– የሰንጋተራ ነጋዴዎች በሰባት ቀናት ውስጥ ልቀቁ መባላቸውን ተቃወሙ (በታምሩ ጽጌ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ አክሲዮን ማኅበራት በሊዝ የተሸጡ ቦታዎችን የክፍለ ከተማ አስተዳደሮች እስከ መስከረም 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ድረስ አጠናቀው ማስከረብ እንዳለባቸው ጥብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በቃለየሱስ በቀለ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስታር አሊያንስ የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የአየር መንገዶች ኅብረት አባል ሊሆን ነው፡፡ በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲሰ በሚካሄድ ሥነ ሥርዓት መቀላቀሉ ይበሰራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

(በብርቱካን ፈንታ፣ ሪፖርተር) ሳመሪታን ፐርስ የተባለ ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በሕገወጥ መንገድ 14 አሜሪካውያን ሲሠሩበት ቆይተዋል በሚልና በሌሎች ተጨማሪ ወንጀሎች ምክንያት፣ ከመስከረም 14 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ መታገዱን የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሰፋ …

የአሜሪካውያን በጎ አድራጎት ድርጅት ታገደ Read more »

(በታምሩ ጽጌ) የቱሪዝም፣ የሆቴሎችና የጠቅላላ አገልግሎት ሠራተኛ ማኅበራት ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን፣ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ በቀበሌ መዝናኛዎች ውስጥ የሚሠሩ ከ15 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ ሊያጡ የሚችሉበት ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን አስታወቀ፡፡

– ለፕሮጀክቱ 1.4 ቢሊዮን ዶላር በጀት ይዟል– በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ንግድ ለማግኘት አቅዷል– ባሮ ወንዝን እንዲጠቀም ተፈቅዶለታል– ጆንዲር ትራክተርን አገር ውስጥ ለመገጣጠም ታስቧል (በውድነህ ዘነበ)

(በኃይሌ ሙሉ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለጨረታ ያቀረበው የላንጋኖ በቀለ ሞላ ሆቴል ገዥ አጣ፡፡ ባንኩ የሆቴሉን የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ሳይጨምር ሕንፃውን ብቻ ለጨረታ ማቅረቡ ገዥ አሳጥቶታል የሚል እምነት እንዳላቸው የሆቴሉ ሥራ አስኪያጅ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

(በኃይሌ ሙሉ) በአገሪቱ ከሚገኙት የግል ባንኮች ውስጥ አንዱ የሆነው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የባልና ሚስት የጋራ ንብረትን ያለሚስት ዕውቅና መያዣ በማድረግ ለባል ብድር መስጠቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

(በጋዜጣው ሪፖርተር) ጠቅላይ ማኒስትር መለስ ዜናው ባለፈው ረቡዕ በአሜሪካ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ንግግር፣ ይህ የመጨረሻ የሥልጣን ዘመናቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

– ከእስራኤል ኩባንያ ጋር በመተባበር የማሪን አካዳሚ ይከፍታል (በኃያል ዓለማየሁ) በአገሪቱ ብቸኛው የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ፣ በቻይና ኩባንያ ለሚያሠራቸው ዘጠኝ መርከቦች ከቻይና ኤግዚም ባንክ (China Exim Bank) ጋር የ234.7 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

– አቅራቢዎችና ኮንትራክተሮች ዋጋ ለማረጋጋት ተስማሙ (በዳዊት ታዬ) የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቀጣይ ዓመታት ትልልቅ መሣሪያዎችን ከመጠቀም ይልቅ፣ መካከለኛና መለስተኛ በትራክተር ኃይል የሚጎተቱ መሣሪያዎች እንዲጠቀም መታሰቡ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽኑ ዕቅድ አንድ አካል እንደሆነ፣ የሥራና የከተማ ልማት ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡

– 4000 ሔክታር መሬት በውኃ ተሸፍኗል (በታምሩ ጽጌ) በአፋር ክልል በዱፍቲና አሳይታ አካባቢ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ጉዳት እንደደረሰበት በቦታው ተገኝተው የተመለከቱ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

* ለክልሉ ተጨማሪ አራት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተሹመዋል (በሰብለወንጌል ሐብታሙ) የደቡብ ክልልን ላለፉት አምስት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲያስተዳድሩ የቆዩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ በድጋሚ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ተመረጡ፡፡

– አንድ ተማሪ 7,000 ዶላር መክፈል ይጠበቅበታል (በመርጋ ዮናስ) የካሊፎርኒያው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ ኤንድ አድሚኒስትሬሽን (ኤምቢኤ) ፕሮግራም ካለፈው ማክሰኞ መስከረም 12 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ ማስተማር ጀመረ፡፡

‹‹ኢሕአዴግ በጉልበት አሸንፏል እኛ ደግሞ የሞራል የበላይነት አለን›› አቶ ገብሩ አስራት (በኃይሌ ሙሉ) በእስር ላይ የሚገኙትን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ለማስፈታት መድረክ የማያቋርጥ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንና ሊቀመንበሩ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ገለጹ፡፡ ድርጅቱ የወ/ት ብርቱካንን ጉዳይ ችላ …

መድረክ የወ/ት ብርቱካንን ጉዳይ ችላ አለማለቱን አስታወቀ Read more »

ባለፈው ሰኞ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በመላ አገሪቱ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር በመታጀብ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ደግፌ ቡላ የሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓቱን የመሩ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ …

የሰንደቅ ዓላማ ቀን Read more »

(በውድነህ ዘነበ) በሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ የተቋቋመው ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኢትዮጵያ ኩባንያና ሌሎች ሁለት አገር በቀል ኩባንያዎች በመንግሥት ሥር የሚገኘውን የቡና ልማት ድርጅትን ለመግዛት የፕራይቬታይዜሽን ቦርድን ውሳኔ እየጠበቁ ነው፡፡

– በሥሩ ስድስት ኩባንያዎች ይቋቋማሉ (በቃለየሱስ በቀለ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ የነደፈውን ራዕይ 2025 የተሰኘውን የ15 ዓመት የዕድገት መርሐ ግብር ተግባራዊ ለማድረገ በዝግጅት ላይ ሲሆን፣ አዲስ የማኔጅመንት መዋቅር ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል፡፡

‹‹ኤሌክትሪክ የሚያስገባልን ኮርፖሬሽኑ ነው ወይስ ጽሕፈት ቤቱ?›› ኮንዶሚኒየም ቤት የተላለፈላቸው ነዋሪዎች ‹‹ላስተላለፍናቸው ቤቶች በሙሉ ክፍያ ፈጽመናል››  የቤቶች ልማት ፕሮጄክት ጽሕፈት ቤት‹‹ቀደም ብሎ ለተከፈለን አስገብተናል፤ በቅርቡ ለተከፈለንም ለማስገባት በዝግጅት ላይ ነን›› የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን (በታምሩ ጽጌ)

(በአሥራት ስዩም) የቪዛ ካርድ ክፍያ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉና ለመስጠት ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ባንኮች፣ ከዓለም አቀፉ የቪዛ ካርድ ኩባንያ በመጡ ባለሙያዎች የክፍያ ሥርዓቱ የደኅንነት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ሥልጠና የተሰጣቸው ሲሆን፣ በቀጣይነትም የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ (ATM) ማሽኖቻቸውን እንደሚያስፈትሹ …

የቪዛ ካርድ አገልግሎት ሰጪ ባንኮች ማሽኖቻቸውን ሊያስፈትሹ ነው Read more »

– በአገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቦንድ ሽያጭ ሊጀመር ነው(በውድነህ ዘነበ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ሠራተኞች …

(በዳዊት ታዬ)የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ ባለቤትነት ሲኤምሲ አካባቢ ለማስገንባት ያቀዱት የአ

(በብርቱካን ፈንታ)ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አነስተኛ ቡና አምራች ለሆኑ 63 ማኅበራት ብድር ለመስጠት የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድ

በቃለየሱስ በቀለ | The Reporter የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት ስድስት ዓመት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ፣ ከዛሬ መስከረም 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ አቶ ግርማን የሚተኳቸው ምክትላቸው አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደሆኑ …

አቶ ግርማ ዋቄ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊነታቸው ለቀቁ Read more »

– ከ1600 በላይ የጉባዔው ታዳሚዎች አዳማ ከተዋል (በውድነህ ዘነበና አስራት ሥዩም) ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አዳማ ዛሬ የሚጀመረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ስምንተኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ለመታደም የመጡ ከ1600 በላይ ተሰብሳቢዎችን ታስተናግዳለች፡፡

– አቶ ብርሃኑ አዴሎ ለማዕከላዊም ሆነ ለሥራ አስፈጻሚነት አልተመረጡም (በታምሩ ጽጌ) የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) በሐዋሳ ከተማ ከመስከረም 2 እስከ 4 ቀን 2003 ዓ.ም. ባካሄደው 7ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ መተካካትን በሚመለከት አጀንዳው እንዳልነበረ አስታወቀ፡፡

(በጋዜጣው ሪፖርተር) በምሥረታ ሒደት ላይ የነበረው ደቡብ ግሎባል ባንክ አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ የባንኩን የባለአክሲዮኖች የመጀመሪያ ጉባዔ ለመስከረም 9 ቀን 2003 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ መጥራቱን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት አስታወቀ፡፡

‹‹ዕቅዱ የሕዝቡን አመለካከት መለወጫ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ነው›› ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው‹‹በበሬ እየታረሰ ከፍተኛ እመርታ ማስመዝገብ አይቻልም›› አቶ ገብሩ አስራት‹‹ኢሕአዴግ በያዛቸው ካድሬዎች ዕድገት ያመጣል ብሎ ማሰብ በህልም ደረጃም ያስቸግራል›› ዶክተር መረራ ጉዲና

– ባለሀብቱ ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ አውጥቼበታለሁ ይላሉ (በምዕራፍ ብርሃኔ) በወረዳ 12 ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አካባቢ በአምስት ዓመታት ውስጥ ተገንብቶ ያለቀ 26 መኝታ ክፍሎች ያሉት ባለሁለት ፎቅ ፔኒሲዮን ‹‹ሕገወጥ ግንባታ ነው›› በሚል መስከረም 3 ቀን 2003 ዓ.ም. በወረዳው ደንብ አስከባሪዎች …

ግንባታው አምስት ዓመታት የፈጀው ፔኒሲዮን ‹‹ሕገወጥ›› በሚል እንዲፈርስ ተደረገ Read more »

(በኃይሌ ሙሉ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) መስከረም 8 ቀን 2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ታወቀ፡፡ በሌሎች ከተሞችም ተከታታይ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ፡፡

(በኃይሌ ሙሉ | The Reporter) አንድ የ16 ዓመት ታዳጊ ወጣት በሰሜን ጐንደር ዞን የጸጥታ ኃላፊ ጠባቂ መገደሉ ተገለጸ፡፡ በተመሳሳይም አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል አንድ ወጣት በጥይት ተኩሶ ከገደለ በኋላ መሰወሩ ታውቋል፡፡ የሟች ቤተሰቦች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ነዋሪነቱ በጐንደር ከተማ የነበረው …

ሁለት ወጣቶች በጸጥታ አስከባሪዎች ተገደሉ Read more »

የ2002 ዓ.ም በኢድ አልፈጥር በዓል ተደምድሞ የ2003 ዓ.ም በእንቁጣጣሽ በዓል ሊጀመር በመሆኑ፣ ገበያው በተከታታይ ሁለት ቀናት በሚስተናገዱ በዓላት ምክንያት በሸማቾች ተጨናንቆ ነው የከረመው፡፡ ወትሮም በዋጋ ንረት ቁምስቅሉን የሚያየው ገበያ በዓውደ ዓመት ምክንያት እንደ እሳት መጋረፍ ጀምሯል፡፡  ድሮና ዘንድሮን በሸማቾች ተሞክሮ …

የዓውደ ዓመት ገበያ ድሮና ዘንድሮ Read more »

(በጋዜጣው ሪፖርተር) በመቀሌ ከተማ ላለፉት አራት ቀናት በተካሄደው የሕወሕት 1ዐኛ ጉባዔ፣ ስምንት የድርጅቱ ከፍተኛ የአመራር አባላት በገዛ ፈቃዳቸው ከድርጅቱ ኃላፊነት መልቀቃቸው ታወቀ፡፡

– ሕዝቡና ሌሎች ተቃዋሚዎች ጫና እንዲፈጥሩም ጠይቋል (በየማነ ናግሽ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ የአገሪቱን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ለመታደግ አምስት ዓበይት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ለመደራደርና ለመነጋገር ለኢሕአዴግ ጥሪ አቀረበ፡፡

(The Reporter) — የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይቅርታ ቦርድ ለ4,721 እስረኞች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ኘሬዚዳንት አባዱላ ገመዳ በትናትናው እለት አስታወቀ፡፡ በዚህም መሠረት ሕፃናት የያዙ እናቶች፣ ከ5ዐ ዓመት በላይ የሆናቸው ጐልማሶች፣ አዛውንቶችና ወጣቶች መታረማቸው በመረጋገጡ በይቅርታ እንዲፈቱ በቦርድ ተወስኗል፡፡ በክልሉ ማረሚያ …

የኦሮሚያ ክልል ለ4,721 እስረኞች ፈታ Read more »

(በኃያል ዓለማየሁ) የኦሮሚያ ኢንቬስትመንተ ኮሚሽን መሬት ወስደው ወደ ልማት ሳይገቡ አጥረው አስቀምጠዋል ካላቸው 124 ባለሀብቶች ላይ፣ ከ145 ሔክታር መሬት በላይ መልሶ መውሰዱን ኮሚሽነሩ አቶ አህመድ ኢብራሒም ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የመሬት ጥያቄ መቀበል ያቆመ ሲሆን፣ መሬት ለማግኘት ወደ አስተዳደሩ የሚሄዱ ባለሀብቶች ተቀባይ በማጣታቸው ቅሬታ እንደተፈጠረባቸው አስታወቁ፡፡

(በብርቱካን ፈንታ) ማጂክ ካርፔት ትምህርት ቤት ለመዋዕለ ሕፃናት ማስተማሪያነት አስገንብቶ ለሁለት ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥበት የቆየው ሕንፃ፣ ሕገወጥ ግንባታ ነው በሚል ባለፈው ማክሰኞ በግብረ ኃይል የፈረሰ ሲሆን፣ ትምህርት ቤቱ በበኩሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈቅዶ የሰጠኝ ቦታ ነው ብሏል፡፡

– ‹‹ጥያቄያቸው መስፈርት የማያሟላ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም›› አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የደኢሕዴግ ሊቀመንበር (በታምሩ ጽጌ) በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠላቸውን መብት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ጥያቄ ያቀረቡ የሰዶ ወረዳ ነዋሪዎች ልጆቻቸው እንደታሰሩባቸውና ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ለሪፖርተር ገለፁ፡፡

– ለትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትሩ ቅሬታቸውን በደብዳቤ አስታወቁ (በታምሩ ጽጌ) በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቃቂ በሚገኘው የመንጃ ፈቃድ ማውጫና ማለማመጃ ማዕከል ውስጥ የሚገኙትን የአውቶሞቢል ባለንብረቶች፣ ተሽከርካሪዎቻቸውን በማሠልጠኛ ተቋማት ሥር እንዲያስመዘግቡ ያስተላለፈውን መመሪያ ተቃወሙ፡፡