‹‹አዲሱ ራዳር የአውሮፕላን ነዳጅ ወጪ ይቆጥባል›› የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን
(በቃለየሱስ በቀለ)
በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተተከለው አዲሱ የአውሮፕላን በረራ መቆጣጠሪያ ራዳር፣ ለማረፍ የሚመጡ አውሮፕላኖች በአየር ላይ እንዲዞሩ የሚያደርገውን አሠራር የሚያስቀር፣ በዚህም በከፍተኛ ደረጃ የአውሮፕላን ነዳጅ ፍጆታ እንደሚቀንስ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡