በጋምቤላ በቀጠለው ግጭት 7 ሰዎች ተገደሉ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር አቶ ኒካው ኦቻላ ለኢሳት እንደገለጹት የንዌር ተወላጆች የጋምቤላ እስር ቤትን ሰብረው በመግባት 7 የአኝዋክ ተወላጆችን ሲገድሉ፣ 7ቱን ደግሞ አቁስለዋል። 4 የሌሎች ብሄረሰቦች አባላት መቁሰላቸውምን ዳይሬክትሩ ገልጸዋል። በሁለቱ ብሄረሰቦች መካካል እንዲህ አይነት ደም የሚያፋሰስ የመረረ ግጭት ተቀስቅሶ እንደማያውቅ የገለጹት አቶ ኒካው፣ ለአሁኑ ግጭት መባባስ …