoing magazine called Chorra (Light). Many of his publications and teachings come in this magazine continuously
በዚያን ዘመን ቤተክርስትያን ካልታደሰች ብለው የሚሲዮናውያንን መልክተኟ በመሆን ቤተክርስትያንን ሲያውኩ ነበሩት ሌላው ቀንደኛ መናፍቅ ዘመንፈስ ቅዱስ አብርሃ ናቸው። ነጋዴው ዘመንፈስ ቅዱስ አብርሃ ዓውደ ነገስት የተባለውን የጥንቆላ መጽሃፍ ለመጀመርያ ግዜ በማሳተም ጥንቆላ እንዲስፋፋ ማድረጋቸው ሳያንሳቸው፡ ተግሳፅና ምክር የተባለ የኑፋቄ መፅሀፋቸውን በሚሲዮናውያን ድጋፍ አሳተሙ ።ይሀው መጽሀፍ ቤተክርስትያን የሉተርን አስተምህሮ በመቀበል እንድትታደስ የሚቀሰቅስ ስድብና ከፍተኛ ድፍረት ፡እቡይነት የታካተተበት መፅሀፍ ነበረ።
በቤተክርስትያን ላይ የተቃጣው ይህ ድፍረት እረፍት ያሳጣቸው የኢትዮጵያውያ ቤ/ን ሊቃውንት በዘመንፈስ ቅዱስ ብእር የተሰየመውን ይህን የሚሲዮናውያን መርዝ ማምከን ጀመሩ። ስመ ገናናው ሊቅ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ተግሳፅና ምክር ለተባለው የዘመንፈስ የኑፋቄ ድርሰት ፣ ኮክህ ሃይማኖት የተባለ ድንቅ የመልስ መጽሀፍ አሳትመው የዘመንፈስን ኑፋቄና የተሀድሶ ግርግር አስተነፈሱት ።
ሁኔታው እንዳልተሳካላቸው አወቁት ዘመንፈስ ቅዱስና መሰረት ስብሀት ለአብ ወደ አሰማሪዎቻቸው የፕሮቴስታንት ( መካነ ኢየሱስን) በይፋ ተቀላቀሉ ።አሰማሪዎቻቸውም በክብር ተቀበሉዋቸው።
ተሀድሶ በዘመነ ደርግና ኢህአዴግ
የደርግ መንግስት መውደቁን የገመቱት ሚሲዮናውያን በ 1980ዎቹ ላይ እንደገና የተሀድሶን ነገር መቀስቀስ ጀመሩ። ለዚህም አላማቸው ማስፈፀሚያ የሚውሉ መልክተኞችን ሃይማኖተ አበው ይባል ከነበረው ማህበርና ሌሎች መመልመል ጀመሩ ።ወዲያው ሚሲዮናውያኑ ከያሉበት ሆነው የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ማዋረድና መሳደብ ጀመሩ።
“ሕልምና ራዕይ ጌታ ገለፀልን ።የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን መታደስ አለባት ።መንግሰትም ይሄንን ካላስፈፀመ መቅሰፍት ያገኘዋል” በማለት የኢትዮጵያ(ኢህአዴግ) ባለስልጣናትን ማስፈራራት ደረጃ ደረሱ። ፓስተር ጆናታን ሀንሰን ተባለው አሜሪካዊ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለነበሩት ታምራት ላይኔና ለፕሬዝዳንቱ “እንዲህ የሚል ራእይ ጌታ ገለፀልኝ “ በማለት ይህንን ዘግናኝ ደብዳቤን እስከመጻፍ ደረሰ
“Your previous government slept with the prostitute of death then; the current government is also sleeping with this Angel of Death. Both governments listened and took her advice. God has warned this present government to break away from her or it will die too; that the next government will continue to sleep, eat and drink with this same prostitute and together they will join others in going against Israel. The prostitute is the Ethiopian Orthodox Church.”… You courted the prostitute then; you’ve courted the prostitute now. Is it not the same prostitute who gave you AIDS (death) then? It is the same prostitute that will also give you AIDS (death) now. Remove yourself from the prostitute if you want to live .The prostitute is the Ethiopian Orthodox Church!”
“የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሴተኛ አዳሪ ናት። ቀድሞ ከዚህች ዘማዊ ጋር ተዳራችሁ፡አሁንም እየተዳራችሁ ነው፡ ይህች ዘማዊ ኤድስን ( ሞትን) ሰጠቻችሁ።ለመኖር ከፈለጋችሁ ከዚህች ቤተክርስትያን ራሳችሁን ለዩ…“የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሴተኛ አዳሪ ናት..”
ሚሲዮናዊያኑ የመንግሰትን ባለስልጣናት እንዲህ እያሉ ሲያደናግሩ ፣ የነዚሁ ሚሲዮናውያን መልእክተኛ የሆኑ አንዳንድ ከሀዲ የኢትዮጵያ ልጆችም “ራእይ ታየን፡ ጌታ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን መታደስ አለባት ብሏል “ እያሉ ቤተክርስትያንን ማመስ ጀመሩ ።
ለዚህም አብነት በናዝሬት ከተማ ሆኖ ይህንን የተሀድሶ እንቅስቃሴ ይመራ ከነበረው ግለሰብ ውስጥ አንዱ (ፓስትር ሆኖ ፕሮቴስታንት ጎራን ከተቀላቀለ በሁዋላ) በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ ሬዲዮ መክሊት ለተባለው የመናፍቃን ሬድዮ ጣብያ እንዲህ ሲል ያብራራል
“ ተሃድሶ የሚል የ እግዚአብሄር መንፈስ (መንፈስ ቅዱስ )ራእይ ሰጠኝ።ደጋግሞ እግዚአብሄር ይናገረኝ ጀመር።በህይወቴ የሚናገረኝ ቃል አንድ ነው።…ተሃድሶ ይለኛል።ደጋግሞ የ እግዚአብሄር መንፈስ የተሀድሶን አገልግሎት እንድጀምር መንፈስ ቅዱስ አነሳሳኝ።
ዻንኤል በናዝሬት በሀረር እና በመሳሰሉት ቦታዎች ምእመናንን ከቤተክርስትያን ለማስኮብለል በከፍተኛ ሁኔታ ዘመተ።ይህንንም የክህደት ስራ ፓስተር ዊሊያም ብላክ እኝዲህ ሲል ዘግቦታል
“የሚሲዎኖቹ ዓላማም እነዚህን መሪዎች ከተዋሕዶም ሆነ ከተሀድሶ በማስወጣት የራሳቸውን የባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን እንዲመሰርቱ ማድረግ ነው። ማታልል በክርስቶስ ስምም ቢሆን ማታለል ነው። ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ታክቲክ በመላው ኢትየጵያ እየተስፋፋ ነው።”
የዚሁ የጥፋት ቡድን በሰሜን ኢትዮጵያ ቤትክርስትያንን ለማፈራረስ የተተቀመው ስልት ደግሞ ለየት ያለ ነበር።ጥንት የሞተውን የቅባትን ትምህርት በመቀስቀስ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅባት ቤተክርስትያን” የሚል ቤተ ክርሰትያን በመመስረት ቤተ ክርስትያንን ለሁለት ለመከፋፋል እነ ጥላሁን የረቀቀ ሴራ ጀመሩ።ጉንደ ወይን ማርያም ቤተክርስትያን( ምስራቅ ጎጃም) ያሉ አንዳንድ ግለሰቦችንም ለማታልለ ቢሞክሩም ፣የማህበረ ቅዱሳን የምስራቅ ጎጃም ንዑስ ማዕከል፣የተዋህዶ አባቶችና ምእመናን ባደረጉት ትጋት ይህም የተሀድሶ ሴራ ፈረሰ።
ኦርቶ ጴንጤ የሚሉት ተሀድሶ መሪ የነበረው ዳንኤል አለማየሁ፣ ጥላሁንና ሌሎችም ሁኔታው እንደተነቃባቸው በማወቃቸው ልክ እንደ ቀደምት አባቶቻቸው ዘመንፈስና ስብሀት ለአብ መጀመርያውኑለዚሁ ስራ ወዳሰማራቻቸው ፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ተቀላቀሉ። ዳንኤልም ፓስተር ሚል ማረግ ተሸለመ። ሌሎቹም የኢትዮጵያ ቤተክርስትያንን በማፍረስ ላደረጉት አስተዋፅዎ የተለያዩ ሽልማቶችን ተቀበሉ።
የማህበረ ቅዱሳንንና የተሀድሶ መራር ጦርነት
የተሀድሶ አራማጆች በቤተክርስትያን ላይ እንክርዳድ እየዘሩና መሆኑን የተረዱ የተዋህዶ አካላት ከተሃድሶ ጋር መራር ጦርነት ገጠሙ። በተለይም ማህበረ ቅዱሳን እነዚህ በግ መሰል ተኩላዎች ቤተክርስትያን ላይ እያደረሱ ያለውን ጉዳትና ኑፋቄያቸውን በመረጃ በማስደገፍ ለሲኖዶስ በማቅረቡና ሲኖዶስም እነዚህን መናፍቃንን ከቤተክርስትያን አውግዞ በማግለሉ የተሃድሶ አከርካሪ ተሰበረ።ይህ ለተዋህዶ ልጆች ያስደሰተ ቢሆንም ተሀድሶና ደጋፊዎቻቸው ግን መራር ነበር። ማህበረ ቅዱሳንን ካላጠፉ ቤተክርስትያንን ማወክ እንደማይችሉ የተገነዘቡት ተሃድሶዎችና የውስጥ አርበኞቻቸው ፣ ማህበረ ቅዱሳንን በተቻላቸው አቅም ማዳከም፣ ስም ማጥፋትና ከቻሉም ለማፈራረስ ዋናው አጀንዳቸው አድርገው መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፤ እነሆ ዛሬም ማህበረ ቅዱሳን ላይ ያነጣጠሩ ዘመቻዎች መነሻቸው ይሄ ነው። ቃላት የሚአስታወከው ተስፋም፣ ስድብ ከታቢው ሙሌጌታም ፣ምላሱን ለስድብና ርግማን ያስረዘመው በጋሻውም፣ የክፍለዘመኑ ቂላቂል መናፍቅ “ ቀሲስ” አስተራየም የዚህ መረብ አባላት እንደሆኑ መገመቱ ብዙ ምርምር አ ይጠይቅም ።
ይቆየን
( ይቀጥላል)