በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረው ግጭት ጉዳቱ ከባድ መሆኑ ተጠቆመሆኖም ግጭቱን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድና ኦሮሚያን ወደ ነበረችበት የመመለስ ሥራ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በግጭቱ ምክንያት ከባድ ጉዳት መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡ የደረሰውን የጉዳት መጠን አስመልክቶ ከመንግሥት እስካሁን ይፋዊ መግለጫ ባይሰጥም፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች …

በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረው ግጭት ጉዳቱ ከባድ መሆኑ ተጠቆመ Read more »

የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ መደረጉን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ እጁ፣ እግሩና ጆሮው ላይ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም ህክምና እንዳያገኝ መደረጉን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን በማዕከላዊ እጁን ታስሮና …

የፀረ ሽብር አዋጁ በወጣ በወራት ውስጥ ከታሰሩት ፖለቲከኞች አንዱ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር ህክምና እንዳያገኝ መደረጉ ተገለፀ Read more »

የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ስላለ የወሰደውን 100 ሺሕ ሔክታር፣ መጋዘን፣ የሠራተኞች ተገጣጣሚ ቤትን ለጨረታ ቢያቀርብም እስካሁን በሃራጅ ተሽጦ ባንኩ ሊያገኘው የቻለው 2.6 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። የካሩቱሪ ዳይሬክተር ራማክሪሽና ካሩቱሪ ለ100 ሺህ ሔክታር ሊዝ መሬት አንድ ጊዜ የሚከፈል 5.6 ሚሊዮን ዶላር በባንክ እንዳይከፍል ታዞ በጥሬ ገንዘብ ጉዳዩ […]

በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ፣ በጉጂ ዞን፣ በሃርቀሎ ወረዳና በሆሮ ጉዱሩ፤ በወለጋ ኢበንቱ ወረዳ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸውና በመከላከያ አባላት እየታሠሩ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡

ታኀሳስ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአሁን በፊት የባህርዳር ነዋሪዎች ባህርዳር ላይ የሚገኘው የአባይ ድልድይ ችግር አጋጥሞታል በማለት በልዩ ልዩ ስብሰባዎች ቢያሳስቡም የገዢው መንግስት አመራሮች በቅርቡ ተለዋጭ ይሰራል በማለት ሲሸነግሉ ቆይተዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የድልድዩ ወደ ሰሜን መውጫ ክፍል ላይ ያለው ንጣፍ ዝቅ እያለ በመሄዱ ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ በቦታው የፌደራልና …

አኩሪ አተርን በተለያየ መንገድ ለምግብነት በርካቶች ይጠቀሙበታል። ከምሥራቅ እስያ አካባቢ መገኘቱ የሚገርለት ይህ የእህል ዘር በፕሮቲን የበለፀገ በመሆኑ ለተለያዩ የተመጣጠኑ ምግቦች ዝግጅት ሲዉል ዓመታት ተቆጥረዋል።

በሰሜን ጎንደር የጭልጋ የቋራ እና የመተማ ሕዝብ እርቀ ሰላም ባለው ወያኔ ላይ ተቃውሞውን ቀጥሏል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Gonder‬ ‪#‎Ethiopiaprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ በሚከተለው የጎሳ ፖለቲካ በሕዝቦች መሃል ግጭትን እየፈጠረ እንደሆነ እና ታሪካዊ የኢትዮጵያ መሬቶች ለሱዳን ለመስጠት መስማማቱን …

በሰሜን ጎንደር የጭልጋ የቋራ እና የመተማ ሕዝብ እርቀ ሰላም ባለው ወያኔ ላይ ተቃውሞውን ቀጥሏል:: Read more »

ለነጻነታቸው በሚያደርጉት ትግል፣ ኢትዮጵያ እንደ እናት ሆና የረዳቻቸዉ ፣ እንደ ጋና፣ ታንዛኒያና ሴኔጋል ያሉ የአፍሪካ አገሮች እንኩዋን ሳይቀሩ የትናየት በደረሱበት ዘመን፣ እንደ ደርግ ዘመን አሁንም በኢትዮጵያ፣ ረሃብና ችጋር የሚገድለን አልበቃ ብሎ፣ ኢትዮጵያዉያን በኢትዮጵያዉያን እጅ እየተገደሉ ነው። በቅርቡ በጎንደር እና በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎቸ እንዳየነው፣ በዜጎች ላይ የደረሰው ግድያ፣ ድብደባና ግፍ እጅግ በጣም ልቤን እንዳደማው መግለጽ እወዳለሁ። […]

The post ግፍ ሲፈጸም ዝምታን ከመረጥን እንደ አገር እንጠፋለን -ሃብታሙ አያሌው appeared first on ሳተናው .

የጂቡቲ የጸጥታ ሃይሎች ዛሬ በአንድ ሀይማኖታዊ ኩነት ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሶማልኛ አገልግሎት ተናግረዋል።

የጸጥታ ሃይሎቹ ሃይማኖታዊው ኩነት እንዳይካሄድ ያስጠነቀቁ ቢሆንም አዘጋጆቹ ችላ እንዳሉትና ሟቹ ሃይማኖታዊ መሪ ሼኽ ዮኒስ ሙሴን ለማሰብ እንደተሰባሰቡ ምንጮች ጠቁመዋል።

የጸጥታ ሃይሎቹ የተሰባሰቡትን ሰዎች ለመበተን ሞክረው እንደነበር ጂቡቲ ያሉት ጋዜጠኞችና እማኞች ተናግረዋል። በሀገሪቱ ያለ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ቢያንስ ሁለት ሰዎች እንደተገድሉ ዘግቧል። ሌሎች ምንጮች ደግሞ ከዛ የበዛ ነው ይላሉ።

የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

 

የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላንን ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል በርካታ ወረዳዎችና ከተሞች  እያቀረቡት ያለው ሠላማዊ ጥያቄ በሰከነ መንገድ መልስ ለመስጠት ከመሞከር ይልቅ ተመጣጣኝ ያልሆነ ሀይል በመጠቀም ጥያቄውን ለማፈን እየተሞከረ ነው፡፡ በዚህ ሂደትም ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ለቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎችም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ሰሞኑን ከሚወጡት መግለጫዎችና የመንግስት ባለስልጣናት ቃለመጠይቆች እንደተረዳነው  ጥያቄዎቻቸውን በሃይል ለመመከት ከመዛትና ዜጎችን ከሰው በታች አውርዶ ቁጣን በሚጋብዝ መልኩ ከመጥራት በዘለለ ሀላፊነት እንደሚሰማው አካል ለችግሩ መፍትሔ  ለመፈለግ ዝግጁነት እንደሌለ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሁሌም እንዲከበር የምንጠይቀውን የሀገሪቱ ሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነውን ሕገ-መንግስት የሚጻረር ነው፡፡

በዚህ ሂደት በጥቂቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሕገ-መንግስቱ አንቀጾች ተጥሰዋል

1.    የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 15 የሕይወት መብት

‹‹ማንኛውም ሰውበሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነበስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› ቢልም ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ8 ዓመት ልጅ አንስቶ እስከ የ80 ዓመት አዛውንት ድረስ ሕይወት እየተቀጠፈ ነው፤ እስከዛሬ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በሶስተኛ ወገን ማረጋገጥ ባይቻልም ጉዳዬን  በቅርበት የሚከታሉ ሰዎች እንደዘግቡት ወደ መቶ እየተጠጋ ይገኛል፡፡

2.   የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 15 የአካል ደኅንነት መብት

‹‹ማንኛውም ሰውበአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስየመጠበቅ መብት አለው፡፡ ›› አሁንም ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ በጥይት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ ድብደባ እና አላግባብ አንግልት የደረሰባቸውንም ቤት ይቁጠራቸው፡፡

3.   አንቀጽ 24.1 የክብርና የመልካም ስም መብት

‹‹ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው፡፡ ›› እየሆነ ያለው ዜጎችን አጋንንት እያሉ መጥራት፣ ጥፋተኛ ተብለው በሕግ ያልተፈረደባቸውን አሸባሪ እያሉ ክብራቸውን በሚዲያ መግፈፍ ነው፡፡

4.   አንቀጽ 30.1 የመሰብሰብ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት

‹‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በሕዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ወይም በመካሔድ ላይ ያለ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምን፣ ዴሞክራሲያዊ መብቶችንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ፡፡ ››  ቢልም መንግስት ይህን የህገ መንግሰቱን አንቀጽ በመጣስ ብዙ ሰብዓዊ ጉዳቶችን አድርሷል፡፡

ዜጎች ለመረጃ ቅርብ በሆኑበት በዚህ ጊዜ መንግስት እያደረጋቸው ያሉትን ተግባራት መካድ፣ እንዲሁም እንደሌሉ አደርጎ ለማስተባበል መሞከር ብዙ ኃላፊነት የሚጠበቅበት መንግስት የሚያሰገምትና ትዝብት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ይህ የመንግስት ግዴለሽነት ብዙኃን ዜጎችን እየገፋ ከመስመር እያስወጣ ነው፡፡ ሰላማዊውን የሕዝብ እንቅስቃሴ ወደ አመጽ እና ወደአልተፈለገ ዕልቂት ከመግፋት ይልቅ የተቀናጀ የጋር ማስተር ፕላኑን  መሰረዝ፣ በዚህ ሒደት ጥፋት የፈጸሙ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትን ለፍርድ ማቅረብ፣ የግል ተበዳዮችን  መካስና ሌሎች አስፈላጊ የመፍትሔ እርምጃዎችን ሁሉ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡  ሁልጊዜም እንደምንለው በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄ ማቅረብ ወንጀል አይደለም፡፡  መንግሰት በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ከሚጠይቁ ዜጎች ጋር እልህ አይጋባ ፣ ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸው ይከበሩ ፣ የመብት ጥሰት ድብደባ እና ግድያው ይቁም፡፡  ሕገ-መንግስታዊነት የታሰርንለት፣ ከሀገር የተሰደድንለት፣ ብዙ ዋጋ የከፈልንበትና አሁንም እየከፈልንበት ያለ ዐሳብ ነውና  በሀገሪቱ ህጋዊነት እንዲሰፍን ህይወታቸውን እስከመስጠት ድረስ ዋጋ ለከፈሉ ዜጎች ክብር እንሰጣለን፡፡ ለሕገ መንግስታዊ ስርዓት መስፈን ዜጎች የከፈሉት ዋጋ እጅግ ብዙ እና ከበቂ በላይ ነውና ተጨማሪ ሰብዓዊ ዋጋ መክፈል ሳያፈልገን ሕገ መንግስቱ እንዲከበር አንጠይቃለን፡፡


ሕገ-መንግስቱ ይከበር!  

በኢትዮጵያ ሱዳን የድንበር መካለል ላይ በሃገር መሸጥ የተሳተፈ ይሁን የደገፈ ከተጠያቂነት አያመልጥም:: ‪ Minilik Salsawi – ለሕዝብ እልቂት የመሪነት ሚና የሚጫወተው ሕወሓት ሸምጥጦ ቢክድም የወያኔው አሻንጉሊት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ማካለል ከሱዳኑ መሪ በሽር ጋር …

በኢትዮጵያ ሱዳን የድንበር መካለል ላይ በሃገር መሸጥ የተሳተፈ ይሁን የደገፈ ከተጠያቂነት አያመልጥም:: ‪ Read more »

በጎጃም ማንኩሳ መሬታችንን አንለቅም ያሉ ግለሰቦችን ንብረት በእሳት አነደደው።በቃጠሎው ከፍተኛ ንብረት የወደመ ሲሆን የአካባቢውን ማህበረሰብ በእጅጉ አስቆጥቶ ለአመፅ አስነስቷቸሗል።ይህንን ቃጠሎ የወያኔ አሽከር በመሆን በዋናነት የፈፀሙት ኮማንደር ሽታሁን እና ደሳለኝ በእውቀት የተባሉ የወያኔ አመራሮች መሆናቸው ታውቋል። እንደሚታወቀው ወያኔ በትላልቅ ከተሞች የሚፈልገውን …

የወያኔ ቡድን የማንኩሳ ነዋሪዎችን ንብረት በእሳት አነደደ። Read more »

ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው የአስተዳደር ብልሹነት፣ የህዝቦች ኑሮ መዘበራረቅና ዓላማ-ቢስ መሆን፣ እንዲያም ሲል በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ አሳቦ ርስ በርሱ እንዲጠላላ ማድረግና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ወደ ርስ በርስ መተላለቅ እንዲያመራ መንገዱን ማዘጋጀት፣ በተራ አነጋገር ከመልካም …

ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል ዘዴ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል- የመጨረሻ መጨረሻም አገርን ያወድማል! በፈቃዱ በቀለ፣ ዶ/ር Read more »

ከአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ መንግስት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም የኢትዮዺያ ሙስሊሞች አንድነት ማህበር መግለጫ አወጣ ። በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው የኢትዮዺያ ሙስሊሞች አንድነት ማህበር ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የኢህአዴግ መንግስት በዜጎች ላይ እየወሰደ ያለውን የኃይል …

ከአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ መንግስት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም የኢትዮዺያ ሙስሊሞች አንድነት ማህበር መግለጫ አወጣ ። Read more »

በደቡብ ኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በሞያሌ ፣ ቡሌ ሆራ፣ ደሬ ፣ ያቤሎ ፣ ዱግደዳዋ ፣ ተልተሌ ፣ አሬሮና በሌሎችም ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሚገኙ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ገበሬዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ትግሉ የሚፈልገውን አስፈላጊውን መሰዋዕትነት በመክፈል እስከ መጨረሻው ለመጓዝ መቁረጣቸውንና እንቅስቃሴ መጀመራቸውን …

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ህዝቡ ትግሉን አፋፍሞ ለመቀጠል እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታወቀ ። Read more »

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ የወሰደውን እርምጃ በጽኑ አውግዘዋል። የኦሮሞ ህዝብ በአጋንንት ተመስሎ ተሰድቧልና ተሳዳቢው ባለስልጣን ይቅርታ ይጠይቅ ብለዋል። መንግስት ለሞቱት ዜጎች ሃላፊነቱን እንዲወስድና ለህዝብ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ አሳስበዋል።በአዲስ አበባ የሚገነቡት ፎቆች የማን ናቸው? ሲሉም ጠይቀዋል።አርጅተናል አልቻልንም ስልጣናችንን እናስረክብ ያሉ አመራሮችም አሉ። ሰፊ ሰአት በሚሸፍነው ስብሰባ …

የሰማያዊ ፓርቲ እና የአራት ደርጅቶች ስብስበ የሆነው መድረክ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። ቀደም ሲል ኦፌኮ በአዳማና ለሌች የኦሮሚያ ቦታዎች ሰልፍ ጠርቶ እንደነበረና በባላስልጣናት ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ እውቅና እንደተነፈገ ይታወቃል። ይህ የአሁኑ ሰልፍ ፣ በመድረክ ያሉትን እና ሰማያዊን ጨመሮ አምስት ደርጅቶች በጋራ የጠሩት ሰልፍ ሲሆን፣ የሚደረገዉን በአዲስ አበባ ነው። ኦፈኮ የጠራው ሰልፍ ማስተር ፕላኑን በመቃወም […]

The post ለታህሳስ 17 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ ተጠርቱዋል – የሚሊዮኖች ድምጽ appeared first on ሳተናው .

#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ የሕወሓት የደህንነት ቢሮ ሪፖርት ለኦሕዲድ ሹሞች ከነአጋሮቻቸው እስር ሲያቅድ ብቻችንን ቀርተናል በማለት መንግስት መነቃነቁን አምኗል:: ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ዛሬ ከከሰአት በኋላ ጀምሮ በአዲስ አበባ የደህንነት ቢሮ ውስጥ የሕወሓት ማፊያዎች ተሰብስበዋል::ስብሰባው ያተኮረው ባለፉት ሳምንታቶች ተከስቶ ስለነበረው …

የሕወሓት የደህንነት ቢሮ ሪፖርት ለኦሕዲድ ሹሞች ከነአጋሮቻቸው እስር ሲያቅድ ብቻችንን ቀርተናል በማለት መንግስት መነቃነቁን አምኗል:: Read more »

ባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ከትናንት ታህሳስ 9/2008 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ቤቱ የሚዘጋጀውን ምግብ እንደማይበሉ ማሳወቃቸውንና ጩኸት በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ያመልጣሉ በሚል በእግር ብረት ታስረው እንደሚገኙ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን እስረኞቹ በርካታ በደሎች እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ በተለይ በሽብር […]

The post ባህርዳር ላይ እስረኞች ተቃውሞ አሰሙ appeared first on ሳተናው .

የወያኔ ሰርጎ ገብ ካድሬዎች የኦሮሞ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተገን አድርገው በአመያ የአማሮችን ቤት አቃጥለዋል:: ማንምም ለወገኑ የሚቆረቆር ሊያረጋግጠዉ የሚችል ሃቅ:: በአመያ ወረዳ በሮሙረያ ቀበሌ ቤታቸው ከተቃጠለባቸው አማራዎች መካከል 1 አባበይ ታዬ 2 ጌታቸው ክር 3 አስጨናቂ ታዬ 4 ጌታቸው መንግስት 5 …

የወያኔ ሰርጎ ገብ ካድሬዎች የኦሮሞ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተገን አድርገው በአመያ የአማሮችን ቤት አቃጥለዋል:: Read more »

ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን እሁድ ታህሳስ …

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ ማስተር ፕላኑ እና ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ:: Read more »

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር ከተማ ህዝቡ የመንግስትን እርምጃ ሙሉ በሙሉ አውግዟል። በሌላ በኩል መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተከትሎ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ ጠርተዋል። የሰልፉ አላማ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት …

የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ባህርዳር ላይ እስረኞች ተቃውሞ አሰሙ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎BahrDar‬ ‪#‎Ethiopiaprotests‬ ‪#‎NegereEthiopia‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ከትናንት ታህሳስ 9/2008 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ቤቱ የሚዘጋጀውን ምግብ እንደማይበሉ ማሳወቃቸውንና ጩኸት በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች …

ባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ተቃውሞ አሰሙ Read more »

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ከዚህች ከኣዲስ ኣበባዋ የመሬት ነጠቃ ጥያቄ በጅጉ ገዝፎ የሄደ ነው። ከፍተኛው ጥያቄ የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ ነው። በመጀመሪያ ህወሃት ይህን ዘረኛ ፖለቲካውን ተሸክሞ ኣዲስ ኣበባ ከገባ በሁዋላ በተለይ ኦሮሞንና ኣማራን ጸጥ ኣድርጎ ለመግዛት የተጠቀመው ዘዴ በነዚህ ክልሎች ውስጥ ከታች እስከ ላይ ያሉትን ባለ ስልጣናት በኣልተማሩና የማስተዳደር ችሎታ በሌላቸው ነገር ግን ታዛዥ ብቻ በሆኑ […]

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ብዙ ፈተናዎችን ያሳለፈች ወጣት ናት። ከልጅነቷ አንስቶ የቤት ሰራተኛ ሆና አገልግላለች ፤ኃላም የጎዳና ተዳዳሪ ነበረች። እዛው ጎዳና ላይም ነፍሰ ጡር እና እመጫት ሊስትሮም ሆና ሰርታለች።

ሰላማዊ ተቃውሞ፣ ከፖሊስ ጋር ግጭት፣ ከዚያ ረብሻና እስር፣ ቃጠሎና ግድያ… ከዚህ አሳዛኝ የጥፋት ሰንሰለት መላቀቅ ያቃተን፤ መውጫ የሌለው አዙሪት የሆነብን ለምንድነው? እንዲህ አይነት ቀውስ በተፈጠረ ቁጥር፤ መንግስት እየደጋገመ የሚናገረው ነገር አለ። ቅሬታዎችን ማቅረብ፣ ተቃውሞን በሰላም መግለፅ፣ ተፈጥሯዊ መብት ነው ይላል …

“የተረገመ አዙሪት” – አገሬውን በአፈናና በጉልበት ዝም ለማሰኘት መሯሯጥ Read more »

የትግራይ ህዝብ ውርደት = Amdom Gebreslasie ************ በኣሁኑ ሰዓት በድርቅ ምክንያት 1.2 ሚልዮን ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ የሚጠባበቅ ሲሆን 1.5 ደግሞ በሴፍትኔት እርዳታ( ሰርቶ ለምግብ) በድምሩ 2.7 ሚልዮን ህዝብ ጥገኛ ሆኖ እንደሚገኝ የትግራይ ክልል ኣደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፅህፈት ቤት ሰነዶች ይገልፃሉ። …

የትግራይ ህዝብ ውርደት :- 1.2 ሚ. ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ የሚጠበቅ -1.5ሚ. ሰርቶ ለምግብ በድምሩ 2.7 ሚልዮን ህዝብ ጥገኛ Read more »

    ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ታመው ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ከገቡትና ለ10 ቀናት በህክምና ላይ ቆይተው ጥቅምት 6 ቀን ህይወታቸው ካለፈው ወይዘሮ አየለች ደግፌ ጆሮ ላይ የጠፋው 5 ግራም የጆሮ ወርቅ፤ ሆስፒታሉንና የሟች ቤተሰብን እያወዛገበ ነው፡፡ የሆስፒታሉ የፅኑ ህሙማን ክፍል ኃላፊ ሲስተር አስናቀች ተጠይቀው ሲመልሱ፤ “ወርቁ ከአስከሬኑ ጋር አብሮ የተገነዘ በመሆኑ መቃብሩ ይቆፈርልኝ” ማለታቸውን የሟች ልጅ አቶ ሰለሞን ጌታቸው ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
እናቴን “ለመጨረሻ ጊዜ ፅኑ ህሙማን ክፍል ገብተን ስናያት ወርቁ ጆሮዋ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ” ያለው አቶ ሰለሞን፤ “ከሞተች በኋላ ወርቁን ስጠይቅ ከአስከሬኑ ጋር ተገንዟል ተባልኩኝ፤ እውነቱ እንዲወጣ ስለምፈልግ መቃብሩ እንዲቆፈር ብፈቅድም እስካሁን ምንም ምላሽ አላገኘሁም” ብሏል፡፡
“ዛሬ ነገ እያሉኝ በመመላለስ ብዙ ተንከራተትኩ፤ እኔ ጉዳዬ ከወርቁ አይደለም፤ ነገር ግን መቃብሩ ተቆፍሮ እውነቱ እንዲወጣና ለሌሎችም ትምህርት እንዲሆን እፈልጋለሁ” ይላል አቶ ሰለሞን፡፡ ሆኖም ሥራዬንና ጊዜዬን ከማባከን በቀር እስካሁን አጥጋቢ ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም ሲል አማርሯል የሟች ልጅ፡፡
የሆስፒታሉን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ስዩምን አነጋግሬ ነበር ያለው አቶ ሰለሞን፤ “ኃላፊዋ ወርቁን እንድትከፍል ወስነው ነበር፤ ነርሷ ዋጋውን ከጠየቀችኝና ከነገርኳት በኋላ ነው መቃብሩ ይቆፈር ያለችኝ” ብሏል፡፡ እኔ ከራሴ ጋር እየታገልኩም ቢሆን እውነት እንዲወጣ፣  ወጪውን ሸፍና ቁፋሮውን እንድታካሂድ ብፈቅድም ኃላፊዋ የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠረች ጊዜዬን እያባከነች ነው ያለው አቶ ሰለሞን፤ ሆስፒታሉ ለጉዳዩ እልባት የማይሰጠኝ ከሆነ ማስረጃዎቼን ይዤ ወደ ፍርድ ቤት አመራለሁ ብሏል፡፡
አንድ ህመምተኛ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል (ICU) ሲገባ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ የጠይቀናቸው የህክምና ባለሙያ እንደነገሩን፤ ህመምተኛው “እንኳን ጌጣጌጥ ከቤቱ ያመጣውን ፒጃማ እንኳን መልበስ አይችልም፤ ብዙ ጊዜ ፅኑ ህሙማን በማሽን ስለሚተነፍሱና የልብ ምታቸው በየጊዜው ስለሚታይ በአብዛኛው ደረታቸው ክፍት መሆን አለበት፤ ስለዚህ በአንሶላና በብርድልብስ ብቻ ይሸፈናሉ” ከዚህ አንፃር ህመምተኞች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል ሊገቡ ሲዘጋጁ ማናቸውም ጌጣጌጥና ብራስሌት ወላልቆ ለቅርብ ቤተሰባቸው እንደሚሰጥ የጠቆሙት ባለሙያዋ፤ ይህም የፅኑ ህሙማን ክፍል ኃላፊዎች ሥራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡  
“የጆሮ ጌጡ ከአስከሬኑ ጋር ተገንዞ ቢሆን እንኳን የፅኑ ህመምተኛ ክፍል ኃላፊዋ ስራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ከተጠያቂነት አያመልጡም” ብለዋል – ባለሙያዋ፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ስዩም ምላሽ እንዲሰጡን ጥረት ብናደርግም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

የሕዝብን ተቃውሞ ማፈን ቀውስን አያስወግድም !!! ( የኢሕአፓ መግለጫ ) ባለፉት ጥቂት ቀናት የወያኔን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሲቃወሙ የነበሩ በርካታ ዜጎችን ወያኔ በግፍ ጨፍጭፏል።ኢሕአፓ አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በዜጎች ላይ ያካሄደውን አረመኔያዊ ድርጊት እየኮነነና እያወገዘ ይህን አጥፊ ቡድን ለማስወገድ የሚካሄደው …

የሕዝብን ተቃውሞ ማፈን ቀውስን አያስወግድም !!! ( የኢሕአፓ መግለጫ ) Read more »

የጥርስ መቦርቦር — (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ==== የጥርስ መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው፣ ይህም በጥርሳችን ላይ የተቦረቦሩ ቀዳዳዎችን (Cavities) እንዲፈጠሩ ያደርጋል። የተቦረቦሩ ጥርሶች ህመም ከማስከተል ባለፈ ለኢንፌክሽን ያጋልጣሉ። ✔ የጥርስ መቦርቦር …

የጥርስ መቦርቦር (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ሲቃወሙ ሰንብተዋል። የተቃውሞን ጅምር የሚያትተውን የማርታ ፋን ደር ቮልፍ የአዲስ አበባ ዘገባ ጨምራ፤ ጽዮን ግርማ የዛሬውን የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ የተመለከት ርእሶችን ይዛለች፡፡

የደንነት መስሪያ ቤቱ በሚንስትሮች ምክር ቤት በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያ የሰባት ቀን የጌዜ ገደብ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ ታውቆአል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ ሳይታሰብ የፈነዳውን አመፅ ለመቆጣጠር ምን አይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አልችል ብሎ ሲወዛገብ መሰንበቱ ሲታወቅ ዛሪ ከጥዋት ጁምሮ ሲአካሂድ በዋለው ውይይት ላይ ግን ማንኛውንም አይነት ሀይል ተጠቅሞ አመፁን ለመቆጣጠር […]

መንግሥት ሁከት በሚፈጥሩት ላይ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል

   በጎንደር ጭልጋ አካባቢ ቅማንትና አማራ በሚል በተደራጁ ቡድኖች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካቶች ለሞት መዳረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ነዋሪዎች በስጋት ከቤታቸው ሳይወጡ እንደሰነበቱ ምንጮች ገለፁ፡፡
ግጭቱ ስር የሰደደ እንደነበር የጠቆሙት የአካባቢው ምንጮቻችን፤ ከመስከረም ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል እንዳልቻሉ፣ ከሳምንት በላይ ባስቆጠረው አደገኛ ግጭትም ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡
ቅማንት በሚል የተደራጀው ቡድን፣ “የቅማንት ጥያቄ እስኪመለስ ትምህርት የለም፤ እናንተም አትማሩም” በሚል ት/ቤቶች ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ እንደነበር የጠቀሱት ምንጮች፤ በዚህም የተነሳ የአካባቢው ልጆች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል ይላሉ፡፡ የቅማንቶች የማንነት ጥያቄ ምላሽ ካገኘ በኋላ ከሰሞኑ ለተፈጠረው ግጭት መነሻ የሆነው “ዞን ይዋቀርልን፣ ድንበር ይከለልልን” በሚል በተነሳ ጥያቄ ነው ተብሏል፡፡
ቅማንቶች የማንነት ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩበት ከ3 ዓመት በፊት አካባቢው ውጥረትና ግጭት ተለይቶት እንደማያውቅ የሚጠቅሱት ነዋሪዎች፤ ከሁለት አመት በፊት ሚያዚያ ወር ላይ በአይከል ከተማ ከፍተኛ ረብሻ ተነስቶ ሰዎች መጎዳታቸውንና በርካታ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ያስታውሳሉ፡፡
ባሳለፍነው ሐሙስ ህዳር 30 ቀን 2008 ዓ.ም ግጭቱ በከፍተኛ ደረጃ መቀስቀሱን የጠቀሱት ምንጮቻችን፤ በእለቱ አንድ የቅማንት ወጣት መገደሉን ተከትሎ ቅማንት በሚል የተደራጁ ቡድኖች፤ ዳቦ ቤት ማቃጠላቸውንና ሱቅ ማውደማቸውን ይጠቅሳሉ፡፡ ይህን ተከትሎ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚል የተደራጁ ወገኖች በቋራ፣ ሺንፋ፣ ነጋዴ በሃርና ገንዳ ውሃ በተባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ቅማንቶችን እያባረሩ ቤት ንብረት ማቃጠል እንደጀመሩ ይገልፃሉ፡፡
ከእነዚህ አካባቢ የተባረሩ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ጭልጋ ውስጥ በየድንኳኑ ተጠልለው የአካባቢው ህብረተሰብ የእለት ጉርስ እያቀረበላቸው እንደሚገኝና ሰሞኑን ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የክልሉ ባለስልጣናት ህዝቡን ሰብስበው እንዳወያዩ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም የተነሳ በአካባቢው ውጥረት መንገሱን የሚጠቅሱት ምንጮች፤ ሰዎች ከቤት መውጣት እንደተሳናቸውና በየመንገዱ ጦር፣ ገጀራ፣ ቢለዋ፣ መጥረቢያና የጦር መሳሪያዎች የያዙ ሰዎች እንደሚዟዟሩ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ትናንት በአንፃሩ ሠላማዊ እንቅስቃሴ እንደነበር ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
በገጠር አካባቢዎች ተደራጅተው ለጠብ የተዘጋጁ የቅማንት ተወላጆችን መበተን እንዳልተቻለ የሚጠቅሱት የሚናገሩት ምንጮች፤ የመንግስት ባለስልጣናት ከህዝቡ ጋር ባደረጉት ውይይት ግን ከዚህ በኋላ በግጭቱ ተሳታፊ የሚሆኑና ፀብ የሚጭሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ መናገራቸን ጠቅሰዋል፡፡ ህብረተሰቡም የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ላለመግባት ተስማምቷል ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ ከቅማንት ብሄረሰብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ግጭቶች በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመው የአካባቢውን ሰላም በሚያውኩት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ንቅናቄያችን የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ የአማራን ህዝብ ህልውና መታደግ ነው።በመሆኑም አሁን በመላው ኢትዮጵያ በአማራው ላይ የሚደርሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሽፋን እየተሰጠው ከመቼውም በላቀ ሁኔታ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የሚከተሉትን አቋም እንድንይዝ አስገድደውናል። ፩- በመላው ኢትዮጵያ የሚገኝ የአማራ ተወላጅ እራሱን ከጥቃት ለመከላከል እርምጃ ቢወስድ …

ከአማራ‬ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ Read more »

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሒውማን ራይትስ ዎች ትናንት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰውና ሣምንታትን ባስቆጠረው ተቃውሞ ቢያንስ 75 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን አስታወቀ።

የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው::በዲሾች ላይ የተጀመረው ነቀላ/ጦርነት ቀጥሏል::ጃኪ ጎሴ የወያኔን ስራ በመቃወም በ2 ሃገራት የሚያካሂደውን ኮንሰርት ሰረዘው::‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ከአዲስ አበባ 60 ኪሎሜትር ላይ በምትገኘው ጫንጮ ከተማ ሕዝቦ አደባባይ በመውጣት ወያኔን ሲያስጨንቀው ታይቷል::በተለያየ ክፍለሃገራት የተሰማሩ የወያኔ ሰራዊት ልብስ …

የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው::በዲሾች ላይ የተጀመረው ነቀላ/ጦርነት ቀጥሏል::ጃኪ ጎሴ የወያኔን ስራ በመቃወም በ2 ሃገራት የሚያካሂደውን ኮንሰርት ሰረዘው: Read more »

Minilik Salsawi – የመከላከያ ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ድረ-ገጾች (ዌብሳይቶች) ተጠለፉ:: የመከላከያ ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ዌብሳይቶች መጠለፋቸውን በማህበራዊ ድህረገጽ የተለቀቁ መረጃዎች ጠቁመዋል:: ድረ ገጾቹ ከተጠለፉ በኋላ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን የሚቃወሙ እና የኦሮሞ ተማሪዎች እና ገበሬዎች የአዲስ አበባ ማስተር …

የመከላከያ ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ድረ-ገጾች (ዌብሳይቶች) ተጠለፉ:: Read more »

ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ እሳት ራሱ ይቃጠላል::ሕወሓት ተረት ተረት የሚሆንበት ቀን ደርሷል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Unity‬ Minilik Salsawi – የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሳ እና በጎጥ ከፋፍሎ ለመግዛት የሞከረው ሕወሓት በተደጋጋሚ የሕዝቡ አንድነት እሳት እየሆነበት መጥቷል::ለስልጣኑ መስረዘሚያ የተለያዩ መርዘኛ የግጭት …

ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ እሳት ራሱ ይቃጠላል::ሕወሓት ተረት ተረት የሚሆንበት ቀን ደርሷል:: ‪ Read more »

         በሀገሪቱ የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭትና ህዝባዊ አመፅ ሀገር ከመበታተኑ በፊት የሃይማኖት አባቶች ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው የሰላም ጥሪ እንዲያቀርቡ ተጠየቁ፡፡
የመግባባት አንድነትና ሰላም ማህበር (ሰላም) ባወጣው መግለጫ፤ በሌሎች ሀገራት የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭት ያስከተለው ጉዳትና ቀውስ በአገራችን እንዳይፈጠር የሃይማኖት አባቶች የሽምግልና ሸንጎ በማቋቋም፣ በሀገሪቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ የብሄራዊ እርቅ ጥሪ እንዲያቀርቡ ተማፅኗል፡፡
ሀገርና ዜጎች ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ የገቡበት አጋጣሚ አለመከሰቱን የጠቆመው ማህበሩ፤ የሃይማኖት አባቶች በሀገሪቱ የሚታየው በዘር፣ በጎሣ፣ በሃይማኖትና በቀዬ የመከፋፈል አባዜ እስራትና ስደት እንዲሁም፣ ግጭትና ጦርነት መፍትሔ ይበጅለት ዘንድ እንዲተጉ ጠይቋል፡፡ በሃይማኖት አባቶች መካከል ያለው ግጭትም እልባት እንዲያገኝ ማህበሩ ተማፅኗል፡፡
ኢትዮጵያ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖባት መቆየቷ ባይካድም ያልተቋረጠ ግጭት እያስተናገደች ባለበት በአሁኑ ሰዓት “ፍፁም ሰላም የሰፈነባት አገር ናት” በሚል ከእውነታው መሸሽ ተገቢ አይደለም ያለው ማኅበሩ፤ “በሀገሪቱ የበቀል እርምጃ እየሰፋና እየከፋ በመምጣቱ ምክንያት ማብቂያ ወደሌለው የጥፋት ጎዳና እያመራን እንገኛለን” ብሏል፡፡
“አስከፊ የእርስ በእርስ ግጭትና ህዝባዊ አመፅ እንደሚመጣ አስቀድመን ስጋታችንን ተናግረን ነበር” ያለው ማህበሩ፤ ሆኖም ለእርቀ ሰላም ስንማፀን “በሀገሪቱ ፍፁም ሰላም ሰፍኗል” በሚል ሰሚ ጆሮ ሳናገኝ ቀርተናል ብሏል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት በመተባበር ሀገሪቱ አሁን ከገባችበት አስጊ ሁኔታ ትወጣ ዘንድ እንዲፀልዩና የሀገር ሽማግሌዎች ሸንጎ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረትም እገዛ እንዲያደርጉ ማኅበሩ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡


የሆነ ጊዜ የሰማኋት ቀልድ ትዝ አለችኝ፤ አንዳንድ የተቃዋሚ ተወካዮች ፓርላማ ውስጥ በነበሩበት በዚያ በደጉ ጊዜ ነው አሉ፡፡ አንድ ተወካይ የሻዕቢያ መንግሥት ላይ ሊደረግ ስለሚገባው እርምጃ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፤ “አሁኑኑ ገብተን ድምጥማጣቸውን ማጥፋት አለብን፡፡ አለበለዚያ ካደሩ አይቆረጠሙም፤ እነዚያ ወያኔዎችም ያኔ ሲመሠረቱ ሳንጨፈልቃቸው ዝም ብለናቸው ነው ዛሬ አናታችን ላይ…” አሉና ያሉበት ቦታ ትዝ ሲላቸው ድንግጥ ብለው ወደአቶ መለስ መቀመጫ አማተሩ፡፡ አቶ መለስ በጥሞና ያዳምጣሉ፤ ተወካዩ እንደደነገጡ “…ልጨርሰው ወይስ ትጨርሰኛለህ?” አሉ ይባላል፡፡
የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወታደሮች አዲስ አበባ ደርሰው “ሲቪል” መንግሥት ከመመሥረታቸው አስቀድሞ “እኩይ” ናቸው በሚል ሲቃወማቸው የነበረ እና እስካሁንም ስክነቱ ያልተለየው አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው፡፡ የታማኝ የአክቲቪስትነት ሪከርድ ከኮሜዲያንነቱ የሚመዘዝ ነው፡፡ በቀልዶቹ ቢጀምርም አሁን ግን በጣም ‹ሲሪዬስ› ነው፡፡ አሁን እነቪኦኤ፣ ዶቸ ቬሊ፣ ኢሳት በየቤቱ እንደሚደመጡት ከደርግ ማክተሚያ ቀደም ብሎ ብዙ ሰው በየቤቱ ‹ድምፂ ወያነ›ን በድብቅ ያደምጥ ነበር፡፡ የፕሮፓጋንዳ ሚዲያዎች አመል ነውና ያው ውሸታቸው አይጣል ነው፡፡ ታዲያ ታማኝ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቀርቦ የምሩን ሲቀልድ ‹እዚህ ቦታ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር፣ እዚያ ቦታ ደግሞ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር ደመሰስን ይላሉ፡፡ ሲደመር ግን ይሄን ያክላል፡፡ ቆይ እኔ የምለው ወያኔዎቹ የሚደመስሱት ጦር ከጠቅላላ ጦሩ በለጠ እኮ፤ ከየት እያመጡ ነው የሚደመስሱት?› ዓይነት ቀልድ ተናግሮ አላገጠባቸው፡፡ ከዚያ በድምፂ ወያነ መልስ ተሰጠው፤ “ቁጥሩን አዲስ አበባ ስንደርስ እናወራርዳለን” የሚል፡፡ ዛቻ የሽፍትነት ዘመንም አመል ነበረች፡፡
ግንቦት 20/1983 – ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲረግጥ፣ ሲ ኤን ኤን ካነጋገራቸው ሰዎች አንዱ ታማኝ በየነ ነበር፡፡ “በመሣሪያ ተከበናል፣ ምንም ሠላም የለም…” የሚል ነገር ለጋዜጠኛው ሲነግረው ይታያል፡፡ ታዲያ ታማኝ ሁኔታውን በቀልድ ሲያስታውስ “ጓደኞቼ ከውጪ ደውለው ‹ሲ ኤን ኤን› ላይ አየንህ ሲሉኝ፣ ወዲያውኑ እንግሊዝኛዬ እንዴት ነበር?” አልኳቸው ይላል፡፡
ታማኝ ከአዲሱ ስርዓት ጋር አብሮ መኖር በማይችልበት ሁኔታ የተቀያየመው፣ ካልተሳሳትኩ የወቅቱ ባለሥልጣናት፣ እነታምራት ላይኔ በተገኙበት ስታዲዬም ውስጥ በቀለደው ቀልድ ነው፡፡ እንደማስታውሰው ቀልዱ በማንነት ላይ የተመሠረተ እና ለኢሕአዴግ የማንነት ብያኔ የማይበገር ዓይነት ቀልድ ነው፡፡

ፍቃዱ ማሕተመወርቅ፣ የቀድሞዋ ዕንቁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነበር፡፡ በመጽሔትና ጋዜጦች አከፋፋይነትም ይታወቃል፡፡ አሁን መጽሔቱ ተዘግቶ “በታክስ ስም” ፍርድ ቤት እየተመላለሰ ይገኛል፡፡ ፍቃዱ ነጻው ፕሬስ ሲጀመር ጀምሮ ምኅዳሩን ያውቀዋል፤ እናም “እናንተ በደጉ ጊዜ ነው የመጣችሁት” እያለ ይቀልድብኛል፡፡ ያኔ (ማለትም የመጀመሪያው አንቀጼ ላይ ‹ደግ› ባልኩት፣  ለፍቃዱ ግን ‹ክፉ› ግዜ) አንድ ሰው ስርዓቱን የሚያስቀይም ንግግር ሲናገር፣ እንዳሁኑ በሕግ ሥም ፍርድ ቤት አይመላለስም፣ የደረሰበት ይጠፋና ከአራት አምስት ወር በኋላ ተመልሶ ይመጣል፡፡ እንዳይሞት እንዳይሽር ተቀጥቅጦ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ከዚያ ወዲህ ያሻሻልነው ነገር ቢኖር ፍርድ ቤት የመቅረብ ዕድል መፈጠሩ ነው ማለት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህን ያነሳሁት ታማኝ ላይ የደረሰውም እንዲህ ያለው ነገር ነው ለማለት ነው፡፡
ታማኝ ተሰደደ፡፡ ብዙዎች ሲሰደዱ አቅላቸውን ያጣሉ፡፡ የሀገር ቤት ናፍቆት መመለስ ካለመቻሉ ጋር ተደማምሮ ይሁን፣ የሄዱበት አገር ኢሕአዴግ የማይደርስባቸው ከመሆኑ በተጨማሪ የሚያዩት ነጻነት ስለሚያስቀናቸው አላውቅም ብቻ ጠርዝ ይይዛሉ፡፡ ጥቂቶች ብቻ ሚዛናቸውን በጥፍራቸው ቆንጥጠው ይቆማሉ፡፡ ታማኝ ለኔ ከጥቂቶቹ አንዱ ነው፤ ያውም በረዥም ቆይታ ይህንን ማስመስከር የቻለ፡፡ ታማኝ አሁን አክቲቪዝሙን የሚሠራው ብዙ ጊዜ የቪዲዮ ማስረጃዎችን እያቀረበ ነው፡፡ ቪዲዮዎቹን ዩቱዩብ ላይ ሳያቸው በክምችቱ እቀናለሁ፡፡ ለረዥም ጊዜ የአገር ቤት ጉዳይን እየተከታተሉ፣ ማስረጃዎችን እየሰበሰቡ የመቆየት ፅናት የገቡበትን ጉዳይ ርዝመት እና ክብደት ከመረዳት ይመነጫል፡፡
የማስረጃ ነገር ከተነሳ አይቀር፣ አሁን እነ ታማኝ ማስረጃ ዶት ኮም (masreja.com) የተባለ ድረአምባ ፈጥረዋል፡፡ ድረአምባው በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ የበላይነት ፈንታ ራሳቸው ከሕግ የበላይ ሆነው ወንጀል የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ ማስረጃ የሚሰበሰብበት ነው፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ እኔ በይቅርታ አምናለሁ፤ እስከዛሬ አዲሱ ያለፈውን እየቀጣ የመጣበት ዑደት ቢያንስ የእኛ ትውልድ ላይ ቢቆም እያልኩ እመኛለሁ፡፡
ይህንን በተመለከተ ጓደኛዬ ሶሊያና “ይቅርታ ከፍትሕ ጋር መጋጨት የለበትም” ብላ ሞግታኛለች፡፡ ልክ ነች፤ በወቅቱ የሰጠችኝን ምሳሌ ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር አዋህጄ ልናገር፤ “#OromoProtests ላይ ልጇ የተገደለባት እናት የስርዓት ለውጥ ቢመጣ እና ለገዳዩ ወታደር ይቅርታ አድርጊለት ብትባል ፍትሕ ተደረገልኝ ብላ ታምናለች?” በወቅቱ፣ ሶሊም እኔም ጥያቄውን ከመጠየቅ በቀር መልስ መስጠት አልቻልንም፡፡ እርግጥ ነው ልጁ የሞተው የመጣው ለውጥ እንዲመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በምሳሌያችን መሠረት አወዛጋቢው ማስተር ፕላን ቢሰረዝ እንኳን ልጁ የለውጡ እሸት ተጋሪ ላይሆን አልፏል፡፡ ይቅርታ ለአገሪቱ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ያስፈልግ ይሆናል፤ የቤተሰቡን አባል ወይም ወዳጁን ላጣው ግለሰብ ግን ፍትሕ ሆኖ ይሰማዋል ማለት አይቻልም፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ለይቅርታውም ቢሆን ማስረጃውን መሰብሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ አጥፊው ጥፋቱን እንዳይክድ፣ ይቅርታ ጠይቁኝ ባዩም በማስረጃ እንዲሞግት፡፡
ማስረጃ መሰብሰብ ሕገ-ወጥ መስሏችሁ የምትፈሩ ካላችሁ አትሳሳቱ፡፡ ሕጋዊ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት ራሱ በፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኩል አላግባብ የተገኘ ሀብት ካለ በሚል የባለሥልጣናቱን ሀብት ምንጭ ሳይቀር የማጣራት ማንዴት አለው፡፡ ቁርጠኝነቱ ስለሌለ አልተሳካላቸውም፤ እኛ ግን ይሳካልናል፡፡ በየቀኑ ከታችኛው እርከን (ወረዳ) እስከ ላይ ድረስ የምንጠየቃቸውን ጉቦዎች፣ ባለሀብቱና ባለሥልጣናቱ (ሁለቱም አንድ ናቸው) ኢ-ርትዓዊ በሆነ መንገድ የሚያካብቱትን ሀብት፤ ከትላልቆቹ እስከ ትናንሾቹ ሹመኞች በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን ግፍ፤ ትንንሽሽም፣ ትልልቅም ሠላማዊ ተቃውሞዎች በተነሱ ቁጥር በንፁሐን ዜጎች ነፍስ ላይ የሚሰነዘሩትን የኃይል እርምጃዎች የሚያጋልጡ ማስረጃዎች ባገኘን ቁጥር ለማስረጃ ዶት ኮም በመላክ ለኢትዮጵያችን የወደፊት መልካም ዕጣ ፈንታ ሲባል እንዲከማቹ የበኩላችንን እናድርግ፡፡ ማስረጃዎቹን መሰብሰቡ ሌላው ቢቀር አጥፊዎቹን ስለሚያስፈራቸው በደላቸውን ሊያላሉልን ይችላሉ፡፡

ቪቫ ላ ታማኝ!!!

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተማሪወችም መንግስት በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች የፈፀማቸውን ግድያዎች በምልክት መቃወማቸው ታወቀ ። በትላንትናው እለት መንግስት አዳአ በርጋ ሙገር ከተማ በወሰደው እርምጀሰ ከሐያ ሰዎች በላይ መግደሉንና ብዛት ያላቸውንም ማቁሰሉን : ተጎጂዎችም በኢንጪኔ ሆስፒታል እንደሚገኙ ታውቋል። በዛሬው እለት በቀለም …

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ ተፋፍሞ ቀጥሏል Read more »

የዘር ፖለቲካ መዘዝ – ግርማ ካሳ የአሜሪካን ዽምጽ ራዲዮ ዘገባ አደመጥኩ። ከ50 በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች እንደተዘረፉና ጥቃት እንደደረሰባቸው ነው ዘገባው የሚገልጸው።በጣም አዝኛለሁ። ዜጎች ከዚህ ወይም ከዚያ ብሄረሰብ በመሆናቸው ብቻ ጥቃት ሲፈጸምባቸው መሰማቱ እንደ አገር አሁን ሕወሃት/ኢሕአዴግ እያራመደው …

የዘር ፖለቲካ መዘዝ – ግርማ ካሳ Read more »

የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል” ናቸው ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል፡፡