የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ታዘዘ
(በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከአራት ወራት በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ የተላለፈን ትዕዛዝ ሳይፈጽም በመገኘቱ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡
(በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከአራት ወራት በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ የተላለፈን ትዕዛዝ ሳይፈጽም በመገኘቱ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡
በሆላንዳዊው የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል በሚስተር ቲዝ በርማን የተመራው የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን፣ ከአምስት ወራት ዝምታ በኋላ የግንቦት 2002 ምርጫ ትዝብት ሪፖርቱን በነገው ዕለት ይፋ ያደርጋል፡፡
(በየማነ ናግሽ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የወለንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ወቋተህዴን) ፓርቲ አምስት ከፍተኛ አመራሮችና አንድ አባል ለ12 ቀናት ታስረው ከቆዩ በኋላ ባለፈው ዓርብ ተፈተዋል፡፡
– አራት ኮሌጆች ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ከስረዋል እየተባለ ነው (በታምሩ ጽጌ) መንግሥት የትምህርት ሥልጠና ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ በሚል፣ ማንኛውም የግል ከፍተኛ ተቋማት የሕግና የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ ያስተላለፈውን ክልከላ ተከትሎ፣ በርካታ የርቀት ትምህርት መምህራን ከሥራ እየተሰናበቱ መሆኑን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
(በጋዜጣው ሪፖርተር) ባለፈው ዓርብ የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ አማካሪዎች ቡድን ሪፖርቱን ለተባበሩት መንግሥታት ሲያቀርብ፣ ካሁን በኋላ ግፊቱና ጫናው የሚበዛው በበለጸጉ አገሮች ላይ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስታወቁ፡፡
(በታደሰ ገብረ ማርያም) ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቦሌና በየካ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ሁለት አካባቢዎች በድምሩ 56 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታዎችን አስፋፍቶ ይዟል ተብሎ የተገለጸው ፍጹም ሀሰት ነው ሲል አስታወቀ፡፡
(በታምሩ ጽጌ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለይ ገርጂ መብራት ኃይል፣ ኢምፔሪያል ሆቴል አካባቢ፣ ካዛንችስ፣ ጐፋ መብራት ኃይልና አልፎ አልፎ በሌሎቹም አካባቢዎች ባሉ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ነዋሪዎች በጠራራ ፀሐይ እየተዘረፉ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
(በሚኪያስ ሰብስቤ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ፣ ሌሎች 13 የወቅቱ የድርጅቱ ሠራተኞች የሚገኙበትን የሙስና ክስ ጉዳይ እያየ ያለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ ደረጃ የወንጀል ችሎት፣ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ለኅዳር 22 ቀን 2003 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዟል፡፡
(በብርቱካን ፈንታ) ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለሀብታሞች በውድ ዋጋ የሚሸጥ ‹‹ሜምበርስ ኦንሊ›› የተባለ ኮንዶም እ.ኤ.አ በ2010 መጨረሻ ላይ ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡
– ብ/ጄ/ ተፈራ ማሞን ጨምሮ አምስት ፍርደኞች በሞት እንዲቀጡ ይግባኝ ተብሏል (በታምሩ ጽጌ)
(በውድነህ ዘነበ) ከስኳር ልማት ብዙ የሚጠብቁት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመቋቋም ሒደት ላይ ለሚገኘው የስኳር ልማት ኮርፖሬሽን፣ በሚኒስትር ማዕርግ አቶ ዓባይ ፀሐዬን ዳይሬክተር ጄነራል አድርገው ያልተጠበቀ ሹመት ሰጡዋቸው፡፡
(በኃይሌ ሙሉ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክን (መድረክ) በመወከል ፓርላማ የገቡት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፣ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበርና የአማካሪ ምክር ቤት አባል ሆነው ተመረጡ፡፡
(በኃያል አለማየሁ) አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ያስገነቡትና ወደፊት የኩባንያዎቹ ዋና መሥሪያ ቤት የሚሆነው ባለመንታ ፎቅ ሕንፃ፣ በመጪው ቅዳሜ በፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ለይኩን ብርሃኑ ለሪፖርተር በላኩት ደብዳቤ አስታወቁ፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር 923,380 ካሬ ሜትር መሬት ነጠቀ (በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያቋቋመው ልዩ ግብረ ኃይል ባለፈው ሳምንት በመጨረሻዎቹ ሦስት ቀናት በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ባካሄደው ዘመቻ 923,380 ካሬ ሜትር መሬት ነጠቀ፡፡
(በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤትን ግንባታና ሌሎች ጉዳዮችንም በሚመለከት እንዲያጣራ ሐምሌ 27 ቀን 2001 ዓ.ም.
(በምዕራፍ ብርሃኔ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በቀበሌ 01/19 ከሰንሻይን ሕንፃ ጀርባ በመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ምክንያት የተነሱ 215 ቤቶች ውስጥ በጥገኝነት ስንኖር ከ20 በላይ የሚሆኑ አባወራዎች፣ በላያቸው ላይ ቤቶቻቸው በመፍረሳቸው መድረሻ እንዳጡ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
(በቃለየሱስ በቀለ) በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተተከለው አዲሱ የአውሮፕላን በረራ መቆጣጠሪያ ራዳር፣ ለማረፍ የሚመጡ አውሮፕላኖች በአየር ላይ እንዲዞሩ የሚያደርገውን አሠራር የሚያስቀር፣ በዚህም በከፍተኛ ደረጃ የአውሮፕላን ነዳጅ ፍጆታ እንደሚቀንስ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
(በኃይሌ ሙሉ) ምርጫ 2002ን ተከትሎ በርካታ ያልተጠበቁ ነገሮች ተከስተዋል፡፡ ኢሕአዴግ የፓርላማ መቀመጫውን በ99.6 በመቶ ማሸነፉ አነጋጋሪ ጉዳይ የነበረ ቢሆንም፣ ብዙም ሳይቆይ ገዥው ፓርቲ ለሕዝብ ያስተዋወቀው የአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሌላ መወያያ አጀንዳ ሆኗል፡፡
(በየማነ ናግሽ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታን ለፖለቲካ አፈና ያውላል›› የሚለው የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርትን የተቃወመውን የልማት ደጋፊዎች ቡድንን (DAG) አወገዘ፡፡
(በታምሩ ጽጌ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገዶች ባለሥልጣንና የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሚያስገነቧቸው ፕሮጀክቶች፣ በተያዘላቸው ዕቅድና ጊዜ ለመጨረስ የማይችሉበት ከፍተኛ የፋይናንስ፣ የሲሚንቶና የግብዓት እጥረት እንዳለባቸው ተቋራጮቹ ገለጹ፡፡
– ሀገረ ስብከቱ ከ4.2 ሚሊዮን ብር በላይ አባክኗል – በሁለት ዓመታት ከ35.4 ሚሊዮን ብር በላይ ለሀገረ ስብከቱ ፈሰስ ተደርጓል (በታምሩ ጽጌ)
(በዳዊት ታዬ) የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባሳለፍነው ሐሙስ ባካሄደው ስድስተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ያገዳቸውን አንድ የቦርድ አባል በሌላ እንዲተኩ ውሳኔ ሰጠ፡፡
(በታደሰ ገብረ ማርያም) አሜሪካ የምትሰጠው ዕርዳታ የኅብረተሰቡን ጤንነትና የአኗኗሩን ሁኔታ ለማሻሻል የሚውል እንጂ፣ ለአገር ውስጥ ፖለቲካ መጠቀሚያ ወይም ማራመጃ መሣሪያ ሊሆን እንደማይገባ ዶክተር ኢዝኪኤል ኢማኑኤል የኋይት ሐውስ የጤና ልዩ አማካሪ አስታወቁ፡፡
– 828 ግለሰቦች ከ391 ሺሕ ካሬ ሜትር በላይ መሬት አጥረዋል (በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕገወጥ ባላቸው የሪል ስቴት አልሚዎች እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ ሲያጠናቅቅ፣ ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን የንግድ ሕንፃዎችን ለመገንባት ቦታ በሊዝ ወስደው ሳያለሙ አጥረው ባስቀመጡት ላይ በማድረግ ዘመቻውን …
የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕንፃ ለመገንባት ቦታ ወስደው ባላለሙት ላይ ዘመቻ እጀምራለሁ አለ Read more »
– ባንኩ ሆቴሉን በድርድር ለመሸጥ አስቧል (በኃይሌ ሙሉ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር መያዣነት ይዤዋለሁ ያለውን የላንጋኖ በቀለ ሞላ ሆቴል በ60 ሚሊዮን ብር መነሻ ዋጋ ለሁለተኛ ጊዜ ለጨረታ ቢያቀርብም ገዥ ሊያገኝ አልቻለም፡፡
(ሪፖርተር) — አቶ አርከበ ዕቁባይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ትናንት አስታውቋል፡፡ በተመሳሳይም አቶ ሽፈራው ጃርሶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ አቶ ንዋየክርስቶስ ገብረአብ በሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር እንዲሁም ፕሮፌሰር …
መንግሥት ለልዩ መልዕክተኛና ለባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነትና ለአምባሳደሮች ሹመት መስጠቱን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
(በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ በወሰደው ዕርምጃ ተጠቂ ከሆኑት 33 አልሚዎች መካከል አንዱ የሆነው አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ‹‹የአስተዳደሩ ውሳኔ አግባብነት የለውም፣ የእኔ ጉዳይ በድጋሚ ሊታይ ይገባዋል፣ ይህ ካልሆነ ግን አስተዳደሩን ወደ ፍርድ ቤት …
(በታደሰ ገብረ ማርያም) በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅትና በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን መካከል ከ900 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ፣ የ500 ተጋጣጣሚ የከተማ አውቶቡሶች ግዥ ውል ስምምነት ትናንት ተፈረመ፡፡
(በየማነ ናግሽ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት በዋለው ዓመታዊ ስብሰባ፣ በቦሌ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ተሰርቶ የነበረው የፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ፣ ከኢትዮጵያ ሚሌኒየም ጊዜ ጀምሮ በየቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢዎች የሚገኙና ምስላቸውን የያዙ ቢልቦርዶች እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
– በዓመት 1.4 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ለማምረት አቅዷል (በኃያል አለማየሁ) ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ. በሲሚንቶ ፋብሪካ ተከላና በግንባታው ዘርፍ ከሚታወቀው ኖርዘርን ሄቪ ኢንዱስትሪ ከተባለው የቻይና ኩባንያ ጋር በትናንትናው ዕለት በሒልተን ሆቴል በተከናወነ ሥነ ሥርዓት ላይ የ79 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ውል ተፈራረመ፡፡
(በውድነህ ዘነበ) መንግሥት በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ከወጪ ንግድ 653.4 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ቢያቅድም፣ ማሳካት የቻለው የዕቅዱን 86 በመቶ ወይም 563.4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን የንግድ ሚኒስቴር ሪፖርት ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡
– መኢብን ከጥምረቱ ራሱን አገለለ (በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጥምረት (ኢዴኃጥ) በሚል ስያሜ ተመስርቶ፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ሰርተፊኬት የተከለከለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ፣ የምርጫ ቦርድን የመጨረሻ ውሳኔ እየተጠባበቀ ነው፡፡
(በቃለየሱስ በቀለ) የኢትዮጵያ መንግሥት ከውጪ አገር በሚገቡ የሞባይል ቀፎዎች ላይ የጣለውን ከፍተኛ የጉምሩክ ቀረጥ ሊቀንስ ነው፡፡
(በኃይሌ ሙሉ) የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በታክስ ማጭበርበርና በተዝረከረከ አሠራር የጠረጠረውን አዳሚ ቱሉ የፀረ ተባይ ማዘጋጃ አክሲዮን ማህበር የተባለን የመንግሥት መሥሪያ ቤትን መመርመር ጀመረ፡፡
– ለምን የሚል ጥያቄ ያነሱት የቦርድ አባል ታግደዋል (በብርቱካን ፈንታ) የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለ2003 ዓ.ም. ያፀደቀው 32 ሚሊዮን ብር በጀት ውዝግብ አስነሳ፡፡
(በኃይሌ ሙሉ) የኢትዮ ጃፓን ናይለን ጨርቃ ጨርቅ አ.ማ ሠራተኞች ከሥራ እየተፈናቀሉ መሆናቸውን ሠራተኞቹና የድርጅቱ መሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
(በዳዊት ታዬ) ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2003 ዓ.ም. በፓርላማ የመንግሥትን አቋም ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ አገሪቱ የገጠማት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ከሥርጭት ኋላቀርነት የመነጨ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
– ገንዘቡን ለማሰባሰብ የምርጫው ‹‹ኔትወርክ›› ሥራ ይጀምራል (በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሁለት ዓመት የሥልጣን ቆይታ በኋላ የቀድሞውን የከተማውን ጊዜያዊ አስተዳደር ዱካ በመከተል፣ ከነዋሪው ሕዝብ 600 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሀብት በማሰባሰብ የልማት ሥራዎችን ማካሄድ የሚያስችለውን አዲስ ዕቅድ ይፋ አደረገ፡፡
– ከ26,400 ተፈታኞች 6,600 ብቻ ናቸው ያለፉት (በታምሩ ጽጌ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ኢንዱስትሪውን በሙያ ብቃት ምዘና ተግባራት ላይ በባለቤትነት እንዲሳተፍ አቅም መፍጠር ባለመቻሉ፣ ከባድ አደጋ እንደተጋረጠበት አስታወቀ፡፡ የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ብቃት እንዲሁ ለአደጋ መጋለጡ …
(በቃለየሱስ በቀለ) የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት የሚውል የ230 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሊፈቅድ ነው፡፡
– አልሚዎች ቅሬታ አላቸው (በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባደረገው ስብሰባ፣ ለሪል ስቴት ልማት የወሰዱትን ቦታ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የተጠቀሙ ባለሀብቶች ጉዳይ በጥልቀት ተመርምሮ ማስተማርያ በሚሆን መንገድ እንዲቀጡ ወሰነ፡፡
– ከቀረጥ ነፃ የገቡ መኪኖች በጉምሩክ ተይዘዋል (በኃይሌ ሙሉ) በአገር አቀፍ ደረጃ በተፈቀደው ብድር መሠረት የቻይና ስሪት የሆኑ ሲኖትራክ መኪኖችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው ተቋራጮችና የትግራይ ቤቶች ልማት ኤጀንሲ የተፈራረሙት ውል የጉምሩክን ሕግ የሚጥስ ሆኖ ተገኘ፡፡
(በምሕረት ሞገስ) ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ በአትክልት ዋጋ ላይ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ተከትሎ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በአትክልት ተራ አላግባብ ዋጋ በመጨመር ላይ የተገኙ ሱቆች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ የመውሰድ ሥራ መጀመሩን አስተዳደሩ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡
(በውድነህ ዘነበ) ላለፉት አሥርት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንግዶቿን ስትጋብዝ የቆየችበት የግብዣ አዳራሽ፣ የመሬት አስተዳደርና ግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ቢሮ አድርጐ እንዲጠቀምበት ተሰጠው፡፡ አዳራሹ ለቢሮዎች በመሸንሸኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር ሠራተኞች ቅሬታ አድሮባቸዋል፡፡
– ከ10 ሰዓት በኋላ እንዲሠሩ አማራጭ በአስተዳደሩ ቀርቦላቸዋል (በብርቱካን ፈንታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል በነበሩት ሁለት የአስተዳደር ወቅቶች ቦታና ፈቃድ እንዲሁም ብድር ተሰጥቷቸው ተደራጅተው ይሠሩ የነበሩ የአነስተኛና ጥቃቅን ነጋዴዎች ሕጋዊ አይደሉም በሚል ቦታቸውን ተነጠቁ፡፡
(በታምሩ ጽጌ) የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በተጠረጠሩበት የ100 ሺሕ ብር የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው የነበሩት የፌዴራል ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነትና ጉዳዮች ኃላፊ ኮማንደር ደምሳሽ ኃይሉን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. …
የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነፃ ተሰናበቱ Read more »
ምዕራፍ ብርሃኔ | ሪፖርተር በክረምት የትምህርት ክፍለ ጊዜ ለአራት ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በሐምሌ ወር 2002 ዓ.ም. የተመረቁ ተማሪዎች፣ ጊዜያዊ ዲግሪያቸውን ለመውሰድ ሲጠይቁ፣ ‹‹አልተመረቃችሁም›› በመባላቸው ቅሬታ እያሰሙ ነው፡፡ እንዳልተመረቁ የተነገራቸው ተማሪዎቹ የእንግሊዝኛን ቋንቋ ዓብይ፣ የኦሮሚኛን ቋንቋን ደግሞ …
– ፀረ ሽብር ሕጉ ከበለፀጉ አገሮች የተሻለ ነው – በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ብድር ከአጋር አገሮች ተገኝቷል
(በዘካሪያስ ስንታየሁ) ለጋሾች ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ዕርዳታ፣ መንግሥት የፖለቲካ ተቃውሞን ለማፈን እየተጠቀመበት ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ትናንትና ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ፡፡