ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ ማስተር ፕላኑ እና ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ::

ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ መጥራታቸውን አቶ ነገሰ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ የጠሩት ሰልፍ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት እየወሰደው ያለውን እርምጃ፤ እንዲሁም መንግስት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም ያለመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉ ላይ በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ መንግስት እየወሰደው ያለውን እፈና እና እርጃዎቸ እንደሚያወግዙ ምክትል ሊቀመንበሩ ተገልፆአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በጋራ የሚያደርጉት ሰልፍ መነሻውን ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አድርጎ፣ በቸርቺል አደባባይ የሚያልፍ ሲሆን መዳረሻው ኢትዮ-ኩባ አደባባይ መሆኑን ታውቋል፡፡ መንግስት እየወሰዳቸው ባሉ የተሳሳቱ እርምጃዎች ሀገራችን አጣብቂኝ ውስጥ መሆኗን የገለፁት አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ሀገራችን ካለችበት ችግር ለማውጣት ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቆሙና በሰልፉም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሰልፉ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ ላይ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡

15 Comments on “ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ ማስተር ፕላኑ እና ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ::”

  1. አይ መጨነቅ ! ! ! ኧረ አርበኞች ግቦት ሰባት እና OLF አንድ ዕዝ ፍጠሩና ይኽንን ሕዝብ ድረሱለት ! ! ! !

  2. ኣፈር ብሉ ኣንድም ቀን ጥሩ ነገር ኣታስቡም ሰለ ኢትዮጵያ ሰላም እድገት ኣታስቡም መቼ ነው ወደ ጤናማ ሰው ወይ ፐርቲ የምትመለሱ ለኢትዮጵያ ሰላም ነው የሚስፈልጋት

  3. ደደብ ወያኔ ነክ

    የአሸባው የወያኔ ቡድን ከሥር መሠረቱ መወገድ ያለበት የኢትዬጵያ አረም ነው።

  4. ኮድ 2-81044 እባካችሁ ወያኔዎች በግለሠብ ታርጋ ወንጀል መሥራት ይቁም

    ከሜቴክ

  5. Gobez Tru new, keqena negeru beziyaw wede betemengst megbat new. Zm blen bnqemeTm ke woyanie gdya, afena alameleTnm, nuro seqeqen new yalenew, kezewetr sqay and gizie ho blo andefarso woyanien meqber ejg yeteshal mrca new.

  6. Lemegbabat
    le lu li la lie l lo
    candle= Sama fork= Suka capital S
    skin color= yeqoda qelem
    cows= lamoC ability= Clota
    we swim= eNa enwaNalen or
    eña enwañalen
    ball= kuas star= kokeb
    lifeless= guz cry= uuta
    ear= jero brave= jegna
    buyer= gex tv= telievixn
    soft drink= leslasa meTeT
    salt= cew shoes= camoC

  7. ቀይ ሽብር ከ1997 ምርጫ በሃላ ጀግና ነኝ ባዩ አፈር ትራሡ የተባለለት መለሥ የበላው ይመለሥና በይፋ እንደገና እንዳሥጀመሩት ምሁራን ይናገራሉ።

  8. ምርጥ ኢትዮጵያዊያን የኦሮሞ ጂምር ውጤቱ
    ለድል ያበቃናል ወያኔ በቆፈርክው ጉርጓድ
    ትገባልህ አማራ ከኦሮሞ ጋር በዓድነት ወያኔን
    ለፍርድ ያቀርባል!!!

  9. Good start … Amhara & Oromo are coming to the same page.

    Weyane will leave the country, if amhara and Oromo sit down together.

  10. It is a Great Leap Forward, this shows that what binds people together is a cause not ethnicity. Actually, I am the one who initiated the idea of working together on common goals, one of which is calling joint front peaceful protest in Addis Ababa, to deliver strong message to the public,if not for Woyane. I would like to invite Addis Ababa residents and who feel concerned about the current situation to participate in the peaceful demonstration and I call up on every one to stay away from any violent behaviour. Bear in your mind that violence can’t be a response for a violence! See you by Subday morning.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*