ዕውቅና የተነፈገው የፓርቲዎች ጥምረት የምርጫ ቦርድ ውሳኔን እየጠበቀ ነው

– መኢብን ከጥምረቱ ራሱን አገለለ

(በታምሩ ጽጌ)

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጥምረት (ኢዴኃጥ) በሚል ስያሜ ተመስርቶ፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ሰርተፊኬት የተከለከለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ፣ የምርጫ ቦርድን የመጨረሻ ውሳኔ እየተጠባበቀ ነው፡፡