የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕንፃ ለመገንባት ቦታ ወስደው ባላለሙት ላይ ዘመቻ እጀምራለሁ አለ

– 828 ግለሰቦች ከ391 ሺሕ ካሬ ሜትር በላይ መሬት አጥረዋል

(በውድነህ ዘነበ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕገወጥ ባላቸው የሪል ስቴት አልሚዎች እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ ሲያጠናቅቅ፣ ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን የንግድ ሕንፃዎችን ለመገንባት ቦታ በሊዝ ወስደው ሳያለሙ አጥረው ባስቀመጡት ላይ በማድረግ ዘመቻውን እንደሚጀምር፣ አንድ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡