የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላንን ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል በርካታ ወረዳዎችና ከተሞች እያቀረቡት ያለው ሠላማዊ ጥያቄ በሰከነ መንገድ መልስ ለመስጠት ከመሞከር ይልቅ ተመጣጣኝ ያልሆነ ሀይል በመጠቀም ጥያቄውን ለማፈን እየተሞከረ ነው፡፡ በዚህ ሂደትም ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ለቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎችም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ሰሞኑን ከሚወጡት መግለጫዎችና የመንግስት ባለስልጣናት ቃለመጠይቆች እንደተረዳነው ጥያቄዎቻቸውን በሃይል ለመመከት ከመዛትና ዜጎችን ከሰው በታች አውርዶ ቁጣን በሚጋብዝ መልኩ ከመጥራት በዘለለ ሀላፊነት እንደሚሰማው አካል ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግ ዝግጁነት እንደሌለ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሁሌም እንዲከበር የምንጠይቀውን የሀገሪቱ ሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነውን ሕገ-መንግስት የሚጻረር ነው፡፡
በዚህ ሂደት በጥቂቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሕገ-መንግስቱ አንቀጾች ተጥሰዋል
1. የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 15 የሕይወት መብት
‹‹ማንኛውም ሰውበሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነበስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› ቢልም ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ8 ዓመት ልጅ አንስቶ እስከ የ80 ዓመት አዛውንት ድረስ ሕይወት እየተቀጠፈ ነው፤ እስከዛሬ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በሶስተኛ ወገን ማረጋገጥ ባይቻልም ጉዳዬን በቅርበት የሚከታሉ ሰዎች እንደዘግቡት ወደ መቶ እየተጠጋ ይገኛል፡፡
2. የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 15 የአካል ደኅንነት መብት
‹‹ማንኛውም ሰውበአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስየመጠበቅ መብት አለው፡፡ ›› አሁንም ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ በጥይት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ ድብደባ እና አላግባብ አንግልት የደረሰባቸውንም ቤት ይቁጠራቸው፡፡
3. አንቀጽ 24.1 የክብርና የመልካም ስም መብት
‹‹ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው፡፡ ›› እየሆነ ያለው ዜጎችን አጋንንት እያሉ መጥራት፣ ጥፋተኛ ተብለው በሕግ ያልተፈረደባቸውን አሸባሪ እያሉ ክብራቸውን በሚዲያ መግፈፍ ነው፡፡
4. አንቀጽ 30.1 የመሰብሰብ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት
‹‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በሕዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ወይም በመካሔድ ላይ ያለ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምን፣ ዴሞክራሲያዊ መብቶችንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ፡፡ ›› ቢልም መንግስት ይህን የህገ መንግሰቱን አንቀጽ በመጣስ ብዙ ሰብዓዊ ጉዳቶችን አድርሷል፡፡
ዜጎች ለመረጃ ቅርብ በሆኑበት በዚህ ጊዜ መንግስት እያደረጋቸው ያሉትን ተግባራት መካድ፣ እንዲሁም እንደሌሉ አደርጎ ለማስተባበል መሞከር ብዙ ኃላፊነት የሚጠበቅበት መንግስት የሚያሰገምትና ትዝብት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ይህ የመንግስት ግዴለሽነት ብዙኃን ዜጎችን እየገፋ ከመስመር እያስወጣ ነው፡፡ ሰላማዊውን የሕዝብ እንቅስቃሴ ወደ አመጽ እና ወደአልተፈለገ ዕልቂት ከመግፋት ይልቅ የተቀናጀ የጋር ማስተር ፕላኑን መሰረዝ፣ በዚህ ሒደት ጥፋት የፈጸሙ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትን ለፍርድ ማቅረብ፣ የግል ተበዳዮችን መካስና ሌሎች አስፈላጊ የመፍትሔ እርምጃዎችን ሁሉ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ ሁልጊዜም እንደምንለው በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄ ማቅረብ ወንጀል አይደለም፡፡ መንግሰት በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ከሚጠይቁ ዜጎች ጋር እልህ አይጋባ ፣ ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸው ይከበሩ ፣ የመብት ጥሰት ድብደባ እና ግድያው ይቁም፡፡ ሕገ-መንግስታዊነት የታሰርንለት፣ ከሀገር የተሰደድንለት፣ ብዙ ዋጋ የከፈልንበትና አሁንም እየከፈልንበት ያለ ዐሳብ ነውና በሀገሪቱ ህጋዊነት እንዲሰፍን ህይወታቸውን እስከመስጠት ድረስ ዋጋ ለከፈሉ ዜጎች ክብር እንሰጣለን፡፡ ለሕገ መንግስታዊ ስርዓት መስፈን ዜጎች የከፈሉት ዋጋ እጅግ ብዙ እና ከበቂ በላይ ነውና ተጨማሪ ሰብዓዊ ዋጋ መክፈል ሳያፈልገን ሕገ መንግስቱ እንዲከበር አንጠይቃለን፡፡
ሕገ-መንግስቱ ይከበር!
ወያኔ በህገ አራዊት ተቀርፃ ያደገ በመሆኑ ቀይ ሽብር በገሀድ በአደባባይ አሁንም ህዝባችን ለመሬቱ ለነፃነቱ እየሞተ ነው ፈጥነን ወያኔን እናሥወግድ።
ባልተደራጀህበትና ማጠፊያው በሌለህ ሁኔታ ክልላቸውን ከኢትዮጵያ ቆርሰው ነፃና ሉዓላዊ አገር ለማድረግ የሚጥሩ ጠላቶችን ሳታስተውል ከደገፍህ፣ ማርሽ ይቀይሩብህና አንተም አገርህም የማይቀለበስ አደጋ ላይ ሰለምትወድቁ ጠንቀቅ በል!
ከአስተዋይ በቀለ
ስማ የእናት አገር ኢትዮጵያ ወገን ሁሉ ! ! !
ከ 7 ሺህ ዘመን በላይ መንግሥት አቋቁማ የኖረችው የእናት ቅድስት አገር ኢትዮጵያ ሕልውና ጉዳይ ስለሆነ፣ ውስጡንና ጥቁረቱን በማታቀው ጉዳይ ዝም ብለህ አትማገድ። ለዚህ እንጨትና ጭራሮ አለ። የዑደተ-መሬትን ሕያው ሃቅ የማያውቁና ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ ብለው የሚያምኑ ደንቆሮዎች፣ ግብዛንና ባንዳዎች አታልለው እንዳያሰልፉህ ተጠንቀቅ።
ስማ ! ፖለቲካ ሁሉን ነገር በውል ልብ ማለትን ይጠይቃል። እንደ እህልም በወንፊት ይነፋል- በሰፌድም ይበጠራል። ቱምቢም ተዘርግቶ ይለካል። አላምጦ በማስተዋል ወለላና ፍቱን አቋም ይዞ ይሄዳል። ይህን ሃቅና መላ ጨርሶ እንዳትዘነጋ !!!!
የዋህነትን ጢም ብሎ በተጋተ ኮስማና አመለካከት ብቻ፣ ቅድስት ኢትዮጵያን በናቀና ባራከሰ፣ ሰንደቅ ዓላማዋን በአደባባይ በረገጠና በቀደደ፣ኢትዮጵያዊያንን ገደል በጣለ፣ ደም ባፈሰሰና ባፈናቀለ በክልል ትዕቢት የሚባዝንን ዘረኛና ጠባብ ትርምስምስና ስውር ሴራ ከተመለከትክ፤ ኤርትራችንን ያስገነጠለውን የትናንቱን የመሀል አገር ስህተት በውል ያልተረዳህና የዛሬውንም ኢትዮጵያ- አድን ቆራጥ ትግል ያልተገነዘብህ ስለሆነ ከእንግዲህ አቋምህን በአስቸኳይ አስተካክለህ አልሞትኩም ብለህ ተደራጅ-ታጠቅ-ዝመት።
ልብ በል የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ! ! !
መከሩ ደርሳል። ማጭዱ ግን ኢትዮጵያ ፣ኢትዮጵያዊነትና አረንጓዴ-ቢጫ- ቀይ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ብቻ ነው።ይህም አንተ አገር ወዳዱ ነህ።እናት አገርህን አፍርሰው ጠባብ ዘረኛነታቸውን አገር ለማድረግ የተነሱና የሚተራመሱን ሁሉ በእንጭጩ መደምሰስ አጣዳፊ ግደታህ ነው። ክንድህ አበርታ ወደፊት ! ድል ምንጊዜም ያንተ ነው።
ወያኔን ፣ ሻቢያን፣ ገንጣይ የክልል ዘረኞችንና ባንዳዎችን ሁሉ እንደመስሳለን ኢትዮጵያ ወይም ሞት !
Tru belehal mengie, woyanien ena jeliewochun sngedl ena habtachewn, betesebachewn snaTeqa bcha new neTa yemnweTa, woyaniem meqabr mnchlew. Mot lewoyanie.
Almen aneTaTren woyanien ena jeliewochun enmta, engdel, meqabr enasgebachew. Mot lewoyanie
Yh qoshasha yedurye yewoyanie qaqa enj ye eña yehon yaTedeqnew ena ye mnakeberew mnm aynet hge mengst yelenm