ይድረስ ለኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር
ሰሞኑን ሥርጭቱን በጀመረው “ቃና ቲቪ” ይዘት እና አሰራር ላይ ለመወያየት በደብዳቤ
ባሳወቅናችሁ መሰረት ተወካያችሁን መላካችሁ ይታወቃል፡፡  የኪነ ጥበብ ሞያ ማኅበር ተወካዮቹ (የእናንተም ባሉበት) በተጠቀሰው ጉዳይ ለሁለት የተለያዩ  ቀናት የጋራ ውይይት አካሂደው የጋራ የአቋም መግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ይህ የጋራ  አቋም በፅሁፍና በንባብ ለሚዲያ ከመቅረቡ በፊት የእናንተ ሁለት ተወካዮችን ጨምሮ የሁሉም   የሞያ ማኅበር ተወካዮች መስመር በመስመር በጥንቃቄ ተመልክተው ማሻሻያና ማረሚያ ካደረጉ  በኋላ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫው የተሰጠ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ መግለጫ ከመሰጠቱ አንድ ቀን ቀደም  ብሎ (በ20/07/2008) የደራስያን ማኅበር ልሳን በሆነውና ዘወትር ማክሰኞ ምሽት በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በሚቀርበው ፕሮግራም ላይ የመግለጫውን ፍሬ ሃሳብ ለህዝብ በመግለፅ ሚዲያዎች እንዲገኙ መረጃ ስታደርሱ እንደነበርም ይታወቃል፡፡ይህ ጥሬ ሀቅ ባለበት ሁኔታ ባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 1 ቀን 2003 ዓ.ም በወጣው የአዲስ አድማስ  ጋዜጣ ላይ የደራስያን ማኅበር ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙሴ ያዕቆብ የሰጡት ከእውነት የራቀና የተዛባ  መግለጫ እጅግ የሚያሳፍርና የሚያሳዝን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ የመላው የደራስያን ማኅበር አመራርና አባላት እምነት እንዳልሆነም እናምናለን፡፡ የእሳቸው ማኅበር ተወካይና ሌሎች የጥበብ ማኅበራት በጋራ ተወያይተው ያወጡትን መግለጫ በምን ምክንያትና መነሳሳት ለመካድ እንዳነሳሳቸው ለጊዜው ያወቅነው ነገር የለም፡፡ በሂደቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ሲሳተፍ የነበረውን የማኅበራቸውን ተወካይ፤ “መግለጫውን ለመከታተል የተገኘ ነው” በማለት ከደራሲያን ማኅበር ተወካይነት ወደ ሚዲያ ተወካይነት ለውጠው፣ ለጋዜጣው ለመግለፅ ለምን እንደተገደዱም አልተረዳንም፡፡ ከዚህም በላይ ማህበራቱ የቴሌቪዥን ጣቢያውን በሚመለከት እያቀረቡት ካለው አመክንዮና ለህዝብ ከገለፁት አቋም ፈፅሞ የራቀና የማናውቀውን ጉዳይ በመናገር አንባቢን ግራ ከማጋባታቸውም በላይ የማኅበራቱን ጥያቄ ያልተገባ ለማስመሰል መሞከራቸው ከምን በመነጨ አስተሳሰብና ዓላማ እንደሆነ ለጊዜው አልደረስንበትም፡፡ በእሳቸውና በመላው የጋዜጣዊ መግለጫው ተሳታፊ በነበሩ የሚዲያ አካላት እጅ በሚገኘው ባለ አምስት ገፁ የሞያ ማኅበራቱ የአቋም መግለጫ በየትኛው አንቀፅ ላይ ይሆን የሳንሱር ጉዳይ የተነሳው!? የኢትዮጵያ ደራስያንን እወክላለሁ የሚል
የማኅበር ፕሬዚደንት የተፃፈን ፅሑፍ አንብቦ መረዳት ተሳነው ቢባልስ ማን ያምን ይሆን!? የሆነስ
ሆነና “እነ በዓሉ ግርማን የመሳሰሉ ፀሐፍት በሳንሱር ምክንያት የሕይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል”
ማለታቸውስ የደራስያን ጉዳይ ጉዳዬ ነው ብሎ የፕሬዚደንትነት ሥልጣን ከተቆናጠጠ ግለሰብ ይጠበቃል ወይ!? ሌላው ቢቀር የደራስያን ማኅበር የአመራር አባል በነበረው ደራሲ እንዳለጌታ  ከበደ ጥልቅ ጥናትና ምርምር የታተሙትን “ማዕቀብ” እና “የበዓሉ ግርማ ሕይወትና ሥራዎች” የተሰኙ በብዙዎች የተነበቡ መፃሕፍትን ቢያነቡ ኖሮ በዓሉ ግርማን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በሳንሱር ምክንያት የሕይወት መስዋዕትነት የከፈለ (የተገደለ) አንድም ደራሲ እንደሌለ በተረዱ ነበር፡፡ እንደሚታወቀው የኪነ ጥበብ ሞያ ማኅበራቱ በመግለጫቸው ያሉት ዋና ፍሬ ሀሳብ ዶ/ር ሙሴ በስህተት አልያም በችኮላ ተረድተው እንዳሉት ሳይሆን “ቃና” ቴሌቪዥን ለውጭ ሀገር ፕሮግራሞች የሰጠው (70%) ተገቢ አይደለም የሚል ነው፡፡ ይህ ሀሳብ የሳንሱር ሳይሆን በሀገር ውስጥ፣ በሀገር አቅም በሚሰሩ ፊልሞች ላይ ጫና ፈጥሮ ፍትሀዊ ተወዳዳሪነት እንዳይኖር በማድረግ፣ ዳዴ በማለት ላይ ያለውንና የብዙ ዓይነት ጥበቦችና ባለሙያዎች ውህደት ውጤት የሆነውን የኢትዮጵያ ሲኒማ አቀጭጮ ያጠፋል፣ አዲስ ለሚከፈቱ ጣቢያዎች በቀላሉና በውስን ሰዎች ሳይለፉ ገንዘብ እንደሚሰራ በማሳየት በመስኩ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ዜጎች በሀገራቸው ስለ ሀገራቸው ጉዳይ የሚተርክ ፊልም በመስራት እንዳይጠቀሙና ሞያውን እንዳያሳድጉ እንቅፋት ይሆናል፣ ህዝብን የሚያረካ ሥራን የሰሩና ይሁንታን በማግኘት የተደነቁ ባለሙያዎችም ዝናቸውን በመጠቀም የደሀ
ህዝባቸውን ችግር ለመቅረፍ በሚደረጉ የማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ የሚያደርጉትን በጎ እንቅስቃሴና ቅስቀሳ ተፅዕኖ አልባ በማድረግ ያዳፍነዋል የሚል ነው፡፡ በእግረ መንገድም ፊልሞቹ በአብዛኛው ከምዕራባውያን የሚመጡ እንደመሆናቸውና የሚተላለፈው ለቤተሰብ ቅርብ በሆነው የቴሌቪዥን ሚዲያ በኩል ከመሆኑ አንፃር አጉል ባህል በቀላሉ ታዳጊ ህፃናትና ልጆች ላይ እንዳይሰርፅ ሥጋታችንን የገለፅንበት ነው፡፡ የኪነ ጥበብ ሞያ ማኅበራቱ በጋራ ባካሄዱት ውይይት ዶ/ር ሙሴ የእሳቸውን ማኅበር በመወከል በተገኘው ግለሰብ እምነት ከሌላቸው፣ ከቢሮአቸው በአራት እርምጃ ከሚርቀው የጋራ ማኅበራቱ
መሰብሰቢያ ቢሮ በመምጣት ጉዳዩን ማጣራት ይችሉ ነበር፡፡ አልያም በአሁን ሰዓት የደራስያን አመራር አባል የሆኑት የሥራ ባልደረባቸው በዚሁ ጋዜጣ ሚያዝያ 26 ቀን 2008 ዓ.ም የፃፉትን ጥልቅና ለብዙዎች ስለ ጉዳዩ የበለጠ ግንዛቤ ያስጨበጠ ፅሑፍ ቢቻል አንብበው ካልሆነም ካነበበ ሰምተው አስተያየታቸውን ቢሰጡ ኖሮ ትዝብት ላይ የሚጥል ስህተት ባልሰሩ፣ መልካም ሥም የነበረውን ማኅበራቸውንም ባላቀለሉ ነበር እንላለን፡፡
(ተፃፈ፡- ከ “የኢትዮጵያ  የኪነ ጥበብ ማኅበራት
ጊዜያዊ አስተባባሪ”)

 ከደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በጠፍ ሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱትና ከ20/07/08 ጀምሮ በአዋሳ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ታስረው የሚገኙት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የኦህዲኅ አባል አቶ አብርሃም ብዙነህና የቀድሞ …

በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በጠፍ ሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱት እነ ዓለማዬሁ ለሳምንት ተቀጠሩ Read more »

የዞኑ መስተዳድር በዞኑ ነዋሪዎች የተቋቋመ ‹ነጻ› በሚባል የልማት ማህበርጋር የገንዘብ ማሰባሰቢያ ባዛር ለማዘጋጀት ህዝቡን በመቀስቀስ ላይ መሆኑን፣ ለዚሁ ባዛር መምህራንን ለማሳመን በየትምህርት ቤቱ ….. በመሰብሰብ ያወያየ ሲሆን ከመምህራን የተለያዩ ጥያቄዎች መነሳታቸውንና ለዚህም በቂ መልስ መስጠት ባለመቻሉ ለሌላ ጊዜ ሰፊ ውይይት …

በጂንካ ከተማ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ባዛር ሊካሄድ ነው ::በልማት ስም ገንዘብ የባለሥልጣናት ኪስ ማደለቢያ ሊውል አንፈቅድም Read more »

በርካታ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ችግሮች ሲፈጠሩ የአገሪቱን ፖሊሲ አውጭዎችና ህግ አስፈጻሚዎችን በድፍረት ከመተቸትም ሆነ መልካም ጎኖችን ከማበረታታት ታቅበው ይታያሉ። ቁጥራቸው በዛ ያሉ አይሁን እንጂ በገዥው ፓርቲ ጉያም ሆነ በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ምሁራንም ምሁራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሲንቀሳቀሱ እናያለን። ከተቃውሞውም …

“አቶ መለስ በታሪክ ሊጠየቁበት የሚችለው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው ነው” ዶክተር ፍሰሃ አሰፋው Read more »

በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ መቋረጡን፣ መብራት ከዕረቡ ጀምሮ መጥፋቱን እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከሠላሳ በላይ ሰዎች መታሠራቸው በዚህ ዘገባ ተካቷል።

በሕክምናው አጠራር “ኮሌስትሮል” በመባል በሚታወቀው፤ በአንድ በኩል ለጤና በእጅጉ አስፈላጊ፤ መጠንና ዓይነቱ ሲለወጥ ደግሞ ጎጂ በሚሆነው በደማችን ውስጥ የሚዘዋወረው ስብ መሠል ንጥረ ነገር ምንነትና የሕክምናው ዓለም ምልከታዎች ዙሪያ የሚያተኩር ተከታታይ ቅንብር ነው። ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን የልብና የውስጥ ደዌ ከፍተኛ አማካሪ …

ኮሌስትሮልን ተከትለው የሚመጡ የጤና ሁከቶችን መከላከያ ቅድመ ጥንቃቄ – VOA Read more »

አዲሱ “ቃና” ቴሌቭዥን የአርቲስቶችን መንደር አናወጠ

      የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች፣ የቲያትር ባለሙያዎች ፣ የሙዚቀኞችና  የሰአሊያን ማህበራት እንዲሁም አላቲኖስ የፊልም ሰሪዎች ማህበር ሰሞኑን በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ አዲሱ የ“ቃና” ቴሌቪዥን የፕሮግራም ይዘት የአገሪቱን የሲኒማ ጥበብ አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ይዘቱን ሊያስተካክል ይገባል አሉ፡፡
“ቃና” ቴሌቪዥን በበኩሉ፤ የአገሪቱን የፊልም ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እተጋለሁ ብሏል፡፡
“ቃና” 70 በመቶ የውጭ ሀገር ፊልሞችን፣ 30 በመቶ የአገር ውስጥ ፕሮግራሞችን ሊያቀርብ መዘጋጀቱን የጠቆሙት ማህበራቱ፤ የይዘት ምጣኔው የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያላገነዘበና የባህል ወረራን የሚያስፋፋ ነው ሲሉ ነቅፈዋል፡፡ የአደጋው ምንጭ በዋናነት የውጭ ሀገር ፊልሞችን ተርጉሞ በዳቢንግ (ድምጽ በመቅዳትና አስመስሎ በመለጠፍ) ማቅረቡ ነው ብለዋል፡፡
በቴሌቪዥን ጣቢያው የሚቀርቡት የውጭ ሀገር ፊልሞች ንግድ ተኮር በመሆናቸው ምንም አይነት ትምህርታዊና ሞራላዊ ይዘት የላቸውም ያሉት ማህበራቱ፤ የባህል ወረራን በማስፋፋት ትውልድን ከማጥፋታቸው በፊት መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡
ጣቢያው አጭር እድሜ ያለውን የተከታታይ ድራማ ታሪካችንን በማቀጨጭ የፊልም ኢንዱስትሪውን ዕድገት የሚያሰናክል በመሆኑ ፕሮግራሙን በድጋሚ ሊከልስ ይገባዋል ብለዋል፤ ማህበራቱ፡፡
ባለፈው ዓመት “ዳና” የቴሌቪዥን ድራማ 8 ሚሊዬን ብር ገቢ ለመንግስት ማስገኘቱን የጠቀሱት ማህበራቱ፤ “ቃና” በዚህ ይዘቱ የሚቀጥል ከሆነ ግን ትውልድ ከማጥፋቱ በተጨማሪ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ያሳጣዋል ብለዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ በብሄራዊ ቲያትር በሰጡት በመግለጫ ላይ የቴሌቪዥን ጣቢያውን የሥራ ሐላፊዎች ለምን እንዳልጋበዙ የተጠየቁት ማህበራቱ፤ የተቻላቸውን ያህል ጥረት ቢያደርጉም ሊያገኙአቸው እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ የ“ቃና” ቴሌቪዥን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ኃይሉ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው፤ ጣቢያው በመግለጫው ላይ አለመጋበዙን ገልፀው፤ በይዘቱ ዙሪያም ቀርቦ ሊያናግራቸው የሞከረ ማህበርም ሆነ ግለሰብ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ በፕሮግራሙ ይዘት ላይ ችግር አለ ብሎ የሚያምን አካል በማንኛውም ጊዜ ሊያነጋግራቸው እንደሚችልም ገልፀዋል – ሃላፊው፡፡
ባለፉት 50 ዓመታት የቴሌቭዥን ታሪክ በተለያዩ አገራት በራሳቸው ቋንቋ ተተርጉመው ባህልና እሴቶችን ሳይጋፉ የቀረቡና እየቀረቡ ያሉ የመዝናኛ ስራዎች፣ በየአገሩ ያሉትን የፊልምና የቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ አሁን ላለበት ደረጃ አድርሰውታልም ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ጣቢያው ከመቋቋሙ በፊት በአገሪቱ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፤ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ከሚመለከቱ ኢትዮጵያውያን ግማሽ ያህሉ የሚያዩት የውጭ አገር ይዘት ያላቸውንና  በሌላ ቋንቋ የተሰሩትን ሲሆን የሚያዩትም እንዲሁ እንደወረዱ መሆኑን የጠቆሙት  አቶ ኃይሉ፤ አሁን ጣቢያው ለእይታ የሚያበቃቸው ፊልሞች ግን የተመረጡና  ለማህበረሰቡ ትርጉም ሊሰጡ የሚችሉት ብቻ ናቸው፡፡
ፊልሞቹ በቀጥታ የተተረጐሙ ሳይሆኑ በእኛ ሀገር ባህል፣ አባባልና አስተሳሰብ የተቃኙ እንደሆኑም ጠቁመው፤ ያልተገቡ የተባሉ የፊልሙ ክፍሎችም ተቆርጠው እንደሚወጡ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
ጣቢያው በቲያትር ጥበባት የተመረቁ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንን በፀሐፊነት፣ በዳይሬክቲንግ፣ በድምጽና በቪዲዮ ኤዲቲንግ ቀጥሮ እያሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ኃይሉ፤ በቀጣይም የእራሱን አገራዊ ስራዎች ለመስራት በእንቅስቃሴ ላይ ነው ብለዋል። ለ“ቃና” ፕሮግራሞቹን የሚያቀርበው “ቢ. ሚዲያ” የተባለው ኢትዮጵያዊ ድርጅትም ፕሮግራሙን በዶላር በመሸጥ፣ የውጪ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገባም የጣቢያው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አክለው ገልፀዋል፡፡
ደራሲያንና የፊልም ምሁራን በጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት ለማወቅ አዲስ አድማስ ሁለት አንጋፋ ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡ የጣቢያው ይዘት ለኢትዮጵያዊው ተመልካች ያን ያህል ይጠቅማል ብዬ አላምንም፤ ጉዳቱ ግን ከፍተኛ ነው ያለው ደራሲ ኃይሉ ፀጋዬ፤ የፕሮግራሙ ይዘት የአገር ውስጥ 30፣ የውጪው 70 እጅ መሆኑ ለአገር ውስጥ እጅግ ዝቅተኛ ትኩረት መሰጠቱን ያሳያል፤ ይሄ ደግሞ እየተንገዳገደ ያለውን የፊልም ኢንዱስትሪ ያቀጭጨዋል ብሏል፡፡
የጣቢያው የፕሮግራም ይዘት ከፍተኛ የባህል ወረራን ከማስፋፋቱም በላይ ለጥቂት ሰዎች የስራ እድል በመፍጠር በመስኩ የተሰማሩ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን ስራ እንደሚያሳጣም ደራሲው ገልጿል፡፡
ተቋሙ ገንዘብን መሰረት ያደረገ መሆኑን የገለፀው ኃይሉ ፀጋዬ፤ ይህ ደግሞ ኃላፊነት የጎደለው ስራ ነው ብሏል፡፡
የትያትር ባለሙያው ረዳት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ጀዋሬ በበኩሉ፤ “የጣቢያው መፈጠር ገንቢ ነገር አለው፤ ለምሳሌ የህብረተሰቡን የፊልም ማጣጣም አቅም ይጨምራል፡፡ ሆኖም ጣቢያው ለውጪ ፊልሞች የሚሰጠው ድርሻ ዝቅ ማለት አለበት” ሲል አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡
“ባህልን ባላገናዘበና ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችል ህግ ባልተረቀቀበት ሁኔታ በስፋት መልቀቁ ግን አደጋ አለው ያለው ፕሮፌሰሩ፤ መጀመሪያ ህግ መውጣት አለበት፤ ፊልሞቹ ባህልን፣ ስነ ልቦናንና፣ እምነትን ጠብቀው ተጣርተው የሚቀርቡና በህግ የሚመሩ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡ “በርግጥ ውድድር መኖር አለበት፤ ውድድር መኖር ያለበት ግን በእኩል የመወዳደሪያ ሜዳ ላይ ነው፡፡ ካልሆነ ግን የውድድር አምዱን ኢ-ፍትሃዊ ያደርገዋል፡፡  ይህ ለኔ ወንጀል ነው” ሲልም አስረድቷል ሙሉጌታ ጀዋሬ፡፡
በሳተላይት የሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፤ “በሳተላይት ለሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፍቃድ አልሰጥም፤ እነዚህ ጣቢያዎች ከውጪ አገራት ፍቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ከባለስልጣኑ እውቅና ውጪ ናቸው” ብሏል፡፡ ሆኖም ጣቢያዎቹ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጁአቸው ፕሮግራሞች ሲኖሩ ባለስልጣን መ/ቤቱ የብቃት ማረጋገጫን እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን የፕሮግራሞች ይዘት የሚቆጣጠርበት አሰራር ግን እንደሌለው ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡   

ከትንሽ ጋር እንደመታገል ምን የሚያደክም ነገር አለ?!! ለኢትዮጵያውያን አብሮ መስራትና ሥርዓት መስርቶ መሄድ ከጊዜ ወደጊዜ ምን ያህል ከባድ እየሆነ እንደመጣ ለመረዳት ያለፉት አርባና ሃምሳ አመታትን ታሪካችንን ምስክር ነው፡፡ አለመተማመንና አምባጓሮ ሳይፈጥርበት ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ተቋም ለመፍጠር ምን ያህል እየተቸገርን እንደሆነ …

ከትንሽ ጋር እንደመታገል ምን የሚያደክም ነገር አለ?!! ወረታው ዋሴ Read more »

በዓለም በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አስራ ሀገሮች ሰባቱ የአፍሪካ ሀገሮች ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ሆና ቆይታለች። የያዝንው የአውሮፓዊያን ዓመት ግን ይሄ ሁኔታ እንደሚቀየር ነው የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ (IMF)በየዓመቱ የሚያወጣው የዓለም ምጣኔ ሀብት ግምገማ ዘገባው አስታውቋል። ባለፈው ዓመት …

የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት IFM አስታወቀ – VOA Read more »

ብዙዎቻችን ቴዲ አፍሮን ከሙዚቃ ሥራውና ከሐገር ወዳድነቱ ባሻገር እምብዛም የግል ሕይወቱን እና ምን አይነት ሰው እንደሆነ አናውቀውም እርሱም ቢሆን ስለራሱ ማውራት ስለማይወድ እና ይህንን ፈፀምኩኝ ብሎ ስለማያወራ የቴዲን ማንነት በግልጽ ልናውቀው አልቻልንም ሆኖም ቴዲ አፍሮ እንደዚህም አይነት ሌላ ገፅታ አለው። ★ ሐምሌ 30,1998 ዓመተ ምሕረት በድሬዳዋ ደርሶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ30 ሺህ ብር […]

ከአምዶም ገብረስላሴ ኣቶ መኮነን ኣስፋው በምርጫ 2007 ዓ/ም በተካሄደው ምርጫ ዓረና-መድረክን ወክለው በኣላማጣ ምርጫ ክልል ለክልል ምክር ቤት ተወዳድረው ህወሓትን ኣምበርክከዋል ዳሩ ድምፃቸው ተዘረፉ እንጂ። ኣቶ መኮንን በ1974 ዓም ወደ በረሃ ወጥቶ ያታገሉ ሲሆኑ ከነ ሓየሎም ኣርኣያና ገብሩ ኣስራት ጎን …

በካድሬዎች ስር የወደቀችው ቤተ ክርስትያን (አምዶም ገብረስላሴ) Read more »

ዛሬ ሚያዚያ 6, 2008ዓ.ም. ዐፄ ቴዎድሮስ የዛሬ 148 ዓመት “ተማርኬ የሐበሻ ንጉሥ ተማረከ! ተብሎ እራሴን ሀገሬንና ሕዝቤን ከማዋርድ ስም ከምሰብር ሞት ይሻለኛል!” ብለው ለሚወዷት ሀገራቸውና ሕዝቧ ክብርና ኩራት ሲሉ ተማርከው በጠላት እጅ ከመውደቅ እራሳቸውን አጥፍተው የጀግና እረፍትን ቢያርፉ መርጠው እራሳቸውን ያጠፉበት የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ “ዐፄ ቴዎድሮስ ለምን ይተቻሉ! ፈጽሞ መተቸት የለባቸው!” ለማለት አይደለም አነሣሴ፡፡ ነገር […]

ወያኔና ትግሬ መስፍን ወልደ ማርያም ሚያዝያ 2008 አዳም በበደለ መድኃኔ ዓለም ካሠ፤ የተጠቀሰውን አባባል የማያውቅ ክርስቲያን ያለ አይመስለኝም፤ ለእስላሞችም ቢሆን አዲስ ነገር አይሆንባቸውም፤ አዳም ትእዛዝ ጥሶ ዕጸ በለስን በላና ተረግሞ ከገነት ወጣ፤ አዳም በደለ የሚባልበት ምክንያት ይህ ነው፤ አዳም በገነት …

ወያኔና ትግሬ – Pro.መስፍን ወልደ ማርያም Read more »

የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ አስታወቀ::-( VOA)- ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎IMF‬ ‪#‎WorldBank‬ ‪#‎Economy‬ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ (IMF) አስታወቀ። በዚህ በያዝንው የአውሮፓዊያን ዓመት …

የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ አስታወቀ Read more »

ኢንተርኔትን በመጠቀም የጽሁፍና የድምጽ መልእክቶች የምናስተላልፍባቸው አፕሊኬሽኖችን ጨምሮ ፌስ ቡክና ትዊተር በኢትዮጵያ የኦሮሚያና በአንዳንድ የደቡብ ክልሎች ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ብሎምበርግ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች በመጥስ ዘግቧል፡፡ የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በስልካቸው የጫኗቸውን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም አገልግሎቶቹን ማግኘት አለመቻላቸውን በመጥቀስ የቴሌ …

በኢትዮጵያ የኦሮሚያና በአንዳንድ የደቡብ ክልሎች ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ብሎምበርግ ዘግቧል፡፡ Read more »

ወጣቶች ትናንት ምሽት በተለያዩ የደሴ ከተማ አካባቢዎች የበተኑት ወረቀት የከተማው ህዝብ ትኩረት መሳቡን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወጣቶች ተናግረዋል፡፡ የትግል ጥሪ ወረቀቶች፣ ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ፣ በወልቃይት ጥያቄ ዙሪያ የደሴ ህዝብ ጥያቄውን ከሚያቀርቡ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ጋር በጋራ እንዲቆም የሚያሳስቡ ናቸው፡፡ በሁለተኛ …

በደሴ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግል ጥሪ ወረቀቶች ተበተኑ Read more »

የማያዛልቅ እያለማን ነው የወያኔ ጸሎት አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎Change‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ የጀመረው የስልጣን ማስረዘሚያ ስልት ራሱን እና በክሎኒግ ያባዛቸውን ጭፍሮቹን ወደ መቃብር እያወረደ መሆኑ ለአፍታ ቆም ብሎ ማስብ …

የማያዛልቅ እያለማን ነው የወያኔ ጸሎት አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል። Read more »

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአቶ አባይ ወልዱ ጋር በወልቃይት ጉዳይ ጸብ ውስጥ ነኝ አሉ የወልቃይትን ማንነት በተመለከተ በተነሳው ጥያቄ ዙሪያ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት፣ ከትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ጋር ፀብ ውስጥ መሆናቸው ተገለጠ። ይህንን የተናገሩት ራሳቸው የአማራ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሲሆኑ፣ …

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአቶ አባይ ወልዱ ጋር በወልቃይት ጉዳይ ጸብ ውስጥ ነኝ አሉ Read more »

ምርጫ 2012 ሳይደርስ ዓረናን ማፍረስ! እንግድህ ወደድንም ጠላንም ሳልሳይ ወያነ (3rd Weyane)የሚባል ድብቅ ፓርቲ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ውስጥ ተመስርተዋል። የዚህ ፓርቲ የመጀመሪያው ድብቅ ኣላማው ዓረናን ማፍረስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ኣላማው ደግሞ ትግራይ ውስጥ ብቻ የአስተዳደር ለውጥ በማምጣት የህውሃትን እድሜ ማራዘም …

ሳልሳይ ወያነ የሚባል ድብቅ ፓርቲ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ውስጥ ተመስርተዋል። Read more »

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የዉኃ እጥረት ተዳርገዋል። የአፍሪቃ ኅብረት ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ በርካታ ዲፕሎማቶችን የምታስተናግድ ብትሆንም የመብራት ኃይልን ጨምሮ የዉኃ አቅርቦት እጥረት ችግር ላይ መዉደቅዋን አስመልክቶ የተለያዩ ዘገባዎች እየወጡ ነዉ።

የሰው ልጅ አራት የጠባይ እርከኖች አሉት ይላሉ ትውፊታውያን ሊቃውንት፡፡ በነባሩ የኢትዮጵያ ትምህርት መሠረት ጠባይና ባሕርይ ይለያያሉ፡፡ ‹ባሕርይ› ማንነት ነው፡፡ በፍጥረትህ ታገኘዋለህ፡፡ ይዘህው ትኖራለህ፡፡ አትለውጠውም፤ አታሻሽለውም፡፡ ለምሳሌ ሰውነት ባሕርይ ነው፡፡ ሰው መሆንን፣ እንስሳ ወይም ዛፍ ወይም ውኃ በመሆን አትለውጠውም፡፡ ‹ጠባይ› ደግሞ …

አራቱ የጠባይ እርከኖች – ዳንኤል ክብረት Read more »

ዓለም አቀፍ አዉቅና ያተረፉት እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ያረፉት ከዓራት ዓመት በፊት ነበር።አዲስ አበባ ዉስጥ በመንበረ ፅባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቅፅር ግቢ የቆመዉን ሐዉልት ያስቀረፀዉ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ነዉ

የሙስሊሞች ጉዳይ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በዛሬው ዕለት ከዕስር ተፈታ!! ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Journalist‬ ‪#‎EthioMuslims‬ ‪#‎SolomonKebede‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ በነ አማን አሰፋ መዝገብ በ24ኛነት የተከሰሰው እና ላለፉት ከ3አመት በላይ በግፍ በማዕከላዊ፣ ቃሊቲ፣ ቂሊንጦ በጋዜጠኛነት ሞያው በመንቀሳቀሱ ብቻ ሲንገላታ የነበረው የሙስሊሞች ጉዳይ ማኔጂንግ ዳይሬክተር …

የሙስሊሞች ጉዳይ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በዛሬው ዕለት ከዕስር ተፈታ!! Read more »

ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓጓዘው የእርዳታ እህል እና ማዳበሪያ ጭነት መብዛት በአገሪቱ የትራንስፖርት ዋጋ ንረት ፈጥሯል። የኢትዮጵያ መንግስት ጅቡቲ ወደብ ላይ የተፈጠረውን መጨናነቅ ለመቀነስ የበርበራ ወደብን ለመጠቀም ስምምነት ፈርሟል። ለመሆኑ የሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ ምን ያክል ለአጠቃቀም ምቹ ነው?

በኢሕኣዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ የሕወሓት ተሰሚነት እያሽቆለቆለ ነው::ለጄኔራሎች እና ለደህንነት ሹሞች ተማጽኖ ቀርቧል:: የኢህኣዴግ ውጥረትና የኣቦይ ስብሓት ጭንቅ ።።።።።።።።።።።።። ሰሞኑን ኢህኣዴግ በኣዲስ ኣበባ ስብሰባ ማካሄድ ጀምሮ ነበር። ስብሰባው ከተጠበቀው በላይ ውጥረት የተሞላበትና የድርጅቶች ሞቧደን የታየበት ነበር። ቡዱኖቹ ህወሓትና ደህዴን በኣንድ በኩል፤ …

በኢሕኣዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ የሕወሓት ተሰሚነት እያሽቆለቆለ ነው::ለጄኔራሎች እና ለደህንነት ሹሞች ተማጽኖ ቀርቧል:: Read more »

ሁለት አነስተኛ ድንኳኖች በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ ሐሩርና ንዳድ ለመከላከል ያስችሉ ዘንድ ተዘርግተዋል፡፡ በአንደኛው ድንኳን ውስጥ አራት ፍራሾች ተዘርግተው፣ ኢልኒኖ ባስከተለው ከፍተኛ ድርቅ የተነሳ የምግብ እጥረት የገጠማቸውን ሕፃናትና እናቶች ለመንከባከብ እንዲያስችሉ አንሶላ ለብሰው ተዘጋጅተዋል፡፡ በእነዚህ ድንኳኖች ውስጥ ደግሞ ‹‹ሴቭ ዘ ቺልድረን›› …

የምግብ እጥረት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በርትቷል፡፡ Read more »

በማሕሌት ፋንታሁን

መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ተቋማት ጋር ማቆራኘት ሳያስፈልገው የጻፈው ጽሑፍ ብቻ ተጠቅሶበት የተከሰሰ እና የተፈረደበት ብቸኛ ጋዜጠኛ ነው – ተመስገን ደሳለኝ። በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተመሠረተችው ፍትህ ጋዜጣ ጥቂቶቹን የግል ሕትመት ሚዲያ ውጤቶች የተቀላለችው በ2000 ነበር። ከምርጫ 97 በኋላ የተከሰተውን የግል ሚዲያ እጥረት አሳስቦት እና የበኩሉን ለመወጣት ብሎ ነው ፍትሕን ለመመሥረት የተነሳሳው። ፍትሕ ጋዜጣ ሕትመት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2004 ሐምሌ ወር (ላይ እስክትታገድ ድረስ) ድረስ ከዓመት ወደ ዓመት የሕትመት ብዛቷ እየጨመረ መጨረሻ አካባቢ እስከ 35ሺ ኮፒ ትታተም ነበር።

ማንኛውም ዓይነት ቅድመ ሳንሱር እንደሌለ በሚደነግገው ሕገመንግሥት መተዳደር ያለበት ፍትሕ ጋዜጣን የሚያትመው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሐምሌ 13/2004 ዓም እትም ላይ ስለ መለስ ዜናዊ የተጻፈ ዜና ካልወጣ እንደማያትሙ አሳወቁ። ይህን የሰማው ተመስገን እያረጉ ያሉት  ቅድመ ሳንሱር መሆኑን፣ ይህ ደግሞ በሕገመንግሥቱ የተከለከለ መሆኑን ከገለጸላቸው በኋላ የታዘዙትን 30ሺ ኮፒ ካተሙ በኋላ እንዳይሰራጭ ከፍትሕ ሚኒስቴር በተላለፈ ትዕዛዝ መሠረት ማገዳቸውን እና የታተመው ጋዜጣም መወረሱን በደብዳቤ ገለፁ። ለ30ሺ ኮፒ ሕትመት፣ ለጸሐፊዎች የሚከፈል እና ለተለያዩ አስተዳደራዊ  ወጪዎች የወጣው ገንዘብ ወደ100ሺ ብር የሚጠጋ ከስሯል። ነሐሴ 2 ቀን  2004 ክስ እንደተመሠረተበት ፋና ዜና ላይ እንደሰማ የሚናገረው ተመስገን፣ በዜናው እንደሰማውም በቀጣይ ቀጠሮ ነሐሴ 9 ቀን 2004 ፍ/ቤት ቀረበ። በ2003 እና በ2004 በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በወጡ 5ት ጽሑፎች ሦስት ክስ እንደቀረበበት ተነግሮት የዋስትና መብቱንም ተነፍጎ የዛኑ ቀን ወደ እስር ቤት ገባ። ለስድስት ቀናት በቃሊቲ ጨለማ ቤት ከቆየ በኋላ ባልተጠበቀ ሰዓት እና ምክንያቱ ሳይነግው  ነሐሴ 16/2004 ከእስር ተለቀቀ። በኋላ ሁላችንም እንደሰማነው ከእስር የተለቀቀው ክሱ ተቋርጦለት መሆኑን ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን የቀረቡበት ክሶች 1ኛ) ወጣቶች በአገሪቱ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱ ላይ እንዲያምፁ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር፣ 2ኛ) የሀገሪቱን መንግሥት ሥም ማጥፋት እና የሐሰት ውንጀላ፣ 3ኛ) ክስ የሐሰት ወሬዎችን በማውራት ሕዝብን በማነሳሳት ወይም አስተሳሰባቸውን ማናወጥ ሲሆኑ ይህን ክስ ሊያስመሠርቱበት የቻሉት ጽሑፎች ደግሞ 1) የፈራ ይመለስ (በተመስገን ደሳለኝ) 2) የሁለተኛ ዜግነት ሕይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ? (በተመስገን ደሳለኝ) 3) መጅሊሱና ሲኖዶሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ (በተመስገን ደሳለኝ) 4) ሞት የማይፈሩ ወጣቶች (በተመስገን ደሳለኝ) እና 5) የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመጨፈር የሚሉት ናቸው።

ፍትሕ በዚ መልኩ ከሕትመት ከታገደች በኋላ ተሜ እጅ እና እግሩን አጣጥፎ አልተቀመጠም ወይም መሰደድን አልመረጠም። በ2005 ፍትሕን በአዲስታይምስ መጽሔት መልክ፣ እሱም እንዲዘጋ ሲደረግ በልዕልና ጋዜጣ እውነትን እንድናነብ ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን ለፍቷል። ልዕልናም ቀኗ ደርሶ ከሕትመቱ ዓለም ስትሰናበት ደግሞ በ2007 በግሉ ዘርፍ ይታተሙ ከነበሩ ተመራጭ ጥቂት መጽሔቶች እና ጋዜጦች ጋር ክስ ተመሥርቶባቸው እንዳይሠሩ ከታገዱት የሕትመት ውጤቶች መሐል አንዷ በሆነችው ፋክት መጽሔት ሥራውን ቀጥሎ ነበር።

በነሐሴ 13፣ 2004 ተቋረጠ የተባለው ክስ መቀስቀሱን አሁንም እሱ በሌለበት በታኅሣሥ ወር 2005 የዋለው ችሎት በፋና ሬዲዮ መዘገቡን ሰማ/ን። በቀጣዩ የቀጠሮ ቀን ሲቀርብ የ50ሺህ ብር የዋስትና ብር አስይዞ ክሱን ከውጪ ሆኖ እንዲከታተል ተፈቀደለት። ክሱን እየተከታተለም ነው ልዕልና ጋዜጣን እና ፋክት መጽሔትን ለኛ ላንባቢዎቹ ሲያደርስ የነበረው። ታኅሣሥ 2005 የተንቀሳቀሰበትን ክስ በዋስትና ሲከታተል ቆይቶ፤  በጥቅምት 3፣ 2007 ጥፋተኛ የተባለው እንዲሁም ጥቅምት 17፣ 2007 ላይ ደግሞ የ3 ዓመት ፍርድ የተፈረደበት።

ተመስገን የሥራ ሰዓት እና የእረፍት ሰዓት የለውም። ብዙውን ጊዜውን በመጻፍ ወይም በማንበብ ነው የሚያሳልፈው። የጻፈውን የኖረ እና እየኖረ ያለ ጋዜጠኛ ነው።

ዝዋይ ከመሄዱ በፊት ቃሊቲ በነበረበት ጊዜያትም ሆነ ዝዋይ ከሄደ በኋላ ተመስገን፣ ሌሎች እስረኞች እንዳይቀርቡት ይደረጋል። ቃሊቲ እያለ የአልሻባብ አባል ተብለው በሽብር ተከሰው ከሱ ጋር የሚኖሩ እስረኞች ከሱ ጋር ካወሩ ወይም ወክ ሲያደርጉ ከታዮ “እንዴት ከአሸባሪ ጋር ትሆናላችሁ?” ይባሉ እና የተለያዩ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርስባቸው ነግረውታል። የዝዋዩ ደግሞ የባሰ ሆኖ ነው ያገኘው። ከሱ ጋር ያወራ ማታ ማታ እየተወሰደ ይደበደባል። ይህን በመፍራት ብዙ እስረኞች ከሱ ጋር መሆን ይፈራሉ። መጽሐፍ አይገባለትም። ሕክምና ለማግኘት ሲጠይቅ “ቆይ ያንተን ጉዳይ እየተነጋገርንበት ነው”  ከሚል ውጪ ያገኘው ምላሽ ስለሌለ ከጀርባ ሕመሙ ስቃይ ጋር አብሮ ይኖራል። ምንም ዓይነት መጽሐፍት አይገቡለትም። ከሌሎች እስረኞች ተውሶ ማንበብም አይችልም። እሱ ያለበት ዞን ላይብረሪ የለም። ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ እንዳይጠይቁት ይከለከላሉ። ብዙ ጓደኞቹ እና ወዳጆቹ ብዙ ርቀት ተጉዘው ከእናቱ እና ወንድሞቹ ውጪ እሱን መጠየቅ አይቻልም ተብለው ይመለሳሉ። የዛሬ ዓመት አካባቢ እናቱን እና ወንድሞቹን ጭምር ለሁለት ወር ያክል እንዳይጠይቁት ተከልክለው ነበር። በተለያዩ ጊዜያትም እነዚሁ የቅርብ ቤተሰቦቹ ገብተው እንዳይጠይቁት ተከልክለው ይመለሳሉ። በአንድ ወቅት ታናሽ ወንድሙ የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ ሊጠይቀው በሄደ ወቅት መግባት እንደማይችል ከነገሩት በኋላ በማያቀው ምክንያት በዝዋይ እስር ቤት ፓሊሶች ተደብድቧል።

ምክንያቱን ባይገባኝም ከቅርብ ቤተሰቦቹ ውጪ መጎብኘት የሚፈቀድለትን አንዳንድ ወቅቶች ተከታትለው የሚጠይቁት ጓደኞቹ ብዙ አይደሉም። ተመስገንን የምንወደው ጓደኛችን ከሆነ ከቤተሰብ ውጪ መጠየቅ አይቻልም ብሎ ቁጭ ከማለት ዝዋይ መጠየቅ ከሚፈቀድለት ቤተሰብ ጋር ሄዶ መልዕክት መላክ ወይም መጠየቅ የሚፈቀድበትን ወቅት ጠብቆ መሄድ።

ተሜ በዝዋይ ከሌሎች እስረኞች በተለየ ብዙ ማእቀቦች ተጥሎበት እየኖረ የመንፈሱ ጥንካሬ የሚገርም ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አራት ፅሁፎችን አስነብቦናል። በእስሩ ወቅት ስላገኛቸው የኢትዮጵያ ሶማሌዎች የሚተርክ በሁለት ክፍል “የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና ከዝዋይ እስር ቤት”  እንዲሁም አሁን በኦሮሚያ ስለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ የጻፈው “ሁለተኛው ምዕራፍ” የሚሉት ጽሑፎች ይገኙበታል።

ከዓመት በፊት በላከው በአንደኛው ጽሑፉ እንዲህ ይላል  “…ግና! ይህ መንግሥታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ሕዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡”

ተሜ እንደቃሉ ጉዞውን እስከቀራኒዮ ያደረገ ጋዜጠኛ ነው። አንድ ዓመት ከአምስት ወር በእስር አሳልፏል። የሚወጣበት ቀን እየቀረበ ነው እንጂ እየራቀ አይደለም የሚሄደው። በቀሪዎቹ ጊዜዎች እና ከወጣ በኋላ በብዕሩ የሚያካፍለንን የኢሕአዴግ መንግሥት ገበናዎች ለማንበብ በጣም ነው የምጓጓው። ተሜ ከዚህ በፊት በብዙ ኮፒ ታትሞ ለገበያ ያበቃው “የመለስ አምልኮ” የተሰኘው መጽሐፍ ተወዳጅነትን አትርፎለታል። በ2007 መጨረሻ አካባቢ ደግሞ ከሙያ ባልደረቦቹ እና ከጋዜጠኛ እስክንድር ጋር (ከቃሊቲ እስር ቤት) በአንድነት በተለያየ ጊዜ የተጻፉ ጽሑፎችን በመጽሐፍ መልክ ታትሟል።

ተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኝነት ሥራው በተጨማሪ ያለውን በማካፈል ይታወቃል። ለጓደኞቹ እና ለወዳጆቹ በችግራቸው ጊዜ ከጎናቸው ሆኖ ለመርዳት የሚችለውን ያደርጋል። በምስሉ ላይ ከተሜ ጋር የሚታዩት ሕፃናት ቤተሰቦቻቸው አቅመ ደካማ በመሆናቸው ወጪያቸውን በመሸፈን የሚረዳቸው ናቸው። ወጪያቸውን ከመሸፈን ባለፈም ባለው ትርፍ ሰዓት ያዝናናቸው፤ እንዲሁም በቋሚነት የሚማሩበት ት/ቤት በመሄድ የትምህርት ሁኔታቸውን ይከታተል ነበር። አሁን ጊዜው ተገልብጦ እነዚህ ህፃናት በወር አንድ ጊዜ ከእናቱ እና ወንድሙ ጋር በመሆን ዝዋይ ድረስ ሄደው ይጠይቁታል።

በነገራችን ላይ ተሜ እነዚህን ሕፃናት እና ቤተሰቡን እንደሚያስተዳድር ለፍ/ቤት ቢገልፅ የቅጣት ፍርዱ ይቀንስለት ነበር። ሆኖም ተሜ ጥፋት ስላላጠፋሁ አቅልሉልኝ ብዬ አልጠይቅም ብሎ ምንም አይነት ማቅለያ ሳያስገባ ነው 3 ዓመት የተፈረደበት።

ብርታትና ጥንካሬን ለተሜ እና ቤተሰቦቹ እየተመኘሁ ተሜን በጨረፍታዬን በዚሁ ላብቃ።

ሰበር ዜና:- አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ዲሲ ፍርድ ቤት ዉሉ።    ሚያዚያ ት 4 ቀን 2008 ዓ.ም.  (April 12, 2016) አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) በዛሬው ዕለት ዋሽንግተን ዲሲ  Office of Capital Reporting Services, 1250 I Street NW, Suite 350, Washington …

ሰበር ዜና:- አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ዲሲ ፍርድ ቤት ዉሉ። የወያኔ ተወካይ ባለስጣን ዓይነት ተቃውሞ አጋጠማቸው። Read more »

Geezedit. ግዕዝኤዲት

ዋና መሥሪያ ቤቱ ብራይተን ኮሎራዶ የሆነው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ቁጥሩ ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ኃምሳ ሰባት የሆነ የዩናይትድ ስቴትስ የባለቤትነት መታወቂያ (ፓተንት) መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. (አፕሪል 7 ቀን 2016 እ.ኤ.አ.) ማግኘቱን አስታወቀ። ፓተንቱ የተሰጠው ለፈጠራውና የኩባንያው ባለቤት ለዶ/ር አበራ ሞላ ሲሆን፤ ኩባንያው የእርሳቸውንና የባለቤታቸው የወ/ሮ ሠናይት ከተማ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደግርማ ካሳ

ማርች 26 እና ማርች 27 ቀን 2016፣ በቪዥን ኢትዮጵያ አማካኝነት አንድ ኮንፍራንስ ተካሄዶ ነበር። በዚህ ኮንፍራንስ ላይ ብዙ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች አቅርበዋል (“የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ”)። ከነዚህ መካከል ፕ/ር መሳይ ከበደ አንዱ ነበሩ። ንግግራቸውን በሦስት ነበር የከፈሉት። የመጀመሪያው ክፍል ስለዘውግ (ethnicity) አንዳንድ ጽንሰ ሃሳቦች ለማሳየት የሞከሩበት ነው። ብዙም የማያከራክር ለጠቅላላ እውቀት የሚሆን ፍልስፍናዊና ቴዎረቲካል ትንተና በመሆኑ እዚያ ላይ ብዙ ጊዜ አላጠፋም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በነዳጅ የከበረችው የናይጄሪያ ናይጄር ዴልታ የቀድሞ አገረ ገዢ፣ የሌላዋ የነዳጅ ባለጸጋ ሃገር የኣንጎላ የነዳጅ ሚኒስትር፣ የሙዋቹ የጊኒ መሪ ላንሳና ኮንቴ ባለቤት እንዲሁም የቀድሞ የተ መድ ዋና ጸሓፊ ኮፊ አናን ልጅ ስምም በፓናማው ሰነድ በተጋለጡት የባንክ ሂሳቦች ስማቸው ተነስቱዋል።

ዘውግና ብሔራዊ አንድነት እንዴት ይታረቃሉ?

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደገለታው ዘለቀ

ይህን ርዕስ የወሰድኩት በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ፕሮፌሠር መሳይ ከበደ “የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ” በሚል ርዕስ ስር ካቀረቡት መሳጭ ጥናታዊ ጽሁፋቸው ስር ካነሷቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መሃል አንዱን መዝዤ ነው። ፕሮፌሠር መሳይ ከበደ በዚህ ፕሮግራም ላይ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፋቸው በርግጥ ደረጃውን የጠበቀና በሚገባ የተደራጀ ነው። ፕሮፌሠሩ ፈላስፋም ስለሆኑ አሳባቸውን በሚገባ ገልጸዋል። አስበውበት ተፈላስፈውበት በመሆኑ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል። በእንዲህ ዓይነት ስብሰባዎች ላይም እንዲህ ዓይነት ትንተና መኖሩ መልካም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መሳይ ከበደ

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደ

ይህ ጽሁፍ በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ ያቀረብኩት ነው።

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በሠላም ወይም በኃይል ከሥልጣን ለማውረድ ቢችሉም እንኳን፤ ባለፉት 24 ዓመታት የተዘረጋውን ዘውጋዊ ክፍፍል ለማብረድና ብሔራዊ አንድነትን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ራዕይና ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚስተዋሉት ችግሮች ሁሉ ተቀዳሚና እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ዘውጋዊ ፖለቲካ በመሆኑ ያለውን መንግሥት ለመጣልና አዲስ ሥርዓት ለመመስርት ስለ ዘውግና ዘውጋዊ ፖለቲካ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘትን ይጠይቃል። ወያኔ ከተሸነፈ የዘውግ ፖለቲካ በራሱ ይጠፋል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት ነው። ይህ ጽሁፍም “የዘውግ ፖለቲካ ዋና ዓላማ ምንድን ነው? ከብሔራዊ አንድነት ጋር በምን ሁኔታ ሊጣጣም ይችላል?” የሚሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ ይዳስሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር #Ethiopia Wetatoch Dimts  መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=1FesCqrygH8]  

የኢትዮጵያ ትልቁ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጭ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሰሞኑን በቫይበር፣ በዋትስ አፕና መሰል የድምፅ ጥሪ አገልግሎቶች መስጫዎች ላይ ክፍያ ለመጠየቅ እንዳቀደ የኩባንያዉ የሥራ አመራር ለተለያዩ ሚዲያዎች መናገራቸዉ ይታወቃል።

ይህ የከተሞች አዋጅ በክልሉ ከተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል። አንቀጾቹ የተሠረዙት ጉዳት ስላላቸው ሳይሆን በሕዝቡ ጥያቄ ስለተነሳባቸው መሆኑን የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አብራርተዋል።

#‎Ethiopia‬ ቴዲ አፍሮ አዲስ አልበሙን በቅርቡ ሊለቅ ነው:: Teddy Afro   #‎MinilikSalsawi‬ ታዋቂው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በቅርቡ እያጠናቀቀ የሚገኘውን አዲስ አልበሙን እንደሚለቅ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ተናግሯል:: ቴዲ አፍሮ ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለአድናቂ ወዳጆቹ አስተላልፏል:: ውድ ወዳጆቼ አዲሱ አልበሜን በማጠናቀቅ ላይ …

ቴዲ አፍሮ አዲስ አልበሙን በቅርቡ ሊለቅ ነው:: Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : በሕወሓት ሚዲያዎች የኦሕዴዽ 26ኛ አመትን አስመልክቶ የምንሰማው ዘገባ ሁሉ የሕወሓት አገዛዝን ድድብና እና የአላዋቂ ሳሚነት እየገለጸለን ነው:;ትላንትና ለነጻነትና ለመብት በሕወሓት ጥይት የተገደሉ የኦሮሞ ልጆች ደም ሳይደርቅ አገዛዙ የመቀባጠሪያ ሚዲያዎቹ የሚለፈልፈው ዲስኩር መበስበሱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::ትግሉ …

የኦሕዴድ 26ኛ አመት በኦሮሞ ሕዝብ ሰማእታት ላይ መሳለቅ ቀጥሏል:: ትግሉ ወደ ዝምታ ተቃውሞ ተቀየረ እንጂ አልቆመም:: Read more »

ዩሱፍ ከዲ

AA traffic police. በደመነፍስ የሚነዱ ትራፊክ ፖሊሶችና የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር

የቅዳሜ ሚያዝያ 1 2008 አጭር ገጠመኝ

ከሜክሲኮ በባልቻ አድርጎ በአብነት ወደ አውቶቡስ ተራ የሚወስደውን በተለምዶ ዶልፊን የሚባለውን ታክሲ ስሳፈር፣ ሰዓቱ ገና አንድ ሰዓት ከሃያ አካባቢ ነበር። ታክሲውም አንድ ወይም ሁለት ሰው ቀርቶት ባልሞላበት ሁኔታም ነበር መንቀሳቀስ የጀመረው። ይህ ድርጊቱ የሾፌሩን “ለሰዓት/ለጊዜ እንዲሁም ለጫናቸው ተሳፋሪዎቹ ያለውን አክብሮት” ያሳየኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁና እንዳከበርከን ክበር እያልኩኝ በውስጤ መልካም እየተመኘሁለት ነው የተጓዝኩት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

Crooked forest and TPLF.

የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያቸው ድል ማግስት መቀሌ ተገኝተው በትግርኛ ባደረጉት የአደባባይ ንግግር፤ “እኛ ከሥልጣን ብንወርድ፤ ነፍጠኞች አንድ ቀን አያሳድሩዋችሁም” ማለታቸውን የዓይን እማኝነታቸውን የሰጡ ሰዎች በወቅቱ አስነብበውናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(አዲስ መረጃ ተካቷል )  ሚያዚያ  3 ቀን 2008 ዓ.ም.  (April 11, 2016) ይህንን ጉዳይ እየተከታተልን አዳዲስ መረጃዎችን እናቀርባለን ባልነው መሰረት አሁን የደረሰን አዲስ መረጃ እንደሚያመለከተው የከሳሽ ወገን ጠበቃ ጥያቄዬን ጨርሻለሁ ብሎ እስኪያበቃ ድረስ  የእምነት ክህደት ቃል በተከታታይ ብዙ ቀናት ሊቆይ …

ሰበር ዜና: – አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) (የእምነት ክህደት ቃል ) ከነገ ጀምሮ ዲሲ ፍርድ ቤት ይሰጣሉ። Read more »

በምስራቅ ኢትዮጵያ ረሃቡ እየባሰ መጥቷል:: #BBC #VIDEO #Ethiopia ለፖለቲካ ፍጆታው የሚሯሯጥ አገዛዝ በተንሰራፋበት ኢትዮጵያ በምስራቁ ግዛት ረሃቡ እየከፋ መቷል ሲል ቢቢሲ በዜናው እወጃው ተናግሯል::ምግብ ለማግኘት ሲባል ሕዝቡ ቀየውን ጥሎ እየተሰደደ ሲሆን ሴቭ ችልድረን እንደጠቆመው በምብ እጥረት ከሚሞቱት በተጨማሪ 16 ሚሊዮን …

በምስራቅ ኢትዮጵያ ረሃቡ እየባሰ መጥቷል:: BBC VIDEO Read more »

በምስራቅ እዝ የሕወሓት ሰራዊት የጦር መሪዎች እና በበታች መኮንኖች መካከል ንትርኩ ከሯል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianArmy‬ ‪#‎Ogaden‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎Change‬ ተቃዋሚዎች ወደሰራዊቱ ዘልቀውለመግባት አለመቻላቸውናፍላጎት አለማሳየታቸው አንዱችግር ነው Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በጎዴ በሚገኘው የሕወሓት ምስራቅ እዝ ክፍለጦር የጦር መሪዎች …

በምስራቅ እዝ የሕወሓት ሰራዊት የጦር መሪዎች እና በበታች መኮንኖች መካከል ንትርኩ ከሯል:: Read more »

ለኢሻ ሰላት በሼህ ሆጀሌ መስጂድ ተገኝተው የነበሩ የተወነሱ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተደበደቡ አቡ ዳውድ ኡስማን ትላንት መጋቢት 2 /2008 ከኢሻ ሰላት በኋላ በታላቁ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ ፖሊሶች ወደ መስጂዱ በመግባት በመስጂዱ የነበሩትን የተወሰኑ ሙስሊሞች ደብድበዋቸዋል፡፡ በተደጋጋሚ በመስጂዱ ረብሻ ፈጥሮ ሙሰሊሙን በመደብደብ …

በሼህ ሆጀሌ መስጂድ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተደበደቡ Read more »

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች የክለቡ ቦርድ ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ:: በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ስታዲይም የቡና ክለብ ደጋፊዎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ተቃውሞ ሲገልጹ አምሽተዋል::በቦታው የነበረ የቡና ክለብ ደጋፊ እንዲህ በጽሁፍ አስፍሮታል:: እግር ኳሳችን ባያድግም እንደ ኢትዮጵያ ቡና የመሰለ ደጋፊ ባለቤት …

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች የክለቡ ቦርድ ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ:: Read more »

አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ናሽቪል፣ ቴኔሲ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰው ፍርድ ቤት እንደቀረቡ ባለፈው ሳምንት የዜና ሽፋን እንደሰጠነው ይታወቃል። አቡነ ፋኑኤል “ወያኔ ይገድለናል” ብለው ከአሜሪካ መንግሥት የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው የተፈቀደላቸው ቢሆንም፣ ከወያኔ ሹመትን ተቀብለው ወደ አሜሪካን ተመልሰው በመምጣት ወያኔን እያገለገሉ …

ትንሽ ስለ አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) አዋናባጅነት ከዜና ማህደራችን Read more »