የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ብቃት አደጋ ውስጥ ነው

– ከ26,400 ተፈታኞች 6,600 ብቻ ናቸው ያለፉት

(በታምሩ ጽጌ)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ኢንዱስትሪውን በሙያ ብቃት ምዘና ተግባራት ላይ በባለቤትነት እንዲሳተፍ አቅም መፍጠር ባለመቻሉ፣ ከባድ አደጋ እንደተጋረጠበት አስታወቀ፡፡ የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ብቃት እንዲሁ ለአደጋ መጋለጡ ታውቋል፡፡