መድረክ የለጋሾችን ቡድን በኢትዮጵያ ለተንሰራፋው ጭቆና ጠበቃ መስሏል አለ

(በየማነ ናግሽ)

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታን ለፖለቲካ አፈና ያውላል›› የሚለው የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርትን የተቃወመውን የልማት ደጋፊዎች ቡድንን (DAG) አወገዘ፡፡