አርከበ ዕቁባይ የመለስ አማካሪ ሆኖ ተሾመ
(ሪፖርተር) — አቶ አርከበ ዕቁባይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ትናንት አስታውቋል፡፡
በተመሳሳይም አቶ ሽፈራው ጃርሶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
አቶ ንዋየክርስቶስ ገብረአብ በሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር እንዲሁም ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ በሚኒስትር ዴኤታ ማእረግ የግብርና ሚኒስትሩ አማካሪ ሆነዋል፡፡
የተሰጠው ሹመት የትምህርት ዝግጅትን እና የፖለቲካ አመራር ብቃትን ከግምት ያስገባ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ተሿሚዎቹ ከጥቅምት 17 ቀን 2003 ዓም ጀምሮ የተሾሙ መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ ጨምሮ አስታውቋል፡፡