በቅርቡ ለሚካሄደው የኦሮሞ ልማት ማኅበር (ኦልማ) የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ገንዘብ ሊያዋጡ የሚችሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በመለየት ላይ ናቸው
(ሙሉ ገ)
የኦህዴድ ካድሬዎች በቅርቡ ለሚካሄደው የኦሮሞ ልማት ማኅበር (ኦልማ) የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ገንዘብ ሊለግሱ የሚችሉ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በደረጃ በመለየት ላይ ናቸው።
ካድሬዎቹ ገንዘብ ሊለግሱ የሚችሉ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በደረጃ በመለየትና ገንዘብ ሊሰባሰብባቸው የሚችሉባቸውን መንገዶች በመለየት ላይ ናቸው ብለዋል የአዲስ ነገር ምንጮች። የኢህአዴግ ግንባር ፓርቲ ካድሬዎች እና የአጋር ፓርቲዎች አባላት አጋዥና ድጋፍ ሰጪ ሥራዎችን እየሰሩ ነው።
የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅቱን በበላይነት የሚመራውና የሚያካሂደው ኦህዴድ – ኢህአዴግ ነው። የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በ2001 ዓ.ም ጀምሮት የነበረውን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በ2002 አጠናቋል። የጉራጌ ልማት ማኅበር (ጉልማ) በ2002 ዓ.ም የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅቱን አካሂዷል ። “ጊዜው የኦሮሞ ልማት ማኅበር (ኦልማ) ነው “ብለዋል ምንጩ፡፡
በቅርቡ የአዲስ አበባ መስተዳድር በከተማዋ እድሮች ለ”ልማት” በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ ኮታ መጣሉ ይታወሳል።