“ከሰማይ የሚወርዱ ጥቃቅን የእሳት ፍንጣሪ መሰል ነገሮች” የሣር ክዳን ቤቶችን እና የተለያዩ ስፍራዎችን አቃጠሉ
| እሳት ወይስ እሳተ እሳት |
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 5/2010፤ ታኅሣሥ 27/2003ዓ.ም)፦ በፊቱ የቀረበለትን ሁሉ የሚያቃጥል – ከሰል፣ ዐመድ፣ ዕመት የሚያደርግ – የሚፋጅ፣ የሚልጥ፣ የሚለመጥጥ ነው ባሕርይው – የዚህ ዓለም እሳት፡፡ እሳቱን የሚያስቆጡት እና የሚያገኑት ነዳድያት እሳታውያንን ሲያገኝ ደግሞ ላንቃው፣ ልሳኑ፣ ወላፈኑ በዝቶ ነበልባለ እሳት(ነደ እሳት) ይሆናል፤‹‹እሳት በላዒ ለዐማፅያን›› እንዲሉ፡፡ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ግራዋ ወረዳ ልዩ ስሙ ታቱ ጀነታ እየተባለ በሚታወቀው ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት የታየው ግን ከዚህ የእሳት ባሕርይ በመጠኑ የተለየ ነበር፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)