ይህ መንግስት ምን ይዞ ቆመ ( ኄኖክ የሺጥላ )
ሰሞኑን በአምቦ ፣ በሐረማያ ፣ በወለጋ ፣ በቡራዩ እና ወዘተ ቦታዎች ኢትዮጵያውያኖች ዛሬም በዘረኛው ወያኔ ትግሬ እየተገደሉ እንደሆነ ሰምቻለሁ ። በጎንደር ኢትዮጵያውያኖች እየተገደሉ እንደሆነ ሰምቻለሁ ። ህዝበ ሙስሊሙ የእምነት ነጻነቱን እንደተነጠቀም አውቃለሁ ። አስራምስት ሚሊዮን ሕዝብ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ በሚሻበት ሁኔታ ላይም እንደሆነ ተረድቻለሁ ፣ በምራብ ጎጃም ንጹሃን ዜጎች እየተሰቃዩ እንደሆነም መረጃ አለኝ ፣ በወሎ ( ኮረም ) ፣ በ ወልቃይት ጠገዴ ፣ ሁመራ እና ወዘተ ህዝቡ አዲስ የተሰጠውን ማንነት አልቀበልም ብሎ ከመንግስት ጋ ግብ ግብ ውስጥ እንዳለም እናውቃለን ፣ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን መንግስትን ( ስርዓቱን ) በመተቸታቸው በቃሊቲ ፣ ቂሊንጦ እና መሰል እስ ቤቶች እንደተታጎሩ ከማንም የተደበቀ ሚስጥር አይደለም ፣ ሰማያዊ ፣ አንድነት እና መድረክ ድምጻቸው ተገሶ ፣ መንግስት 100% እንደተመረጠ እንደተናገረም ሰምተናል ። ታዲያ ያልገባኝ ይሄን መንግስት ” ምን ይሆን ቆሞ እንዲሄድ ያድረገው ?” ከነዚህ ሁሉ ብጥብጦች እና መከራዎች ጀረባ የትግራይ ሕዝብ ሚና ምንድን ነው የሚለውን በጥሞና እንመርምር ። ከትግራይ በስተቀር በሁሉም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያኖች ይገደላሉ ፣ ይህ በየትኛውም አይነት ስርዓት ያልሆነ ነው ። ለምሳሌ ወያኔ ያማራ ስርዓት የሚለው ደርግ ፣ በኢሕአፓ ስም የበላው የጎንደር ትውልድ ( ሕዝብ ) አንዱ ምሳሌ ነው ።
ስለዚህ ሁኔታውን ከይሉኝታ እና ከምን ይሉናል ልክ ወጣ አድርጉና ፣ የትግራይ ሕዝብ ሚና ምንድን ነው የሚለውን መርምሩ ። ለኔ ቁልፉ ያለው አንድ አለመሆናችንና የትግራይ ህዝብን እንደ ሕዝብ አጋር አድርጎ መመልከቱ ላይ ይመስለኛል ። እደግመዋለሁ ፣ የትግራይ ሕዝብ ሚሊዮን ኦሮሞዎች ብታረዱ ፣ ሚሊዮን አማሮች ቢሞቱ ፣ አሁን ባሉበት ስብእናቸው አንዳች ስሜት የሚሰጣቸው ሰዎች አይደሉም ። የመንግስት ህብለሰረሰሮች ስለመሆናቸው 25 ዓመት እየራባቸው እንኳ ባሳዩት ትዕግስት ልንመዝናቸው እንችላለን ። ደርግ ላይ ተቆጥተው በረሃ የወረዱት የትግራይ ልጆች ፣ እና ስንቅ በድብቅ ለታጋዮች ሲቋጥሩ የነበሩ የትግራይ እናት እና አባቶች ፣ ዝም ያሉት ምንም ስለማያውቁ ነው ብትሉ ፣ ምክንያታችሁ በቁም ለመታረድ ከመፈረም የተለየ አድርጌ አላየውም ። ስለዚህ ይህ መንግስት ምን ይዞ ቆመ የሚለውን ድጋሚ ድጋሚ መርምሩት !