ኤጀንሲው የአቶ በረከት ስምዖንን መኖሪያ ቤት ለባለቤቱ እንዲያስረክብ ታዘዘ

ኤጀንሲው የአቶ በረከት ስምዖንን መኖሪያ ቤት ለባለቤቱ እንዲያስረክብ ታዘዘ
የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 17 ቀበሌ 19 ውስጥ የሚገኘውን፣ የቤት ቁጥር 119 የሆነውንና የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ በረከት ስምዖን እየኖሩበት የሚገኘውን መኖሪያ ቤት፣ ታኅሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲያስረክብ ታዘዘ፡፡ 

ኤጀንሲው ቤቱን ለባለ ንብረቱ አቶ መሐሪ ተወልደ ብርሃን እንዲያስረክብ፣ የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ከ17 ዓመታት በፊት ሚያዝያ 28 ቀን 1990 ዓ.ም. ትዕዛዝ ያስተላለፈ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን አለማስረከቡ ተጠቁሟል፡፡

የቤቱ ባለቤት አቶ መሐሪ ጥቅምት 5 ቀን 1988 ዓ.ም. ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ባቀረቡት አቤቱታ እንዳስታወቁት፣ ቤቱ የተወረሰው ከአዋጅ ውጪ በመሆኑ እንዲመለስላቸው መጠየቃቸውን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡ ኤጀንሲውም ባደረገው ምርመራ የአመልካቹ ቤት በአዋጅ ቁጥር 110/87 አንቀጽ 2(3) መሠረት ከአዋጅ ውጪ የተወረሰ መሆኑን እንዳረጋገጠ ጠቁሞ፣ ኤጀንሲው ለቤቱ ማሠሪያ የዋለ የባንክ ዕዳ ካለ ተሳስቦ ለባንክ እንዲከፍልና ምንም ዓይነት የዕዳ ጥያቄ ሳያቀርብ ቤቱን ለአቶ መሐሪ እንዲያስረክብ አዞት እንደነበር ሰነዱ ያሳያል፡፡ ነገር ግን ቤቱ ተጨማሪ ማጣራት እንደሚያስፈልገው ተገልጾ፣ ከሰኔ 12 ቀን 1990 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ታግዶ የቆየ ቢሆንም፣ ቤቱ እንዲመለስላቸው የተሰጠው ውሳኔ ትክክል መሆኑ ስለተረጋገጠ፣ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ ቦርድ እግዱ እንዲነሳ ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በመወሰኑ፣ ቤቶች ኤጀንሲ ቤቱን ለአቶ መሐሪ እንዲያስረክብ በድጋሚ ማዘዙን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

ቤቶች ኤጀንሲ እንዲያስፈጽም ለተላለፈለት ትዕዛዝ በሰጠው ምላሽ፣ ‹‹ቤቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ ውሳኔ ያስተላለፈው ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ነው፡፡ ውሳኔው የሚፈጸመው በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት በውክልና ነው፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለማስፈጸም ሥልጣን የለውም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን እንዳብራራው፣ ኤጀንሲው ፍርድ ቤቱ ሥልጣን እንደሌለው ቢገልጽም ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ኤጀንሲው ጊዜ እንደሚያስፈልገው ቢገልጽም፣ እንዲያስፈጽም ከስምንት ወራት በላይ ስለተሰጠው በቂ ጊዜ እንደሆነና በቤቱ ውስጥ የሚኖሩት ከፍተኛ ባለሥልጣን ናቸው የሚለው ተቀባይነት እንደሌለው በመዘርዘር፣ ቀደም ብሎ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አቶ በረከት ስምዖን የሚኖሩበት መኖሪያ ቤት ለባለቤቱ አቶ መሐሪ ተወልደ ብርሃን እንዲያስረክብ፣ የቤቶች ኤጀንሲ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ኅዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ትዕዛዝ ተላልፎለታል፡፡

 

7 Comments on “ኤጀንሲው የአቶ በረከት ስምዖንን መኖሪያ ቤት ለባለቤቱ እንዲያስረክብ ታዘዘ”

  1. bereket smon ertrawi new ethiopiyawi aydelem beamhara sm yeamharan zer lematfat yetekemete banda new enatum abatum ertrawi nachew meles tgrina ertrawi new enezih bandawoch ertrana tgi hlwnaw yemitebekew ,amharana oromo ,endihum lilaw bezer tebetatnw zerun snatefana agerun lebaed snchebechb new bemalet ethiopiyan endeager endatkom bezer kefaflew letgri zer hlwna ethiopiyan kebaed gar gara bemesharek eyechebechebu invester teblew yedehawn bit merit eyekemu yalu nachew bereket bezer kehone keamhara gar gnunet yelewm amharanm aywklm slezih amharana oromo degmo kankachew bileyaym zerachew tedebelalko lebzu shi zemenat yetewaleduna yetedebelaleku agerachew and yehone mahbereseboch lemn bezer endileyayu yderegal bereket bezer kehone mn abatu yseral adis abeban aydelem melaw agerachnn bezer eyekemu new

  2. That is funny, for me it is means of diverting the hot current issue to individuals. We Ethiopians demand justice for every body. We gonna do it after we got independent at TPLF ruling junta.

  3. ይድረሥ ለውድ ጓዴ በረከት ሥምኦን አታ ወዲ ሸርሙጣ ተዋሪድና ብናትኩም አታ እንታይ ኮንካ አታ ወዲ ለቆማፅ በል ፈጥንላካ አብ ገዛሀ እታው

    ወያኔታት ኩሎም ሸርሙጣ ጉጅሌታት እዬም

  4. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    የምታናፋ አህያ በአጋጋጧ ትለያለች

    ይህ ወያኔው ኢሠፖኮ መሪ ሀ.ማርያም ደሣለኝ የተነገረች ቀልድ ናት

    እናት ሀገር ወይም ሞት

  5. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    fuck every woyane

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*