“የተረገመ አዙሪት” – አገሬውን በአፈናና በጉልበት ዝም ለማሰኘት መሯሯጥ

“የተረገመ አዙሪት”  –  አገሬውን በአፈናና በጉልበት ዝም ለማሰኘት መሯሯጥ

ሰላማዊ ተቃውሞ፣ ከፖሊስ ጋር ግጭት፣ ከዚያ ረብሻና እስር፣ ቃጠሎና ግድያ… ከዚህ አሳዛኝ የጥፋት ሰንሰለት መላቀቅ ያቃተን፤ መውጫ የሌለው አዙሪት የሆነብን ለምንድነው?
እንዲህ አይነት ቀውስ በተፈጠረ ቁጥር፤ መንግስት እየደጋገመ የሚናገረው ነገር አለ። ቅሬታዎችን ማቅረብ፣ ተቃውሞን በሰላም መግለፅ፣ ተፈጥሯዊ መብት ነው ይላል – ሁልጊዜ። እና፤ መንግስት ይህንን መብት ከምር የሚያከብር ከሆነ፤ ለምን… ሰላማዊ ተቃውሞ ወደ ረብሻና ግድያ ይሸጋገራል?
በየጊዜው የሚፈጠሩ ቅሬታዎችንና ተቃውሞዎችን፣ አንድ በአንድ በቀጥታ እያስተናገደ ምላሽ ለመስጠትና ለማስተካከል ቢተጋ ኖሮ፤ ችግሮችን ለመፍታት ከማገዝ አልፎ፤ ረብሻ የማይነካካው ሰላማዊ  ተቃውሞ እንዲለመድ ይረዳ ነበር፡፡
መንግስት ይህንን ሃላፊነቱን አልተወጣም፡፡ ስልጡን የፖለቲካ ባህል እገነባለሁ እያለ ለአመታት ቢናገርም፤ ከነባሩ አዙሪት አልወጣንም፡፡
ነገር ግን፤ መንግስት፣ ሰላማዊ ተቃውሞን ለማስተናገድ ጨርሶ የማይፈልግ ቢሆንም እንኳ፣ በዚህም ሃላፊነቱን ባለመወጣት ዋና ተጠያቂ ቢሆንም እንኳ፣ እኛስ በራሳችን አቅም፣ ሰላማዊ ተቃውሞ ወደ ብጥብጥ እንዳያመራ መከላከል አንችልም?
መቼም፣ አብዛኛው ሰው፣ ጨዋ ነው። የተቃውሞ ድምፅ ለማሰማትና አቤቱታ ለማቅረብ፣ ወደ አደባባይ የሚወጡ ብዙዎቹ ሰዎችም፣ በአመዛኙ የሰውን ሕይወትና ንብረት ለመጉዳት አይፈልጉም። ታዲያ፣ ለምንድነው በየጊዜው፣ እንዲህ አይነት ቀውስ የሚፈጠረው?
እዚህ ላይ ችግር አለ። አብዛኞቹ ሰዎች  ጨዋ ቢሆኑም፣ የሰውን ሕይወትና ንብረት ለመንካት ፍላጎት ባይኖራቸውም፤ በሰላማዊ ተቃውሞ መሃል፤ ዝርፊያንና ጥቃትን ለማስቆም ይቸገራሉ። በሌላ አነጋገር፤ መዝረፍና ማቃጠል ለሚፈልግ ሰው ‘ጥሩ’ አጋጣሚ ይሆንለታል። ከዚያም አልፎ ራሱን፤ ‘ዋና የነፃነት ታጋይ፣ ዋና ተቆርቋሪ፣ ዋና ተወካይ’ አስመስሎ ስለሚሾም፣ ‘ተው የሰው ንብረት አትዝረፍ፣ አታቃጥል’ ብለን በድፍረት አንጋፈጠውም። እንዲያውም፣ አለቃ ወይም መሪ ይሆንብናል።
አንድ መጥፎ ሰው፤ ነገሩን ሁሉ የሚረብሽብን፤ አድራጊ ፈጣሪ የሚሆንብንና ወደ ጥፋት አቅጣጫ የሚመራን፣ አለምክንያት አይደለም። እሱን ለመገሰፅና ለማረም ከሞከርን፤ ‘ከሃዲ፣ ሰርጎ ገብ፣ ተብለን አጣብቂኝ ውስጥ እንዳንገባ እንሰጋለን፡፡ ‘ከሃዲ… ያዘው፣ ፈንክተው’ ብሎ ቢያነሳሳብን፣ በዚያ ግርግር መሃል፣ ምን ሊፈጠር እንደሚችልና ምን ሊደረስብን እንደሚችል ለመገመት ያስቸግራል። “ወደ ጥፋት መንገድ አንሄድም፤ ሰላማዊ ተቃውሟችንን አትረብሽብን” የሚል ትችትንም ሆነ ተግሳፅ መስማት፣ እንደ ጥቃትና እንደ ሽንፈት ይቆጥረዋል – ትችታችን ትክክለኛና ተገቢ ቢሆንም እንኳ። ግን፣ እንዲያው፣ ትችታችን ተገቢ ባይሆንስ? ትችት ስለተሰነዘረበት ብቻ… “ያዘው ፈንክተው”…?
ይሄማ፣ አምባገነን መንግስት ከሚፈፅመው አፈናና ረገጣ በምን ይለያል?
አዙሪቱ ይህንን ይመስላል።
የመንግስት ጭፍን ፕሮፖጋንዳንና ጥፋትን፣ አፈናንና ጉልበተኝነትን ለመቃወም፤ እንከን የሌለው ትክክለኛና ጥርት ያለ ሰላማዊ ተቃውሞ ለማሰማት ብንችል እንኳ፤ እዚያው ከመሃላችን አንድ ሁለት መጥፎ ሰው አይጠፋም። ስልጣን ባይኖረውም፣ ትንሽ “አምባገነን ሊሆንብን ይሞክራል፡፡ እሱ ከሚነግረን ወሬ ውጪ፤ ለየት ያለ አንዳች መረጃ መስማት ያንጨረጭረዋል፡፡ አንዳች የተለየ የአስተያየት አማራጭ ለማየትም አይፈልግም። አለመፈለግ ብቻ አይደለም፡፡ በከሃዲነት እንድንፈረጅ ማድረግ እንደሚችል ያውቃል፡፡ እናም ጭፍን ስሜትን በማራገብና በአሉባልታ፣ በዛቻና በጉልበት፣ ዙሪያውን ‘ዝም’ በማሰኘት፣ አለቃና መሪ ሆኖ ያርፈዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው እንደሚኖር ስለምናውቅና ስለምንሰጋም ነው፤ ጭፍን ስሜቶችንና መጥፎ ድርጊቶችን ለማስቆም ብዙም ለመጣር የማንነሳሳው። እናም፤ ሰላማዊው ተቃውሞ፣ በአንድ በሁለት ሰው ተረብሾ ወደ ግርግር ይቀየርብናል። ይሄ አንደኛው ምክንያት ነው፡፡
ሁለተኛው ምክንያትስ?
የተቃውሞ ድምፃችንን ለማጉላላትና እንዳይደበዝዝ መመኘት ተገቢ ቢሆንም፤ ለዚህ በትጋት ከመጣጣር ይልቅ፣ ወደ “ቀላል” የአቋራጭ መንገድ ካዘነበልን፣ ለስህተት እንጋለጣለን፡፡ እንዴት በሉ፡፡
አንደኛ ነገር፤ የተቃውሞ ድምፅን የሚያበርድና የሚያደበዝዝ ከመሰለን፣ እውነተኛ መረጃንና ምክንያታዊ አስተያየትንም ጭምር ችላ ብለን፣ ሰምተን እንዳልሰማን እናልፋለን። [ከድካምና ከጥረት የሚገላግል አቋረጭ መንገድ ያገኘን ይመስለናል። ግን፤ መዘዝ አለው። በዚሁ ምክንያት፣ አስተዋይ፣ ብልህና ቀና ሰዎችን እያገለልን እንደምንሄድ አናውቅም]። ይህም ብቻ አይደለም።
የተቃውሞ ድምፅን ለማማሟሟቅና ለማድመቅ የሚረዳ እስከመሰለን ድረስ፣ ተገቢ ላልሆኑ ነገሮችም ጭምር ቦታ መስጠት እንጀምራለን፡፡ ለምሳሌ፤ አንድ ሁለት ሰዎች በጭፍን የሚያስተጋቡትን የውሸት መረጃም ሆነ የጥፋት አዝማሚያ፣ ለማስተካከልና ለማረም ከመሞከር ይልቅ፣ አይተን እንዳላየን ማለፍ ይቀለናል። [ለጊዜው፣ ‘ቀላል’ ነው። ነገር ግን፣ እነዚያ በጭፍን ስሜት የተዋጡ አንድ ሁለት ሰዎች፣ ራሳቸውን አለቃና መሪ አድርገው በእኛው ላይ እንዲሾሙ፣ እድል እንከፍትላቸዋለን።] ለዚህም ነው፤ በመጀመሪያው ቀንና በማግስቱ፣ ሰላማዊ የነበረው የተቃውሞ ድምፅ፣ ቀስ በቀስ በረብሻ እየተዋጠና እየተወረሰ እንዳይሄድ ለመከላከል የምንቸገረው።
አንዴ መበላሸት ከጀመረ በኋላ ደግሞ፤ እየከበደና እየተባባሰ ይቀጥላል፡፡
ጭራሽ፣ ‘ይሄ አገር ወዴት እያመራ ነው?” የሚል ጥርጣሬ እስኪያድርብን ድረስ፣ አገር ምድሩ ይቀወጣል። “የተሻለ ነገር ያስገኝ ይሆናል” ብለን የጀመርነው ነገር፤ ከቀድሞው ወደ ባሰ ውጥንቅጥ እንዳያወርደን መስጋት ይመጣል። ያኔ፤ ለጉልበተኛ ባለስልጣን፣ መንገዱ ተመቻቸለት።
ከሰላማዊ ተቃውሞ ይልቅ፣ ረብሻ የሚመቻቸው ባለስልጣናት አሉ። ለምን? አሃ፤ ጥያቄዎችንና ትችቶችን የማስተናገድ ጣጣን ያስቀርላቸዋል፡፡ ሰላማዊ ተቃውሞ በረብሻ ከተወረሰ… በቃ፤ በማንኛውም መንገድ፣ (በፕሮፓጋንዳ፣ በዛቻና በጉልበት)… ሁሉንም ሰው ፀጥ ለማሰኘት፣ በቂ ሰበብ ይሆንላቸዋል። በሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ ሰዎችን ብቻ በህግ ከመዳኘት ይልቅ፤ በዚህችው አጋጣሚና ሰበብ፣ አገሬውን ሁሉ ዝም ለማሰኘት፣ የትችትና የተቃውሞ ድምጽን ጨርሶ ለማጥፋት ይሞክራሉ።
ፕሮፓጋንዳውን፣ አፈናውን፣ ጉልበተኝነቱን፣ ከቀድሞው የባሰ ለማድረግ የሚጠቅም ማመካኛ ይሆንላቸዋል – ረብሻው። ጥያቄዎችን፣ አቤቱታዎችንና ትችቶቸን እያስተናገዱ፣ ስህተቶችን ለማስተካከልና ጥፋቶችን ለማረም ከመትጋት ይልቅ፤ ሁሉንም ሰው ዝም ማሰኘት  ይቀላቸዋል። ለጊዜው፣ ‘ቀላል’ ይመስላል። ግን፤ መፍትሄ አይሆንም። ባለስልጣናትና መንግስታት፣ በሰበብ አስባቡ፣ ‘ገናና’ እየሆኑ መሄድ፤ “ቀላል” መስሎ ቢታያቸውም፤  ብዙም አያዛልቅም። ቢሆንም ግን፤ ሰበብ ተገኘ ተብሎ፣ ‘ገናና’ ለመሆን መሯሯጥ፤ በየአቅጣጫውና የየጊዜው፣ በተደጋጋሚ የሚታይ፣ የተለመደ የበርካታ ባለስልጣናት  ባህርይ ነው። ቀውስ በተፈጠረ ቁጥር፤ ለቀውሱ ሁነኛ መፍትሔ ከማበጀት ይልቅ፤ በዚያ ሰበብ፤ ከዜጐች ላይ ገናና ለመሆን ይገለገሉበታል፡፡
በአገራችን ብቻ ሳይሆን፤ ደረጃው ቢለያይም፣ በሁሉም አገራት፣ የዘመናችን ሦስቱ ዋነኛ አለማቀፍ የቀውስ ምንጮችን ተመልከቱ።
በመንግስት እልፍ ቁጥጥሮችና ጫናዎች ሳቢያ የሚፈጠር “የቅይጥ ኢኮኖሚ ቀውስ”፣ በአለም ዙሪያ፣ ከድሃ እስከ ሃብታም አገራት፤ ሁሉንም እያናወጠ አይደል? ግን፤ ጥፋተኞቹ መንግስታት ብቻ አይደሉም፡፡ እኛም እንተባበራቸዋለን፡፡
በአንድ በኩል፤… የግል ኢንቨስትመንትንና ቢዝነስን፣ የግል ስኬትንና ብልፅግናን፣ በአድናቆትና በአርአያነት ለማየት የሚቸገር ኋላቀር ባህል በአገራችን ሞልቷል። በሌላ በኩል ደግሞ፤… በዚህም በዚያም በአየር ባየር አልያም በሙስና፣ በድጐማም ሆነ በልዩ ድጋፍ … (ያለ ስራ እና ያለ ጥረት) ሃብት ለማግኘትና ተጠቃሚ ለመሆን መዋከብም የተለመደ ነው፡፡ እነዚህ አዝማሚያዎች፤ በብዙ ዜጐች ዘንድ የሚታዩ ስህተቶች ናቸው፡፡ የመንግስት ምላሽስ?
መንግስት፤ ቢዝነስን የሚያናንቅን ባህል ለመግታትና የአየርባየር ወከባን ለማስተካከል ከመጣር ይልቅ ወደ ነፃ ገበያ ስርዓት ለመጓዝ ከመትጋት ይልቅ፤ በዚሁ ሰበብ፤ ከነአካቴው ቢዝነስንና ነፃ ገበያን በእንጭጩ የሚቀጭ፣ የዋጋ ቁጥጥርና የዋጋ ተመን፣ የገደብና የክልከላ፣ የታክስ ጫናና የመዋጮ ዘመቻ ማካሄድ ቀላል ይሆንለታል።
ያው፤ ቢዝነስ ሳይስፋፋ ደግሞ፣ ከስራ አጥነትና ከድህነት መላቀቅ አይቻልም። አሳዛኙ ነገር፤ በስራ አጥነትና በድህነት እየተማረርን፣ ለዚህ ችግር መፍትሄ እንዲፈለግለት ‘ድማፃችንን ለማሰማት’ አደባባይ ብንወጣ፤ ከሁሉም በላይ ጎልቶ የሚወጣው ድምፅ፣ “የሸቀጦች የዋጋ ቁጥጥር ይደረግ”… የሚል መፈክር ይሆናል።
መንግስት ይህንን አግኝቶ ነው?
በዚሁ ሰበብ፤ ቢዝነስ ላይ፣ ተጨማሪ ጫናና ቁጥጥር በማወጅ፣ ይበልጥ የመንግስትን ገናናነት ለማግዘፍ የሚመኝ ባለስልጣን፣ እንደሚኖር አትጠራጠሩ። በግል ኢንቨስትመንትና በቢዝነስ ላይ ጭፍን ጥላቻን እያራገብን፣ መንገዱን ለመንግስት አመቻቸንለት ማለት ነው። እናም፣ ቢዝነስ እየተደናቀፈ፤ ከስራ አጥነትና ከድህነት ጋር እንደተቆራኘን እንቀጥላለን።
አዙሪት ነው። ለኛ አይበጅም። ለመንግስትም አያዛልቀውም። ቢዝነስን እየገታ፣ ‘ገናና’ መሆን፣ ውሎ ሲያድር መዘዙ እየከፋ ይሄዳል። በጊዜ ካልባነነ፣ መውደቂያው ይሆናል።
ሁለተኛና ሦስተኛ የቀውስ ምንጮች፤ የሃይማኖት አክራሪነትና የዘረኝነት አባዜዎች ናቸው፡፡ በአንድ በኩል፣ መንግስታት፣ የአክራሪነት ሽብርንና የዘረኝነት ግጭትን በቀጥታ ከመከላከል ይልቅ፤ በዚሁ ሰበብ፣ የዜጎችን ቅሬታ፣ ትችትንና ሰላማዊ ተቃውሞን አፍነው ዝም ለማሰኘት፣ ይጠቀሙበታል። በአገሬው ላይ ‘ገናና’ ለመሆን፣ አስተማማኝ ማመካኛ ይሆንላቸዋል። “አገርን ከሽብር ለመታደግ፤ ሕዝብን ከዘረኝነት እልቂት ለማዳን”…እያሉ፤ ያሻቸውን ነገር ለማድረግ ይሞክራሉ።
አሳዛኙ ነገር፤ እኛም፣ እንመቻችላቸዋለን። የተቃውሞ ድምፅን ለማድመቅ የሚጠቅም እየመሰለን፣ ወይም ደግሞ የተቃውሞ ድምፅ እንዳይደበዝዝ በመስጋት፣… በፅናትና በትጋት ትክክለኛ መላ ከማበጀት ይልቅ፤ ሃይማኖትንና ተወላጅነትን ከፖለቲካ ጋር የማደበላለቅ አዝማሚያ፣ አቋራጭ መፍትሄ ሆኖ ይታየናል፡፡ ወይም “ጊዜያዊ ችግር ነው” ብለን በቸልታ እንቀበለዋለን።
በዚሁ አዝማሚያ ለመንሸራተት፣ አእምሯችን ፈቃደኛ ባይሆን እንኳ፤ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን… አክራሪነትንና ዘረኝነትን የሚያስተጋቡ መጥፎ ሰዎችን በዝምታ ለማለፍ፣ ወይም እንደ ጊዜያዊ ችግር አይተን ቸል ለማለት ይዳዳናል። ነገር ግን፣ አንድ ሁለት ሰው የሚያስተጋባው የዘረኝነት ወይም የአክራሪነት መርዝ፣ ከጎናችን ተሰልፎ በዝምታ ስናልፈው፤… ለአፍታ በአዳማቂነት አገልግሎ፣ በራሱ ጊዜ የሚከስም፣ ተራ ችግር አይሆንልንም።
በተገላቢጦሽ፣ ዋና ጉዳያችንን ሁሉ ጠቅልሎ እየዋጠና እየቀበረ፣ ከመክሰም ይልቅ እየተግለበለበና እየተቀጣጠለ ለመስፋፋት እድል ያገኛል፡፡ ብዙም ሳይቆዩ፤ በሃይማኖት ተከታይነት ወይም በዘር ወደ ማቧደን ይሸጋገራሉ፤ ከዚያም በየፊናቸው የየቡዱኑ አለቃ፣… አድራጊ ፈጣሪ ይሆኑብናል።
እንዲህ፣ ነገር እየተበላሸ፣ አገሬው ወደ መናወጥ እያመራ፤ ብዙዎቻችን ‘የባሰ መጣ’ ብለን መስጋት ስንጀምር፤ መንግስት ምን ያደርጋል?
የአክራሪነትን ሽብር፣ የዘረኝነትን ግጭት እየተከላከለ፤ የዜጎችን ቅሬታና ሰላማዊ ተቃውሞ ለማስተናገድ፤ እንዲሁም… የዜጎችን ነፃነትና መብት ለማስከበር መትጋትና መጣር ይችላል። ግን፤ ይሄ አድካሚ ነው። ከዚያ ይልቅ፤ አክራሪነትንና ሽብርን፤ ዘረኝነትንና ግጭትን በመዋጋት ሰበብ፤ ቅሬታዎችንና ተቃውሞዎችን በሙሉ እያፈነ ‘አይነኬ ገናና መንግስት’ ለመሆን መሞከር ይቀላል።
በእርግጥ፤ ‘ቀላልነቱ’ ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው። አፈናው ሲደራረብና የዜጎች እሮሮ ሲባባስ፤ ውሎ አድሮ፣ የተቃውሞ ድምፅ ግንፍል ብሎ መውጣቱ አይቀርም። ግን፤ ምን ዋጋ አለው? ያቺ ታፍና የነበረች የተቃውሞ ድምፅ፣ እንድትጎላ በመጓጓትና እንዳትደበዝዝ በመስጋት፤ መንግስትን የሚቃወም ማንኛውንም ነገር (አክራሪነትንና ዘረኝነትንም ጭምር…) የማስተናገድ አዝማሚያ ይሰፋል። የአቋራጭ መፍትሔ ምርኮኞች እንሆናለን፡፡
ያው፤ በበርካታ አገራት እንደታየው፤ የዜጎች የተቃውሞ ድምፅ፣ በአክራሪዎች ወይም በዘረኞች ድምፅ እየተዋጠ፣ ነገሩ ሁሉ ይቃወሳል። ብዙ ሰዎች በስጋት ይጨነቃሉ።
ያኔ፣ የመንግስት ስራ፣ አክራሪነትንና ዘረኝነትን መከላከል ሳይሆን፣ እግረመንገዱን አገሬውን በአፈናና በጉልበት ዝም ለማሰኘት መሯሯጥ ይሆናል። ኡደቱ ይቀጥላል። የታሪክ ጉዞ ሳይሆን፣ የታሪክ አዙሪት ውስጥ እየተሽከረከሩ፤ መከራን እየደጋገሙ ማየት!

ADDIS ADMASS

6 Comments on ““የተረገመ አዙሪት” – አገሬውን በአፈናና በጉልበት ዝም ለማሰኘት መሯሯጥ”

  1. This is a wonderful advice for both the protesters and the government bodies; they have to read and use wisely if they love Ethiopia. If not the fire will destroy all of us because if a gunman is supposed to fire into himself it kills him without considering his ownership. Please think of the next generation we are going to this earth soon; being selfish will leave you to stressful life.

  2. አዲስ አበባዎች ሊነሱ ነው!!!!
    የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚከተሉትን መፎክሮች አንግበው
    መንግስት በአገሪቱ ላይ እየወሰደ
    ያለውን መንግስታዊ ውንብድና ለመቃወም እየተዘጋጁ መሆናቸው
    ታወቀ፡፡ የውስጥ ወሬ
    ምንጮቻችን እነደገለፁት መቸ በይፋ እንደሚጀምሩት በምስጥጢር
    ተይዝዋል በማለት ክፍለ ሀገር
    ያሉ(በኦሮሚያ፣በአማራ፣በደቡብ፣…) የተጀመረውን ትግላቸውን
    አጠናክረው እንዲቀጥሉ
    አሳስበዋል፡፡
    ማህበረሰቡ፡-
    1. በኦሮሚያና በአማራ እየተደረገ ያለው ደም ማፋሰስ ይቁም!
    2. በልማት ስም ህዝብን ከይዞታቸው ማፈናቀሉ ይቁም!
    3. መሬት የህዝብ እንጂ የመንግስት አይደለም!
    4. የብሄር ፖለቲካ ይቁም! ሆን ተብሎ ብሄርን ከብሄር የማጋጨት
    ሴራው ይምከን!
    5. መንግስት የከፋፍለህ ግዛው ስትራትጅውን ያቁም!
    6. በርሀብ አለንጋ እየተገረፉ ያሉ ዜጎች አስቸኳይ መፍትሄ ይሻሉ!
    7. የታሰሩ የፖለቲካና የህሌና እስረኞች ይፈቱ!
    8. የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደቦታው ይመለስ!
    9. የፍትህ ስርአቱ ይስተካከል!
    10. መንግስት አይን ያወጣ ውሸቱን ያቁም!
    11. መሰረት የሌላቸው መግለጫዎች፣የውሸት ፕሮፖጋንዳዎች፣ዛቻና
    ማስፈራሪያዎች
    ይቁሙ! ህዝቡ እውነቱን የውቃል! ማንም አያምናችሁም!
    12. ኢህድግ የሚሰማ ጀሮ፣የሚያይ አይን የለውም! በእብሪት
    ተወጥሯል!
    13. ኢህድግ የበሰበሰ ድርጂት ነው! ህዝብን ማሰተዳደርና አገርን
    መምራት ተስኖታል!
    14. ታፍነን አንግዛም፣አባቶቻችን አላወረሱንም!
    15. ዝርፊያው ይቁም!ሙሰኞችና ኪራይ ሰብሳቢዎች ለፍርድ
    ይቅረቡ!
    16. በጎንደር ዳርቻ ለሱዳን በሚሥጥር የተሰጠው መሬት ይመለስ!
    17. አሸባሪው ህዝብ ሳይሆን መንግሰት ነው!
    18. አሰመሳይ መንግስት ሊሆን አይችልም!
    19. የአንድ ብሄር የበላይነት ይቁም!
    20. መንግስት ውሸት፣ማጭበርበር እና ሌብነትን ባገሪቱ ላይ
    አንግሷል!
    21. ባገሪቱ ላይ ያሉ አደገኛ እፆች(ጫት፣ሲሻ፣አሸሽ፣…) ይወገዱ!
    መንግስትም ከማምረት
    ይቆጠብ!
    22. ህገመንግስቱ ይከበር! አፋኝ ህጎች ይሻሩ!
    23. ህንፃ፣ባቡር፣… ለኛ ምናችንም አይደለም፤በቅድሚያ ነፃነት!
    24. መንግስት የግል ጥቅሙን ትቶ በአገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ
    ላይ የጋራ ውይይት
    ይጥራ! ከማንኛውም ተቃዋሚ ሀይል ጋር ብሄራዊ እርቅ ያካሂድ!
    25. የሽግግር መንግስት ይቋቋም! ፍትሀዊ ምርጫ እንደገና
    ይካሄድ!
    26. ዳግመኛ ደርግን አናስተናግድም!
    ተማሪዎች፣መምህራን እና የመንገስት ሰራተኞች፡-
    1. መንግስት ማህበረሰቡን ማጋጨት ያቁም!
    2. በማህበረሰቡ ላይ የሚደረገው ማዋከብ ይቁም!
    3. ፍታዊ የሀብት ክፍፍል ይኑር!
    4. በአገሪቱ ላይ ወጥ የሆኑ መመሪያች ይኑሩ!
    5. የትምህርት ጥራት ይጠበቅ!
    6. መልካም አስተዳደር እንሻለን!
    7. የታክስ ማሻሻያ ይደረግ!
    8. የደመወዝ ጭማሪ ይደረግ!
    9. የአርከን ጭማሪ ይፈቀድ!የደረጃ እደገቱ ማሻሻያ ይደረግ!
    10. የውሎ አበል፣የትርፍ ሰአት ክፍያ፣የትራንስፖርት እና የቤት
    አልዋንስ ይሻሻሉ!
    11. ስራ ቅጥር/ስልጣን በደብዳቤ ሳይሆን በውድድር/በብቃት
    ይሁን!
    12. መንግሰት የውሸት ድራማ መስረቱን ያቁም!
    13. መንግስት ከመንገድ/ከህንፃ ይልቅ በቅድሚያ ማህበረሰቡን
    ያልማ!
    14. መንግስት ነጋዴ ነው!
    15. መንግሰት የህዝብ አገልጋይ አንጅ ህዝብ የመንግሰት አገልጋይ
    መሆን የለበትም!
    16. አገሪቱ “አርቲፊሻል” እድገት ላይ መመስረት የለባትም!
    ማጭበርበሩ ይብቃ!
    17. ከ2 ጊዜ በላይ ታክስ እየተደረግን ነው! (ደመወዝ ሲከፈል-የስራ
    ግብር፣እቃ ስንገዛ-ቫት
    እና የሰርቪስ አገልገሎት፡፡ ስለሆነም 35%+15%+5%=55%
    ደመወዛችን ታክስ ይደረጋል!)
    በቃ! በቃ! በቃ! በቃ! በቃ! በቃ!………………..
    እነኢህን መፎክሮች በጋራ በማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ
    እነዳሰቡና መንገስት ለሚወስደው
    ማንኛውም እንቅስቃሴ እነደማይታገሱትና የመግደል ሙከራ
    ካደረገም አስፈላጊውን ምላሽ
    እነደሚያደርጉ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ አንደሆነ በምሬት
    ተናግረዋል፡፡ ማንም ሀይል
    እነደማያደራጃቸው የገለፁ ሲሆን የአመፁ መንስኤ የመንግሰት
    ብልሹ አሰራር፣አፈና፣ማዋከብ፣
    መግደል፣ማፈናቀል፣ግፍ፣አድሎ፣ማሰር፣የኑሮ ውድነቱ፣ፍትህ
    ማጣቱ፣ብሄርን ከብሄር
    ማጋጨቱ፣የስነ ልቦና ጫናው ተደማምረው ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት
    ስለፈጠሩባቸው ከዚህ የባሰ
    ምን ይመጣል ወይ ሞት ወይ ነፃነት በማለት ከሰፊው የኢትዮጵያ
    ማሀበረሰብ ተቃዋሚዎችጋር
    ለመቀላቀል እነደወሰኑ ለወሬ ምነጫችን ተናግረዋል፡፡
    የመንግስትን ሀይል ለመቋቋምም ሰላማዊ አመፁ ለሊት ላይ
    በመጀመር መንግሰትን አከርካሪውን
    ለመስበር አስበዋል፡፡ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል (ሴት፣ወንድ፣
    አዋቂ፣ህፃን፣አረጋውያን፣
    የሀይማኖት አባቶች፣መምህራን፣የቢሮ ሰራተኞች፣ሙስሊም፣
    ክርስቲያን፣ሹፌሮች፣ነጋዴዎች፣ጎዳና ተዳዳሪዎች፣ተማሪዎች….) ወደ
    ጎዳና መውጣት
    የመጀመሪያው የሰልፉ/የአመፁ ምእራፍ ነው፡፡ ማንኛውንም ንብረት
    ማውደም “በህግ” የተከለከለ
    ነው፣ከላይ የተዘረዘሩትን መፎክሮች ማሰማት ብቻ በቂ ነው፡፡
    መምህራንና የመንግስት ሰረተኞችም
    ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምረው የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉም
    አበክረው ገልፀዋል፡፡መቸም
    ቢሆን ከዚህ በኋላ ትግሉ እንደማይቆም አክለው ገልፀዋል!!
    በተጨማሪም ከህዝብ አብራክ የወጣውን ፌድራል ፖሊስንና
    መከላከያ ሰረዊትን ከጎናቸው
    እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡
    ሸር በማድረግ የትግሉ አጋር ይሁኑ!
    ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!!!!!

  3. መቼ መንገድ ሆነ
    መች ህንጻ ነውና
    ይህ ቆሞ’ምናየው
    የሰው አጥንት ጠጠር
    በሰው ደም ማቡኪያነት
    የተገነባ ነው
    ያንን “ባለቤቱን”
    ሁሌ’ሚያባንነው

  4. የኦሮሞ ወድሞች ጠላቶቻችን ወያኔዎች አማራና ኦሮሞን አጥፍተውን እና አጠፋፍተውን እነሱ የትግራይን ንፃነት አውጀው ለመቀመጥ ያላቸው አሳብ ግልፅ እየሆነ ስለመጣ ይህነን ክስተት ተከትሎ ለሚፈጠረው ሁኔታ ክወዲሁ ዝግጅት ማድረጉ ችላ የማይባል ጉዳይ ነው።

  5. ወያኔ አንድነት ያጠፋዋል/ያመዋል/ያሰጋዋል
    ነገር ግን ወያኔ ሻቢን ግብጽ፣ሱዳን ኢትዮጵያን ከማጥፋት ወደላለ አይሉም
    ጎንደርን ወሎን አፈራረሱ በታተኑ
    አዎ ገብሩ አስራት በስልጣን በነበረበት ወቅት በሁመራ የሠራው ደባ ሲጋለጠ 40 ወጣቶችን በእስር ቤት ውስጥ መግደሉ መቼ ይሆን ይህ ነፍሰገዳይ ዛሬ በእኛ መካከል መኖሩ ሳይ ያመኛል እንድታውቁት ላልሰማ አሰማ

    ሳተናው አሊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*