ቀን እየቆጠሩ ከማስጨፈር የግለሰብ ከዚያ የብሄረሰቦችን መብት ማክበር ይቅደም::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)– የወያኔን ጉጅሌ አገዛዝ ጭካኔ እና እኩይ ተግባር ብናወራው አያልቅም::በሕግ እና በሕዝብ ስም ሽፋን በርካታ አደገኛ ወንጀሎች በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ ነው::በለውጥ ሃይሉ መካከል በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት እስካሌለ ድረስ ወያኔ ይህንኑ ክፋቱን ከሰይጣን የበለጠ ተግባሩን አስፋፍቶ ይቀጥላል::ሕዝብ እምነት የሚጥላባቸው ምርጥ የለውጥ ፖለቲከኞች ማነስ በስሮቻቸውን ያሉ አባሎቻቸው በድርጅታዊ ዲሲፒሊን/ስነስርኣት/አለመታነፅ የውስጥ ብስለት እጥረት ደንቃራ ቢሆንም የወያኔን ጉጅሌ መንግስት ለመጣል በጋራ መቆም አሁንም ችላ ሊባል የማይገባ ጉዳይ ሲሆን በቀን ቁጥር አመት እየተጠበቀ ለብሄር ብሄረሰብ ቀን ለጭፈራ እንዲወጣ የሚደረገውን ቀሪዎቹን የአመት ቀናቶች የሚደበደበውን የሚገደለውን የሚታሰረውን ሕዝብ መብት እንዲከበር እጅግ በጥንካሬ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል::
ከታህሳስ አንድ ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 28 ከአመት አመት ሕዝባችን ወገናችን እየተረገጠ እየተገደለ እየተደበደበ እየታሰረ እየተሰደደ የብሄር ብሄረሰብ ቀንን ህዳር 29 እየጠበቁ ማስጨፈር ምን የሚሉት ጉዳይ እንደሆነ ግልጽ አልሆነም:;የብሄረሰብ መብቶችን ለማስከበር ሕገመንግስት አጸደኩ የሚለው የፖለቲካ ፕሮግራሞቹን ገልብጦ ሕዝብን እያስተዳደርኩ ነው የሚለው አገዛዝ ለራሱ ሕገመንግስት ተገዢ መሆኑ ባልተረጋገጠበት በገሃድ የሕግ የበላይነት በደፈጠጠበት አገር ላይ በየትኛው ሞራሉ የብሄር ብሄረሰብ ቀን ብሎ እንደሚያከብር ግልጽ ካለመሆኑም ሌላ ከጭፈራ እና የሃገሪቱን በጀት ከማባከን ውጪ የትኛው ብሄረሰብ መብቱ ተከብሮለት ድምጹ ተሰምቶ አለ የሚባለው ሕግ እንደተተገበረ በተግባር የታየ ነገር የሌለ ሲሆን ከድብደባ ከእስር ከጭፈራ እና ከስደት ውጪ ምንም የተፈየደ ነገር አልታየም::
ሕገመንግስቱ የመደገፍ የመቃወም መብት ሰጥቷል ቢባለም የደገፈም የተቃወመም ሕዝብ በአንድነት በመሳሪያ ሃይል እየተጨፈለቀ ባለበት ሃገር የብሄረሰብ ቀን ብሎ ወያኔ ሲያከብረው ሕዝቡን በግዳን እና በገንዘብ ድለላ ሲሰበስበው ምንም አይሰቀጥጠውም:: በየአመቱ ቀን እየተቆጠረ የብሄረሰቦች ቀን በጭፈራ ይከበር እንጂ ሕዝቦች በፖለቲካ ይሁን በኢኮኖሚ ሲደሄዩ በካድሬዎች ሰበካ እርስ በእርስ እንዲባሉ ሙከራ ሲደረግ ከቀያቸው ሕዝቦች ሲፈናቀሉ የመብት ጥያቄ ያነሱ ሲገደሉ እና ሲታሰሩ ስለ አንድነት የተናገሩ ከአገር እንዲሰደዱ ሲደረግ የነጻው ፕሬስ ስለብሄር መብቶች ሲናገር በፍረጃ በመዝጋት እና በማስፈራራት የፍትህ አካላት የባለስልጣን አገልጋዮች ሆነው የፍትህ ስራን ከጨዋታ ውጪ እንዲሆን በማድረግ ሕዝቡ ጸድቆልሃል የተባለው ሕገመንግስት ባጸደቀው አካል ሲተረማመስ ሲቀዳደድ እና ሲጥመለመል እያየን ነው::ለዚህ ሁላ መፍትሄው ግን ቀን እየቆጠሩ ከማስጨፈር የግለሰብ ከዚያ የብሄረሰቦችን መብት ማክበር ማስቀደም ሲሆን የተሻለው ደሞ አገዛዙ ስልጣኑን ለቆ ለሕዝብ ቢያስረክብ ይበለጠ የተሻለ ቢሆንም በተለይ ግን መውደቂያው እየደረሰ ያለው ይህ አገዛዝ በሕዝብ ልጆች እንደሚደመሰስ ሌላኛው ትልቁ ማረጋገጫ ነው::#ምንሊክሳልሳዊ

ብሄር ተኮር ህገመንግሥት በእንቅርት ላይ ጆሮደግፍ
ሦሥቱ የወያኔ መርሆች
ወያኔ
ብሄር
ከበሮ
ኦህዴድ መፈንቅለ መንግሥት ጀመረ እንዴ?
እንዲያው ግልፁን እንነጋገርና እውነት በታሪክ ሥለ ባርነት እንጂ ታሪክ የሚያሥረዳው የእከሌ ብሄር የእከሌ ባርያ እያለ ሣይሆን ጥንት በነበረው የቆዳ ልዩነት ብቻ ባርነት ምልመላ ይደረግ ነበር ይህን ይዘነው የመጣውን ቅሪት ኮሮኔል መንግሥቱ እንኳን ለትውልድ ሥፍራው ሣያደላ የባሮ ድልድይን ሠርቶ የተረሡትን ህዝቦች አንድ አድረገ እንጂ የብሄር ግጭት ፈፅሞ ታይቶ አይታወቅም ባሣለፍናቸው የሀገር ፍቅት ሥሜት ያላቸው መንግሥታት እነሆ ዛሬ ወሮ ባላ መጤ ሽብርተኛ መንግሥት ለ24 አመት እያምታታ መራሁ ቢለን የብሄር መብት በኔ ተከበረ ቢለን እነሆ በታሪክ መዝገብ ሊሠፍር ሊፃፍ የሚችል ቀይ ሥህተት የብሄር የጎሣ ግጭት ከምንግዜውም ተባብሦ አልበቃ ብሎ ረሀብ ጠኔን አሥፋፉ ወገን ዝም ብለን እንደ ብአዴን ኦህዴድ ደህዴን መሠል ባለቤት ያጡ አህዬች ሆነን አብረን ከመነዳት እግዚያብሄር ይሠውረን አንድ ህዝብ አንድ ሀገር አንድ ባንዲራን ነው አባቶቻችን ያሥረከቡን ይህን አንድነታችንን እና ወኔያችንን በቁም በኮሮጆ የሠለበው ወያኔን ለማሥወገድ ትግሉ መቀጠል ይኖርበታል በርቱ።
Ethiopia is going to live in peace forever. Nothing you guys say or do is going to make a tiny difference simply because you are irrelevant.
badin sijemer amhara tewekellNa chaka weteh ethiopiyan bezer kefafllN alalewm ayweklewm beterefe weyani yetgri asgentay ena ohded yeoromo asgentayoch 25 amet begara yenegerun ena le ethiopiya hzb eyesebeku yasalefut amhara yeyandandu bhir telat new teblo kageru eyetelekem endichefechef tedergal weyani zer atfto yetgri kfle hagerun siyasfafa ohded degmo amhara kageri ywta weron new bemalet weyanin sitebaberu norewal enezih hayloch zer bematfat zer bemasdat lezerochachn kll ager enmesertalen bemalet 25 amet simodamodu weyani be amhara sm ertrawi yehonewn bereket smon askemto zerun siyatefa nore keza wede gabila zoru keza …eyalu zari bewananet bechakm sidegfuachew yeneberu yeoromon yezer lhikanoch gziachewn siyarazmulachew yeneberutn zorew ye master planun yeoromo zer tewelajoch tekawemu bemasbal siyaschefechfu yasaznal yh weyani ena yeoromo yezer lhikanoch poletika lemetekem yemiyadergut fukcha dehaw oromo megedelu yasaznal slezih enezih yeoromo lhikanoch begzi ke ethiopiyawyan gar btkelakelu yshalachhal ethiopiyanu bezer kll ayamnm mknyatum ageru yegara new ethiopiyawinet wrs new stotam aydelem slezih wshetn atwdedat ewnetn tasresachuhalech ena yemibalew teret lezih new liba siserk ysmamana sikafel ychefachfal ewnetu yh new
የወያኔ መወገድ ግድ ይለናል