ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የአዲስ አበባ አስተዳደርን እከሳለሁ አለ

(በውድነህ ዘነበ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ በወሰደው ዕርምጃ ተጠቂ ከሆኑት 33 አልሚዎች መካከል አንዱ የሆነው አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ‹‹የአስተዳደሩ ውሳኔ አግባብነት የለውም፣ የእኔ ጉዳይ በድጋሚ ሊታይ ይገባዋል፣ ይህ ካልሆነ ግን አስተዳደሩን ወደ ፍርድ ቤት እወስደዋለሁ፤›› ሲል አስታወቀ፡፡