‹‹ዘመቻ ሪል ስቴት››

የአዲስ አበባ አስተዳደር 923,380 ካሬ ሜትር መሬት ነጠቀ

(በውድነህ ዘነበ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያቋቋመው ልዩ ግብረ ኃይል ባለፈው ሳምንት በመጨረሻዎቹ ሦስት ቀናት በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ባካሄደው ዘመቻ 923,380 ካሬ ሜትር መሬት ነጠቀ፡፡