በደቡብ ክልል የአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ አምስት ከፍተኛ አመራሮች ለ12 ቀናት ታስረው ነበር ‹‹ድርጊቱ ሕገወጥና አሳዛኝ ነው›› ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
(በየማነ ናግሽ)
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የወለንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ወቋተህዴን) ፓርቲ አምስት ከፍተኛ አመራሮችና አንድ አባል ለ12 ቀናት ታስረው ከቆዩ በኋላ ባለፈው ዓርብ ተፈተዋል፡፡