አዋሽ ባንክና ኢንሹራንስ ያስገነቡት መንታ ሕንፃ በመጪው ቅዳሜ ይመረቃል
(በኃያል አለማየሁ)
አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ያስገነቡትና ወደፊት የኩባንያዎቹ ዋና መሥሪያ ቤት የሚሆነው ባለመንታ ፎቅ ሕንፃ፣ በመጪው ቅዳሜ በፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ለይኩን ብርሃኑ ለሪፖርተር በላኩት ደብዳቤ አስታወቁ፡፡