የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው::በዲሾች ላይ የተጀመረው ነቀላ/ጦርነት ቀጥሏል::ጃኪ ጎሴ የወያኔን ስራ በመቃወም በ2 ሃገራት የሚያካሂደውን ኮንሰርት ሰረዘው:
የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው::በዲሾች ላይ የተጀመረው ነቀላ/ጦርነት ቀጥሏል::ጃኪ ጎሴ የወያኔን ስራ በመቃወም በ2 ሃገራት የሚያካሂደውን ኮንሰርት ሰረዘው::#Ethiopia #OromoProtests #AddisAbabaMasterPlan #MinilikSalsawi
ከአዲስ አበባ 60 ኪሎሜትር ላይ በምትገኘው ጫንጮ ከተማ ሕዝቦ አደባባይ በመውጣት ወያኔን ሲያስጨንቀው ታይቷል::በተለያየ ክፍለሃገራት የተሰማሩ የወያኔ ሰራዊት ልብስ የለበሱ ደም መጣጭ የአግኣዚ ጦር አባላት ከሕዝቡ ጋር ተፋጠው ይገኛሉ::በጊንዶ ምእራብ ሸዋ ሕዝቡ ፊትለፊት የወያኔ አግኣዚ ጦርን ካለምንም ፍራቻ በመጋፈጥ ለነጻነቱ ያለውን ቀናኢነት አሳይቷል::ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ተቃውሞ በተሰማባቸው አከባቢዎች የሳተላይት ዲሽ ነቀላ እየተካሄደ ይገኛል::ይህ በሳተላይት ዲሽ ላይ የሚደረገው ጦርነት እንዳበቃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እንደሚዘመት ታውቋል:: በእስራኤል ቴላቭኢቭ የሚገኘው ጃኪ ጎሴ የተባለው ዘፋኝ በተቃውሞ ሕይወታቸው ላጡ የኦሮሞ ልጆች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጾ በእስራኤል እና ስዊዲን ሊያካሂደው ያሰበውን ኮንሰርት በመሰረዝ ከሰማእታት ኢትዮጵያውያን ጎን መቆሙን አረጋግጧል::
#Ethiopia : Jacky Gosee cancels his concerts to pay tribute to the victims of the recent protest http://www.hahuvideos.com/watch.php?vid=5d8f21c66 … … #OromoProtests
እርማት :- ጃኪ ጎሲ በአሁን ሰአት አትላንታ የሚገኝ ሲሆን ይህን ቭድዮ ያስተላለፍኩት በአይሲስ ወገኖቼ በታረዱ ጊዜ እንጂ አሁን አይደለም ይህን ቭድዮ ያወጣው የወያኔ አሽቃላጭ ድህረገጽ አይቼ ራሴ ገርሞኛል ሲል ተናግሯል:: Jacky Gosee cancels his concerts to pay tribute to the victims of the recent protest http://www.hahuvideos.com/watch.php?vid=5d8f21c66 … #OromoProtests

