ከርሳም መሬት!- ለእናቴ የጻፍኩት ጦማር – Muluken Tesfaw
ከርሳም መሬት!- ለእናቴ የጻፍኩት ጦማር – Muluken tesfaw እናቴ ዛሬ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ‹ሲከፋህ ቤተ ክርስቲያን ሂድ!› ባልሽኝ ምክር መሠረት እስከዛሬ አድባር ላድባር ስዞር ኖርኩ፡፡ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያን ሂጄ ‹ምክርሽን ባልሰማ ኖሮ› እያልኩ ተጸጽቻለሁ፡፡ ይህች ከርሳም መሬት ይህን ሁሉ ሕዝብ …
ከርሳም መሬት!- ለእናቴ የጻፍኩት ጦማር – Muluken tesfaw እናቴ ዛሬ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ‹ሲከፋህ ቤተ ክርስቲያን ሂድ!› ባልሽኝ ምክር መሠረት እስከዛሬ አድባር ላድባር ስዞር ኖርኩ፡፡ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያን ሂጄ ‹ምክርሽን ባልሰማ ኖሮ› እያልኩ ተጸጽቻለሁ፡፡ ይህች ከርሳም መሬት ይህን ሁሉ ሕዝብ …
በትግራይ ክልል የእምባስነይቲ ህዝብ ቀድሞ የነበረውን ወረዳ እንዲመለስለት ከ20 ዓመታት በላይ ጠይቆ አወንታዊ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት የተሰማውን ቅሬታ ትላንት በሰላማዊ ሰልፍ ገልጿል።
መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል ህዝቡ።
ከ500 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕለተ ስቅለትን እንዴት ታከብር እንደነበር በመጠኑ ሊያሳዩን ከሚችሉ መዛግብት አንዱ ‹ዜና ደብረ ሊባኖስ› የተሰኘው መዝገብ ነው፡፡ ዜና ደብረ ሊባኖስ በ1586 ዓም የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ አምስት ነገሮችን ይዟል፡፡ የደብረ ሊባኖስን ታሪክ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት …
“ጠዋት ቂሊንጦ ስንሄድ አራቱ ሰዎች የሉም። ያሉበትን የሚነግረን አላገኘንም።” ወ/ሮ ዓይናለም ደበሎ፤ ላለፉት አራት ወራት በማዕከላዊ እሥር ቤት የነበሩትና ካለፈው አርብ አንስቶ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል፤ ከተባሉት የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባላት ቤተሰብ አባላት አንዷ ናቸው። ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ → …
እስር ላይ የሚገኙትን አራት የኦፌኮ አመራር አባላት መጠየቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ – VOA Read more »
ያዳምጡ → listen
በበፍቃዱ ኃይሉ
ዓይን የሚፈታተን ደብዛዛ ብርሃን ያለበት ክፍል ውስጥ አስገብተው ከኋላዬ ወፍራሙን የብረት በር፣ ልብ በሚያደባልቅ ጓጓታ ድብልቅ አድርገው ዘጉት፡፡ ወደመታሰሪያ ክፍል የገባሁት እንዲህ ነበር፡፡ ሰዓቱ ከምሽቱ 3፡00 ወይም 4፡00 ሰዐት ገደማ ነው፣ ሚያዝያ 17፣ 2006፡፡ ከውስጥ መሬት ላይ የተኙ ሰዎች ይታዩኛል፡፡ በእጄ ያንጠለጠልኩትን ፌስታል እንደያዝኩ ተራ በተራ አየኋቸው፡፡ አንደኛው ከተኛበት ተነስቶ ቁጢጥ አለ፡፡ ‹ካቦው ይሄንኛው ነው ማለት ነው› አልኩ በልቤ፡፡ ‹የሻማ ሲጠይቁኝ ኪሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ሰጥቼ ለመገላገል ፈልጌያለሁ› እነርሱ ግን የሻማ አልጠየቁኝም፡፡ ‹አረፍ በል› አሉኝ፡፡ ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ‹ራት በልተሃል?› አሉኝ፤ ‹አዎ በልቻለሁ›፡፡
‹ምን አድርገህ ነው?›
‹ጸሐፊ ነኝ፡፡›
‹አሃ፣ ጋዜጠኛ ነህ?›
‹አይ፣ ኢንተርኔት ላይ ነው የምጽፈው፡፡›
‹ሙስሊም ነህ?›
‹አይ አይደለሁም፡፡›
የሚያስፈራ ዝምታ ሰፈነ፡፡ ‹እናንተስ?› አልኳቸው፤ ዝምታውን ለመስበር፡፡
ቁጢጥ ያለው፣ ‹እኔ እና እሱ› አለ ወደ አንደኛው ልጅ እየጠቆሙ ‹በሙስሊሞች ጉዳይ ነው፤ እነሱ› አለኝ ወደሌሎች ሦስት ልጆች እየጠቆመ ‹ከጋምቤላ ነው የመጡት፤ እኚህ ከሶማሊ ክልል ነው የመጡት፡፡ ያኛው› ወደጥግ ወዳለው እየጠቆመ ‹በግንቦት ሰባት ነው የተጠረጠረው› አለኝ፡፡ ሰባት ነበሩ፡፡ እኔ ስምንተኛ ሆንኩላቸው፡፡ በሳይቤሪያ የዘጠኝ ቁጥር እስረኛ ሆኜ ተቀላቀልኳቸው፡፡ ማብራሪያውን የሰጠኝ ረደላ ሸፋ ነበር፡፡ ሦስቱ አኙዋኮች ኡማን ኝኬው፣ ኡጁሉ ቻም እና ኝጎ ኩምቻሬ ነበሩ፡፡ ሶማሌው፣ እኔ በገባሁ በሁለተኛው ቀን ስለተፈታ ዘነጋሁት፡፡ የረደላ አባሪ ሐሰን ነው፡፡ ጥግ ላይ የነበረውና በክፍላችን ብቸኛው የግንቦት ሰባት ወታደርነት ተጠርጣሪ የነበረው አበበ ካሴ ነበር፡፡
ኒጎ ኩምቻሬ እሱ ተኝቶባት የነበረውን ፍራሽ ለቆልኝ እስከመጨረሻ ድረስ የቆየሁባትን ጥግ ላይ ያለች ምቹ ቦታ አወረሰኝ፡፡ ‹በቃ፣ አሁን ተኛ እና ነገ እናወራለን› አሉኝ፡፡ እሺ አልኳቸው፡፡ እነርሱ ተኙ፡፡
አበበ ካሴ እኔ በገባሁበት ሰዐት ምርመራ ጨርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን በአስፈሪ ዝምታ የተዋጠ ሰው ነበር፡፡ ተሰብስበን ኮንከር (ካርታ) ስንጫወት ብቻ፣ እየዳኘ በተራው ይጫወታል፡፡ እየቆየን ስንመጣ ግን ቀስ በቀስ ያዋራኝ ጀመር፡፡ ጠርጣራ ስለነበር፣ ድምፁን በጣም ዝቅ አድርጎ በእርጋታ ነበር የሚያዋራኝ፡፡ ምርመራ አምሽቼ ስመጣ፣ እልሄን የምወጣው እነሱ ጋር ነበር፡፡ ያሉኝን ብስጭቶችና ብሶቶች ሁሉ እነርሱ ላይ እዘረግፈዋለሁ፡፡ እነርሱም፣ አብዛኞቹ ምርመራቸውን ጨርሰው ክስ የሚጠባበቁ ስለነበሩ፣ እኔን ከበው ማፅናናት ብቻ ሆነ ሥራቸው፡፡ አበበ አንድ ቀን ማታ መጥቼ እንደለመድኩት ‹ሊገሉኝ ነው፤ ካልገደሉኝ አይለቁኝም› እያልኩ ሳማርር፡፡
‹አሁን ይቺን ተመታሁ ብለህ ነው?› አለኝ፡፡
በአባባሉ ተናድጄ መልስ ከመስጠቴ በፊት የእጆቹን አይበሉባ አሳየኝ፡፡ ‹ጥፍሮቼን እያቸው› አለኝ፡፡ ጥፍሮቹ ጣቶቹ ላይ የሉም፡፡ ‹እኔ እንኳን እንዲህ አድርገውኝ ዋጥ ነው ያደረግኳት፡፡ ወንድ ልጅ ቻል ነው ማድረግ ያለበት፡፡ ወንድ አደለህ እንዴ?› እኔ የወንድነት ጀብድ የምመኝበት ጊዜ ላይ አልነበርኩም፡፡ ይልቁንም እሱ እኔን ለመምከሪያ ያሳየኝ ጣቶቹ ማስፈራሪያ ሆነው አረፉት፡፡ እኔም ባለተራ ነኝ ብዬ አሰብኩ፡፡
አበበ ካሴ ቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበረ፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተዋጋ፣ ከዚያ በኋላ ግን ለቅቆ ግንቦት ሰባትን የተቀላቀለ ወታደር ነበር፡፡ ሲራመድ ያነክሳል፡፡ ‹ምን አርገውህ ነው?› ስለው ‹ምኑን አውቄ› አለኝ፡፡ ሲደበደብ ራሱን ይስት ነበር፡፡ አበበ ካሴ ከኤርትራ ጎንደር የዘመዱን ሠርግ ለመታደም መጥቶ ነው የተያዘው፡፡ በምርመራ ወቅት የግንቦት ሰባት ወታደር መሆኑን በፍፁም አላመነም ነበር፡፡ ያደገበት እና የኖረበት ኩራት በዱላ ፊት መንበርከክ አልፈቀደለትም፡፡ ክስ ከተመሠረተበት በኋላ ግን ለፍርድ ቤቱ “አዎ፣ የግንቦት ሰባት ወታደር ነኝ፤ የሆንኩትም አምኜበት ነው” ብሏል፡፡
አበበ ካሴ ከኔ ክፍል ተቀይሮ ተስፋለም ታስሮበት ወደነበረው 4 ቁጥር የተዛወረው ከአጭር ቀናት በኋላ ነበር፡፡ ነገር ግን መልሰን ቂሊንጦ ዞን ሁለት ተገናኘን፡፡ አበበ መጀመሪያ የተከሰሰው በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ በአንቀጽ 4 ቢሆንም፣ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከተደመጡ በኋላ ተቀይሮለት 7/1 ሆኖለታል፡፡ የዛኔ ‹እንኳን ደስ አለህ› ልለው ክፍሉ ሄጄ ነበር፡፡ ሳቀብኝ፡፡ ‹ታስሬ እያለሁ ቁጥር ተቀነሰልኝ ብዬ የምደሰት ይመስልሃል?› ስሜቱን አላጣሁትም፡፡
እንደአበበ ካሴ በቂሊንጦ አስተዳደር የሚጠላ የፖለቲካ እስረኛ አልገጠመኝም፡፡ አበበ ሕክምና ተከልክሎ እግሩ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሸመቀቀ አጥሮ ግቢ ውስጥ በምርኩዝ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ ብልቱ ላይ በምርመራ ወቅት በደረሰበት ጉዳት የሚያዥ ነገር ተከስቶበት ሕክምና ሲጠይቅ ተከልክሏል፡፡ በጥቅሉ የሰው ልጅ ላይ የሰው ልጅ ሊያደርስበት የሚችለው በደል ሁሉ እየደረሰበት ነው፡፡
አበበ ካሴ አሁን 7 ዓመት ከዘጠኝ ወር ፅኑ እስራት ተፈርዶበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገብቷል፡፡
እንደ አበበ ሁሉ አዱኛ እና መገርሳም በየቀኑ ሐሳቤ ናቸው፡፡ ማዕከላዊ ሳይቤሪያ የሚባለው ወንዶች ክፍል፤ ዘጠኝ ቁጥር ውስጥ ሁለት ሳምንት ከቆየሁ በኋላ ከክፍላችን የሚወጡ ሰዎች በዙ፡፡ ከሦስቱ የአኙዋ ልጆች አንዱ – ኝጎ ኩምቻሬ – ጓደኞቹ ላይ ሊመሰክር ተስማምቶ ወደጣውላ ክፍል ተዛወረ፡፡ ኡማን እና ኡጁሉ ክስ እስኪመሠረትባቸው ድረስ ወደሚቆዩበት ሸራተን ተዛወሩ፡፡ የሶማሊ ክልሉ ሰው ተፈታ፡፡ በምትካቸው ግን ብዙ ሰዎች መጡ፡፡
የአዳማ ዩንቨርስቲው አዱኛ ኬሶ መጣ፡፡ ገብረሚካኤል እና ሌላ ሥሙን የዘነጋሁት ሰው ከትግራይ ክልል መጡ፡፡ ሌላም ሰውዬ ከሶማሊ ክልል መጡ፡፡ አጀሌ ከቤንሻንጉል/ጉምዝ መጣ፡፡ ሁሉም የተጠረጠሩት በሽብርተኝነት ወንጀል ነው፡፡
ከሁሉም ሳቂታና ተጫዋች የነበረው አዱኛ ኬሶ ነበር፡፡ አዱኛ ከተያዘ 19 ቀናት እንደሆነው ነገረን፡፡ ‹የት ቆየህ?› አያውቀውም፡፡ ምክንያቱም፣ ወደቆየበት ቦታ ሲሄድም ሆነ ወደእኛ ሲመጣ ዓይኖቹ በጨርቅ ተሸፍነው ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ወደሽንት ቤት ሲወሰድ እና ሲመለስ ዓይኖቹ በጨርቅ ይሸፈኑ ነበር፡፡ አዱኛ ወደኔ ክፍል ሲመጣ ግራ ዓይኑ ስር የበለዘ ነገር ነበረው፡፡ ‹ምንድን ነው?› ብዬ ስጠይቀው፣ ‹ሲይዙኝ በቡጢ የነረቱኝ ነው› አለኝ፡፡ አሁን ድረስ ያ የቡጢ አሻራ ጠባሳ ሁኖ ቀርቷል፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ በፖሊስ ተደግፎ መጥቶ፣ በፖሊስ ተደግፎ 8 ቁጥር (የብቻ ጨለማ ቤት) ሲወጣና ሲገባ የቆየው መገርሳ ወደእኛ ክፍል ገባ፡፡ መገርሳ ወርቁ የሐሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነበር፡፡ መገርሳ መጀመሪያ የተያዘው ሐረማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ በተወረወረ ቦምብ ተሳትፈሃል በሚል ተጠርጥሮ ነበር፡፡ መገርሳን ሐሮማያ ከተማ ተደብድቧል፡፡ ድብደባው እርቃን ነበር፡፡ እጆቹ በገመድ ተጠፍረው ጉልበቱን ያቅፍና በእጆቹ መታጠፊያ እና በቋንጃው መካከል እንጨት ያልፍና ይሰቀላል – ወፌ ይላላ፡፡ ከዚያ ይደበደባል፡፡ መገርሳ ይህንን ይነግረኝ የነበረው፣ እግሮቹ መታጠፊያ ላይ የቀረውን ሰምበር የመሰለ ነገር እያሳየኝ ነው፡፡ ‹ተንጠልጥዬ እየተሰቃየሁ ብልቴን ይጎትቱታል› ብሎኛል ሲነግረኝ፡፡ በመሐሉ ራሱን ይስታል፡፡ ‹ከዚያ ቅዝቅዝ ሲለኝ እነቃለሁ፤ ስነቃ አውርደውኝ አገኛለሁ፡፡ አሁንስ ታምናለህ አታምንም ይሉኛል፡፡ የማምነው ነገር እንደሌለ ሲያውቁ መልሰው ይሰቅሉኛል፡፡› አለ፡፡ በመጨረሻ ግን መገርሳ ተረታ፡፡
‹ሳስበው ከምሞት፣ ዕድሜ ልክ ተፈርዶብኝ በሕይወት ብኖር ይሻለኛል ብዬ አሰብኩ› አለ፡፡ ‹አዎ፣ እኔ ነኝ ቦንቡን የወረወርኩት› አላቸው፡፡ መርማሪዎቹ ተደሰቱ፡፡ ራቁቱን የሆነ ክፍል ውስጥ መሬት ላይ አጋድመውት ሄዱ፡፡ ከዚያ ‹በሕይወቴ የማይዘነጋኝ ዘግናኝ ነገር ተከሰተ› ብሎ የሚከተለውን አጫወተኝ፡፡ ቤቱ ውስጥ የዶሮ ጫጩቶች ነበሩ (የአንዱ የደህንነት ሰራተኛ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይመስለዋል ያለው)፡፡ ጫጩቶቹ መጥተው እየተራመዱ እላዩ ላይ ይወጡበታል፡፡ መገርሳ እነርሱን “እሽ” ብሎ የሚያባርርበት አቅም አልነበረውም፡፡ እግራቸው ይበላዋል፡፡ ሲነግረኝ ‹ጫጩቶቹን ጠላኋቸው› ነበር ያለኝ፡፡ ግን ምንም ሊያደርጋቸው አልቻለም፡፡
በማግስቱ በካሜራ ፊት ሐረማያ ዩንቨርስቲ ግቢ ውስጥ የፈነዳውን ቦምብ ያፈነዳው እሱ እንደሆነ አመነ፡፡ እሱ በወቅቱ ዩንቨርስቲው ግቢ ውስጥ አልነበረም፡፡ እንዲያውም የታቀደ ረብሻ እንዳለ መረጃው ቀድሞ ደርሶት ለዩንቨርስቲ ግቢው የኦሕዴድ ጽ/ቤት ደውሎ ማስጠንቀቁን ነግሮኛል፡፡ ያ ሁሉ አልፎ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ ነገር ግን፣ እሱ ወደአዲስ አበባ እየመጣ እያለ ፖሊስ የእውነትም ቦንቡን ወርውሮታል ብሎ ያመነበትን ሰው ያዝኩኝ አለ፡፡ ነገር ግን ካፈርኩ አይመልሰኝ ባይ መንግሥት መገርሳን ከመክሰስ አልተመለሰም፡፡ ጽፈኸዋል በተባለው ግጥም ክስ ተመስርቶበት ‹ተከላከል› ተብሎ፣ መከላከያ ምስክሮቹን አስደምጦ ‹የነጻ› ወይም ‹ጥፋተኛ› ብይን እየተጠባበቀ ነው፡፡ አዱኛ ኬሶም በተመሳሳይ መዝገብ ‹በቄሮ አባልነት› ተከላከል ተብሎ መከላከያ ምስክሮቹን እያስደመጠ ነው፡፡
ታስሮ መፈታት ቅጣት ነው፡፡ ሰቅጣጭ በደል በሚፈፀምባት ከተማ፣ አገር ሠላም ብሎ ከሚኖር ሰው ጋር ምንም እንዳላየ፣ ምንም እንዳልሰሙ መስለው የመኖር ቅጣት፡፡
ማዕከላዊ ምርመራ ወጥቼ ስገባ፣ መታሸት ሲያስፈልገኝ ሲያሸኝ፣ ጨዋታ ሲያመምረኝ ሲያጫውተኝ የነበረው ረደላ ሸፋ እና አባሪው ሀሰን ሁለቱም ‹ነጻ ለመውጣት ወይም ጥፋተኛ ለመባል ተከላከሉ› ተብለው መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማስደመጥ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ የቤንሻንጉሉ አጄላ አራት ዓመት ተፈርዶበት ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ተወስዷል፡፡ አቦይ ገብረሚካኤል ‹ተከላከሉ› ተብለው መከላከያ ምስክር እያስደመጡ ነው፡፡ ኡማን እና ኡጁሉም ‹ጥፋተኛ› ተብለው ፍርዳቸውን ለመመቀበል ቀጠሮ ተይዞላቸዋል፡፡
እስረኞች ይመጣሉ፣ ከሰሜን ይመጣሉ፣ ከደቡብ ይመጣሉ፣ ከምሥራቅ ይመጣሉ፣ ከምዕራብ ይመጣሉ፡፡ በሕዝብ ጥቅም ሥም ጦር መዝዞ ሥልጣን የተቆጣጠረው መንግሥት ዛሬም የፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፡፡
ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በፌደራል ትምሕርት ሚኒስቴርና በቤንሻጉል ክልል ምክር ቤት ላይ የፍትሐቤር ክስ መመስረታቸው ታወቀ። ለክክልሉ ምክር ቤት መጥሪያ ሊሰጡ የሄዱት የአርሶ አደሮቹ ተወካይ ተይዘው መታሰራቸውም ይሰማል። የክልሉን ምክትል አስተዳዳሪ እና የቤንሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች …
ከ400 በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ክስ መመስረታቸው ታወቀ – VOA Read more »
«የሽምብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ የትም የትም ዞሬ ትዝ አለኝ ሀገሬ» የዛሬ ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን «የመሰንቆው ሊቅ» ጌታመሳይ አበበ ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ የባህል ሙዚቃ ጨዋታዎች በግንባር ቀደምትነቱ የሚታወቀዉ ነዉ። ሁለ ገቡ ከያኒ ጌታመሳይ አበበ «የጥበብ ገበሪም » በመባል ይታወቃሉ። …
አቡነ ፋኑዔል (አባ መላኩ) ኤፕሪል 14 ቀን 2016 በዩቱብ ያሰራጩት ቪዲዮhttps://www.youtube.com/watch?v=AV-Twe0a9jM የሚያሳየው በጥቅሉ መልዕክቱ አንድ ነው። ይሄውም:- የናሽቪሉን ደብረ ቀራንዮ መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን መነሻ አድረገው ያው የተለመደዉን የካድሬነት መልክታቸዉን ለማስተለልፍ ነው። ‘እስካሁን ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ ያልተጠቃለላችሁ አብያተ ክርስቲያናት እድሉ ሳያመልጣችሁ …
አቡነ ፋኑዔል (አባ መላኩ) ለናሽቪል ደ/ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ/ክ ላሰራጩት መልዕክት የተሰጠ መልስ Read more »
ከፍተኛው ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል

– የህክምና ስህተቱን የፈፀሙት ሃኪም ከሥራ ተባረዋል
– “የሃሞት ጠጠሩ በነፃ ስለወጣልሽ ዕድለኛ ነሽ” ሲሉ ዋሽተዋታል
በዘውዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በተፈፀመ የህክምና ስህተት ሣቢያ እንቅርት ለማስወጣት የሄደችው ታካሚ በስመ ሞክሼ በተፈጠረ ስህተት ለሃሞት ጠጠር ህክምና ሆዷ ተከፈተ። ታካሚዋ ከሁለት ዓመታት ወረፋ ጥበቃ በኋላ ተራዋ ደርሶ በአንገቷ ላይ የወጣውን እንቅርት ለማስወጣት ነበር ወደ ሆስፒታሉ የሄደችው፡፡
ሠላም ደሞዜ የተባለችው ታካሚ በአንገቷ ላይ የወጣውን እንቅርት ለማስወጣት አስፈላጊውን ምርመራ አድርጋ በሆስፒታሉ አልጋ ትይዛለች። በሌላ በኩል ሰላም ኪሮስ የተባለች ታካሚ ደግሞ ለሃሞት ከረጢት ጠጠር ህክምና ወረፋ ጠብቃ ቀጠሮዋ በመድረሱ ነበር ወደ ሆስፒታሉ ያመራችው፡፡ ወጣቷ በቀዶ ህክምና ከህመሟ ለመፈወስ አስፈላጊውን ምርመራ አከናውና በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ እንድተኛ ይደረጋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ሁለቱም ህሙማን የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው ቀጠሮ ተይዞላቸው ሲጠባበቁ ከቆዩ በኋላ ለእንቅርት ህክምና ወደ ሆስፒታሉ ያመራችው ሰላም ደሞዜ በቅድሚያ ወደ ቀዶ ህክምናው ክፍል ትገባለች። የእንቅርት ታካሚዋ በቀዶ ህክምናው ክፍል ከገባች በኋላ ለሃሞት ከረጢት ጠጠር ህክምና ሆዷ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ በታካሚዋ ሃሞት ውስጥ ለቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር አለመኖሩን ያስተዋሉት የቀዶ ህክምና ባለሙያው፤ ሆዷን መልሰው በመዝጋት የእንቅርት ማውጣት ህክምናውን ያደርጉላታል፡፡
ጉዳዩ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረባቸው ሃኪሙ፤ በወቅቱ ስለተፈፀመው ሁኔታ አንዳችም ነገር ሳይናገሩ የቀዶ ህክምና ክፍሉን ለቀው ይወጣሉ። ከስፍራው ያገኘናቸው ምንጮች እንደገለፁልን፤ የሀኪሙ ረዳቶችና በስፍራው የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ችግሩን ለመሸፈንና የተፈጠረውን ስህተት ለመደበቅ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ ታማሚዋ ለእንቅርት ቀዶ ህክምና ወደ ሆስፒታሉ ቢመጡም የሃሞት ከረጢት ጠጠር ችግር ስለተገኘባቸው ህክምናው በነፃ እንደተደረገላቸውና በዚህም ዕድለኛ እንደሆኑ በመንገር ቤተሰቦቻቸውን ለማሳመን ጥረት አድርገዋል ተብሏል፡፡ ሁኔታው ያልተዋጠላቸው የታማሚዋ ቤተሰቦች ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የህመም ምልክት ባልታየበት፣ ምርመራና ቅድመ ህክምና ባልተደረገበት ሁኔታ በድንገት ለሃሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር ሊፈጠር አይችልም በሚል ከሆስፒታሉ አስተዳደርና ከህክምና ባለሙያዎቹ ጋር ውዝግብ ይፈጥራሉ፡፡ ጉዳዩ የሆስፒታሉ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ደርሶም እንዲጣራ ከተደረገ በኋላ ትልቅ የህክምና ስህተት መፈጠሩ ታምኖበት፣ የህክምና ባለሙያዎቹና አስተዳደሩ ቤተሰቦቿን ይቅርታ በመጠየቅ ለታካሚዋ የቅርብ የህክምና ክትትል እንዲደረግላት የተወሰነ ሲሆን የቀዶ ህክምና ባለሙያውና ረዳቶቹ ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የዘውዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ተረፈ አሰፋ፤ የህክምና ስህተቱ መፈፀሙን አምነው ስህተቱ የተፈፀመው በወቅቱ የቀዶ ህክምናውን ያደረጉት ሃኪምና ረዳቶቻቸው ታካሚዋ በትክክል የመጣችው ምን ዓይነት ህክምና ልትፈጽም መሆኑንና ሌሎች ሁኔታዎችን በአግባቡ ሳያረጋግጡ ህክምናውን በመጀመራቸው ነው ብለዋል፡፡
አንድ ሰው የቀዶ ህክምና ከማድረጉ በፊት በአግባቡ ሊደረግ የሚገባው “ሰርጂካል ሴፍቲ ቼክ ሊስት” መኖሩን የጠቆሙት ዶ/ር ተረፈ፤ በዚህች ወጣት ታካሚ ላይ ይህ ጥንቃቄ ሳይደረግ በመቅረቱ ስህተቱ መከሰቱን አስረድተዋል፡፡
የስህተቱ መፈፀም ሳያንስ በወቅቱ ስህተቱ አምኖና ስለ ሁኔታው ለቤተሰቦቿ ትክክለኛ መረጃ ሰጥቶ ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ የነበረ ቢሆንም ይህም አለመደረጉን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
“አሁን ታካሚዋ ለህይወቷ የሚያሰጋት ምንም አይነት ችግር የሌለባት መሆኑ በህክምና ባለሙያዎች በሚገባ ስለተረጋገጠ ስለጉዳዩ ለቤተሰቦቿ በቂ መረጃ በመስጠት ይቅርታ ጠይቀናቸዋል፡፡ ታማሚዋ ግን ከሆስፒታሉ እንድትወጣ በሃኪሞቿ ቢፈቀድላትም ሁለት ቀዶ ህክምና በማድረጓ በቅርብ ሆና የጤናዋን ሁኔታ እንድንከታተላት ስለፈለግን አሁንም በሆስፒታሉ ውስጥ ትገኛለች፡፡ የጤናዋ ሁኔታ ግን በጣም ጥሩ ነው” ብለዋል – ዶ/ር ተረፈ አሰፋ፡፡ ስህተቱን የፈፀሙት የቀዶ ጥገና ሃኪም በኮንትራት የተቀጠሩ መሆናቸውን ያመለከቱት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ፤ ከሥራና ከደመወዝ እንዲታገዱ በማድረግ የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል፡፡
ትልቁ ስህተት የቀዶ ሃኪሙ ቢሆንም ሥራው ላይ የተሳተፉት የሀኪሙ ረዳቶችም ከተጠያቂነት ሊያመልጡ እንደማይችሉ ጠቁመው እነሱም የዲሲፕሊን እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል – ዶ/ር ተረፈ፡፡
እስከአሁን ባደረግነው ክትትል በትናንትናው ዕለት 14 ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንና አስከሬኖቻቸው ተለይተው ዛሬ ለዘመድ አዝማድ መላካቸውን ለሆስፒታል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል። አስክሬን ፍለጋው መቀጠሉ ተነግሯል። ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen
የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል። የውሣኔ ሃሣቡን የያዘው ሰነድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን መግደላቸው በተገለፀበት በአሁኑ ሁኔታ የአሜሪካው …

ጥር 9/2008 ዓ.ም. ማለዳ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ አዲስ በተገነባው የፍጥነት መንገድ ላይ ይጓዝ የነበረ አሽከርካሪ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖታል። የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪው በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ነው። ከተቃራኒ አቅጣጫ አንድ መለስተኛ አዉቶቡስ አስራ ስድስት ሰዎች ጭኖ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘ ነው። የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪው የሚጓዝበትን መንገድ ስቶ
በታንዛኒያ በሕገወጥ ስደተኝነት ተፈርዶባቸው በእስር የቆዩ 74 ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ድንበር ከተማ ታቬታ ተጥለዋል። ድርጊቱ ያስቆጣት ኬንያ “በዓለምአቀፍ ሕግ የታንዛኒያን ሸክም የምቀበልበት እዳ የለብኝም” በማለት አውግዛ ባሳለፍነው ማክሰኞ ከእስር የተፈቱትን ኢትዮጵያዊያን ወደ ታንዛኒያ እንደምትመልስ ገልጻለች። ታንዛንያ እስረኞቹን ወደሀገራቸው ኢትዮጵያ ከመመለስ ይልቅ ወደ ኬንያ ወስዳ የመልቀቋ ምክንያት የታወቀ ነገር የለም (ምንጭ:- ኒውስ24) Filed under: NEWS![]()

• ከዩኒቨርስቲው ጋር የተፈራረሙት የደብረ ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪ ከሥራቸው ታግደው ነበር
• ሐዋርድ ያዘጋጀው ውል የባለቤትነት መብትን ይነፍጋል
• ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትቀበለው ውል እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል
“እውነት እና አገልግሎት” ተቋማዊ ብሂሉና መፈክሩ ነው፡፡ በተለይ፣ ለጥቁሮች በሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ዕድልና አስተምሮ በሚያወጣቸው ጥቁር ምሁራን ብዛት ይታወቃል – የአሜሪካው ሐዋርድ ዩኒቨርስቲ፡፡
የዘርና የቀለም ልዩነቶች፣ ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ በደሎች ያስከተሏቸውን መድልዎች፤ ለማኅበራዊ ፍትሕ በቆሙና ለሰብአዊ ነፃነት በሚሟገቱ ምሁራን ማስወገድ ዓላማው ያደረገው ዩኒቨርስቲው፤ በአፍሪካ፣ በአሜሪካና በሌላውም ዓለም የተበተኑ ጥቁሮችን የታሪክና የባህል ቅርሶች ያካበተበት የምርምር ማዕከሉም ከዓለም በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት መካከል ያደርገዋል፡፡
በየአጋጣሚው ያሰባሰባቸውን ቅርሶችና ውርሶች፣ ወደ ጥንት ቦታቸውና ትክክለኛ ባለቤቶቻቸው በሕጋዊ መንገድ መመለስ፣ “ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶቹን ማክበር ነው፤” ይላሉ፣ የዩኒቨርስቲው የሥነ መለኰት ት/ቤት የአካዳሚያዊ ጉዳዮች ተባባሪ ዲን ዶ/ር ጌይ ባይረን፡፡ በተለይም ኢትዮጵያዊ ቅርሶችን ለኢትዮጵያ የመመለስ ጉዳይ፣ የት/ቤቱ የቆየ ፍላጎት እንደነበርና ይህም በአሜሪካም ሆነ በሌላው ዓለም ቅርሶቹን በግልና በተቋም ለያዙ ግለሰቦች፣ ሙዝየሞችና ተቋማት አርኣያነት እንዳለውና ተነሣሽነትንም እንደሚፈጥር ዶ/ር ባይረን ያስረዳሉ፡፡
በት/ቤቱ ማኅደረ ቅርስ ከተከማቹት ኢትዮጵያዊ የብራና ሥነ ጽሑፍ ሀብቶች መካከል፣ ገድለ ቅዱስ ሰራባሞንና ገድለ ቅዱስ ጳውሎስ አንዱ ነው፡፡ የብራና መጽሐፉ፣ በ1993 ዓ.ም. ዶ/ር አንድሬ ቲውድ ከተባሉ የዩኒቨርስቲው የቀድሞው ተማሪ በስጦታ የተበረከተ ሲሆን የ4ኛው መ/ክ/ዘመኑን ሰማዕት ቅዱስ ሰራባሞንና የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ገድል በአንድ ጥራዝ የያዘ ነው፡፡ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከዐረብኛ ወደ ግእዝ የተተረጎመው በዘጠነኛው የደብረ ሊባኖስ ዕጨጌ አባ መርሐ ክርስቶስ አስተዳደር(ከ1456-1490 ዓ.ም.) ነበር፡፡
የጥንተ ክርስትና እና የሐዲስ ኪዳን ምሁር የሆኑት ዶ/ር ባይረን፣ የብራና መጽሐፉን ወደ ዲጅታል በመለወጥ፣ የትመጣውን ለማወቅ ጥናት ካደረጉት የሥነ መለኰት ት/ቤቱ ምሁራን አንዱ እንደነበሩ፣ የዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ ዘግቧል፤ የገድሉ ጥንተ ባለቤት የደብረ ሊባኖስ ገዳም መሆኑ የታወቀውና ወደ ጥንት ቦታው ለመመለስ የተወሰነውም በጥናቱ ሒደት እንደነበር በዘገባው ተገልጧል፡፡ ከገድሉ ይዞታ ጋር በተያያዘ አስተዳደራዊና ሕጋዊ አካሔዶችን ጨምሮ የተለያዩ ዕንቅፋቶች ዩኒቨርስቲውን እንዳጋጠሙት፣ ድረ ገጹ በጥናቱ የተሳተፉ ምሁራንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ዩኒቨርስቲው ገድሉን ወደ ጥንት ቦታው በሕጋዊ መንገድ ለመመለስ በማሰብ፣ በሕግ አማካሪው አርቃቂነት “የስጦታ ውል” የተሰኘና በስምንት ነጥቦች የተዘረዘረ የስምምነት ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡ ውሉ በሐዋርድ ዩኒቨርስቲና በደብረ ሊባኖስ ገዳም መካከል የተፈፀመ መሆኑን የሚገልፀው ዘገባው፤ በሥነ መለኰት ት/ቤቱ ዋና ዲን ዶ/ር አልቶን ፖላርድና በገዳሙ ፀባቴ (አስተዳዳሪ) አባ ወልደ ማርያም አድማሱ እንደተፈረመበትም ጠቁሟል፡፡ ይሁንና የውሉ ይዘት ከባለቤትነት መብትና ከቅርሱ አመላለስ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ሆኖ ተገኝቷል ይላሉ ምንጮች፡፡
ዩኒቨርስቲው÷ “ከማናቸውም ግዴታ ነፃ የሆነ የባለቤትነት መብት በብራና መጽሐፉ ላይ አለው” የሚለው የውሉ መግቢያ፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚመልሰውም “በስጦታ ለመስጠት በመፈለጉ” እንደኾነ ይገልፃል፡፡ የብራና መጽሐፉን ለገዳሙ በስጦታ የሚሰጥበት የባለቤትነት መብት እንዳለው ገዳሙ መስማማቱን የሚገልፀው ውሉ፤ ገዳሙም የብራና መጽሐፉን ሲቀበል፣ ዩኒቨርስቲው ሙሉ በሙሉ የሚያስተላልፈው፣ “አካላዊ የባለቤትነት መብት”ን እንደሆነ አስፍሯል፡፡ ገዳሙን በመወከል የፈረሙት ሓላፊም፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውል ስምምነቱን እንድታከብር የሚያደርግ ዋስትና የመስጠት ሥልጣን እንዳላቸው በውል ሰነዱ ላይ ተመልክቷል፡፡
ባለፈው ሰኞ፣ የዩኒቨርስቲው ሓላፊዎችና ምሁራን በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ተገኝተው ገድለ ቅዱስ ሰራባሞን ወጳውሎስን ለገዳሙ ባስረከቡበት ወቅት፣ በግልጽ የተነሡት ተቃውሞዎችና ስጋቶች፣ አስተዳዳሪው ከዩኒቨርስቲው ጋር የተፈራረሙት ሰነድ፣ የገድሉን ባለቤትነት ለገዳሙ ሳይሆን ለዩኒቨርስቲው መስጠቱን አረጋግጧል፡፡
ዩኒቨርስቲው ገድሉን ወደ ጥንት ቦታው መመለሱን ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፍተኛ አድናቆት እንደምትመለከተውና እንደሚያስደስታት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተናግረዋል፡፡ “ጥንታዊው ብራና ቅርሳችን በመሆኑ ብንቀበለውም ስምምነቱ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ የባለቤትነት መብት የሚጎዳ፣ በትውልዱም ዘንድ የሚያስነቅፍ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤” ሲሉ ተቃውመዋል፡፡
የውል ሰነዱም፣ በልዩ ጽ/ቤታቸው፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የውጭ ግንኙነት መምሪያ፣ በሕግ አገልግሎቱና በቅርሳቅርስ ጥበቃ መምሪያ በጋራ እንዲታይና እንዲመረመርም ፓትርያርኩ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
የደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኝበትን የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሊቀ ጳጳስነት የሚመሩት አቡነ ቀውስጦስ በበኩላቸው፣ የቅርሱ መመለስ የሁላችን ደስታ ቢሆንም የተመለሰበት ሒደት ግን የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓትና መዋቅር እንዲሁም የገዳሙን ክብር እንዳልጠበቀ ገልጸዋል፡፡ ሦስተኛ ወገን በማስገባት በአስተዳዳሪውና በዩኒቨርስቲው የተፈረመውን ስምምነት÷ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት፣ ሊቀ ጳጳሱ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሳያውቁትና ሳይመረምሩት ሕጋዊ የባለቤትነት መብትን በሚያሳጣ መልኩ መፈጸሙን ብፁዕነታቸው አስረድተዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናና መዋቅር በመጣስ “ለመታየት እና ለመግነን” ሲባል የተፈጸመው ድርጊት አግባብ ያለመሆኑን ሊቀ ጳጳሱ በርክክቡ ወቅት በመናገራቸውም፣ “እዚያች ገዳም ትኖራታለህ፤ እንተያያለን፤ የፈለከውን ሹምበት” በሚል በገዳሙ አስተዳዳሪ መዘለፋቸው ተጠቅሷል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የገዳሙ አስተዳዳሪ ባለፈው ረቡዕ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ÷ ከሥራ፣ ከደመወዝና ከአገልግሎት ታግደው እንደነበር ታውቋል፡፡ ከትላንት በስቲያ የገዳሙን መነኰሳት አስከትለው በመምጣት በፓትርያርኩ ፊት ሊቀ ጳጳሱን ይቅርታ በመጠየቃቸው በመካከላቸው ዕርቀ ሰላም ወርዷል፤ ተብሏል፡፡ ይኹንና አስተዳዳሪው “ተጠሪነቴ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ነው” በሚል ያለሥልጣናቸው ከዩኒቨርስቲው ጋር ፈጽመውታል የተባለው ስምምነት ያስነሣቸው ስጋቶችና ተቃውሞዎች ግን መቋጫ አላገኙም፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ የባለቤትነት መብቷን አሳልፋ ሰጥታ መልሳ በስጦታ መልክ የምትቀበልበት አንዳችም ምክንያት እንደሌለና የዩኒቨርስቲውም ፍላጐት እንዳልሆነ ሒደቱን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የስጦታ ውሉ ባስነሳው ውዝግብ ሳቢያ ዩኒቨርስቲው የሕግ አማካሪውን ሳያሰናብት እንዳልቀረም እኒሁ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቷ በበኩሏ፤ “የስጦታ ውል” ሰነዱን እንደምትቃወመው ለዩኒቨርስቲው በይፋ በማሳወቅ፣ ተቀባይነት ያለው ስምምነት እንዲዘጋጅ ጥያቄ ማቅረብ እንዳለበት ተወስኗል፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ቤ/ክርስቲያኗ የአሜሪካንና የአውሮፓን ዩኒቨርሲቲዎች፣ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ባደመቁት ሌሎች ቅርሶቿ አመላለስ ላይ የራሱ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡
የበሽታዎቹን መከሰት ከወዲሁ የሚጠቁሙ አስቀድመው የሚታዩ ምልክቶች ይኖሩ ይሆን? የስኳር ሕሙማን በራሳቸው ሊወስዱ የሚችሏቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን? የስኳር በሽታን ተከትለው የሚከሰቱት አሳሳቢዎቹ የዓይን ሕመም ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው? ተከታታይ ቅንብሮቹ የሕክምና አማራጮቹን ጨምረው ሕሙማንና የቤተሰብ አባላት ሊጠይቁና ሊመልሱ የሚሿቸውን ጭብጦች ይዳሳሳሉ።
ሚስትና ልጁን ያጣ፣ እናትና ወንድሞቹን ውሃ የበላበት፣ እህቱን እና 28 ጓደኞቹን ያጣ ናቸው። ስላሳለፉት ጉዞ አስቸጋሪነትና ለመሄድ ስለተዘጋጁ ስደተኖች የሚነግረን ወጣትም ከግብጽ አነጋግረናል። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ 500 ስደተኞች ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ …
ከመስመጥ የተርፉት ኢትዮጵያውያን 11 ብቻ ናቸው፤ ሦስቱን አነጋግረናቸዋል – VOA Read more »
በደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ የሕወሓት ሰራዊት እንቅስቃሴ ምንም እንዳሌለ ምንጮች ጠቆሙ:: #Ethiopia #SouthSudan #Gambella #EUPF #MinilikSalsawi Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – የጋምቤላ ፖሊስ እና ልዩ ሃይል ወደ ካምፕ ሆን ተብሎ ሰብስቦ ማስገባትን መሳሪያ ማስፈታትን ወታደሩን ክፍል ከድንበር አከባቢ …
በደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ የሕወሓት ሰራዊት እንቅስቃሴ ምንም እንዳሌለ ምንጮች ጠቆሙ:: Read more »
ራሱን ‹‹የደቡብ ሱዳን ቡድን›› በማለት የሚጠራው የሙርሌ ጎሳ ታጣቂ ቡድን የደቡብ ሱዳንን ወታደራዊ ዩኒፎርም በመልበስና ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በመታጠቅ መቼ እንደተነሳ እስካሁን ማረጋገጫ ባይገኝም፣ ዓርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ለቅዳሜ አጥቢያ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጋምቤላ ደረሰ፡፡ ታጣቂው ኃይል ከደቡብ …
የደም ባንክ በመኪና አደጋ ብዛት የደም እጥረት ያጋጠመው መሆኑን አስታወቀ በኢትዮጵያ በየዕለቱ የሚሰቀጥጡ የመኪና አደጋዎችን መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤፍ ኤም ሬዲዩ ጣብያዎችም በየማለዳው ከተለያዩ አካባቢዎች መረጃዎችን በማጠናቀር የሚጠብቋቸውን የትራፊክ ባለሞያዎች በማስተናገድ የደረሱትን የመኪና አደጋዎች ለህዝብ ያስተላልፋሉ፡፡ የህክምና ባለሞያዎችና …
የዓለም የጤና ድርጅት ሰነድ እንደሚለዉ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን 37 ሚሊየን ሕዝብ HIV ተሐዋሲ በደሙ ዉስጥ ይገኛል። ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ላይ 16 ሚሊየኑ ፀረ ኤች አይቪ መድኃኒት እንደሚወስዱ ተመዝግቧል። በሽታዉ እስካሁን ከ34 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። የመድኃኒቱ ስርጭት እና …
የሰማያዊ ፓርቲ የውስጥ ፍትጊያ ለበጎ ወይስ ለጥፋት ? መልካሙን ማሰብ ከመልካም ያደርሳልና— ጠንካራውን ሰማያዊ እንጠብቅ// (የሰማያዊ የውስጥ ፍትጊያ ለሚያስጨንቃችሁ፣ በተለይ ክፍተቱን ለማጥበብ የነበረኝን ድርሻ በሚመለከት አስተያየት እንድሰጥ ለጠየቃችሁኝ ) በቅድሚያ ይህን ጥረት ለማድረግ ያቀረብኩትን ጥያቄ በሙሉ ልብ ተቀብላችሁ በመተማመን ስሜት …
በጋምቤላ ለተፈጠረዉ የሰዉ ሕይወት መጥፋት እና መታገት ምክንያቱ የመንግሥት ንዝህላልነት የፈጠረዉ ችግር ነዉ ሲሉ የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ወቀሱ።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈዉ ሳምንት በሰጠዉ ዉሳኔ ነጻ ያሰናበታቸዉ ሁለት ሰዎች እንዳልተፈቱ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ፖሊስ ማእከላዊ የወንጀል ምርመራ እንደወሰዳቸዉም ተገልጿል። የፖሊስ እርምጃ ምክንያት ግን አልታወቀም። ዝርዝሩን ከመለስካቸዉ አመሃ ዘገባ ያድምጡ → listen
በተለያዩ ምክንያቶች ከአፍንጫ ደም ሊፈስ ይችላል። ነስር የምንለዉ ማለት ነዉ። ብዙዎች መንስኤዉ ምንድነዉ ብለዉ ይጨነቃሉ። ነስር ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የመሆኑን ያህል አብዛኛዉን ጊዜ ቤት ዉስጥ ሊቆጣጠሩት የሚቻል እንደሆነ አንዳንድ የህክምና ጽሑፎች ይጠቁማሉ። ሆኖም አልፎ አልፎ ደግሞ ብዙ ደም የሚፈስበት ከባድ …
የ86 መንትዮች እናት በምጥ ትሰቃያለች– የአዋላጅ ሃኪሞች ‹‹ ቡድን ›› እየተጣራች ነው፤ በእናት የምትመሰለው አገራችን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በተለይም ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ከአንድ ምንጭ በሚቀዱ ህመሞች እየተሰቃየች በመፍትሄ ምጥ/መድሃኒት ፍለጋ/ ውስጥ ነች፡፡ እኛ ልጇቿ ከጊዜ ወደ ጊዜ የለቅሶ …
News #Ethiopia Wetatoch Dimts – መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=afh4A-rNteM]
በ120ኛው የቦሰተን ማራቶን በሴቶቹ ተከታትለው በመግባት ያሸነፉት፥ አፀደ ባይሣና ትርፊ ነገሪ ናቸው። የወንዶቹን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ሥፍራ የወሰዱትና ታሪክ የሠሩት የኢትዮጵያ ሯጮች ደግሞ፥ ለሚ ብርሃኑ፥ ያለፉት ሁለት ዓመታት ሻምቲዮኑ ሌሊሣ ዴሢሣና ፀጋዬ ናቸው። listen
በኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ድንበር ያለው የጎሳ ግጭትና የወያኔ ሚና #Ethiopia #Gambella #SouthSudan #Sudan #MinilikSalsawi #CivilWar Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በጃኮው እና በኒያኒያንግ አቅራቢያ ሰፍረው የነበሩ ወታደሮች ለምን አከባቢውን እንዲለቁ እንደተደረገ የወያኔ አገዛዝ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል::ጭፍጨፋውን ተከትሎ ለምንስ አከባቢዎቹን መክበብ እና ወጪ …
አንድነትን ማጥበቅ በቁርጠኝነታችን ተማምነን እንጂ እንደው በሞቅ ሞቅና በሰሞነኛ መንገኝነት ተገፋፍተን እንዳይሆን እንጠንቀቅ፡፡ #Ethiopia #Ethiopianoppositionparties #EPRDF #Miniliksalsawi Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – አላዋቂ እጅ መውደቅ እርግማን ነው፡፡ ደጋግመን መፈክር ስላሰገርንና፣ ደጋግመን በቃል ቃል ስለገባን ግባችንን በተግባር እንመታለን ማለት አይደለም፡፡ የምንጓዘው …
አንድነትን ማጥበቅ በቁርጠኝነታችን ተማምነን እንጂ እንደው በሞቅ ሞቅና በሰሞነኛ መንገኝነት ተገፋፍተን እንዳይሆን እንጠንቀቅ፡፡ Read more »
ማኅደረ ማርያም ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በፋርጣ ወረዳ፣ ከደብረ ታቦር 28 ኪሎ ሜት ርቀት ላይ፣ በ2450 ሜትር ከፍታ ከባሕር ወለል በላይ፣ በቧኢት ተራራ ላይ ወደተተከለቺው ማኅደረ ማርያም ደብር ተጉዤ ነበር፡፡ የጉዞዬ ዋና ዓላማ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ለምሠራው ጥናት …
በኦሮሚያ ክልል አልፎ አልፎ በተማሪዎችና በነዋሪዎች የሚካሄደዉ ተቃዉሞና የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ ምላሽም ቀጥሏል። በጉጂ ዞን ኦዶሻኪሶ ወረዳ መጋደር በተባለ መንደር ባለፈዉ ማክሰኞ በዳዳ ጋልቹ የሚባል ወጣት በመንግስት ሃይሎች መገደሉን የአካባቢ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ገልጸዋል። በወረዳዉ የሻኪሶ ከተማ አስተዳዳሪዎች …
በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ በዳዳ ገልቹ የሚባል ወጣት በመንግስት ታጣቂዎች መገደሉ ተነገረ – VOA Read more »
ሰሞኑን በአዲስ አበባ አንድ ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የአዲስ አበባ ደረጃ አንድ ሌቦች ስብሰባ አድርገው ነበር፡፡ የስብሰባው መሪ ቃል ‹የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ሌቦች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?› የሚል ነው፡፡ ስብሰባው እንደተጀመረ አንደኛው የታወቀ ሌባ እጁን አወጣና ‹መፈክሩ ላይ የተጠቀስንበት ስም ትክክል …
በምዕራብ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ድንበር የተሻገሩ ታጣቂዎች በዕለተ አርብ ማለዳ በፈጸሙት ጥቃት ህጻናት መታገታቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ተናገሩ። ቃል-አቀባዩ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ በጥቃቱ ምን ያኽል ሰዎች ታግተው እንደተወሰዱ አለመናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በኦሮሚያ በየደረጃው የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ሃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ከ 800 በላይ አመራሮች ከደረጃ ዝቅ ብለው እንዲሰሩ የማድረግና ከሀላፊነት የማንሳት እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። በክልሉ የተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን የኦሮሚያ ክልልና የፌደራሉ መንግስት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ዘጋብያችን እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ የላከው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።
በእንዳለ ጌታ ከበደ የካቲት 2008 ዓም ዋጋ፡- 120 ብር እንዳለ ጌታ ከበደ በዓሉ ግርማን እንደ ጌታ ነፍስ ዘርቶ እንደደአልዓዛር ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ከትውልድ ቀየው ጀምሮ ‹እስከ መቃብሩ› ደረስ እየተከተለ፡፡ መዛግብቱን ያገላብጣል፣ እናውቃለን የሚሉትን ይጠይቃል፣ ያውቃሉ ብሎ የገመታቸውን ያናግራል፤ ሄዶበታል፣ ውሎበታል፣ ገብቶበታል፣ …
ከአስቻለው ከበደ አበበ – ቶረንቶ፣ ካናዳ ስሞኑን ለአንድ ጉዳይ ዳውን ታዎን ደርሼ ስመለስ የባህል ምግብ መአዛው ናፍቆኝ ከአንድ የኢትዮጵያኖች ቅመማ ቅመም መሸጪያ ቤት ጎራ አልኩኝ፡፡የምሸምተውን ሸምቼ ከሱቁ ስውጣ አንድ ጎለማሳ ሰው አቆመኝና ጃማካዊ ነህ ብሎ ጠየቀኝ፡፡አይደለሁም አልኩት፡፡ ቀጠለና ኤርትራዊ፣ሩዋንዳዊ…ኢትዮጵያዊ የሚለው …
ወልቃይት ጠገዴ በከፍተኛ የህወሃት ማይከላዊ አመራሮች በሆኑ በአቶ ተክለወይኒና አባይ ወልዱ እንዲሁም የትግራይ ክልል የደህንነት ቢሮ ሓላፊ የሆኑ አቶ ዘነበ ሐዱሽ የተመራው ጥቂት ታማኝ ካድሬዎች ብቻ የተገኙበት የትላንት ወዲያ (የሚያዚያ 13/2008 አ/ም) የመቀሌው ስብሰባ ከአንድ በመቀሌ ኗሪ የሆነ የአዲግራት አከባቢ …
ወያኔ በመቀሌ ከተማ ኢትዮጵያውያንን በዘርና ሐይማኖት ከፋፍሎ ያካሔደውን የማጋጨትን ዘመቻ ስውርና አስደንጋጭ ግምገማ አደረገ Read more »
የቦሌ ደብረ ሳ ሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ካህናትና ሠራተኞች፤ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ያዋጣነው ከ400ሺሕ ብር በላይ ገንዘብ የገባበትን አናውቅም፤ አሉ፡፡ ገንዘቡ ከ4 ዓመት በፊት 160 ከሚሆኑ ሠራተኞች ደመወዝ የተሰበሰበ መሆኑን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ እንደ ምንጮቹ ገለፃ፤ ካህናቱ በወቅቱ በተደጋጋሚ ለካቴድራሉ አስተዳደር …
“ለሕዳሴ ግድብ ቦንድ ያዋጣነው 400ሺ ብር የገባበትን አናውቅም” የቦሌ መድኃኔዓለም ካህናት Read more »
እንደወትሮው መንግስት እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት፣ የኢኮኖሚ እድገትንበተመለከት ያወጡት መረጃ ዘንድሮም የተራራቀ ሆኗል፡፡ ባለፉት አስር ዓመታት ኢኮኖሚው በአስር በመቶ ሲያድግ መቆየቱን መንግስት የሚገልፅ ሲሆን፣ የዓለም ገንዘብ ድርጅት በበኩሉ፤ የእድገቱ መጠን 8 በመቶ ገደማ እንደነበረ ይናገራል፡ ፡ ዘንድሮ በድርቁ ሳቢያ ኢኮኖሚው …
የኢኮኖሚ እድገቱ ወደ 4.5 በመቶ ያሽቆለቁላል – IMF // መንግስት በ7 በመቶ ያድጋል ብሏል Read more »
– አምስት ምእመናን ለእስር ተዳርገዋል – የውጭ ጉዳይ ሓላፊው ተጠያቂ ተደርገዋል – ሰበካ ጉባኤው በፕሪቶርያ ፍ/ቤት ክሥ መሥርቷል አለማየሁ አንበሴ በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደር ሳቢያ የተፈጠረ አለመግባት ወደ ዐምባጓሮ አምርቶ 8 ምእመናን የተጎዱ ሲሆን ጉዳዩም …
በኩዌት በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ የምትሰራ ስሟ ያልተጠቀሰ ኢትዮጵያዊት፣ የአሰሪዎቿን ቤተሰቦች የሰው ስጋ ይበላሉ ስትል መክሰሷን ገልፍ ዲጂታል ኒውስ የተባለው ድረገጽ ዘገበ፡፡ሳላዋ በተባለው የአገሪቱ አውራጃ በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ የምትሰራው ኢትዮጵያዊቷ፣ በአሰሪዎቿ መኖሪያ ቤት ውስጥ የሰው ራስ ቅል ተደብቆ ማየቷን በመጥቀስ ለፖሊስ …
• ፓርቲው የውስጥ ችግሩን መፍታት ለምን ተሳነው? • ለፓርቲው ቀውስ ተጠያቂው ማን ነው? • የመበታተን አደጋ ያሰጋው ይሆን ? ሰማያዊ ፓርቲ በተለይ ሊቀመንበሩና ሌሎች አመራሮች መዝብረዋል የተባለውን ገንዘብ መነሻ በማድረግ በአጋጅ ታጋጅ ድራማ ታጅቦ በቀውስ እየተናጠ ይገኛል፡፡ በፓርቲው ችግሮች፣ በመፍትሄዎቹ፣ …
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንደተምኔት ሳይሆን እንደተጨባጭ ነገር ማስተዋል ይገባናል፡፡ ፅንፍና ፅንፍ እየቆሙ፣ ማዶና ማዶ የጎሪጥ እየተያዩ፣ በደፈረሰ ልብ እያሰሉ፣ የምንመኘውን ዓይነት ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው፡፡ ከቶውንም፤ በትንሹ የምንመኛቸውን ነገሮች እንኳ በእጃችን ማስገባት አዳጋች ይሆናል፡፡ እንደሶስተኛው ዓለም …
መንቃት ያለብን ወሳኝ ወቅት – የምንፈልገውን ነጻነት ለማረጋገጥ ጊዜው በፍጹም አረፈደም !!! Read more »
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች ዐርብ ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተገደሉ። የኑዌር ጎሳ አባላት የመኖሪያ መንደሮች ላይ ባነጣጠረው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ221 በላይ መሆኑን ሱዳን ትሪቡዩን ዘግቧል። ሱዳን ትሪቢዩን የደቡብ ሱዳን ጦር መለዮ የለበሱ …
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተገደሉ። Read more »
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች ዐርብ ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተገደሉ። የኑዌር ጎሳ አባላት የመኖሪያ መንደሮች ላይ ባነጣጠረው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ221 በላይ መሆኑን ሱዳን ትሪቡዩን ዘግቧል።
ጫት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ጥቅምና በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በቅጡ እንዲጤን ስለ ጫት ጥናታዊ ጽሁፎች ያቀረቡ ምሁራን አሳሰቡ ። «ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ» የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ባዘጋጀው አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት ቀናት በተካሄደው ዐውደ ጥናት ላይ የጫት ኤኮኖሚያዊ እና ባህላዊ …
በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ውስጥ ሰኞ እና ማክሰኞ በተማሪዎችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎች ገለጹ። ከግጭቱም በኋላ ከሰላሳ ሰው በላይ መታሰሩን ተናግረዋል። የከተማው ፖሊስ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ይላል። የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ቱጁቤ ኩሳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ …
በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከ30 በላይ ሰዎች መታሠራቸውን ተማሪዎች ተናገሩ – VOA Read more »