ዶክተር መረራ ጉዲና ከሃገር እንዳይወጡ ተከለከሉ::

ዶክተር መረራ ጉዲና ከሃገር እንዳይወጡ ተከለከሉ::

የወያኔ አገዛዝ ትላንትና ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ አሜሪካ ለመብረር በዝግጅት ላይ የነበሩትን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲናን ከሃገር እንዳይወጡ ማገዱን የድርጅቱ የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል::

አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ “ቪዥን ኢትዮጵያ” (ራዕይ ኢትዮጵያ) በተሰኘ ተቋም ጋባዥነት በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሊጓዙ እንደነበር የጠቆሙት ዶ/ር መረራ፤ ሻንጣቸው ተፈትሾ ከተጫነ በኋላ “ፓስፖርቱ ላይ ያለውን ቁጥር የኛ ሲስተም ማንበብ አልቻለም” ተብለው ከቦሌ አየር መንገድ እንዲመለሱ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ “ፓስፖርቱን ኬሚካል ወይም ሽቶ አሊያም ዘይት ነክቶት ይሆናል” ብለውኛል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ከአየር መንገዱ ከተመለሱ በኋላም ለኢምግሬሽን አቤቱታ ማቅረባቸውንና እስከ ትናንት ረፋድ ድረስ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ፓስፖርቱ የ3 ዓመታት የአገልግሎት ጊዜ እንዳለው የገለፁት ዶ/ር መረራ፤ ወደ ውጭ ሀገር መመላለስ ከጀመሩ ከ30 ዓመት በላይ እንደሆናቸውና ይህ አይነቱ ሁኔታ ሲገጥማቸው የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች” በሚል ርዕስ ለአንባቢያን ያቀረቡት መፅሃፍ፤ ሁለተኛ ህትመት መውጣቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡   የሕወሓት አገዛዝ የሕዝብ ድጋፍ ያላቸውን የፖለቲካ መሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ በቁም እስር ላይ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥበብ ክፍተኛ እንግልት እየፈጠረ ሲሆን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ላይ እንዲሁ ሕገወጥ መንግስታዊ ወንጀል ተፈጽሟል::#MinilikSalsawi

 

 

11 Comments on “ዶክተር መረራ ጉዲና ከሃገር እንዳይወጡ ተከለከሉ::”

  1. Le 41 amet le and afta
    sayaqom Telatachn yetgrai
    woyanie eñan eyegedele
    ena agerachn eyaTefat
    ygeñal.
    Lemedan and bcha mrcha
    alen.
    Esum: woyanien megdel
    new.
    Jegnoch, beyalenbet
    beyegiziew wedaj meslen
    bemeqreb, lemanm
    sanasawq bedbq yetgrai
    woyanien engdel.
    woyaniewochn sngelachew
    yeterefut sisheshu weym
    siyalqu bcha neTanet ygeñal.
    Megdeya mesariyana
    sltoch:
    Tyit, bomb, slu mesariya
    (goradie, seyf, meTrebiya,
    bilawa, Tor, ankasie),
    bebox, qomeT, dngay, merz,
    maqaTel, maneq, mafen,
    wede gedel, gudguad
    megefter, kewha masmeT,
    bebeshta maslekef, etc new.
    Zm blen mawelawel lemaleq
    new.
    Saichersun qedmen megdel
    alebn.

  2. This guy should held accountable and faces justice for the death of young Oromos. This MESON
    homeless Professor
    should be im

  3. Selam! ጋዲሳን አምባሻዋ አነቃት ብለሀል? በዚህ በጠፋ ውሀ ይህን ጊዜ አምባሻዋን እንደጎረሰች ክልትው ብላ ይሆናል። ነፍስ ይማር ብለናል!!!!

  4. kehoala huno belaw akatlw malt sayhon chgrunm
    abro megaft neaw . Hetanatin asgdlo Humburgerun
    lemegmt irteban lemesebsb merot duro kere .
    Auhun qeye mesmr talfoal . indezihema chewata
    yelem . 24 amet afun indekefte mechershaw homeless
    mehon . kkkkkkkk

  5. EPRDF izeh seawye lay lemin indmychkin aygebagnem ?
    afu dorro maneqiya kalut Shermutoch yebltal
    minim yetmare seaw shetawum yelewm .
    Political science , Ecomomics , History , Geography
    Law timehirt neaw bilw gizachwn yatefu sewoch yegrmugnal
    lehager menim yemayfeyd demo Doctor professor yebalulugnal
    iski temlktu andim ye science mehur gize norot beyembassy
    ina sebseba gize norot yemiyawdeledl ayeche alawkim .

  6. Thank you Beiwketu you speak my mind .
    Apart form those who specialized in
    social science aren’t playing a decisive
    role as science the professionals do .

  7. ኢትዬጵያን እንደጥእሎ እያጣቀሰ ከፋፍሎ እየጎረሰ ያለው ወያኔ ይወገድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*