በደመነፍስ የሚነዱ ትራፊክ ፖሊሶችና የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር
ዩሱፍ ከዲ

የቅዳሜ ሚያዝያ 1 2008 አጭር ገጠመኝ
ከሜክሲኮ በባልቻ አድርጎ በአብነት ወደ አውቶቡስ ተራ የሚወስደውን በተለምዶ ዶልፊን የሚባለውን ታክሲ ስሳፈር፣ ሰዓቱ ገና አንድ ሰዓት ከሃያ አካባቢ ነበር። ታክሲውም አንድ ወይም ሁለት ሰው ቀርቶት ባልሞላበት ሁኔታም ነበር መንቀሳቀስ የጀመረው። ይህ ድርጊቱ የሾፌሩን “ለሰዓት/ለጊዜ እንዲሁም ለጫናቸው ተሳፋሪዎቹ ያለውን አክብሮት” ያሳየኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁና እንዳከበርከን ክበር እያልኩኝ በውስጤ መልካም እየተመኘሁለት ነው የተጓዝኩት።