ሕወሓት ካድሬዎቿን ይዛ ወደ አፋር ክልል ለመስፋፋት ‪#‎ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ‬ ዘመቻ ጀምራለች::

ሕወሓት ካድሬዎቿን ይዛ ወደ አፋር ክልል ለመስፋፋት ‪#‎ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ‬ ዘመቻ ጀምራለች:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Afar‬ ‪#‎Shihet‬ ‪#‎Tigray‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ሕዝብ ለሕዝብ የሚያናክሰው የሕወሓት የመስፋፋት ፖሊሲ ተከዜን የወልቃይት እና ጠገዴን ምድር ከነሕዝቡ ወደ ትግራይ በማካለል በአከባቢው ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ እንዲነሳ ያደረገ ሲሆን ቀውሱ እየተባባሰ ሕዝቡ መሳሪያውን እንደታጠቀ በዱር ሲገኝ በሽምግልና ለማዘናጋት እና ጊዜ ለመግዛት ሽምግልና አልቀመጥም ሲሉ በግዳጅ በዛቻ የሽምግልናው መሪ የሆኑት አንድ ጳጳስ ጨምሮ የተደረገው ሙከራ እንደተንጠለጠለ ይገኛል::#ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ የሚለው ዘመቻ የአፋር ክልል ወረዳዎችን በሙሉ ከጥንት ጀምሮ የትግራይ መሬዎች ናቸው የሚል እደምታ ይዞ ተጀምሯል::

እንዲሁም በቅማንት ሕዝብ አከባቢ እየተደረገ ያለው ሕዝብን የማጨፋጨፍ እና የመጨፍጨፍ ስራ በተክል ድንጋይ እንዲፈነዳ የተደረገ ሲሆን የውልቃይት ሕዝብን ጥያቄ ለማድበስበስ እና ለጊዜ መግዣ የሚደረጉ ሕወሓታዊ ተኮሎች ቀጥለዋል::አስተዳደራዊ ጉዳዩን መቀሌ እየመጣ እንዲያስፈጽም እየተደረገ ያለው የቅማንት ሕዝብን ወደ ትግራይ ጠቅልሎ እስከ ጎንደር መግቢያ ድረስ ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት እስካሁን ሊሳካ አልቻልም::ለዚህ ስራ የሚረዱ የሕወሓት ሚሊሻዎች እና የጦር መሳሪያዎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተንጠባጠቡ በአከባቢው ሰፍረዋል::ሕዝቡን ይህንን በማወቁ መሳሪያውን ወልውሎ በተግባር እየተንቀስቀሰ ለሕወሓት ጦር የእግር እሳት ሆኖበታል::

ይህንን የአማራ ክልልን ሰነጣጥቆ የራሱን ግዛት ለማስፋፋት የሚመኘው የሕወሓት አገዛዝ የሱዳን ድንበርን ይዞ ከኩምሩክ ጀምሮ እስከ ሁመራ ድረስ የጉምዝ ተወላጆችን እና የሕወሓት ሚሊሻዎችን በማስፈር አስፈላጊውን እየሰራ ሲገኝ በአፋር ክልል ደግሞ ለመስፋፋት ያለውን እቅድ ለማሳካት #ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ የሚል አዲስ ዘመቻ በካድሬዎቹ እና በአሽቃባጭ ዘረኛ አማሳኞቹ በኩል ዘመቻ መጀመሩን ታውቋል::ይሕው ዘመቻ ተያይዞ የአፋር ክልል ሕዝብን አሳዶ ግዛቱን በማስፋፋት አከባቢዎቹን ከትግራይ ክልል ጋር ለመቀላቀል ነው::ይህ ‪#‎ሽኸት‬ የተባለ ቦታ ከጥንት ጀምሮ የትግራይ መሬት ነው ለስራ ጉዳይ አፋር ክልል የገቡ መሬትች ስለሚገኙ ከትግራይ ካልተቀላቀለ በትግሪኛ ትምሕርት ካልተሰጠ አፋርና አከባቢው ላይ መነገር ካልቆመ ለትግራይ ትልቅ ችግር አለ በማለት ሕወሓት እና ካድሬዎቹ እያራገቡ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

15 Comments on “ሕወሓት ካድሬዎቿን ይዛ ወደ አፋር ክልል ለመስፋፋት ‪#‎ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ‬ ዘመቻ ጀምራለች::”

  1. woyanien megdel new melkam.
    Yegedele jegna kbru aynekam.
    woyanien mefrat.
    Muto megñet.
    Mta aferarsew ye woyanien Tor.
    Lehzb alwegene alTeqem ager.
    Menoru trgum alba new.
    Ager sayhon woyanien Tebaqiw.

  2. እነዚህ የሱዳን ውሽሞች የሚሰራቸውን አሳጣቸው እኮ። ዋ! ይቺ አላርፍ ያለች ————!!!

  3. አምሃራው እርሳህን ዘርህን ለማዳን አገር አልባም ላለመሆን ወገኖችህን ለመርዳት በያለህበት መረጃ በመቀባበል ባገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለህ የዘር ማዳን ዘመቻ እና እርዳታ ማድረግ አለብህ አምሃራነኝ የምትል ሁሉ ተደራጅ እነዚህ ጠላቶችህን አንተን ለማጥፋት መስለው ስለሚገቡ እንደነሱ እየሰለይክ መንቅረህ ከመሃልህ አውጣ ለምን ለማጥፋትም አብረው እየበሉ እየጠጡ ስለሚገሉ አረመኒዎች ስለሆኑ አንተ የክርስቲያን ዘር ነህ ከነ ስምህ አምሃራ ክርስቲያን ነው ምክንያቱም በክርስትና ሃይማኖት የሰው ልጅ ሁሉም አንድ ነው ክርስትና ሃይማኖት ፍቅር ነው ስለዚህ ክርስቲያን በመሆንህ ነው አይሲስ ወያኒ ትግሪ ሊያጠፋህ የተነሳው ለኢትዮፒያዊነቱ የሚታገል ወገንህን ሁሉ እርዳ ደግፍ ግን አንተ እራስህ ካልኖርክ ለማንም አትሆንም የኢትዮፒያ ነገዶችንም መርዳት አትችልም 25 አመት በግልጽ አምሃራ እና ኦርቶዶክስ ጠላት ተብሎ ተፈርጆ አገር ማፍረሻ ፖለቲካ ባንተላይ ተሰርታል በዘርፈ ብዙ ታክቲክ አምሃራ እንዲጠፋ ተደርጋል ኢትዮፒያን የምትወድ ከሆነ መጀመሪያ እራስህን አድን በየ አገሩ ያላችሁ የተማራችሁ የአምሃራ ነገዶች ለወገን መድረስ መቻል አለባችሁ እንዲሁም የተቀርው ማህበረሰብ አምሃራ ነው የምትለውን ሁሉ እያካካህ መቀስቀስ አለብህ በየ አገሩ እየተደራጃችሁ ታማኝ የሆኑ የዘር አድን ድርጅቶችን እንደ ሞረሽ ወገኒ ያሉትን መርዳት አለብን:: በኢትዮፒያዊነታቸው የሚያምኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮፒያን ለኢትዮፒያኖች እኩል አገር የሚያደርጉ ሃይሎች በአምሃራው ነገድ ላይ 100% ኢትዮፒያዊነት እንጂ ሊላ ጥርጣሪ እንዳይኖራቸው ማሳመን ለዚህም ዋነኛው ከፖለቲካ ነጻ የሆነና የአምሃራን ዘር አድን ድርጅት እንደሆነ ማሳወቅ ምክንያቱም ወያኒ ወረራውን እያካሂደ ዘር ለማጥፋት እና ግዛቱን ለማስፋት አምሃራው ክፍል በጎንደር እና በወሎ ስለሚያዋስነው ኢትዮፒያንም በመንግስት ደረጃ በፋሺስት ሲስተም እየገዛ ስለሆነ ለምን ግዛት ታሰፋለህ ብሎ ጠያቂ እንዳይኖር በዘር ከፋፍሎ አንዱ ላንዱ እንዳይነሳ አገራዊ አንድነት ፖለቲካ እንዳይኖር ያደረገው ለዚህም ነው ስለዚህ አምሃራውንም ሆነ አፋሩንም ድበር እየጣሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ወረራ ሲያካሂድ ዘር ሲያጠፋ ብቸኛው ጉለብተኛ ሆኖ ፈላጭ ቆራጭ ያለምንም ተጠያቂነት አገሪቱን ነጻ የሆነች ትግራይን ለማቆም የሚችልበትን ታክቲክ ህወሃት በራሱ ሚስጥር ብቻ ስለሚያስፈጽም የሚጠቀምባቸው ኢሃድጎችም እንዲያውቁ የሚደረግበት ነገር የለም ቢያውቁም ስለራሳቸው ክልል እንካን ወሳኞቹ እንዳልሆኑ ታይታል:: ኢትዮፒያን የሚፈልግ ሁሉ ይህን ሲራ በያለበት መዋጋት አለበት በቃ! በቃ!

  4. እስከ ዓሰብ፣
    የወያኔ ሰዎች ይህንን ያህል ድረስ ተጨንቀው ኢትዮጵያን የወደብ ባለቤት ያደርጓታል የሚለውን እስኪ ዘርዘር አድርገን እንየው። ምክንያቱም የዓሰብ ወደብ የኢትዮጵያ የባለቤትነትን በተለያዬ ጊዜ የተቃወሙት የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ ጀምር ያሁኑም ጭምር ያለ ምንም ማወላወል ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው እየታወቀ አሁን ለትግራይ ሲሆን በየትኛው አገባብ ነው እውን ሊሆን የታሰበው።
    በዶክተር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም የተጻፈውን ዓሰብ የማን ናት የሚለውን መጽሐፍ ላነበበ ሰው፣ ወያኔ ሆነ ብሎ ኢትዮጵያ የራሷን የሆነውን የዓሰብ ወደብ የማግኘት ዕድሏን እያወቀ ሳይከራከር አሳልፎ ለኢርትራ እንዲሰጥ ያደረገውን አካሄድ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦታል።
    ስለዚህ ይሄንን አያደርጉትም እንጂ ካደረጉትማ፣ ይህን ሁሉ ዙርያ ጥምጥም ከሚሄዱ አሸማጋዩ ፍርድ ቤት ላይ ጉዳዩን አንስተው የኢትዮጵያን መብት ካስከበሩ በኋላ ሲፈልጉ ትግራይ፣ ዓፋር፣ ወሎ ወደተመቸው ሊያደርጉት ይችሉ አልነበረም ወይ?
    እና ኃሳቡ ትክክል መስሎ ስላልተሰማኝ ነውና፣ ከወያኔ ባኅሪይ አንጻር ሲታይ የማይገጣጠም ስለሆነ ነው። ከሆነማ እሰየው ነው እንጂ።

  5. Ethiopian mostly amharas do not belive eritrea or asab.we now our enemy.you said woyane sold eritrea our port.yes we have proplem with woyane but he accepted eritrea is eritrea.But you mostly amharas are in dream.eritrea is for eritreans

  6. This is bull crap. Woyanne and Tigray already the owner of Ethiopia for past 25 years. People missing the big picture,we worried about piece of land while they control the entire country.they target us one by one. They destroy our unity and make us narrow minded. We don’t associate with other ethiopian,we seek our ethnic people to talk,organised,relationship etc. we lost the battle and cry for little thing. We expect others to pay the ultimate instead of we pay that price to free our country. We become sub human and should be treat like one. Let us ask ourselves,what did we do lately to free up ourselves? Even we scared to protest against this blood suckers in the West Countries let alone fight them face to face. We don’t sacrifice our time or money to change the situation. Fear hold us and make us crippled. I am Amhara, I am Oromo, I am this and that so what? 25 years nothing learn. We should be ashamed of ourselves. What a loser generation,what we known are just run from our problems. Always they do this and that,cry like little girl. Lets change ourselves then we can change the situation. Or shut up.

  7. Asebn tgrai woyanie sigeneTel le tgrai lemadreg eqd alew.
    Be Tornet woim esayasn kelto mismamawn be meshom.
    Gn ethiopia kaferarese behuala new.

  8. ምኞት አንድ ነገር ነው ተጨባጩ ዕውነታ እና የሚሻለው ግን እፍኝ ቆሎ ይዘህ ካለው ጋር ተጠጋ ይባል የለ፣
    ስስት ሆኖባቸው እንጂ ዓለም ከተፈጠረች ጊዜ አንስቶ ሲሳይዋን አጉድላ አታውቅም። የተገኘውን አብሮ ተካፍሎ መብላትና በሰላም መኖር እየተቻለ፣ ይህ ሁሉ ዙሪያ ጥምጥም ባላስፈለገ ነበር።
    እንግዲህ ይህ ካሰኛቸው በመሃል እኮ ሞት የሚሉት ባላጋራ አለ፣ መቀደምም ይመጣል። ስለዚህ ኤርትራውያን ወንድሞቻችንንም ከእኛው ጋር ነው የሚያምርባችሁ እና ለአንድነቱ እናንተም ጠንክሩ አደራ። እነዚህ እንደሆን እኛን አፋጅተው የሰበሰቡትን ዘርፈው ሊሄዱ እንጅ ማንንም አይወክሉም።
    እግዚአብሄር ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን ያብዛ።

  9. This is agenda of least civilized , narrow nationalist and separatist in Gondar/Amhara, Tigray and Oromia.
    Ethiopia is one and it has only one sovereign territory,the rest is irrelevant.

  10. ዋናው ጠላት ወያኔ ስለሆነ ሁላችንም ተባብረን ይህን ቅንቡርስ ማስወገድ ይገባናል። ወደድንም ጠላንም ማለት ነው፣ አለበለዚያ ዝም ብለን በየጊዜው የምናደርገውን ማላዘን አቁመን፣ ወያኔ ጌታዬ ሺ ዓመት ግዛን እንደፈለግክ አድርገን፣ አሜን ብለን መገዛት ነው።
    በተለይ አንዳንዶቻችንማ ዓመል ሆኖብን ነው መሰል ዝም ብለን የባጥ የቆጡን ስንቀባጥር እንውላለን። የማንችለውን መስክ ለሚችሉት በመስጠት እኛ ደግሞ በምንችለው ያቅማችንን እናበርክት።

    ሞት ለወያኔ
    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች
    ጠላቶቿ ሁሌም እግሯ ስር ይወድቃሉ።

  11. የክልሎች አለመግባባት የብሄር ብሄረሰቦች ግጭት 90 ሚሊየን ህዝብ የወደብ አልባ መሆን መንስኤ የፊደራሊዝም ስርዐት ውጤት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*