በአማራ ከልል የህወሀት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው የብአዴን ኮሚኒኬሽን ሐላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የስርጭት አድማሱ በአዲስ አበባና ዙሪያ ብቻ በተገደበው ሸገር ኤፍ.ኤፍ.ኤም ራዲዮ ቀርበው ‹‹ሕዝባዊ ንቅናቄ እያደረገ ባለው የአማራ ክልል ህዝብ ላይ የመከላካያ ሰራዊት እርምጃ እንዲወሰድ ታዟል›› ብለዋል!! ይህ የዘር ፍጅት የታወጀው በምእራብውያን አጋዥነት በቆመው የህወሀት ስርዓት መሆኑ አፅእኖት ሊሰጠው ይገባል!! በተያያዘ ዜናም ዛሬ ማምሻውን ሀይለማሪያም ደሳለኝ […]

“መንግስት የፀረ – ሽብር አዋጁን ተቃውሞን ለማፈን እየተጠቀመበት ነው” በሽብርተኝነት ተጠርጥረውና ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸኳይ እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግስትን የጠየቁት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፤ መንግስት የፀረ ሽብር አዋጁን …

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፤ መንግስት የፀረ ሽብር አዋጁን ተቃውሞዎችን ለማፈን እየተጠቀመበት ነው ብለዋል፡፡ Read more »

በማሕሌት ፋንታሁን

መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ተቋማት ጋር ማቆራኘት ሳያስፈልገው የጻፈው ጽሑፍ ብቻ ተጠቅሶበት የተከሰሰ እና የተፈረደበት ብቸኛ ጋዜጠኛ ነው – ተመስገን ደሳለኝ። በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተመሠረተችው ፍትህ ጋዜጣ ጥቂቶቹን የግል ሕትመት ሚዲያ ውጤቶች የተቀላለችው በ2000 ነበር። ከምርጫ 97 በኋላ የተከሰተውን የግል ሚዲያ እጥረት አሳስቦት እና የበኩሉን ለመወጣት ብሎ ነው ፍትሕን ለመመሥረት የተነሳሳው። ፍትሕ ጋዜጣ ሕትመት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2004 ሐምሌ ወር (ላይ እስክትታገድ ድረስ) ድረስ ከዓመት ወደ ዓመት የሕትመት ብዛቷ እየጨመረ መጨረሻ አካባቢ እስከ 35ሺ ኮፒ ትታተም ነበር።

ማንኛውም ዓይነት ቅድመ ሳንሱር እንደሌለ በሚደነግገው ሕገመንግሥት መተዳደር ያለበት ፍትሕ ጋዜጣን የሚያትመው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሐምሌ 13/2004 ዓም እትም ላይ ስለ መለስ ዜናዊ የተጻፈ ዜና ካልወጣ እንደማያትሙ አሳወቁ። ይህን የሰማው ተመስገን እያረጉ ያሉት  ቅድመ ሳንሱር መሆኑን፣ ይህ ደግሞ በሕገመንግሥቱ የተከለከለ መሆኑን ከገለጸላቸው በኋላ የታዘዙትን 30ሺ ኮፒ ካተሙ በኋላ እንዳይሰራጭ ከፍትሕ ሚኒስቴር በተላለፈ ትዕዛዝ መሠረት ማገዳቸውን እና የታተመው ጋዜጣም መወረሱን በደብዳቤ ገለፁ። ለ30ሺ ኮፒ ሕትመት፣ ለጸሐፊዎች የሚከፈል እና ለተለያዩ አስተዳደራዊ  ወጪዎች የወጣው ገንዘብ ወደ100ሺ ብር የሚጠጋ ከስሯል። ነሐሴ 2 ቀን  2004 ክስ እንደተመሠረተበት ፋና ዜና ላይ እንደሰማ የሚናገረው ተመስገን፣ በዜናው እንደሰማውም በቀጣይ ቀጠሮ ነሐሴ 9 ቀን 2004 ፍ/ቤት ቀረበ። በ2003 እና በ2004 በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በወጡ 5ት ጽሑፎች ሦስት ክስ እንደቀረበበት ተነግሮት የዋስትና መብቱንም ተነፍጎ የዛኑ ቀን ወደ እስር ቤት ገባ። ለስድስት ቀናት በቃሊቲ ጨለማ ቤት ከቆየ በኋላ ባልተጠበቀ ሰዓት እና ምክንያቱ ሳይነግው  ነሐሴ 16/2004 ከእስር ተለቀቀ። በኋላ ሁላችንም እንደሰማነው ከእስር የተለቀቀው ክሱ ተቋርጦለት መሆኑን ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን የቀረቡበት ክሶች 1ኛ) ወጣቶች በአገሪቱ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱ ላይ እንዲያምፁ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር፣ 2ኛ) የሀገሪቱን መንግሥት ሥም ማጥፋት እና የሐሰት ውንጀላ፣ 3ኛ) ክስ የሐሰት ወሬዎችን በማውራት ሕዝብን በማነሳሳት ወይም አስተሳሰባቸውን ማናወጥ ሲሆኑ ይህን ክስ ሊያስመሠርቱበት የቻሉት ጽሑፎች ደግሞ 1) የፈራ ይመለስ (በተመስገን ደሳለኝ) 2) የሁለተኛ ዜግነት ሕይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ? (በተመስገን ደሳለኝ) 3) መጅሊሱና ሲኖዶሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ (በተመስገን ደሳለኝ) 4) ሞት የማይፈሩ ወጣቶች (በተመስገን ደሳለኝ) እና 5) የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመጨፈር የሚሉት ናቸው።

ፍትሕ በዚ መልኩ ከሕትመት ከታገደች በኋላ ተሜ እጅ እና እግሩን አጣጥፎ አልተቀመጠም ወይም መሰደድን አልመረጠም። በ2005 ፍትሕን በአዲስታይምስ መጽሔት መልክ፣ እሱም እንዲዘጋ ሲደረግ በልዕልና ጋዜጣ እውነትን እንድናነብ ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን ለፍቷል። ልዕልናም ቀኗ ደርሶ ከሕትመቱ ዓለም ስትሰናበት ደግሞ በ2007 በግሉ ዘርፍ ይታተሙ ከነበሩ ተመራጭ ጥቂት መጽሔቶች እና ጋዜጦች ጋር ክስ ተመሥርቶባቸው እንዳይሠሩ ከታገዱት የሕትመት ውጤቶች መሐል አንዷ በሆነችው ፋክት መጽሔት ሥራውን ቀጥሎ ነበር።

በነሐሴ 13፣ 2004 ተቋረጠ የተባለው ክስ መቀስቀሱን አሁንም እሱ በሌለበት በታኅሣሥ ወር 2005 የዋለው ችሎት በፋና ሬዲዮ መዘገቡን ሰማ/ን። በቀጣዩ የቀጠሮ ቀን ሲቀርብ የ50ሺህ ብር የዋስትና ብር አስይዞ ክሱን ከውጪ ሆኖ እንዲከታተል ተፈቀደለት። ክሱን እየተከታተለም ነው ልዕልና ጋዜጣን እና ፋክት መጽሔትን ለኛ ላንባቢዎቹ ሲያደርስ የነበረው። ታኅሣሥ 2005 የተንቀሳቀሰበትን ክስ በዋስትና ሲከታተል ቆይቶ፤  በጥቅምት 3፣ 2007 ጥፋተኛ የተባለው እንዲሁም ጥቅምት 17፣ 2007 ላይ ደግሞ የ3 ዓመት ፍርድ የተፈረደበት።

ተመስገን የሥራ ሰዓት እና የእረፍት ሰዓት የለውም። ብዙውን ጊዜውን በመጻፍ ወይም በማንበብ ነው የሚያሳልፈው። የጻፈውን የኖረ እና እየኖረ ያለ ጋዜጠኛ ነው።

ዝዋይ ከመሄዱ በፊት ቃሊቲ በነበረበት ጊዜያትም ሆነ ዝዋይ ከሄደ በኋላ ተመስገን፣ ሌሎች እስረኞች እንዳይቀርቡት ይደረጋል። ቃሊቲ እያለ የአልሻባብ አባል ተብለው በሽብር ተከሰው ከሱ ጋር የሚኖሩ እስረኞች ከሱ ጋር ካወሩ ወይም ወክ ሲያደርጉ ከታዮ “እንዴት ከአሸባሪ ጋር ትሆናላችሁ?” ይባሉ እና የተለያዩ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርስባቸው ነግረውታል። የዝዋዩ ደግሞ የባሰ ሆኖ ነው ያገኘው። ከሱ ጋር ያወራ ማታ ማታ እየተወሰደ ይደበደባል። ይህን በመፍራት ብዙ እስረኞች ከሱ ጋር መሆን ይፈራሉ። መጽሐፍ አይገባለትም። ሕክምና ለማግኘት ሲጠይቅ “ቆይ ያንተን ጉዳይ እየተነጋገርንበት ነው”  ከሚል ውጪ ያገኘው ምላሽ ስለሌለ ከጀርባ ሕመሙ ስቃይ ጋር አብሮ ይኖራል። ምንም ዓይነት መጽሐፍት አይገቡለትም። ከሌሎች እስረኞች ተውሶ ማንበብም አይችልም። እሱ ያለበት ዞን ላይብረሪ የለም። ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ እንዳይጠይቁት ይከለከላሉ። ብዙ ጓደኞቹ እና ወዳጆቹ ብዙ ርቀት ተጉዘው ከእናቱ እና ወንድሞቹ ውጪ እሱን መጠየቅ አይቻልም ተብለው ይመለሳሉ። የዛሬ ዓመት አካባቢ እናቱን እና ወንድሞቹን ጭምር ለሁለት ወር ያክል እንዳይጠይቁት ተከልክለው ነበር። በተለያዩ ጊዜያትም እነዚሁ የቅርብ ቤተሰቦቹ ገብተው እንዳይጠይቁት ተከልክለው ይመለሳሉ። በአንድ ወቅት ታናሽ ወንድሙ የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ ሊጠይቀው በሄደ ወቅት መግባት እንደማይችል ከነገሩት በኋላ በማያቀው ምክንያት በዝዋይ እስር ቤት ፓሊሶች ተደብድቧል።

ምክንያቱን ባይገባኝም ከቅርብ ቤተሰቦቹ ውጪ መጎብኘት የሚፈቀድለትን አንዳንድ ወቅቶች ተከታትለው የሚጠይቁት ጓደኞቹ ብዙ አይደሉም። ተመስገንን የምንወደው ጓደኛችን ከሆነ ከቤተሰብ ውጪ መጠየቅ አይቻልም ብሎ ቁጭ ከማለት ዝዋይ መጠየቅ ከሚፈቀድለት ቤተሰብ ጋር ሄዶ መልዕክት መላክ ወይም መጠየቅ የሚፈቀድበትን ወቅት ጠብቆ መሄድ።

ተሜ በዝዋይ ከሌሎች እስረኞች በተለየ ብዙ ማእቀቦች ተጥሎበት እየኖረ የመንፈሱ ጥንካሬ የሚገርም ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አራት ፅሁፎችን አስነብቦናል። በእስሩ ወቅት ስላገኛቸው የኢትዮጵያ ሶማሌዎች የሚተርክ በሁለት ክፍል “የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና ከዝዋይ እስር ቤት”  እንዲሁም አሁን በኦሮሚያ ስለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ የጻፈው “ሁለተኛው ምዕራፍ” የሚሉት ጽሑፎች ይገኙበታል።

ከዓመት በፊት በላከው በአንደኛው ጽሑፉ እንዲህ ይላል  “…ግና! ይህ መንግሥታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ሕዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡”

ተሜ እንደቃሉ ጉዞውን እስከቀራኒዮ ያደረገ ጋዜጠኛ ነው። አንድ ዓመት ከአምስት ወር በእስር አሳልፏል። የሚወጣበት ቀን እየቀረበ ነው እንጂ እየራቀ አይደለም የሚሄደው። በቀሪዎቹ ጊዜዎች እና ከወጣ በኋላ በብዕሩ የሚያካፍለንን የኢሕአዴግ መንግሥት ገበናዎች ለማንበብ በጣም ነው የምጓጓው። ተሜ ከዚህ በፊት በብዙ ኮፒ ታትሞ ለገበያ ያበቃው “የመለስ አምልኮ” የተሰኘው መጽሐፍ ተወዳጅነትን አትርፎለታል። በ2007 መጨረሻ አካባቢ ደግሞ ከሙያ ባልደረቦቹ እና ከጋዜጠኛ እስክንድር ጋር (ከቃሊቲ እስር ቤት) በአንድነት በተለያየ ጊዜ የተጻፉ ጽሑፎችን በመጽሐፍ መልክ ታትሟል።

ተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኝነት ሥራው በተጨማሪ ያለውን በማካፈል ይታወቃል። ለጓደኞቹ እና ለወዳጆቹ በችግራቸው ጊዜ ከጎናቸው ሆኖ ለመርዳት የሚችለውን ያደርጋል። በምስሉ ላይ ከተሜ ጋር የሚታዩት ሕፃናት ቤተሰቦቻቸው አቅመ ደካማ በመሆናቸው ወጪያቸውን በመሸፈን የሚረዳቸው ናቸው። ወጪያቸውን ከመሸፈን ባለፈም ባለው ትርፍ ሰዓት ያዝናናቸው፤ እንዲሁም በቋሚነት የሚማሩበት ት/ቤት በመሄድ የትምህርት ሁኔታቸውን ይከታተል ነበር። አሁን ጊዜው ተገልብጦ እነዚህ ህፃናት በወር አንድ ጊዜ ከእናቱ እና ወንድሙ ጋር በመሆን ዝዋይ ድረስ ሄደው ይጠይቁታል።

በነገራችን ላይ ተሜ እነዚህን ሕፃናት እና ቤተሰቡን እንደሚያስተዳድር ለፍ/ቤት ቢገልፅ የቅጣት ፍርዱ ይቀንስለት ነበር። ሆኖም ተሜ ጥፋት ስላላጠፋሁ አቅልሉልኝ ብዬ አልጠይቅም ብሎ ምንም አይነት ማቅለያ ሳያስገባ ነው 3 ዓመት የተፈረደበት።

ብርታትና ጥንካሬን ለተሜ እና ቤተሰቦቹ እየተመኘሁ ተሜን በጨረፍታዬን በዚሁ ላብቃ።

ኣማራ ሲሞት ሌላ ኣማራ ሲፈራ ( ሄኖክ የሺጥላ ) እነዚህን ከስር የምትመለከቷቸውን ፎቶዎች ወዳጆቼ ከባህር ዳር ዛሬ ሌሊት ላኩልኝ። ስለ ፎቶዎቹ ምንነት ባጭሩ ላስቀምጥ ተደብዳቢው — አማራ! ደብዳቢው— ወያኔ ትግሬ! የድብደባው ምክንያት— አማራ መሆን! ተጠያቂ —የለም!!! ይህንን ለማስቆም የሚቆም አማራ— …

ኣማራ ሲሞት ሌላ ኣማራ ሲፈራ ( ሄኖክ የሺጥላ ) Read more »

VOA ዋሽንግተን ዲሲ— በሰብዓዊ መብት ጥበቃ እረገድ ያለፈው የአሮፓውያኑ 2015 ዓ.ም. በተለይም ለአፍሪቃ ቀንድ አገሮቹ ኢትዮጵያና ኤሪትራ ጥሩ ዘመን እንዳልነበረ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International) ገለጸ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪቃ ሕዝቦች ሽብርተኛነትን በመዋጋት የከፈሉትን መስዋዕትነት የዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ …

በሰብዓዊ መብት ጥበቃ እረገድ ያለፈው 2015 ዓ.ም. ኢትዮጵያና ኤሪትራ ጥሩ ዘመን እንዳልነበረ፣ አምነስቲ ገለጸ። Read more »

“ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ምንድን ነው? ማበሳጨትን ካላካተተ፣ ሕልውና የለውም፡፡” ~ ሰልማን ሩሽዲ
፩ – ማበሳጨት

‹‹በመስከረም ወር 1997፣ ዢላንድስ ፖስተን የተባለ የዴንማርክ ጋዜጣ ነብዩ መሐመድ ላይ የሚሳለቁ ካርቱኖችን ይዞ ወጣ፡፡ የዚህ ሕትመት ዜና በመላው ዓለም እንደተሰማ በየቦታው ያሉ ሙስሊሞች ቁጣቸውን በአደባባይ መግለጽ ጀመሩ፡፡ የተቃዋሚዎቹ ምክንያቶቻቸው ሁለት ናቸው፤ አንደኛ፣ ነብዩ መሐመድን በምስል መግለጽ በእስልምና ሃይማኖት አይፈቀድም የሚልና፤ ሁለተኛ፣ ካርቱኖቹ በጥቅሉ እስልምናን እና ሙስሊሞችን ከሽብር ጋር አቆራኝተው ይገልጻሉ የሚል ናቸው፡፡  ሠላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በጋዜጣው አዘጋጆች እና በዴንማርክ መንግሥት ላይ ተቀሰቀሰ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሕይወት እስከመቅጠፍ የዘለቀ አመጽ የተቀላቀለባቸው የተቃውሞ ሰልፎች ነበሩ፡፡ ካርቱኖቹ ግን በመላው ዓለም በሚገኙ በሌሎች ጋዜጦች ላይ ለዢላንድስ ፖስተን ጋዜጠኞች የሞራል አጋርነት ለማሳየት በሚል ሰበብ ድጋሚ ታትመው ይበልጥ ተሰራጩ፡፡›› (Paul Sturges, 2006)

ሌላ ምሳሌ እንውሰድ፡፡ አንድ ወንድ “‹ሴቶችን ማስተማር የአገርን ሀብት ማባከን ነው፤ ስለዚህ ሴቶችን ማስተማር ካለብን የቤት አያያዝ፣ ምግብ ማብሰል እና ልጅ አስተዳደግ እናስተምር እንጂ ሌላ ‹የነጭ ኮሌታ› ሥራ የሚያስይዝ ትምህርት ማስተማር የለብንም› የሚል አስተያየት ሲሰጥ በቴሌቪዥን ተላለፈ፡፡ ይህን ተከትሎ የከተማው ሴቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ፡፡ ወንድ አሽከርካሪዎች የሚነዷቸውን መኪኖች ሰባበሩ፡፡ ወንዶችን እያሳደዱ ደበደቡ፡፡” በዚህ የፈጠራ ታሪክ ውስጥ የአስተያየት ሰጪው ሐሳብ ሴቶቹን አበሳጭቷቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለአመጹ እነርሱን አነሳስቷቸዋል ብሎ መደምደም ከባድ ይሆናል፡፡ አማጺዎቹ ሴቶች ስሜታቸውን መቆጣጠርና ሐሳቡን በሐሳብ መመከት ካልቻሉ ድክመቱ የነርሱ የራሳቸው ይሆናል፡፡

የዴንማርክ ፍርድቤት የፈረደውም፣ እኔ በላይኛው አንቀጽ አመጸኞቹ ሴቶች ላይ የሰጠሁትን ዓይነት ብይን ነው፡፡ “እርግጥ ነው ስዕሎቹ የተወሰኑ ሙስሊሞችን ማበሳጨታቸው አይካድም፤ነገር ግን የካርቱኖቹ ዓላማ ሙስሊሞችን ማንኳሰስ አልነበረም›› ብሏል ፍ/ቤቱ፡፡ ሲያብራራውም፣ “ስዕሎቹን አመጽ ወይም ቦንብ የመወርወር ድርጊት በእስልምና ሥም እየተደረገ ነው፤” በሚል መረዳት የካርቱኖቹ ተመልካቾች ድርሻ ነበር ብሏል፡፡ የዴንማርክ ፍርድ ቤት ብይን ለካርቱኒስቶቹ ያደላ ቢመስልም ካርቱኒስቶች ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ክስተቱ አስገድዷቸዋል፡፡ ነገር ግን የአንድ ሐሳብ (expression) አንባቢ፣ ተመልካች ወይም አድማጭ የራሱን ስሜት መቆጣጠር ድርሻ የራሱ መሆን ካልቻለ ቢያንስ የሆነ ሰውን የማያበሳጭ ሐሳብ ማፍለቅ በጣም አስቸጋሪ ስለሚሆን፣ ‹በነጻ› ቀርቶ ሐሳብን መግለጽ የሚባለው ጉዳይ ራሱ አይኖርም፡፡

 አምና የፈረንሳዩ ‹ሼርሎ ሆብዶ› መጽሔት ባወጣቸው ካርቱኖች ተበሳጭተው ጋዜጠኞችን፣ ካርቱኒስቶችን እና ፖሊሶችን የገደሉ ፅንፈኛ-ሃይማኖተኞች ጉዳይም ሊታይ የሚችለው በዚሁ ዓይን ነው፡፡ ፅንፈኞቹ የእነርሱን እሴት ያላከበረ፣ በእነርሱ እሴት መሠረት መቀጣት አለበት የሚል እርምጃ ነው የወሰዱት፡፡ ክስተቱ ለሐሳብ ነጻነት አራማጆች መርዶ ነው፡፡ አጋጣሚውን ተከትሎ ተቀጣጥሎ የመጣውም ውይይት ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው ሳንሱር እንዲያደርጉ የሚያስፈራራ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አጋጣሚው የኢትዮጵያውን ጨምሮ ለአምባገነን (authoritarian) መንግሥታት ፕሮፓጋንዳ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ ሐሳብ እንዴት መገደብ እንዳለበት ክስተቱን አስታክከው ደስኩረዋል፡፡ እነዚህ መንግሥታት ሊያስተውሉት ያልፈለጉት ነገር ቢኖር ከዴንማርክ እስከ ፓሪስ የተከሰተው ነገር ጋዜጠኞች ሐሳባቸውን በነጻነት ሲገልጹ የመንግሥት ከለላ እንደሚያስፈልጋቸው እንጂ ሐሳባቸውን በበነጻነት ከመግለጽ እንዲቆጠቡ የሚመክራቸው አልነበረም፡፡
ሌሎችን ማበሳጨት የተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ ወይም ግለሰቦች ላይ ሲከሰት ከሞላ ጎደል ከላይ ባየነው ሁኔታ ሊያልፍ ይችላል፡፡ ችግሩ የተበሳጨው አምባገነን መንግሥት (የመንግሥት ባለሥልጣናት) ሲሆኑ ነው፡፡ እነ ኤልያስ ገብሩ (አምሳሉ ገ/ኪዳን ዕንቁ መጽሔት ላይ በሚያዝያ ወር 2006 የጻፈውን ጽሑፍ ተከትሎ ጅማ ዩንቨርስቲ አካባቢ በተነሳው የተቃውሞ ብጥብጥ ሳቢያ) የተከፈተባቸው የአመጽ ማነሳሳት ክስ መታየት የሚኖርበት በዚህ ዓይን ነው፡፡ መንግሥት ጸሐፊዎቹንም፣ ለጽሑፉ የጽሑፍ ምላሽ በመስጠት ፈንታ በኃይል የጸሐፊውን ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት የተቃወሙትን፣ ሁለቱንም በክስ በማስተናገድ ጉዳዩን ለመፍታት እየጣረ፣ ጉዳዩ እስካሁን በእንጥልጥል ነው፡፡ ተመስገን ደሳለኝ ሦስት ዓመት የተፈረደበት የመንግሥት ባለሥልጣናትን የማያስደስት አልፎም የሚያበሳጭ ጽሑፍ ስለጻፈ ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ክሱ ከሽብር ወደ ‹በጽሑፍ አመጽ ማነሳሳት› የተቀየረው በተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡ ተጠያቂነት የሌለባቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት በሐሳብ ሲበሳጩ ውጤቱ የከፋ ይሆናል፡፡

፪ – የጥላቻ ንግግር እና አመጽ ማነሳሳት

በ1987 ሩዋንዳ በዓለማችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ ሰቅጣጭ የሆነውን ዜና ለዓለም አርድታለች፡፡ በ100 ቀናት ውስጥ 800 ሺሕ ያህል ሰዎች ተጨፍጭፈዋል፡፡ በጭፍጨፋው 70 በመቶ ቱትሲዎች (ወይም 20 በመቶ ሩዋንዳውያን አልቀዋል)፡፡ የጭፍጨፋው መነሾ ላይ የታሪክ ባለሙያዎች ሙሉ ለሙሉ ባይስማሙም በጎሳ ስም አመጽ እንዲቀጣጠል ያደረገው ግን የሚዲያ የጥላቻ ንግግር እንደሆነ ብዙዎቹ ይስማማሉ፡፡ ከዘር ጭፍጨፋው ዓመት ቀድሞ የተቋቋመው ሬዲዮ-ቴሌቪዥን ሊብሬ ደስ ሚል ኮሊንስ (አር.ቲ.ኤል.ኤም.ሲ) ዋነኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች በዘር ጭፍጨፋው የዚህን ሚዲያ ተቋም ሚና እስከ 10 በመቶ ያደርሱታል፡፡ ሬዲዮው በጣም ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ ከዜጎቹ ጋር በአጭር ጊዜ ለመዋሃድ በቅቷል፡፡ ይህ ሬዲዮ ነበር ቱትሲዎችን “በረሮ” ብሎ መጥራት የጀመረው፡፡ “በረሮዎቹን ደግሞ ማስወገድ አስፈላጊ ነበር፡፡” አለበለዚያ ችግር ያስከትላሉ፡፡ ሬዲዮው በተጨማሪም “በረሮ” ብሎ የጠራቸውን ዜጎች ማስወገድ ስለማስፈለጉ ብቻ ሳይሆን እንዴት መወገድ እንዳለባቸው ጭምር ተንትኗል፡፡ የጭፍጨፋው ፈፃሚዎች በአንድ እጃቸው ቆንጨራ፣ በሌላኛው ሬዲዮ ይዘው እንደነበር ሪፖርት ተደርጓል፡፡

በሩዋንዳ ጭፍጨፋ የነበረው ሬዲዮ ብቻ አልነበረም፡፡ ጋዜጣም የበኩሉን ተጫውቷል፡፡ ካንጉራ የተባለ ሳምንታዊ ጋዜጣ ‹የሁቱ ዐሥርቱ ትዕዛዛት› የተሰኘ ተወዳጅ ጋዜጣ ነበረው፡፡ ጋዜጣው በይፋ ሁቱዎች ከቱትሲዎች ጋር ምንም ወዳጅነት እንደሌላቸው አውጇል፡፡ ጠላት ናቸው በሚል ሚስቶች በባሎቻቸው፣ ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ በዚህ የማንነት ጠላትነት ላይ ተመሥርተው እንዲነሱ አድርጓል፡፡

የሩዋንዳ ሚዲያዎች የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እና ዘመቻ ውጤቱ እልቂት ሆኗል፡፡ ሚዲያዎቹ ወደዘር ጭፍጨፋ የደረሱት በሦስት ደረጃዎች ነው፤ መንግሥት ሚዲያውን በተሳሳተ መንገድ ተጠቅሞበታል – በጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ለዘር ጭፍጨፋ ማዘጋጃ አድርጎታል (1)፣ በጭፍጨፋው ወቅት አመፁን አቀጣጥሏል (2)፣ ከዚያም የጥፋቱ መጠን በትክክል ለሕዝብ እንዳይደርስ አድርጓል (3)፡፡

አሁን የሩዋንዳ መንግሥት ያንን መጥፎ ጠባሳ የጣለበትን ታሪክ ለማጥፋት በማሰብ የሁለቱንም ጎሳዎች ማንነት ክዷል፡፡ በሩዋንዳ አንዱ ሌላውን የእከሌ ጎሳ አባል ነው ብሎ በይፋ መናገር አይፈቀድለትም፡፡ ይህንን የዘር ጭፍጨፋን በማፈን ፈንታ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን ያፈነ እርምጃ እንደሆነ አጥኚዎች ይከራከራሉ፡፡ (Yakaré-Oulé (Nani) Jansen, 2014) ለሩዋንዳ መንግሥት ግን ጉዳዩ ግራ አጋቢ ነው፡፡ ለሩዋንዳ መንግሥት ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ሌሎችን እስከ ማበሳጨት በሚደርሰው ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት፣ በጥላቻ ንግግር እና በአመጽ ቅስቀሳ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት አስቸጋሪ ፈተና ይሆንባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያም ጭምር የፈረመችው የሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች ዓለምዐቀፍ ቃልኪዳን እንደሚለው “ማንኛውም ዓይነት በብሔር፣ ዘር፣ ወይም ሃይማኖት ላይ የተመሠረተ የማግለል፣ ጠላትነት ወይም አመጽ የሚያነሳሳ መልዕክት በሕግ መከልከል አለበት፡፡” ሆኖም አንድ ንግግር ወይም መልዕክት የጥላቻ ሊባል የሚችለው የትኛው ደረጃ ላይ ሲደርስ እንደሆነ መግባቢያ የለም፡፡

አስቀድመን ባየናቸው ምሳሌዎች የሚዲያ እና አመጽን ግንኙነት ስንመለከት፤ አበሳጭ የተባሉ ይዘቶችን ይዘው የወጡ የሕትመት ውጤቶች፣ አመጽ አልቀሰቀሱም፡፡ ይልቁንም የተቃውሞ አመጽ ተቀስቅሶባቸዋል፡፡ የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ደግሞ በተቃራኒው አመጹ የተካሄደው በሚዲያዎቹ የጥላቻና ጥፋት ስብከት መሪነት ነው፡፡ በነዚህ ሁለት ምሳሌዎች መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ከባድ ላይሆን ይችላል፡፡ የአመጽ ቅስቀሳ ከመደረጉ በፊት ለመከላከል ያንን ዓይነት አዝማሚያ ያለውን የሚዲያ ተቋም ቀድሞ መቆጣጠር ግን ከባድ ይሆናል፡፡ የማይቻል ግን አይደለም፡፡ ይህንን የሚቻል-ከባድ የመንግሥት ሥራ ክፍተት የሚረዱ አምባገነኖች ሚዲያን (ወይም ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን) ለማፈኛ እንደምክንያት ይጠቀሙበታል፣ እየተጠቀሙበትም ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት በብሔር ላይ ያተኮሩ አንዱን የሚያጠለሹ፣ ሌላውን ተበዳይ የሚያደርጉ የቁርሾ ታሪኮችን እንዲያውም በበጎ ሲመለከታቸውና ሲታገሳቸው ይታያል፡፡ የገዢው ፓርቲ አመሠራረትም ሆነ አቋቋም የብሔር በዳይ-ተበዳይ ግንኙነትን አጠፋለሁ በሚል ሥም ስለሆነ እነዚህ ዓይነቶቹ ትረካዎች የተስማሙት ይመስላል፡፡ ነገር ግን መንግሥት ለእነዚህ አደገኛ አዝማሚያ ላላቸው ሐሳቦች/ጽሑፎች ያለውን ትዕግሥት ቅንጣት ታክል እንኳን ስርዓቱን ለሚተቹት የለውም፡፡ ይህም የሚያስገነዝበው መንግሥት ለሐሳብ ነጻነትም፣ ይሁን ሕዝቦች ላይ ለሚደርሰው አመጽ እንደማይጨነቅ፤ ይልቁንም ለሥልጣኑ ብቻ እንደሚሳሳ ነው፡፡ ሐሳብን በመግለጽ ነጻነት እና አመጽ በመቀስቀስ መካከል ያለው ልዩነት ጠርቶ በሕግና መመሪያ እንዲደነገግ የማይፈልገውም ለዚያው ነው፡፡

“ማንም ከብስጭት የመጠበቅ መብት የለውም፡፡ ይህ መብት እስከዛሬ ባነበብኳቸው ድንጋጌዎች ሁሉ ላይ የለም፡፡ ከተበሳጫችሁ፣ የራሳችሁ ችግር ነው፤ እንደእውነቱ ብዙ ነገሮች ብዙ ሰዎችን ያበሳጯቸዋል፡፡” ~ አሕመድ ሰልማን ሩሽዲ!

This article is published on Addis_Gets magazine, on Tahsas 3, 2008 issue. 

በዚሁ ሰፊ አዳራሽ ባለው ጠባብ በር ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ተጋፍቶ የወጣው ለምሳ ነበር፡፡ ርቦታልም፡፡ ደጃፍ ላይ ቆሞ ግን አጠገቡ ከሚታየው የምግብ ገበታ ይልቅ ዩኒቨርሲቲው በር ላይ የሆነ ነገር ቀልቡን የሳበው ይመስላል፡፡ እጃቸው ላይ ደብተርና ስክርቢቶ የያዙ በርከት ያሉ ተማሪዎችና ሌሎችም …

ለሰብዓዊ መብት ውይይት መቋረጥ ምክንያት የሆነው የመብት ጥያቄ Read more »

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በተመሠረተባቸው ክስ ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙት የትድሀር ኤክስካቬሺን ኤንድ ኧርዝ ሙቪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ እስራኤላዊው ሚናሼ ሌቭ ዮሴፍ፣ በሌላ የውጭ አገር እስረኛ ተደብድበው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቆመ፡፡ ሚስተር ዮሴፍ በእስር ላይ በሚገኙበት በአዲስ …

በእስር ላይ የሚገኙት እስራኤላዊው የትድሀር ኩባንያ ባለቤት የሱዳን ዜግነት ባለው እስረኛ ተደብድበው መጎዳታቸው ተጠቆመ Read more »

ሰመጉ ይህን ያስታወቀው ‹‹ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ ይቁሙ›› በሚል ርዕስ ታኅሳስ 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አማካይነት ነው፡፡ ሰመጉ በመግለጫው የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ለተቃውሞ በወጡ ዜጎች …

በኦሮሚያ ክልል የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ገለልተኛ አካል እንዲቋቋም ሰመጉ ጠየቀ Read more »

የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ መደረጉን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ እጁ፣ እግሩና ጆሮው ላይ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም ህክምና እንዳያገኝ መደረጉን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን በማዕከላዊ እጁን ታስሮና …

የፀረ ሽብር አዋጁ በወጣ በወራት ውስጥ ከታሰሩት ፖለቲከኞች አንዱ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር ህክምና እንዳያገኝ መደረጉ ተገለፀ Read more »


የሆነ ጊዜ የሰማኋት ቀልድ ትዝ አለችኝ፤ አንዳንድ የተቃዋሚ ተወካዮች ፓርላማ ውስጥ በነበሩበት በዚያ በደጉ ጊዜ ነው አሉ፡፡ አንድ ተወካይ የሻዕቢያ መንግሥት ላይ ሊደረግ ስለሚገባው እርምጃ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፤ “አሁኑኑ ገብተን ድምጥማጣቸውን ማጥፋት አለብን፡፡ አለበለዚያ ካደሩ አይቆረጠሙም፤ እነዚያ ወያኔዎችም ያኔ ሲመሠረቱ ሳንጨፈልቃቸው ዝም ብለናቸው ነው ዛሬ አናታችን ላይ…” አሉና ያሉበት ቦታ ትዝ ሲላቸው ድንግጥ ብለው ወደአቶ መለስ መቀመጫ አማተሩ፡፡ አቶ መለስ በጥሞና ያዳምጣሉ፤ ተወካዩ እንደደነገጡ “…ልጨርሰው ወይስ ትጨርሰኛለህ?” አሉ ይባላል፡፡
የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወታደሮች አዲስ አበባ ደርሰው “ሲቪል” መንግሥት ከመመሥረታቸው አስቀድሞ “እኩይ” ናቸው በሚል ሲቃወማቸው የነበረ እና እስካሁንም ስክነቱ ያልተለየው አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው፡፡ የታማኝ የአክቲቪስትነት ሪከርድ ከኮሜዲያንነቱ የሚመዘዝ ነው፡፡ በቀልዶቹ ቢጀምርም አሁን ግን በጣም ‹ሲሪዬስ› ነው፡፡ አሁን እነቪኦኤ፣ ዶቸ ቬሊ፣ ኢሳት በየቤቱ እንደሚደመጡት ከደርግ ማክተሚያ ቀደም ብሎ ብዙ ሰው በየቤቱ ‹ድምፂ ወያነ›ን በድብቅ ያደምጥ ነበር፡፡ የፕሮፓጋንዳ ሚዲያዎች አመል ነውና ያው ውሸታቸው አይጣል ነው፡፡ ታዲያ ታማኝ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቀርቦ የምሩን ሲቀልድ ‹እዚህ ቦታ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር፣ እዚያ ቦታ ደግሞ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር ደመሰስን ይላሉ፡፡ ሲደመር ግን ይሄን ያክላል፡፡ ቆይ እኔ የምለው ወያኔዎቹ የሚደመስሱት ጦር ከጠቅላላ ጦሩ በለጠ እኮ፤ ከየት እያመጡ ነው የሚደመስሱት?› ዓይነት ቀልድ ተናግሮ አላገጠባቸው፡፡ ከዚያ በድምፂ ወያነ መልስ ተሰጠው፤ “ቁጥሩን አዲስ አበባ ስንደርስ እናወራርዳለን” የሚል፡፡ ዛቻ የሽፍትነት ዘመንም አመል ነበረች፡፡
ግንቦት 20/1983 – ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲረግጥ፣ ሲ ኤን ኤን ካነጋገራቸው ሰዎች አንዱ ታማኝ በየነ ነበር፡፡ “በመሣሪያ ተከበናል፣ ምንም ሠላም የለም…” የሚል ነገር ለጋዜጠኛው ሲነግረው ይታያል፡፡ ታዲያ ታማኝ ሁኔታውን በቀልድ ሲያስታውስ “ጓደኞቼ ከውጪ ደውለው ‹ሲ ኤን ኤን› ላይ አየንህ ሲሉኝ፣ ወዲያውኑ እንግሊዝኛዬ እንዴት ነበር?” አልኳቸው ይላል፡፡
ታማኝ ከአዲሱ ስርዓት ጋር አብሮ መኖር በማይችልበት ሁኔታ የተቀያየመው፣ ካልተሳሳትኩ የወቅቱ ባለሥልጣናት፣ እነታምራት ላይኔ በተገኙበት ስታዲዬም ውስጥ በቀለደው ቀልድ ነው፡፡ እንደማስታውሰው ቀልዱ በማንነት ላይ የተመሠረተ እና ለኢሕአዴግ የማንነት ብያኔ የማይበገር ዓይነት ቀልድ ነው፡፡

ፍቃዱ ማሕተመወርቅ፣ የቀድሞዋ ዕንቁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነበር፡፡ በመጽሔትና ጋዜጦች አከፋፋይነትም ይታወቃል፡፡ አሁን መጽሔቱ ተዘግቶ “በታክስ ስም” ፍርድ ቤት እየተመላለሰ ይገኛል፡፡ ፍቃዱ ነጻው ፕሬስ ሲጀመር ጀምሮ ምኅዳሩን ያውቀዋል፤ እናም “እናንተ በደጉ ጊዜ ነው የመጣችሁት” እያለ ይቀልድብኛል፡፡ ያኔ (ማለትም የመጀመሪያው አንቀጼ ላይ ‹ደግ› ባልኩት፣  ለፍቃዱ ግን ‹ክፉ› ግዜ) አንድ ሰው ስርዓቱን የሚያስቀይም ንግግር ሲናገር፣ እንዳሁኑ በሕግ ሥም ፍርድ ቤት አይመላለስም፣ የደረሰበት ይጠፋና ከአራት አምስት ወር በኋላ ተመልሶ ይመጣል፡፡ እንዳይሞት እንዳይሽር ተቀጥቅጦ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ከዚያ ወዲህ ያሻሻልነው ነገር ቢኖር ፍርድ ቤት የመቅረብ ዕድል መፈጠሩ ነው ማለት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህን ያነሳሁት ታማኝ ላይ የደረሰውም እንዲህ ያለው ነገር ነው ለማለት ነው፡፡
ታማኝ ተሰደደ፡፡ ብዙዎች ሲሰደዱ አቅላቸውን ያጣሉ፡፡ የሀገር ቤት ናፍቆት መመለስ ካለመቻሉ ጋር ተደማምሮ ይሁን፣ የሄዱበት አገር ኢሕአዴግ የማይደርስባቸው ከመሆኑ በተጨማሪ የሚያዩት ነጻነት ስለሚያስቀናቸው አላውቅም ብቻ ጠርዝ ይይዛሉ፡፡ ጥቂቶች ብቻ ሚዛናቸውን በጥፍራቸው ቆንጥጠው ይቆማሉ፡፡ ታማኝ ለኔ ከጥቂቶቹ አንዱ ነው፤ ያውም በረዥም ቆይታ ይህንን ማስመስከር የቻለ፡፡ ታማኝ አሁን አክቲቪዝሙን የሚሠራው ብዙ ጊዜ የቪዲዮ ማስረጃዎችን እያቀረበ ነው፡፡ ቪዲዮዎቹን ዩቱዩብ ላይ ሳያቸው በክምችቱ እቀናለሁ፡፡ ለረዥም ጊዜ የአገር ቤት ጉዳይን እየተከታተሉ፣ ማስረጃዎችን እየሰበሰቡ የመቆየት ፅናት የገቡበትን ጉዳይ ርዝመት እና ክብደት ከመረዳት ይመነጫል፡፡
የማስረጃ ነገር ከተነሳ አይቀር፣ አሁን እነ ታማኝ ማስረጃ ዶት ኮም (masreja.com) የተባለ ድረአምባ ፈጥረዋል፡፡ ድረአምባው በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ የበላይነት ፈንታ ራሳቸው ከሕግ የበላይ ሆነው ወንጀል የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ ማስረጃ የሚሰበሰብበት ነው፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ እኔ በይቅርታ አምናለሁ፤ እስከዛሬ አዲሱ ያለፈውን እየቀጣ የመጣበት ዑደት ቢያንስ የእኛ ትውልድ ላይ ቢቆም እያልኩ እመኛለሁ፡፡
ይህንን በተመለከተ ጓደኛዬ ሶሊያና “ይቅርታ ከፍትሕ ጋር መጋጨት የለበትም” ብላ ሞግታኛለች፡፡ ልክ ነች፤ በወቅቱ የሰጠችኝን ምሳሌ ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር አዋህጄ ልናገር፤ “#OromoProtests ላይ ልጇ የተገደለባት እናት የስርዓት ለውጥ ቢመጣ እና ለገዳዩ ወታደር ይቅርታ አድርጊለት ብትባል ፍትሕ ተደረገልኝ ብላ ታምናለች?” በወቅቱ፣ ሶሊም እኔም ጥያቄውን ከመጠየቅ በቀር መልስ መስጠት አልቻልንም፡፡ እርግጥ ነው ልጁ የሞተው የመጣው ለውጥ እንዲመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በምሳሌያችን መሠረት አወዛጋቢው ማስተር ፕላን ቢሰረዝ እንኳን ልጁ የለውጡ እሸት ተጋሪ ላይሆን አልፏል፡፡ ይቅርታ ለአገሪቱ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ያስፈልግ ይሆናል፤ የቤተሰቡን አባል ወይም ወዳጁን ላጣው ግለሰብ ግን ፍትሕ ሆኖ ይሰማዋል ማለት አይቻልም፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ለይቅርታውም ቢሆን ማስረጃውን መሰብሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ አጥፊው ጥፋቱን እንዳይክድ፣ ይቅርታ ጠይቁኝ ባዩም በማስረጃ እንዲሞግት፡፡
ማስረጃ መሰብሰብ ሕገ-ወጥ መስሏችሁ የምትፈሩ ካላችሁ አትሳሳቱ፡፡ ሕጋዊ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት ራሱ በፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኩል አላግባብ የተገኘ ሀብት ካለ በሚል የባለሥልጣናቱን ሀብት ምንጭ ሳይቀር የማጣራት ማንዴት አለው፡፡ ቁርጠኝነቱ ስለሌለ አልተሳካላቸውም፤ እኛ ግን ይሳካልናል፡፡ በየቀኑ ከታችኛው እርከን (ወረዳ) እስከ ላይ ድረስ የምንጠየቃቸውን ጉቦዎች፣ ባለሀብቱና ባለሥልጣናቱ (ሁለቱም አንድ ናቸው) ኢ-ርትዓዊ በሆነ መንገድ የሚያካብቱትን ሀብት፤ ከትላልቆቹ እስከ ትናንሾቹ ሹመኞች በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን ግፍ፤ ትንንሽሽም፣ ትልልቅም ሠላማዊ ተቃውሞዎች በተነሱ ቁጥር በንፁሐን ዜጎች ነፍስ ላይ የሚሰነዘሩትን የኃይል እርምጃዎች የሚያጋልጡ ማስረጃዎች ባገኘን ቁጥር ለማስረጃ ዶት ኮም በመላክ ለኢትዮጵያችን የወደፊት መልካም ዕጣ ፈንታ ሲባል እንዲከማቹ የበኩላችንን እናድርግ፡፡ ማስረጃዎቹን መሰብሰቡ ሌላው ቢቀር አጥፊዎቹን ስለሚያስፈራቸው በደላቸውን ሊያላሉልን ይችላሉ፡፡

ቪቫ ላ ታማኝ!!!

ከአዲስ አበባ ጎንደር የገቡት የአገዛዙ ባለስልጣናት የህወሓቱ አባይ ፀሀዬ፣ የህወሓት ተላላኪ የሆነው ብአዴን ቁንጮዎች በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ ናቸው፡፡ የክልሉ ሹም ገዱ አንዳርጋቸውም በአጃቢነት ተገኝቷል፡፡ አባይ፣ በረከትና አዲሱ በትናንትናው ዕለት የዞኑን ካቢኔ አባላትና ጥቂት የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎችን በጎሃ ሆቴል ሰብስበው በጎንደር ስለሰፈነው አለመረጋጋት፣ አመፅና ጦርነት ለማነጋገር ሞክረው “ይህ ሁሉ ችግር ከደረሰና ሁኔታው ከቁጥጥር […]

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)– የወያኔን ጉጅሌ አገዛዝ ጭካኔ እና እኩይ ተግባር ብናወራው አያልቅም::በሕግ እና በሕዝብ ስም ሽፋን በርካታ አደገኛ ወንጀሎች በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ ነው::በለውጥ ሃይሉ መካከል በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት እስካሌለ ድረስ ወያኔ ይህንኑ ክፋቱን ከሰይጣን የበለጠ ተግባሩን አስፋፍቶ ይቀጥላል::ሕዝብ እምነት …

ቀን እየቆጠሩ ከማስጨፈር የግለሰብ ከዚያ የብሄረሰቦችን መብት ማክበር ይቅደም:: Read more »

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ኅዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ብሔር ተኮርና ልማትን መሠረት ያደረጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ እየተባባሱ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡ የአገር ውስጥና የውጭ የመገናኛ ብዙኃን አባላት፣ የተለያዩ ኤምባሲ ተወካዮችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት …

ሰመጉ ብሔር ተኮርና ልማትን መሠረት ያደረጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ እየተባባሱ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡ Read more »

በኦነግ አባልነት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር ተከለከለች ‪#Ethiopia #Oromo በ2004 ዓ.ም በኦሮሞ ነፃአውጭ ግንባር (ኦነግ) አባልነት ተጠርጥራ ከታሰረች በኋላ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር መከልከሏን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው አሊማ (ቢፍቱ) …

በኦነግ አባልነት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር ተከለከለች ‪ Read more »