የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለማዬሁ መኮንንና በንቁ የፖለቲካ ተሳትፎው የሚታወቀው አባል አቶ አብረሃም ብዙነህ በጂንካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ እስራቱ የተፈጸመው መጋቢት 17 ቀን 2008 ዓ.ም ቤታቸው ከማለዳው 12 ሰዓት እስከረፋዱ 4፡20 ከተፈተሸ …

በደቡብ ኦሞ የኦህዲኅ መሪ አቶ ዓለማዬሁ መኮንንና አንድ ጠንካራ አባል ታሰሩ – ግርማ በቀለ Read more »

የኖርዌይ ከለላ ጠያቂዎች ድርጅት ከፍተኛ አማካሪና የሕግ ባለሞያ በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ስደተኞች ስጋታቸው ተገቢ ነው ይላሉ።

በፍቃዱ ኃይሉ

የሥም ነገር ሳልወድ በግዴ ያፈላስመኛል። ሥም ተራ መለያ መጠሪያ ብቻ ነው ብዬ አልቀበልም። ምናልባት መጀመሪያ ላይ እንዲያ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አሁን፣ ሥም በባሕልና የሥልጣኔ ዝግመተ ለውጥ ሒደት (evolution of civilizations) ውስጥ ብዙ ውስብስብ ነገሮችን እያነገበ በጊዜ ባቡር ተሳፍሮ ውስብስብ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሥም የባሕል መገለጫ፣ የፖለቲካ አመለካከት መንፀባረቂያ፣ የወላጆች ለልጆች ውርስ ነው። ለዚያም ይመስለኛል “ሥምና ማንነት” የሚለው ጉዳይ የመጽሐፍ ምዕራፍ እና የጥናት ርዕስ ለመሆን እየበቃ ያለው።  አባቶቻችን በፈረንጆች ‘የሊትሬቸር’ አጻጻፍ ደምብ ስላልጻፉልን ፍልስፍና መስለው ያልታዩን አፈላሳፊ አባባሎች አሏቸው። የሊቃውንቱ “ሥሙ ይመርሖ ኀበ ግብሩ” (ሥሙ ተግባሩን ይመራዋል) የምትለው አባባላቸው አሁን ምዕራባውያን እያጠኑት ያሉት ጉዳይ ላይ እነርሱ የደረሱበት ድምዳሜ ነው። በነገራችን ላይ በተቀራራቢ ሮማውያንም ‹nomen est omen› (ሥም ዕጣፈንታ ነው) የሚሉት አባባል አላቸው፡፡ ሳይንቲስቶች «ሰው ወደሥሙ ወይም ከሥሙ ወዲያ (እየተጎተተ ወይም እየተገፋ) የሚኖር ብኩን ፍጡር ነው» ወደማለቱ እየዳዳቸው ነው። ለመሆኑ አንድ ሰው ለመለያ ይሆነው ዘንድ የተሰጠው ሥም ማንነቱን ያሳብቃል? ባሕሪው ላይ ወይም ተግባሩስ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል?

የሥም ቅርፅ

ሥም ከአገር አገር ብቻ ሳይሆን ከዘመን ዘመን ቅርፁና ፀባዩን እየቀያየረ ይሄዳል። ለምሳሌ ምዕራባውያን ‘የቤተሰብ ሥም’ የሚሉት እኛ የለንም፤ አንዳንዶች የጎሳ ሥም እሱን ይተካል ይላሉ። በጊዜ መሥመር ደግሞ ለምሳሌ በኢትዮጵያ በ19ኛው ክ/ዘመን (ከ1900ቹ በፊት) የኢትዮጵያውያን ሥም የሚጻፈው (የሚገለጸው) ‘ከአያት ሥም➡ የአባት ሥም ➡ የልጅ ሥም’ በሚለው ቅደም ተከተል ነበር። ከዚያ ወዲህ ግን (‘የእከሌ ልጅ’ ዘመን አልፎ፣ ‘የእከሌ አባት’ ዘመን ሲጠባ) በተቃራኒው ተደርጓል። በቱርክ እ.ኤ.አ. ከ1943 በፊት የቤተሰብ ሥም የሚባል ነገር አልነበረም። አንዱን ሰው ከሌላኛው ለመለየት ሲባል እስከ ሦስት ሥሞች ድረስ ይወጡለትና በዚያ መደዳ (በእኛ እስከ አያት ሥም በምንለው መንገድ) ይጠራ ነበር። በዚህ የአሰያየም ስርዓት የአባትና የልጅ ሥም ምንም የሚያዛምዳቸው ነገር የለም። ለምሳሌ የቱርክ አባት የሚባለው አታቱርክ (Atatürk) ሥሙ ሙስጠፋ ከማል ነበር። አታቱርክ የተጨመረው ኋላ ለክብሩ ሲባል ነው። የአባቱ ሥም ደግሞ አሊ ሪዛ ነበር። በቱርክ የተጠፋፉ ዘመዳሞች በሥም ተፈላልገው የመገናኘት አማራጭ አልነበራቸውም ማለት ነው። በሌላው ባሕል የልጅ ሥም፣ የአባት ሥም፣ የቤተሰብ ሥም… የምንለው ነገር ዝምድና መቁጠሪያም ጭምር ነው ማለት ነው፡፡

በአገራችን በተለያዩ ማኅበረሰቦች የተለያየ ዓይነት የሥም አወጣጥ አላቸው። ለምሳሌ በጋምቤላ የአኙዋክ ብሔረሰብ ሥም አወጣጥ ሥሙን ሰምቶ ስለሰውዬው ጥቂት ቤተሰባዊ መረጃ ማግኘት ይቻላል። በአኙዋክ፣ የመጀመሪያ ልጅ ኡመድ ይባላል፤ ሁለተኛ ኡጁሉ፣ ሦስተኛ ደግሞ ኦባንግ እያለ ይቀጥላል። አንዳንዴ አባትና ልጅ አንድ ዓይነት ሥም ሊኖራቸው ይችላል። ታላላቆቹ ሴቶች ሆነው መጀመሪያ የሚወለድ ወንድ ኦማን ይባላል። ለምሳሌ እኔ ከአኙዋክ ቢሆን የተወለድኩት ኦማን እባል ነበር እንደማለት ነው።…

በአማራ ተወላጆች ዘንድ ደግሞ ትንሽ ለየት ይላል። ለምሳሌ መንዞች “ርስትና ውትድርና ይወዳሉ” ይባልላቸዋል። ይህም በሥማቸው ሳይቀር ይስተዋላል። ለምሳሌ “ሸዋጉልቱ” የመንዜ ሥም ነው። አምበርብር፣ ደምሰው፣ ዳምጠው፣ አሸብር፣ የመሳሰሉትም የመንዜ ሥሞች ናቸው። ጎንደሬ ደሞ “ሹመት ይወዳል” ይባላል። የጎንደሬ ሥሞች ሹመቴ፣ መኳንንት ወይም መኮንን የመሳሰሉት ናቸው (ወይም ነበሩ)። ቀደም ብዬ እንዳልኩት የሥም አወጣጥ እንደጊዜው ይለዋወጣል። ጎጃም የሄድን እንደሆነ ደግሞ ከልጅ እስከ አባት (ወይም አያት) ያለው ሥም ተገጣጥሞ ዓረፍተ ነገር የሚሰጥበት ጊዜ አለ። በጣም ታዋቂ ከሆኑት መካከል ብንጠቅስ እንኳ ሐዲስ ዓለምአየሁ፣ በዕውቀቱ ሥዩም፣ ፍቅር ይልቃል፣ እያደር አዲስን ማግኘት ይቻላል።

ሥም እና ፖለቲካ

ሥም የፖለቲካ መሣሪያም ነው። የአብዮቱ ሰሞን የተወለዱ ልጆች ‘አብዮት’፣ ‘ትቅደም’… የሚል ሥም ተሰጥቷቸው ዕድሜያቸውን እንኳ እንዳይደብቁ ሆነዋል። አሁንም ያ ባሕል ቀጥሎ “ሕዳሴ” ከሥም ዝርዝሮች ውስጥ ገብቷል። የኦሮሞ ብሔርተኞች ‘የአማራ’ ሥማቸውን እየቀየሩ ቢሊሱማ (ነፃነት)፣ ኒሞና (አሸናፊ) የመሳሰሉት የወጣት ‘አክቲቪስቶች’ ተመራጭ ሥሞች እየሆኑ ነው። ኦቦ ሌንጮ (“አንበሳው” እንደማለት) ለታ (ከዮሐንስ ለታ) እና ብዙዎቹ የኦነግ አንጋፋዎችም ሥሞቻቸውን በመቀየር ነው ትግላቸውን የጀመሩት። በዕውቀቱ ሥዩም የአያቱ ቀዳማይ ሥም በዻዻ መሆኑን መጥቀሱ የኦሮሞ ብሔርተኝነትን ለመተቸት እንደነፃ ፈቃድ ሆኖለታል (ወይም ተጠቅሞበታል)። ዮናታን ተስፋዬ ደግሞ የአባቱን ቀዳማይ ሥም (ቴሬሳ) ፈልጎ የተጠቀመው የኦሮሞ ብሔርተኝነትን በአዎንታዊ መንገድ መረዳቱን ለማመልከት ነበር። በተመሳሳይ በ‘ያ ትውልድ’ ዘመን ሥምን ለፖለቲካ ዓላማ ራስን ለመደበቅ ሲባል መቀየር የተለመደ ነበር። ሕወሓቶች የሞቱ ጓዶቻቸውን ሥም ይወርሱ ነበር። ለገሰ ዜናዊ መለስ ዜናዊ እንደሆኑት ማለት ነው። በሕወሓት ለፖለቲካ ዓላማ ስዩም መስፍን ከአረቦች (ሶርያዎች) እርዳታ ለማግኘት ራሳቸውን ሙስሊም አስመስለው ለማቅረብ የአባታቸውን ሥም ሙሳ ነው ብለዋል። ብዙዎቹ የኦህዴድ ሰዎችም ከምርኮ ወደትግል ሲገቡ የ“አቢሲኒያ” ሥሞቻቸውን ወደ “ኦሮሞ” ቀይረዋል።

ሥምን ለፖለቲካ አገልግሎት መቀየር በዓለም ዙሪያ የተለመደ ነው። አምባገነኑ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ ‘የአውሮጳውያን’ ነው ያሉትን ሥማቸውን ቀይረው ነው ሴሴ ሴኮን በማስጨመር የትግል ሥም ያገኙት። በአገራቸው ዛየር (የአሁኗ ኮንጎ) የክርስቲያን ሥም (Middle Name የሚባለው) ‘የእብራይስጥን ሥም’ ለአፍሪካውያን ሲሰጥ የተገኘ ቄስ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ እስር እንዲቀጣ የሚያደርግ ሕግ አውጥቷል። ጥቁር አሜሪካዊው ታጋይ ማልኮም ኤክስ የቤተሰቡን ሥም በ‘X’ የተካው እና ሌሎችም አጋሮቹ እንደዚያው ያደረጉት “የነጮች” ነው ያሉትን የክርስትና ሥም ለመቃወም ነበር።

ሥም እና ሃይማኖት

መጤ ሃይማኖት ነባር ባሕሎችን ሁሉ ደምስሶ የመተካት አቅሙ ኃያል ነው። ክርስትና እና እስልምና የዓለም ሥም አወጣጥ ቅርፅን የለወጡት በዚሁ ኃይላቸው ነው። በዓለማችን ላይ በብዛት ወንዶች የሚጠሩበት ሥም ‘መሐመድ’ ነው የሚል ነገር ማንበቤ ትዝ ይለኛል። በአገራችን ወላጆች ለልጆቻቸው ሥም ሲያወጡ ወይ አምላካቸውን መጥቀስ ወይም ከቅዱስ ባለታሪኮቻቸው የአንዱን ታሪክ መጥቀስ ይቀናቸዋል። በሱፍቃድ (በእግዜር ፍቃድ)፣ ዋቅጅራ (እግዜር አለ)፣ ገብረእግዚኣብሔር (የእግዜር ሥራ)… ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው።

በቅዱሳን ባለታሪኮች ልጅን መሰየም በተለይ አሁን አሁን ፋሽን እየሆነ መጥቷል። አገር በቀል ሥሞችን ለልጆች ማውጣት ልጆቹን “ፋራ” (ወይም “አራዳ” ያልሆኑ) የሚያሰኝ ይመስላል።

በሌላ በኩል በቀድሞ ጊዜ ለንግሥና ሲባል ሥምን መቀየር የተለመደ ነበር። ብዙ ጊዜ ንግሥናን በጳጳሳት ተቀብቶ ለማፅደቅ ሲባል በክርስትና ሥም መጠራት ደንብ ነበር። (ነገሥታት ራሳቸውን ሥዩመ-እግዚአብሔር ይሉ ነበር። ስለዚህ ንግሥና ፖለቲካዊ ብቻም ሳይሆን ሃይማኖታዊም ነበር) ተፈሪ መኮንን [ቀዳማዊ] ኃይለሥላሴ የተባሉት በዚያ መንገድ ነው። “ቴዎድሮስ የተባለ ንጉሥ እስከ እስራኤል ይገዛል” የተባለውን ትንቢት ወይም ጥንቆላ ተከትሎ ነው ካሣ ኃይሉ ራሳቸውን [ዳግማዊ] ቴዎድሮስ ብለው ያነገሡት። ቀዳማዊ ቴዎድሮስም ሥማቸውን ያገኙት በትንቢቱ መሠረት እሰከ እስራኤል የመግዛት (ካልሆነም ትንቢቱን ሰምተው በሥም የሚግገዙላቸው እንዲያገኙ) ተመኝተው ነው። አውሮጳውያን አፍሪቃዊ ኃያል የክርስቲያን መንግሥት መሥርቷል ብለው በአንዲት ደብዳቤ መነሻ ብዙ ያወሩለት የነበረውን ቄስ ዮሐንስ (Prester John) ለመሆንም ሲባል ነው እስከ አራተኛ የተደረሰው። ዐፄ ዮሓንስ እና የወሎ ሙስሊሞች የገቡበት ቁርሾ መነሻም የዐፄው እንደሥማቸው የማደር ምኞት ይመስለኛል።

ሥም እና ስርዓተ—ፆታ

ሥም ስርዓተ-ፆታን የሚገልፅበት ሁኔታም ቀላል አይደለም። ወንዶች በአማራው ተወላጅ ዘንድ በጥቅሉ ምናባዊ ጀግንነትን የሚያጎናፅፍ ሥም ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ ወንዳፍራሽ፣ ናደው፣ ሺመክት፣ መኩሪያ፣ የመሳሰሉትን ሥሞች መጥቀስ ይቻላል። በኦሮምኛ ሌንጮ (አንበሳው)፣ ኬራንሶ (ነብሩ፣ ደፋሩ)፣ ዋንጎ (ቀበሮው) የሚሉ በኃይለኛ አራዊቶች ሥም ለወንዶች የሚሰጡ ስያሜዎች ጀግንነትን ለወንድ የማልበሱ ማኅበራዊ ትውፊት አካል ናቸው። ጫላ (ቀዳሚው)፣ ሁንዳራ/ኢራና (የበላይ)፣ ኩማራ (ሺመክት) የመሳሰሉትም የተጠቀሰውን ምናባዊ ጀግንነት አልባሽ ኦሮምኛ ስያሜዎች ናቸው። በሲዳምኛ አዳቶ (ደፋሩ)፣ ዳፉርሳ (የማይዳፈሩት) የመሳሰሉት ሥያሜዎች የላይኞቹ ዓይነት ሚና አላቸው። በሌሎቹም ቋንቋ እና ባሕሎች ውስጥ ተመሳሳይ አጠራሮች አሉ።

ለሴቶች ሲሆን ውበታቸውን፣ ወይም በቁስ የሚተመን ዋጋቸውን የሚገልፅ ሥም ይሰጣቸዋል፦ መድፈሪያሽ ወርቅ፣ ሺብሬ፣ ወርቂቱ፣ ብሪቱ፣ ሸጊቱ፣ ቆንጂት…የሴቶች ሥም አወጣጥ ሴቶችን በአትክልትና ፍራፍሬ የሚመስልበትም ጊዜ ቀላል አይደለም፤ አበባ፣ ወይኒቱ፣ ትርንጎ፣ ብርቱኳን፣ ሸዊት (በትግርኛ “እሸት” ማለት ነው) ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። በኦሮምኛ ቢፍቱ (ብሩህ፣ ፀሐይቱ/ጣይቱ)፣ ፋኖሴ (መብራቴ)፣ መጋሌ (ጠይም/ቆንጆ)፣ ዱንጉጄ (ሽንኩርት፣ አጭር ቆንጆ)፣ በከልቻ (ኮኮብ፣ ለዓይነ ቆንጆ) የመሳሰሉት ሥሞችና በሲዳምኛ ዳንቺሌ (ቆንጆ፣ ፀባየ ሸጋ)፣ ደራርቱ (አበባ፣ ፍካት (ኦሮምኛም ነው)) ሴትን በውበቷ የመግለፅ ትውፊታዊ ወግ ያሳያሉ።

ሥም እና የቤተሰብ ታሪክ

ሥም አንዳንዴ የሐዘን መግለጫ ነው። አባቱ (ተፀንሶ እያለ ወይም በልጅነቱ) ወይም ታላቅ ወንድሙ የሞተበት ልጅ ለምሳሌ በአማርኛ ምትኩ፣ ማስረሻ… ይባላል፤ በትግርኛ ካልኣዩ፤… ታላላቆቹ ሲወለዱ እየሞቱ እሱ ግን ያንን መሰናክል ያለፈ ልጅ ለምሳሌ በአኙዋክ ኞም ይባላል፤ በሲዳማ ሪቂዋ ይባላል።

ሥም አወጣጥ ልጁ በተወለደ ጊዜ ወላጆች የነበራቸውን ግንኙነት፣ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ወዘተ የሚናገርበትም ሁኔታ አለ፤ ለምሳሌ አስማማው፣ አስታርቄ… የመሳሰሉት ሥሞች ብዙ ጊዜ የሚወጡት እየተጥጣሉ (በተለይ በልጅ እጦት) የነበሩ ጥንዶች የልጅ መገኘቱን ተከትሎ ሲስማሙ ነው። ወላጆች ልጅ ሲወልዱና የጥሩ ዕድል (በተለይ የሀብት) መምጣት ከተገጣጠመ ልጃቸውን ሀብታሙ፣ ጥጋቡ፣… ብለው ሊሰይሙት ይችላሉ። በተቃራኒው ከገጠማቸው ደግሞ ያንኑ የሚያንፀባርቅ ሥም ይሰጡታል፤ ለምሳሌ ‘በድሉ’ የሚለው ሥም በዕድሉ ይደግ ከሚለው የመጣ ነው፤ ወይም ሳይታቀድ ከመጣ ነው። በኦሮሞ ትውፊት ተጨማሪ ልጅ የማይፈልጉ መሆኑን ለመግለጽ ወላጆች ለ“መጨረሻ” ልጃቸው ጉታ የሚል ሥም ያወጣሉ።

«ሥምህን ንገረኝና ማንነትን እነግርሃለሁ»

የኒው ሳይንቲስት ጋዜጠኛ ጆን ሆይላንድ “nominative determinism” (ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት) የሚለው ነገር አለው። ‘ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት’ የሚወክለው በሥማቸው ተገፍተው ለስያሜያቸው የሚስማማ ሙያ ሲከተሉ ነው። ለምሳሌ በዕውቀቱ ሥዩም ኃይለኛ ቦክሰኛ ቢሆን ኖሮ ሥሙ ከሙያው ጋር አይሰምርም እንል ነበር። በቡጢው ሥዩም ይሆን ነበርና። ስለዚህ የበዕውቀቱ ‘ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት’ ኋላ ቀር የሚለውን ስርዓት (social order) በነውጥ/ነፍጥ ሳይሆን በዕውቀት በመሞገት መንገሥ/መሰየም ነው።

ብዙ መንግሥቱ፣ ንጉሡ የተባሉ ሰዎች መራኄ መንግሥትነት ማዕረግ ሳያገኙ አንድ መንግሥቱ ኃይለማርያም ቦታውን መቆናጠጡ ብቻ መንግሥቱ የተባለ ሰው ሁሉ የመንግሥት ኃላፊ ይሆናል ማለት ባይቻልም ሥማቸው ግብራቸውን ቀድሞ እንዲመራው በማድረጉ ረገድ ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል በሚለው ግን መስማማት እንችላለን፡፡

በአማራው ማኅበረሰብ ዘንድ ‹ደመላሽ› የሚለው ሥም የሚሰጠው “ደም የተቃቡ” ቤተሰቦች መካከል ከአንደኛው ወገን ተበቃይ ባልነበረበት ጊዜ ለተወለደ ልጅ ነው፡፡ የዚህ ልጅ ዕጣፈንታ ባስተዳደግ ይወሰናል፡፡ ሥሙን ያወጡለት ሰዎች ሥሙን ለምን እንዳወጡለት ብቻ ሳይሆን ምን እንዲያደርግላቸው እንደሚፈልጉም ጭምር እያስተማሩት ነው፡፡ ስለሆነም፣ አድጎ “ጠላት” የሚለውን ወገን ለመግደል መሠማራቱ ሰፊ ዕድል ያለው የሕይወቱ ምዕራፍ ነው የሚሆነው፡፡

ሥም እና ማንነት ግንኙነት አላቸው የሚሉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፣ “ሥማችን – ወይም ሰዎች ሥማችንን ሲሰሙ በሚያሳዩት ግብረ-መልስ ወይም የማንነት ግምት ላይ ተመሥርቶ ባሕሪያችንን ይወስናል፡፡” ወደድንም ጠላንም በሥማችን ብቻ ሰዎች ዘውጋዊ ማንነታችንን፣ የቤተሰባችንን ሁኔታ፣ እና ሌሎችም መሠረታዊ ግምቶችን ስለኛ ያሳልፋሉ፡፡ እኛም ይህንኑ ስለምንረዳ የሰዎቹን ግምት ለማጠናከር ወይም ለማስተባበል የበኩላችንን ጥረት በማወቅም፣ ባለማወቅም ማድረጋችን አይቀርም፡፡

ሥም በባለቤቱ ላይ የሚያመጣውን ማንኛወንም ዓይነት ተፅዕኖ ለመቀነስ የተለመደ-ሥም (popular name) መስጠት እንደመፍትሔ ይጠቆማል፡፡ ልጆች በሥማቸው ማንነታቸው እየተገመተ፣ እነሱም በምላሹ በሥማቸው እና ሥማቸውን ሰምተው ሰዎች በሚያሳልፉት ግምት ተፅዕኖ ሥር እየወደቁ ‹የሥማቸው ፍሬ› እንዳይሆኑ ሲባል ለልጆች በሚያድጉበት አካባቢ የተለመደ የሚባለው ዓይነት ሥም ቢሰጣቸው የገዛ ሥማቸው ሰለባ ከመሆን ይድናሉ፡፡ 


እንደ ዋቢ:-
– የነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ ድርሰቶች፣
– Atatürk (biography), by Andrew Mango
– Wax and Gold, by Donald Levine
– ፍቅር እስከ መቃብርን የጻፉት «ሐዲስ» ናቸው ወይስ «ዓለማየሁ»? (የሚከራዩ አማት እና ሌሎች)፣ በዳንኤል ክብረት
– ሉኣላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ፣ በገብሩ አሥራት
– ሥምና ማንነት (ከአሜን ባሻገር)፣ በበዕውቀቱ ሥዩም
– Typology of Oromo Personal Names, by Tesfaye Gudeta Gerba
– እና የተለያዩ ድረገጾች እና ሌሎችም…

‹‹ በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ እየሆነ ያለው በሰራተኞች አንደበት ሲገለጽ››// በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የህዳሴና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን (ከ 2002 እስከ 2007) በአገራችን ሊከናወኑ በዕቅድ ከተያዙ ሜጋ -ፕሮጀክቶች -እንደ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጄክቶች /የህዳሴው ግድብ የለበትም፣በድንገት የተጀመረ ነው/፣ የባቡር ትራንስፖርት መስመር ግንባታ …

በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ እየሆነ ያለው በሰራተኞች አንደበት ሲገለጽ – ኢዮብ ዓለም — Read more »

አህመድ 29 ዓመቱ ነው። ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ፤ ከኬንያ ደግሞ በብራዚል በኩል አድርጎ ወደ ፐሩ ኢኳዶር፤ ኮሎምቢያ፤ ፓናማ ይሸጋገርና በማእከላዊ አሜሪካ ደግሞ ወራት የፈጀውን የኮስታሪካ፤ ኒካራጓ፣ ሆንዱራስ፤ ጓቲማላ፣ ከዚያ በሜክሲኮ በኩል ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ ያደረጉትን ጉዞ ያብራራል።

እነ ዓለማዬሁ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ 60 ሰዓት አለፈ// ቤተሰብ በሄርፒስ ኮርፒስ መብት ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ነው ፡፡ በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጂንካ ፖሊስ ጣቢያ ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ የኦህዲኅ ም/ሰብሳቢ አቶ ዓለማዬሁን ጨምሮ የታሰሩት ሦስት ሰዎች በተጠረጠሩበት ጉዳይ ቃላቸውን ሳሰጡና ፍርድ …

በደቡብ ኦሞ ወደ አመጽ እየተገፋ ያለው- ህዝባዊ እምቢተኝነት Read more »

ሕወሓት ካድሬዎቿን ይዛ ወደ አፋር ክልል ለመስፋፋት ‪#‎ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ‬ ዘመቻ ጀምራለች:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Afar‬ ‪#‎Shihet‬ ‪#‎Tigray‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ሕዝብ ለሕዝብ የሚያናክሰው የሕወሓት የመስፋፋት ፖሊሲ ተከዜን የወልቃይት እና ጠገዴን ምድር ከነሕዝቡ ወደ ትግራይ በማካለል በአከባቢው ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ እንዲነሳ …

ሕወሓት ካድሬዎቿን ይዛ ወደ አፋር ክልል ለመስፋፋት ‪#‎ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ‬ ዘመቻ ጀምራለች:: Read more »

ማኅበረ ቅዱሳን “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ለ 1 ሳምንት ለማሳየት ያዘጋጀው ዐውደ ርእይ ለዕይታ ለመቅረብ ሰዓታት ሲቀሩት “ባልታወቀ አካል” ቀጭን ትዕዛዝ መታገዱን በዘመኑ ፈጣን የመገናኛ መንገዶች ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው ዓለም …

ማንንም የማይፈራው እውሩ መንግሥታችን!!! (ዲባባ ዘለቀ) Read more »

በሕመምተኛ ልጁ ሕክምና ስም በርካታ አጥቢያዎች በ፻ሺሕዎች እያወጡ በሰጡበት ኹኔታ፥ “እኔ ሳላውቅ ስሜን ለማስጠፋት የተሠራ ነው” በሚል ምዝበራውን ለማስተባበል እየጣረ ነው ግማሽ ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው የተወሰነበት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት አስተዳደር ኮሚቴ ውሳኔ ቃለ ጉባኤ፣ በአስተዳደራዊ ውሳኔ ተሽሮ ውሳኔውን በሚያስተባብል ሌላ ቃለ …

ፓትርያርኩ: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስን “ቀንደኛ ሌባ” አሉት Read more »

የመሃል አገሩ ዝምታ እስከመቼ ነው ? – የህዝብ ማእበል = የትጥቅ ትግል = ካልደፈረሰ አይጠራም !!! ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎Ethiopianoppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ኢሕአዴግ ሃብትና ሥልጣንን ለሕዝብ አያጋራም። ሁሌም የበላይ ሆኖ ሌሎችን መምራትና መቆጣጠር ብቻ ነው የሚፈልገው። ሌሎቹ እሱን እንዲያጅቡት ነው እቅዱ። ለሚቀጥሉት …

የመሃል አገሩ ዝምታ እስከመቼ ነው ? – የህዝብ ማእበል = የትጥቅ ትግል = ካልደፈረሰ አይጠራም !!! Read more »

ለኦሮሞ ህዝብ ከዚህ የሚበልጥ አጀንዳ የለም!! ከ18 የኦሮሚያ ዞኖች 14ቱ ዞኖች በ2009 ዓ.ም. ዩኒቨርሲቲ የሚገባ ተማሪ የለም ማለት ነው። ኦሮሚያ ውስጥ 18 ዞኖቹ አሉ። እስካሁን ባለው መረጃ ከ18ቱ ዞኖች የመማር ማስተማር ሂደት ያልተቋረጠው በ4 ዞኖች ብቻ ነው። ትምህርት ሙሉ በሙሉ …

ከ18 የኦሮሚያ ዞኖች 14ቱ ዞኖች በ2009 ዓ.ም. ዩኒቨርሲቲ የሚገባ ተማሪ የለም ማለት ነው። Read more »

<<የነፃነት ትግላችን ዋነኛ ምሰሶ ለነፃነታችን በፈቃደኝነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችን ነው።>>  ማዲባ “Long walk to Freedom” (Natnail Feleke= Zone 9 ) አንዳንዴ <<ተስፋ>> ጠላታችን ይሆናል። ነገሮች እንደሚሻሻሉ ወይንም ከዚህ የባሰ እንዳይከፉ እያልን በተስፋ እየተታለልን ማድረግ የሚገባንን ሳናደርግ ወደን ሳይሆን ተገደን እንከፍላለን። …

የነፃነት ትግላችን ዋነኛ ምሰሶ ለነፃነታችን በፈቃደኝነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችን ነው። ማዲባ (Natnail Feleke) Read more »

የሰማያዊ ፓርቲ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሊቀመንበሩን ኢንጂነር ይልቃልን እና አቶ ወረታውን አባረርኩ አለ:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Blueparty‬ @Semayawiparty ‪#‎MinilikSalsawi‬   Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ጠንካራ ፓርቲዎችን ሰርጎ ገብ አስገብቶ በመበታተን ጠንካራ አመራሮችን በመወንጀል ፓርቲዎችን አዳክሞ ብመቃብራቸው ላይ ተለጣፊ ታማኝ ተቃዋሚዎችን የሚተክለው …

የሰማያዊ ፓርቲ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሊቀመንበሩን ኢንጂነር ይልቃልን እና አቶ ወረታውን አባረርኩ አለ:: Read more »

የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ እና ህዝበ ሙስሊሙ በፊርማው ጥያቄዬን በሰላማዊ መንገድ ያቀርቡልኛል ያላቸን ኮሚቴዎችንን አሸባሪ በማለት የሚዎነጅለው ጀሀዳዊ ሀረካት የተሰኘውን ዶክመንተሪ ፊልምን ያዘጋጀው የወያኔ ለጋሲ አስቀጣይ የሆነው ብርሀኔ ንጉሴ የተባለው ግለሰብ አዲስ የሰራው ቤዛ የተሰኘ ፊልም በማህበራዊ ሚዲያ ፊልሙን እንዳታዩ የሚል …

የጀሀዳዊ ሀረካት ዶክመንተሪ አዘጋጅ የተሰራው አዲስ ቤዛ የተሰኘ ፊልም ላይ በማህበራዊ ሚዲያ የቦይኮት ዘመቻ ተካሄደበት:: Read more »

የሕወሓት የመስፋፋት እቅድ የወለደው የእርስ በእርስ ጦርነት በተክል ድንጋይ ፈንድቷል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AmharaProtests‬ ‪#‎Qimant‬ ‪#‎TekilDingay‬ ‪#‎Gonder‬ ‪#‎TPLF‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከትላንትና ጠዋት ጀምሮ የሚደርሱ መረጃዎችን ተከትሎ ለማረጋገጥ እንደተቻለው የሕወሓት የመስፋፋት ፖሊሲ እና ታላቋን ትግራይ የመመስረት አላማውን ለማሳካት ሲል የሚሰራቸው …

የሕወሓት የመስፋፋት እቅድ የወለደው የእርስ በእርስ ጦርነት በተክል ድንጋይ ፈንድቷል:: Read more »

በአሁኑ ወቅት ከቃሊቲ የማጎሪያ ካምፕ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በኦሮሞ ልጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እየደረሰ ሲሆን ስም ዝርዝራቸውን እና የተፈረደባቸው ጊዜ እንደሚከተለው ነው::ቀሪ መረጃዎች እና ስሞች ያሏቹህ ከታች አስፍሩበት::   1. Masfiin Ittaanaa Fufaa……………………………….Umrii guutuu 2. Charinnet Yamanee………………………………… Umrii guutuu …

ቃሊቲ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የኦሮሞ ወገኖቻችን ስቃይ ቀጥሏል::(ስም ዝርዝራቸውን ይመልከቱ) Read more »

መግቢያ እንደምንከታተለው የአብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮች፣ በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች እጣ፣ እንደህብረተሰብና እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። አብዛኛዎች አገዛዞችና መሪዎቻቸው የአገርና የህዝቦቻቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው አይመስልም። የፖለቲካ አርቆ-አስተዋይነት የጎደላቸውና፣ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነት የማይሰማቸው መሪዎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን …

ነፃነት፣ ዲሞክራሲ ፣ የብሄረሰብ ጥያቄና የኢኮኖሚ ዕድገት ! -እንዴትና ለማን እንዲሁም ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ዕድገት፟ ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) Read more »

በሀገሪቱ አሁን የተከሰተው የረሀብ አደጋ በህዝብ ቁጥርና ስፋት በታሪክ ተወዳዳሪ የለውም። አሁን የተረጂዎች ቁጥር 20 ሚሊየን ደርሷል። ለመሆኑ ረሀቡን በተመለከተ የመንግስት ምላሽ፣ የለጋሾች አቋምና በአጠቃላይ ለችግሩ የተሰጠው ትኩረት አደጋውን የሚመጥን አይመስልም። በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን አሰባስበን ውይይት አድርገንባቸዋል። አድምጡት ተወያዩበት …

በነገራችን ላይ- ኢህአዴግና ሀያ ሚሊየኖቹ ! Wazema Radio Read more »

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ኢዴፓን ጨምሮ ስምንት ፓርቲዎች አባል ከሆኑበት አገር አቀፍ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት ጋር ሰሞኑን ተወያይተዋል። አዲስ አበባ — VOA — ተመጣጣኝ የዉክልና ሥርዓት በሚባለዉ የፓርላማ ምርጫ ሥርዓት ላይ ዉይይት እንዲደረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ …

ተመጣጣኝ የዉክልና ምርጫ ሥርዓት ዉይይት እንዲደረግ ይሁንታ አለ ተባለ (VOA) Read more »

ረሃብ ጊዜ አይሰጥም::ለቻይና እና ቱርክ ሸቀጦች ቅድሚያ እንዲራገፉ በማድረግ በረሃብ አለንጋ ዜጎቹን በመግረፍ የሚገድል አገዛዝ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiopiafamine‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በምግብ እሕል ራሳችንን ችለናል እየተባለ ከውጭ አገራት 450 ሺህ ሜትሪክ ቶን የእርዳታ ስንዴ በውጪ ሃይሎች ድጋፍ መግዛት …

ረሃብ ጊዜ አይሰጥም::ለቻይና እና ቱርክ ሸቀጦች ቅድሚያ እንዲራገፉ በማድረግ በረሃብ አለንጋ ዜጎቹን በመግረፍ የሚገድል አገዛዝ Read more »

 Addis Admass : ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው ነው፡፡ እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ፡፡ አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማህረሰብ፤ ሀገር ግን …

‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ! (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ) Read more »

በደቡብ ኦሞ የእነ አቶ ዓለማዬሁ እስራት ‹‹ ከአርበኞች ግንቦት 7 ›› ጋር የተያያዘ ነው// ‹‹ አይ ፍርሃት– ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ሲያንከራትት›› ከሰዐት በፊት ባቀረብነው መረጃ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበር አቶ ዓለማዬሁ መኮንን፣ አንድ ጠንካራ አባልና አንድ የከተማው ነዋሪ …

በደቡብ ኦሞ የእነ አቶ ዓለማዬሁ እስራት ‹‹ ከአርበኞች ግንቦት 7 ›› ጋር ግንኑነት አላቸው በሚል ጥርጣሬ ነው:: Read more »

በደቡብ ኦሞ የኦህዲኅ መሪ አቶ ዓለማዬሁ መኮንንና አንድ ጠንካራ አባል ታሰሩ// • አሸባሪነትን ለህዝብ ማሸበር መጠቀም // • ከማለዳው 12፡00 ጀምሮ እስከ ረፋዱ 4፡20 ቤታቸው ሲበረበር አርፍዷል፤ • በዕለት ሁኔታ መዝገብ ሳንመዘገብ አንታሰርም ብለው እየተከራከሩ ነው፤ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት …

በደቡብ ኦሞ የኦህዲኅ መሪ አቶ ዓለማዬሁ መኮንንና አንድ ጠንካራ አባል ታሰሩ Read more »

የባጃጅ ኣድማ 4ተኛ ቀኑ ይዟል ============= መቐለ ከተማ እየተደረገ ያለው የባጃጅ ኣድማ 4ተኛ ቀኑ ይዘዋል። Bajaj Protests መንግስት “ከ300 በላይ ባጃጆች ላጠፉት ጥፋት 500 ብር እየተቀጡ የይቅርታ ደብዳቤ ኣስተስገብተው ታፔላ እየወሰዱ ነው” በኤፍ ኤም ራዲዮዎች ቢናገም በተግባር ግን ኣድማው ተጠናክሮ …

መቐለ ከተማ እየተደረገ ያለው የባጃጅ ኣድማ 4ተኛ ቀኑ ይዘዋል። Read more »

ዶክተር መረራ በዚህ ቅዳሜና እሁድ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ የሚካሄድ ”Vision Ethiopia”  የተባለ ሲቪል ማህበረሰቦችና የፓለቲካ ድርጅቶች ጉባኤ ላይ ንግግር ሊያደርጉ ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሊመጡ ነበር።

ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት ( ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)   ‹የክርስቶስ አንዲት በግ መከራን ስትቀበል ከማይ እኔ የበጉ እረኛ መከራ መቀበልን እመርጣለሁ› ይህንን የተናገረው ዮሐንስ አፈወርቅ ነበር፡፡ የቁስጥንጥንያዋ ንግሥት አውዶቅስያ የአንዲት ክርስቲያን ምእመንን መሬት ወስዳ ባሰቃየቻት ጊዜ ለተግሣጽ የተናገረው …

ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት ( ዲያቆን ዳንኤል ክብረት) Read more »

ይህን የመለስን ፋውንዴሽን መዘጋት በሚመለከት “ዜና ላድርገው ወይንስ መጣጥፍ?” ብዬ ብዙ ተጨነቅሁ፡፡ ዜናም ላድርገው መጣጥፍ መቼም እስካሁን የቀደመኝ እንደማይኖር ተስፋ አለኝ፡፡ ወደሰበር ዜናው ላምራ፡፡ የሕዝብ ዋይታ የፈጠረው ዕንባና ያፈሰሰው የንጹሓን ደም ፈጣሪ ዘንድ ጮኸው ባመጡት የጸሎት መልስ ለገሠ ዜናዊ – …

የመለስ ፋውንዴሽን ተዘጋ! (ነፃነት ዘለቀ ነኝ ከአዲስ አበባ) Read more »

ፍትህ ሚኒስቴር ሊፈርስ ነው አሉ….. ‘’የባልሽ ቂጣ እንክትክቱ ይውጣ….’’ ብዬዋለሁ። እስከዛሬም ስሙ ከብዶት አለመውደቁ ምን ያህል ይሉኝታ ቢስ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ሌላው ፌደራል ፖሊስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እዝ ስር ሊሆን ነው። (ወይ ጠቅላይ ሚኒስትር… !) እርሳቸውም አንድ ቀን ይሄ ስም ከብዷቸው …

ፍትህ ሚኒስቴር ሊፈርስ ነው አሉ….. (አቤ ቶኪቻው) Read more »

በሃገራችን ለተከሰቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች የኢሕኣዴግ የፖሊሲ ክምር በፍጹም መፍትሄ አይሆንም:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Ethiopiaprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሃላፊነት የጎደለው የወያኔ አገዛዝ ወንጀል ብንናገረው ብንናገረው ተዘርዝሮ አያልቅም::እየሰራን ነው እያለማን ነው በሚል የልማታዊ ዲሞክራሲ ሽፋን ላለፉት 25 …

በሃገራችን ለተከሰቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች የኢሕኣዴግ የፖሊሲ ክምር በፍጹም መፍትሄ አይሆንም:: ‪ Read more »

ኢሳት ዜና :-ድርቁ በተለየ መልኩ በከፋባቸው እንደ ሶማሌና አፋር ባሉ ክልሎች ሁኔታውን ተዘዋውረው የተመለከቱ የረድኤት ሰራተኞች ለኢሳት እንደተናገሩት ፤ በተጠቀሱት ክልሎች ባሉ የማገገሚያ ጣቢያዎች ከመክሳታቸው ብዛት ቆዳቸው አጥንታቸው ጋር የተጣበቀና ጭንቅላቶቻቸው ብቻ የቀሩ ህጻናት በሞት ቋፍ ላይ ሆነው እያጣጣሩ ይታያሉ። …

በረሀብ ሳቢያ ህጻናት እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ እንደሚገኙ የረድኤት ሰራተኞች ለኢሳት ተናገሩ:: Read more »

በገዛ ፍዳቸው ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ ሀብቴ ፊቻላ በሁለት ወራት ልዩነት ውስጥ የፌዴራል ፍ/ቤቶችን ከለቀቁ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አራተኛው ሆነዋል። ባለፈው የካቲት ወር የመጀመሪያ ሳምንት የጤና እክል ገጥሞኛል በሚል በገዛ ፈቃዳቸው ከሀላፊነታቸው የለቀቁት የፌዴራል ጠ/ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት እና የህገመንግስት አጣሪ ጉባኤ …

የፌዴራል ፍ/ቤቶችን ከለቀቁ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አራተኛው ከሀላፊነታቸው ለቀቁ :: Read more »

ሠማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። የሚባረሩ ፖለቲከኞች ተለይተው ታውቀዋል (ኤርሚያስ ቶኩማ‬) ሠማያዊ ፓርቲ በሃገራችን ሠላማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ተስፋ ከተጣለባቸው ፓርቲዎች ውስጥ በእድሜ አጭር ቢሆንም በውስጡ በያዛቸው ጠንካራ አባላቱ የተነሳ ለአመታት ተኝቶ የነበረውን የሰላማዊ ትግል ከሞተበት አንስቶ መልካም የሚባል በወሬ …

ሠማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። የሚባረሩ ፖለቲከኞች ተለይተው ታውቀዋል (ኤርሚያስ ቶኩማ‬) Read more »

ከወራት በፊት100 በመቶ / 100 %/ መረጠኝ ያሉት ህዝብ ለሚያሰማው ተቃውሞ እንደምን ጥይት መልስ ሊሆን ይችላል ? ይቅርታ ያሉበትን ጥፋት አጠናክረው፣ የጥፋት ጎዳናውን አስፍተው እየተጓዙ እንደምን በህዝብ አመኔታ ማግኘት ወይም መጠበቅ ይቻላል ? አብሮኣቸው ሲያቦኩ የነበሩ ባለስልጣናትን ማባረር እንደምን ለህዝብ …

አይቻልም !!! ከ25 ዓመታት በኋላም …ለማታለልና ለማጭበርበር ? Girma Bekele Read more »

«የዶክተር» ገላውዲዮስ አርኣያ አይን ያወጣ ውሸት! (Achamyeleh Tamiru) ኒዮርክ ውስጥ «ታሪክ» የሚያስተምሩት የትግራይ ብሔርተኛው «የታሪክ ዶክተር» ገላውዲዮስ አርኣያ፤ ትናንትና በአሜሪካ ድምጽ ትግርኛ ክልፍ ቀርበው «በታሪክ ወልቃይት የትግራይ እንደነበር» ሲያስረዱ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በElizabel Filleul በፖርቹጋል ቋንቋ የተጻፈውን «Tractatus tres …

«የዶክተር» ገላውዲዮስ አርኣያ አይን ያወጣ ውሸት! (Achamyeleh Tamiru) Read more »

ወልቃይት ጠገዴ የዛሬ ውሎ (መጋቢት 15 ቀን 2008) By Muluken tesfaw ከ400 በላይ የሚሆኑ የዳንሻ እናቶች ልጆቻችንና ባሎቻችን መልሱ ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ፡፡ የትግራይ ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በጠመንጃ ከበባቸው፡፡ የወልቃይት እናቶች ጣሊያን ላይ እንዳደረጉት ሁሉ በርበሬ እየበጠበጡ በዐይናቸው ላይ ደፉባቸው፡፡ …

የወልቃይት ጠገዴ እናቶች የሕወሓትን ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በበርበሬ ብጥብጥ መማረክ ችለዋል፡፡ Read more »

ዶክተር መረራ ጉዲና ከሃገር እንዳይወጡ ተከለከሉ:: የወያኔ አገዛዝ ትላንትና ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ አሜሪካ ለመብረር በዝግጅት ላይ የነበሩትን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲናን ከሃገር እንዳይወጡ ማገዱን የድርጅቱ የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል:: አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ “ቪዥን ኢትዮጵያ” (ራዕይ ኢትዮጵያ) በተሰኘ …

ዶክተር መረራ ጉዲና ከሃገር እንዳይወጡ ተከለከሉ:: Read more »

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ መሬቶችን በእጅ አዙር ለመግዛት ሕወሓት ደላሎችን ሊያሰማራ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterplan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሕወሓት ስልጣኑን እና ጠበንጃን መከታ በማድረግ ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ አከባቢዎች ገበሬዎችን በማፈናቀል እጅግ በርካታ ዜጎችን ለችግር የዳረገ ሲሁን ይህን …

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ መሬቶችን በእጅ አዙር ለመግዛት ሕወሓት ደላሎችን ሊያሰማራ ነው:: Read more »

ሰላም ወዲ ተስፋይ ( ሄኖክ የሺጥላ ) ስለዚ’ች ልጅ ትንሽ ኣውቃለሁ ። ቤተሰቦቿ የኣዜብ መስፍን የቅርብ ዘመዶች ናቸው ። ራሷ ኣርቲስቷ ኣዜብ መስፍን ተወልዳ ካደገችበት ኣካባቢ ተወልዳ ያደገች ልጅ ነች ። የመለስ ዜናዊ ልጅ (የሰመሃል መለስ ) የቅርብ ጓደኛ ስለመሆኗም …

ሰላም ወዲ ተስፋይ ( ሄኖክ የሺጥላ ) BOYCOTT BEZA FILM Read more »

ኤግዚቢሽን ማዕከሉ፣ ማኅበሩ ከአዲስ አበባ አስተዳደር የፈቃድ ደብዳቤ እንዲያጽፍ ጠይቋል በማዕከሉ ኤግዚቢሽን የሚያዘጋጁ አካላት፥ ፈቃድ የሚያቀርቡት ዕውቅና ካገኙበት ተቋም ነው ማኅበሩ ከማዕከሉ ጋር የፈጸመው ውል በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ደብዳቤ የተደገፈ ነው ያለሰዓቱ የተጠየቀው ፈቃድ፥ በማዕከሉ አሠራር ያልተለመደና በአ/አ አስተዳደርም …

የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ መክፈቻ ጊዜ ባልተለመደ ሕገ ወጥ አሠራር እክል ገጠመው፤ መርሐ ግብሩን በዕቅዱ ለማስቀጠል ጥረቱ ቀጥሏል Read more »

ይግባኝ የተጠየቀባቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መጋቢት 20 ለብይን ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባሉ ★★★★ በእነ ሶሊያና ሽመልስ መዝገብ ህብረተሰብን አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሳችኋል በመባል በፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ 4 ክስ ከተመሰረተብን ሰባት የዞን 9 ጦማሪያን እና ሶስት ጋዜጠኞች ውስጥ የአምስቱ ክስ ተቋርጦ፣ …

ይግባኝ የተጠየቀባቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መጋቢት 20 ለብይን ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባሉ Read more »

በትግራይ መዲና መቐለ የባለ ባጃጆች ኣድማ ቀጥለዋል:: #Mekelle ትናንት ዕሮብ መጋቢት14 /08 ዓ/ም በትግራይ መዲና መቐለ የባለ ባጃጆች ኣድማ ተመትቶ ውለዋል። መንግስት ኣድማው በሃይል ለማንበርከክ ያለ ታፔላና ያለ ስምሪት ቦታ ለመስራት የሞከሩ ባለ ባጃጆች በክልሉ ልዩ ሃይል፣ የፖሊስ ና ትራፊክ …

በትግራይ መዲና መቐለ የባለ ባጃጆች ኣድማ ቀጥለዋል:: Read more »

በክልሉ ከተካሄደዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ጋር በተያያዘ ሃላፊነታቸዉን በአግባቡ አልተወጡም በተባሉ አመራሮች ላይ የሚወሰደዉ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ርእሰ መስተዳደሩ አቶ እሼቱ ደሴ ተናግረዋል። አዲስ አበባ — በኦሮሚያ ክልል ከሚካሄደዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸዉ የተነሱ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት ቁጥር 300 …

በኦሮሚያ 300 የሚሆኑ ባለሥልጣናት ከሥራ ተባረሩ (VOA) Read more »

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (March 23, 2016 NEWS) ‪#‎የዳንሻ‬ ከተማ በትግራይ ሚሺያዎችና በወያኔ ጦር ስትወረር ሕዝቡም የመኪና መንግደኦችን በመዝጋት ወደ ጎንደርና ሁመራ የሚወስዱ መንገዶችን የዘጋ ሲሆን የታስሩት የሕዝብ ወኪሎች እንዲፈቱ …

የወያኔ‬ መሪዎች ጦራቸውን ወደ ኮንሶ በመላክ ከተማዋን በወታደራዊ ቁጥጥር ስር አድርገዋል። Read more »

  ክቡር ሚኒስትሩ ኮንትሮባድ ያስገቡት እቃዎች ኬላ ላይ መያዛቸው ተሰምቷል:: [ክቡር ሚኒስትሩ የሚያስገቡት ዕቃ ኬላ ላይ ተይዞባቸዋል፡፡ ሚስታቸው ደወሉላቸው] –    ሰላም ዋልሽ? –    ምን ሰላም አለ? –    ምን ሆንሽ ደግሞ? –    ምን የማልሆነው ነገር አለ? –    ጠዋት ሰላም አልነበርሽ እንዴ? …

ክቡር ሚኒስትሩ ኮንትሮባድ ያስገቡት እቃዎች ኬላ ላይ መያዛቸው ተሰምቷል:: Read more »

መፍረስ ያለበት የፍትሕ ሚኒስቴር ሳይሆን ሕወሓት የሚባለው ገዳይ ድርጅት ነው:: ምንሊክ ሳልሳዊ – ከነሰው በላዎቹ ከነአዘናጊዎቹ ከነገዳዮቹ መንደር የሚመጡ የጊዜ መግዣ እና ማጭበርበሪያ ዘገባዎች አሁንም አልቆሙም:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለምንም የፖለቲካ ድርጅት ይሁን አስተባባሪ ተቋም መሪነት በራሱ ስለመብቱ እና ነጻነቱ አደባባይ …

መፍረስ ያለበት የፍትሕ ሚኒስቴር ሳይሆን ሕወሓት የሚባለው ገዳይ ድርጅት ነው:: Read more »

ዋሊያዎቹ ከብዙ መንገላታት በኋላ አልጀርስ ገቡ! ዋሊያዎቹ ከብዙ መንገላታት በኋላ አልጀርስ ገቡ!   ዘገባ – ናታ   በጋቦን አስተናጋጅነት ለሚካሔደው የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ “J” ከአልጄሪያ፣ ሌሴቶ እና ሲሺየልስ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አልጀርስ አቅንቷል። ሁለቱ ቡድኖች ቀዳሚውን …

ዋሊያዎቹ ከብዙ መንገላታት በኋላ አልጀርስ ገቡ! (ኢትዮ አዲስ ስፖርት) በአልጀሪያ ሆቴልና ማረፊያ ስላልተዘጋጀላቸው መንገላታታቸው ተዘግቧል። Read more »

ሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በእርስ በእርስ ጦርነት ልትታመስ ነው::የወልቃይት ሕዝብ ዱር ቤቴ ብሏል:: #MinilikSalsawi Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል መካከል ያለውን ድንበር የሕወሓት አምባገነን አገዛዝ ዘልቆ በመግባት ወደ ትግራይ ክልል በሃይል በማካለሉ የመጠ የወልቃይት …

ሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በእርስ በእርስ ጦርነት ልትታመስ ነው::የወልቃይት ሕዝብ ዱር ቤቴ ብሏል:: Read more »

ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ዲቃላውን ብኣዴንን እየወነጀለ ነው:: ሰሜን ጎንደር ውጥረቱ ከሯል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Dinsha‬ ‪#‎Welkaite‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብሎ ራሱን የሚጠራው እና ታላቋን ትግራይ በመስፋፋት ካልመሰረትኩ ነጻ አውጪ የሚለውን ስሜን አልቀይርም …

ሰሜን ጎንደር ውጥረቱ ከሯል:: ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ዲቃላውን ብኣዴንን እየወነጀለ ነው:: Read more »

News #Ethiopia Wetatoch Dimts  #MinilikSalsawi መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=iz0ffmO48VY]