ዛሬም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸው መሆናቸውን እየተናገሩ ነው – VOA

Oromo protest in Bako, Western Shoa, Ethiopia

በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ፣ በጉጂ ዞን፣ በሃርቀሎ ወረዳና በሆሮ ጉዱሩ፤ በወለጋ ኢበንቱ ወረዳ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸውና በመከላከያ አባላት እየታሠሩ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡

አንድ የአሰላ ከተማ ነዋሪ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ የአንደኛ፣ የሁለተኛና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ሠላማዊ ሠልፍ ወጥተው የአዲስ አበባን የአካባቢዋን ከተሞች የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላንና ኦሮሚያ ውስጥ ይካሄዳል ያሉትን እሥራትና ግድያ መቃወማቸውን ገልፀዋል፡፡

አንዲት የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ከሰልፉ ወቅት ስትሮጥ ሽቦ ላይ ወድቃ የአንድ ዐይኗን ብርሃን ለማጣት መዳረጓን የከተማይቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ አንድ የከተማይቱ ነዋሪ ደግሞ ሆዷ ላይ በዱላ ተመትታ በብርቱ መጎዳቷን አመልክተው ትምህርት ተቋርጦ ከተማይቱ በጦር እየተጠበቀች ነው ብለዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ ↓

4 Comments on “ዛሬም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸው መሆናቸውን እየተናገሩ ነው – VOA”

  1. Kehulum yasazenugne Ye esat weyalawoch
    nachew lelit ina ken inkelef atetew
    silefelefu akeremoachew ya hulu ye
    istudio drama ena interview . kkkkkkkk

  2. ባልተደራጀህበትና ማጠፊያው በሌለህ ሁኔታ ክልላቸውን ከኢትዮጵያ ቆርሰው ነፃና ሉዓላዊ አገር ለማድረግ የሚጥሩ ጠላቶችን ሳታስተውል ከደገፍህ፣ ማርሽ ይቀይሩብህና አንተም አገርህም የማይቀለበስ አደጋ ላይ ሰለምትወድቁ ጠንቀቅ በል!

    ከአስተዋይ በቀለ

    ስማ የእናት አገር ኢትዮጵያ ወገን ሁሉ ! ! !
    ከ 7 ሺህ ዘመን በላይ መንግሥት አቋቁማ የኖረችው የእናት ቅድስት አገር ኢትዮጵያ ሕልውና ጉዳይ ስለሆነ፣ ውስጡንና ጥቁረቱን በማታቀው ጉዳይ ዝም ብለህ አትማገድ። ለዚህ እንጨትና ጭራሮ አለ። የዑደተ-መሬትን ሕያው ሃቅ የማያውቁና ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ ብለው የሚያምኑ ደንቆሮዎች፣ ግብዛንና ባንዳዎች አታልለው እንዳያሰልፉህ ተጠንቀቅ።
    ስማ ! ፖለቲካ ሁሉን ነገር በውል ልብ ማለትን ይጠይቃል። እንደ እህልም በወንፊት ይነፋል- በሰፌድም ይበጠራል። ቱምቢም ተዘርግቶ ይለካል። አላምጦ በማስተዋል ወለላና ፍቱን አቋም ይዞ ይሄዳል። ይህን ሃቅና መላ ጨርሶ እንዳትዘነጋ !!!!
    የዋህነትን ጢም ብሎ በተጋተ ኮስማና አመለካከት ብቻ፣ ቅድስት ኢትዮጵያን በናቀና ባራከሰ፣ ሰንደቅ ዓላማዋን በአደባባይ በረገጠና በቀደደ፣ኢትዮጵያዊያንን ገደል በጣለ፣ ደም ባፈሰሰና ባፈናቀለ በክልል ትዕቢት የሚባዝንን ዘረኛና ጠባብ ትርምስምስና ስውር ሴራ ከተመለከትክ፤ ኤርትራችንን ያስገነጠለውን የትናንቱን የመሀል አገር ስህተት በውል ያልተረዳህና የዛሬውንም ኢትዮጵያ- አድን ቆራጥ ትግል ያልተገነዘብህ ስለሆነ ከእንግዲህ አቋምህን በአስቸኳይ አስተካክለህ አልሞትኩም ብለህ ተደራጅ-ታጠቅ-ዝመት።
    ልብ በል የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ! ! !
    መከሩ ደርሳል። ማጭዱ ግን ኢትዮጵያ ፣ኢትዮጵያዊነትና አረንጓዴ-ቢጫ- ቀይ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ብቻ ነው።ይህም አንተ አገር ወዳዱ ነህ።እናት አገርህን አፍርሰው ጠባብ ዘረኛነታቸውን አገር ለማድረግ የተነሱና የሚተራመሱን ሁሉ በእንጭጩ መደምሰስ አጣዳፊ ግደታህ ነው። ክንድህ አበርታ ወደፊት ! ድል ምንጊዜም ያንተ ነው።
    ወያኔን ፣ ሻቢያን፣ ገንጣይ የክልል ዘረኞችንና ባንዳዎችን ሁሉ እንደመስሳለን ኢትዮጵያ ወይም ሞት !

  3. Beyebotaw begonder, badis abeba, beoromo, begambiela, besumalie, besidamo, be omo, bemejenger etiopiawiyann woyanie eyegedele, akal eyagodele, eyasere, eyedebedebe, hzb eyafenaqele, eyezerefe, eyasrabe eyadeheye, woyanie tedeladlo beslTan miqeTlbet andam mknyat yelem. Begd bewotader hail aschenqo beshbr eyegezan new. Zm blen kemaleq kemeseqayet gbgb woyanien geTmen masweged amarach yelielew yehluwna Tyaqie new. Tenesu ennesa, woyanien gdelu engdel ena kewoyanie gf neTa enwTa.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*