የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት IFM አስታወቀ – VOA

በዓለም በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አስራ ሀገሮች ሰባቱ የአፍሪካ ሀገሮች ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ሆና ቆይታለች። የያዝንው የአውሮፓዊያን ዓመት ግን ይሄ ሁኔታ እንደሚቀየር ነው የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ (IMF)በየዓመቱ የሚያወጣው የዓለም ምጣኔ ሀብት ግምገማ ዘገባው አስታውቋል። ባለፈው ዓመት 10.2 ከመቶ ያደገው ምጣኔ አሁን በያዝንው ዓመት 4.5 ከመቶ የሀገራዊ ምርት እንደሚኖር ድርጅቱ አስታውቋል።

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጥናት ቡድንን የመሩት ኦያ ሴላሰን፤ በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገሮች የምጣኔ ሀብት ትንበያ ላይ ጉልህ ተጽኖ ያሳደሩ ሁኔታዎችን እንዲህ አስረድተዋል። “አንዱ ምክንያት ምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ብርቱ ድርቅ ተከስቶባቸምብዋል። የዝናብ መጠኑ ለበርካታ ዓመታት ከተመዘገበው አማካይ በ40 ከመቶ ቀንሷል። ይሄ ሁኔታ በምጣኔ ሀብት እድገት ትንበያው ላይ ተንጸባርቋል፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ምጣኔ ሀብቶችን ጎድቷል። ማላዊ፣ ዝምባብዌ፣ ዛምቢያና ደቡብ አፍሪካንም ጎድቷል” ብለዋል። የምጣኔ ሀብት መቀዛቀዙ በአፍሪካ አማካይ እድገትም ተመዝግቧል። ባለፈው ዓመት በ3.4 ከመቶ ያደገው የአፍሪካ ምርት በያዝንው ዓመት ወደ 3ከመቶ ዝቅ እንደሚል ነው፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት የተነበየው። በተለይ በአፍሪካ እንደ ናይጀሪያ፣ አንጎላ፣ ደቡብ ሱዳንና ሌሎች የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገሮች በነዳጅ ዘይት ዋጋ መቀነስ ሳቢያ ምጣኔያቸው ተንኮታኩቷል።

የዓለም የገንዘብ ድጅርትን ጥናት የመሩት ኦያ ሴላሰን “የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገሮች አሉ፣ ነዳጅ የማያመርቱ ግን በዓለም የሸቀጥ ገበያ በቀጥታ የሚሳተፉ ሀገሮችም አሉ። በስፋት በሸቀጥ ገበያው የማይሳተፉ ሀገሮችም እንዲሁ በርካታ ናቸው። የነዳጅ ዘይት ዋጋና የሌሎች ሸቀጦች ዋጋ ሲቀንስ የሀገሮቹ ምጣኔም አብሮ ይታወካል። በእርግጥ ሁኔታውን ለመለወጥ የጀመሯቸው በርካታ ውጥኖች አሉ። ሆኖም ምጣኔ ሀብታቸውን መጎዳቱ አልቀረም። ለዚህ ነው በሚቀጥለው ዓመት የምጣኔ ሀብታቸው እድገት ትንበያ አሉታዊ ተጽኖ ያሳደረውል።” በማለት ለአሜሪካ ድምጽ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

በድርቅ የተነሳ ጉዳይ ያልደረሰባቸው የአፍሪካና የዓለም ሀገሮች፤ በተለይ የነዳጅ ዘይት አምራች ያልሆኑት በዚህ ዓመት የተሻለ የምጣኔ ሀብት እድገት ትንበያ አግኝተዋል። ሆኖም የዓለም ምጣኔ ሀብት ባለው ትስስር የተነሳ በተዘዋዋሪ እድገታቸው ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊኖረው እንደሚችል ነው የIMF ጥናት ያስቀመጠው።

“የዓለም አቀፍ የሸቀጥ ገበያ ተጽኖ የማያሳድርባቸው ሀገሮች በሁኔታው ክፉኛ አልተጎዱም። ሆኖም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ገበያና የመዋእለንዋይ ፍሰት ስለሚደርቅ፤ በተዘዋዋሪ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ምጣኔ ሀብቶች ላይ ተጽኖ እንደሚያሳድር በጥናታችን ተንጸባርቋል።” ብለዋል።

በዓጠቃላይ የዓለም ምጣኔ ሀብት በዚህ በያዝንው ዓመት በ3.2 ከመቶ እንደሚያድግ ተገልጿል። ቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት 2017 በተለይ የተሻለ የእድገት ዘመን እንደሚሆን ነው ጥናቱ የጠቆመው። ለኢትዮጵያ ምጣኔም ከዘንድሮው የተሻለ እድገት እንደሚጠበቅ ትንበያው ያስረዳል።

የVOA ዘጋቢ ሔኖክ ሰማእግዜር የአመታዊው የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ (IMF) ጉባዔ ላይ ተገኝቶ ያጠናቀረውን ዘገባ ያዳምጡ → listen

3 Comments on “የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት IFM አስታወቀ – VOA”

  1. ድሮም በአሸዋ ላይ የተዘራ የውሸት እድገት ነበር ።

  2. እድገት እና ውድቀት/ፍልሰት፣ስደት፣ግድያ
    የምጣኔ ሃብት እድገት መቼ አለእና በእውነት ድቀት ነው እድገት! አዎን ሕዝብን ትውልድን ያስራቡ፣ያሰደቱ፣የገደሉ አድገዋል!
    10.2 ሚሊዩን ሕዝብ ተራበ እያልን የለም ርሃብ ዐልተከሰተም ይላሉ እውነታቸውን ነው የተራበ ሕዝብና ድርቅ ባይኖር ነው በ2.4 ቢሊዩን ብር እስቴድዩም የሚገነባው ገንቢዎቹ ርሃብ አልተራቡማ! እነሱ አልታረዙ፣አልተራቡ መቼስ ነው እነሱ ጋር ርሃብ የሚደርሰው ተውን አይ ህሊና
    ው.ድ

  3. I’m confused on economic growth ethiopia,
    imf and epdrf reported the same figure,while experts are un figure out,
    which org we believe ?
    Can economic growth change individual life standard?
    What ever all sides giving opposite perception toward economic growth, this year it is known no growth or less zan previous due to declining of agri products by drought,

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*