የማያዛልቅ እያለማን ነው የወያኔ ጸሎት አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።

የማያዛልቅ እያለማን ነው የወያኔ ጸሎት አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎Change‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ የጀመረው የስልጣን ማስረዘሚያ ስልት ራሱን እና በክሎኒግ ያባዛቸውን ጭፍሮቹን ወደ መቃብር እያወረደ መሆኑ ለአፍታ ቆም ብሎ ማስብ አልቻለም። ካለወያኔ መኖር የማይችሉ በጥቅም የታሰሩ በደረቅ ፖለቲካ የታወሩ እውቀት አልባ ካድሬዎች እና ሹምባሽ ደህንነቶች የአገሪቱ አንጡረ ሃብት በመዝረፍ እና ዜጎችን በመግደል በዚሁ የሚቀጠል መሆኑን አስበውት ከሆነ ተሳስተዋል። በአሁን ሰአት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለውጥ ፈላጊ ሃይል መሆኑን ወደው ሳይሆን በግድ እውነትን እንዲውጡ እናደርጋቸዋለን።

የህዝቦች እኩልነት ያልተረጋገጠባት ኢትዮጵያ :የብሄር ብሄረሰብ መብቶች ለይስሙላ በሚሰበኩባት ኢትዮጵያ ዜጎች ህግ ይከበር ብቻ ስላሉ በሌላው አለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሸባሪ ተብለው ወህኒ የሚወርዱባት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ምሁራን ከአያት ቅድማያቶቻቸውን የተረከቡትን እምነታቸውን በነጻነት ለማካሄድ ሲሰሩ ታፍሰው ለእስር የተዳረጉባት አገር ኢትዮጵያ: እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዘረፋ ላይ እና ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈን እና ማሰር ላይ የተሰማራ መንግስት በነገሰበት አገር ውስጥ የምንኖር ተጨቋኝ ብዙሃን የህዝቦች የጋራ መተባበር እና ለለውጥ መነሳት አስፈላጊ እና እጅግ ወሳኝ ወቅት ላይ መሆኑን ማወቅ ይገባናል::

ወያኔ የያዘው መንገድ አጥፍተህ ጥፋ የሚል ጸረ ሰላም እና ጸረ ሕዝብ ከመሆኑም በላይ በጸረ አሸባሪነት ቁማር ምእራባውያንን ተገን በማድረግ ዜጎችን ለከፍተኛ እንግልት እና ሰቆቃ እየዳረገ ሲሆን በየትኛውም አለማችን ክፍል ያልታየ እና የሽብርተኝነት ውጊያ እናካሂዳለን የሚሉ ሃያላኖች እንኳን በተግብር በሃገራቸው ወንጀል እና ሽብር ሲፍጠር በፍጹም ዜጎቻቸውን የማይወነጅሉበትን ህግ ወያኔ ግን ህግ ይከበር የሰው ልጆች እኩልነት እና ነጻነት ይረጋገጥ ባሉ ዜጎች ላይ አጸያፊ እርምጃ ለመውሰድ እየተጠቀመበት ነው::ይህ የማያዛልቅ የወያኔ ጸሎት አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።

ነጻነት በእጃችን ነው ስለዚህ ለነገው ትውልድ እና ለዛሬው እኛነታችን ድል ተጎናጽፈን መብታችንን ለማረጋገጥ የዜግነት ድርሻችንን ማበርከት ግድ ይለናል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

8 Comments on “የማያዛልቅ እያለማን ነው የወያኔ ጸሎት አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።”

  1. የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 10 አሰቸኳይ መመሪያ
    +-+++++++++++++++
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ባንዲራችን ላይ በጋኔኑ አስገዳጅነት የጋኔን ምልክት አርገው ሕዝባችንን የእኩልነት ብሔር ብለው ጅል አረጉን። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራትን። የአገራችን ህዝቦች አገራችን በየአቅጣጫው መከራ ተደቅኖባታል ሰለዚህ ሁሉም እንደእምነቱ ወደ ፈጣሪ ከልብ የሚያለቅስበት ጊዜ ላይ ነን። ተራማጅ የአገር ውስጥ አሮሞ ኢትዮጵያዊያን የጋራ ጠላታችን ጋኔኗ ኢሕአዴግ ብቻ ነች ብለን ከሌሎች ወድ ኢትዮጵያዊያን ጋር የዱሮ ፈቅራችንን መልሰን በጋራ ለሁላችን ብለን የምንተሰብበት ደረጃ ላይ ደርሰን በማንዴላን አርእያ አና ገድል የዘርን ፓለቲካ እጥፈተን ወደ ዋናው ድህነታችን ወግያ በጋራ ቀጥታ እንገባለን። የአገር ውስጥ ኦሮሞዎች የዘር ፓለቲካ ነቃንብሸ ኢሐዲግዬ ብለውታል። አደዎዎቹ ሌላውን የትግራይ ህዝብ አፉን አፍነው የተሰወረ ግፍ ሲያደርሱበት ቆይተዋል አይ እንዳይናገር ሌሎች ብሔሮች ይሰሙናል እያሉ በጀርባው ሲሳለቁበት ኖረዋል፣ በየአንዳንዱ ከተማ ሠራዊታችን ገብቷል እና ለቆረጣ ወግያ 30 ሚሊዬን ኢሕአዴግ ከ10ኘ ከፈል ያባረራቸው ወጣቶች በትንሹ ተዘጋጅተዎል። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ለ ሕዝባችን።
    1ኛ፣ የኢሕአዴግ ስላዬቸ እና ጦሩን አብዛኛውን ሰለ ስራ አስመስለው ለወገናቻችን እና ለአገራቸው እንዲስሩ ታዘዎል። በሰሞኑ የጦር ግምገማ እርቃናቸውን እንደቀሩ አዩት።
    2ኛ ኢህአዲግ አስከ አሁን ኢሳትን ላማፈን $26 ሚሊዬን፣ ዜጎችን ለማፈን $48 ሚሊዩን ከፈሏል፣ ሰሞኑን ደግም ቫይበር እና ጓደኛውን ለማፈን $10 ሚሊዬን ቅድሚያ ክፍያ አደርጓል። የውስጥ አርበኞቻችን እንዲሁም በቴሌ ውስጥ ያላችሁ የማፈኛ ቦታዎችን ለአባሎቻችን መረጃ ስጡ። ለኢሳት ባንክ በስውር አሳውቁ።
    3ኛ አቡነ ማቲያስ ከግበረአበሮቹ ተሐድሶዎች ጋር አንድ ያለህን እምነትህን ሊያጠፈብህ ነው። ፈረንጅ አንተ ስትጎብዝ ነው የሚያከብርህ። ወሬ በቃን ሰው እየሞተ ነው። እርምጃ ዶ/ር ብርሀኑ/ ጀነራል ከማል። ኢሳትን፣ግንቦት7፣የተራበውን ወገናቹን ፣ ወድ የአቶ ኦባንግን ድርጅት እርዱ አደራ በተጨቆነው ኢትዮጵያዊ ስም እንለምናችሃለን።
    4ኛ የወንድም ፓሮስቴንታንት እምነት እንደ አሸን የቸርች ቢዝነስ የከፈታቹ እነ ፓስተር ዳንኤል እና ሁለት ፓስተሮች መርዝ ህዝባችን ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሌላ በጭፈራ እየአደነጋገራችሁ ስለ ኢትዮጵያ አታስቡ አሮሚያ ለኢትዮጵያ ይጨነቅ?። ሰለዚህ በእምነቱ ስም የግል አላማችሁን ለኢሐዲግ ከፋፋይነተት አትጠቀሙ።
    5ኛ በውጭ አገር ምሁራኖቻችን በአቶ አባንግ አሰተባባረነት ለተደረገው ሀሳብ እናመሰግናለን። የኛዎች የቀድሞው ኦነግ ኦሮሞዎች መሪዎች ጥሩ እርምጃ ተራምደዎል እናመስግናለን። አሁን አገር ውስጥ ያለው በተግባር የተራማጅ ማንዴላ አርእያ ቀይረነው ከአስመራ ትእዛዝ ደ/ር ብርሐኑ/ ጀ°ከማል ጅምሮ አገር ውስጥ በኮር ሰንሰለት ተገናኝቷል። ግን ዋናው አሁን ኢትዮጵያ የምትፈልገው በእኩል የሚያስዳድር ብቻ ነው። ያለፉትን መሪዎችን መውቀስ ማቆም አለብን።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር። ንጉሡ ሞቱማ ተራማጅ የኦሮሞ ማህበር የታጋዮች ኮር አዛዥ ከአምቦ።

  2. Gebra Gebru says:

    April 14, 2016 at 1:28 pm

    You are hero Negussu and you brought us together. We shall make it!!!!!!!!!!

  3. Stiqoamt idmehn fejith temotalh keingdh wedhoal yelem. Besbesh izaw
    tekberalachu Ethiopia ye bandawoch reisa mtaya aydelechim

  4. Akrariwoch keruq neaw yemitshetut
    Yenanyin akheid
    bdenb iytbknachuh
    Yematfenklut degay
    Indelele yawknew lematachn yezewetr
    tselotachu neaw.
    Gin ARAMOCH nachehu yeseat lej.

    indidnakf

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*