ሁለት አነስተኛ ድንኳኖች በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ ሐሩርና ንዳድ ለመከላከል ያስችሉ ዘንድ ተዘርግተዋል፡፡ በአንደኛው ድንኳን ውስጥ አራት ፍራሾች ተዘርግተው፣ ኢልኒኖ ባስከተለው ከፍተኛ ድርቅ የተነሳ የምግብ እጥረት የገጠማቸውን ሕፃናትና እናቶች ለመንከባከብ እንዲያስችሉ አንሶላ ለብሰው ተዘጋጅተዋል፡፡ በእነዚህ ድንኳኖች ውስጥ ደግሞ ‹‹ሴቭ ዘ ቺልድረን›› …

የምግብ እጥረት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በርትቷል፡፡ Read more »

በማሕሌት ፋንታሁን

መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ተቋማት ጋር ማቆራኘት ሳያስፈልገው የጻፈው ጽሑፍ ብቻ ተጠቅሶበት የተከሰሰ እና የተፈረደበት ብቸኛ ጋዜጠኛ ነው – ተመስገን ደሳለኝ። በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተመሠረተችው ፍትህ ጋዜጣ ጥቂቶቹን የግል ሕትመት ሚዲያ ውጤቶች የተቀላለችው በ2000 ነበር። ከምርጫ 97 በኋላ የተከሰተውን የግል ሚዲያ እጥረት አሳስቦት እና የበኩሉን ለመወጣት ብሎ ነው ፍትሕን ለመመሥረት የተነሳሳው። ፍትሕ ጋዜጣ ሕትመት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2004 ሐምሌ ወር (ላይ እስክትታገድ ድረስ) ድረስ ከዓመት ወደ ዓመት የሕትመት ብዛቷ እየጨመረ መጨረሻ አካባቢ እስከ 35ሺ ኮፒ ትታተም ነበር።

ማንኛውም ዓይነት ቅድመ ሳንሱር እንደሌለ በሚደነግገው ሕገመንግሥት መተዳደር ያለበት ፍትሕ ጋዜጣን የሚያትመው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሐምሌ 13/2004 ዓም እትም ላይ ስለ መለስ ዜናዊ የተጻፈ ዜና ካልወጣ እንደማያትሙ አሳወቁ። ይህን የሰማው ተመስገን እያረጉ ያሉት  ቅድመ ሳንሱር መሆኑን፣ ይህ ደግሞ በሕገመንግሥቱ የተከለከለ መሆኑን ከገለጸላቸው በኋላ የታዘዙትን 30ሺ ኮፒ ካተሙ በኋላ እንዳይሰራጭ ከፍትሕ ሚኒስቴር በተላለፈ ትዕዛዝ መሠረት ማገዳቸውን እና የታተመው ጋዜጣም መወረሱን በደብዳቤ ገለፁ። ለ30ሺ ኮፒ ሕትመት፣ ለጸሐፊዎች የሚከፈል እና ለተለያዩ አስተዳደራዊ  ወጪዎች የወጣው ገንዘብ ወደ100ሺ ብር የሚጠጋ ከስሯል። ነሐሴ 2 ቀን  2004 ክስ እንደተመሠረተበት ፋና ዜና ላይ እንደሰማ የሚናገረው ተመስገን፣ በዜናው እንደሰማውም በቀጣይ ቀጠሮ ነሐሴ 9 ቀን 2004 ፍ/ቤት ቀረበ። በ2003 እና በ2004 በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በወጡ 5ት ጽሑፎች ሦስት ክስ እንደቀረበበት ተነግሮት የዋስትና መብቱንም ተነፍጎ የዛኑ ቀን ወደ እስር ቤት ገባ። ለስድስት ቀናት በቃሊቲ ጨለማ ቤት ከቆየ በኋላ ባልተጠበቀ ሰዓት እና ምክንያቱ ሳይነግው  ነሐሴ 16/2004 ከእስር ተለቀቀ። በኋላ ሁላችንም እንደሰማነው ከእስር የተለቀቀው ክሱ ተቋርጦለት መሆኑን ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን የቀረቡበት ክሶች 1ኛ) ወጣቶች በአገሪቱ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱ ላይ እንዲያምፁ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር፣ 2ኛ) የሀገሪቱን መንግሥት ሥም ማጥፋት እና የሐሰት ውንጀላ፣ 3ኛ) ክስ የሐሰት ወሬዎችን በማውራት ሕዝብን በማነሳሳት ወይም አስተሳሰባቸውን ማናወጥ ሲሆኑ ይህን ክስ ሊያስመሠርቱበት የቻሉት ጽሑፎች ደግሞ 1) የፈራ ይመለስ (በተመስገን ደሳለኝ) 2) የሁለተኛ ዜግነት ሕይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ? (በተመስገን ደሳለኝ) 3) መጅሊሱና ሲኖዶሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ (በተመስገን ደሳለኝ) 4) ሞት የማይፈሩ ወጣቶች (በተመስገን ደሳለኝ) እና 5) የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመጨፈር የሚሉት ናቸው።

ፍትሕ በዚ መልኩ ከሕትመት ከታገደች በኋላ ተሜ እጅ እና እግሩን አጣጥፎ አልተቀመጠም ወይም መሰደድን አልመረጠም። በ2005 ፍትሕን በአዲስታይምስ መጽሔት መልክ፣ እሱም እንዲዘጋ ሲደረግ በልዕልና ጋዜጣ እውነትን እንድናነብ ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን ለፍቷል። ልዕልናም ቀኗ ደርሶ ከሕትመቱ ዓለም ስትሰናበት ደግሞ በ2007 በግሉ ዘርፍ ይታተሙ ከነበሩ ተመራጭ ጥቂት መጽሔቶች እና ጋዜጦች ጋር ክስ ተመሥርቶባቸው እንዳይሠሩ ከታገዱት የሕትመት ውጤቶች መሐል አንዷ በሆነችው ፋክት መጽሔት ሥራውን ቀጥሎ ነበር።

በነሐሴ 13፣ 2004 ተቋረጠ የተባለው ክስ መቀስቀሱን አሁንም እሱ በሌለበት በታኅሣሥ ወር 2005 የዋለው ችሎት በፋና ሬዲዮ መዘገቡን ሰማ/ን። በቀጣዩ የቀጠሮ ቀን ሲቀርብ የ50ሺህ ብር የዋስትና ብር አስይዞ ክሱን ከውጪ ሆኖ እንዲከታተል ተፈቀደለት። ክሱን እየተከታተለም ነው ልዕልና ጋዜጣን እና ፋክት መጽሔትን ለኛ ላንባቢዎቹ ሲያደርስ የነበረው። ታኅሣሥ 2005 የተንቀሳቀሰበትን ክስ በዋስትና ሲከታተል ቆይቶ፤  በጥቅምት 3፣ 2007 ጥፋተኛ የተባለው እንዲሁም ጥቅምት 17፣ 2007 ላይ ደግሞ የ3 ዓመት ፍርድ የተፈረደበት።

ተመስገን የሥራ ሰዓት እና የእረፍት ሰዓት የለውም። ብዙውን ጊዜውን በመጻፍ ወይም በማንበብ ነው የሚያሳልፈው። የጻፈውን የኖረ እና እየኖረ ያለ ጋዜጠኛ ነው።

ዝዋይ ከመሄዱ በፊት ቃሊቲ በነበረበት ጊዜያትም ሆነ ዝዋይ ከሄደ በኋላ ተመስገን፣ ሌሎች እስረኞች እንዳይቀርቡት ይደረጋል። ቃሊቲ እያለ የአልሻባብ አባል ተብለው በሽብር ተከሰው ከሱ ጋር የሚኖሩ እስረኞች ከሱ ጋር ካወሩ ወይም ወክ ሲያደርጉ ከታዮ “እንዴት ከአሸባሪ ጋር ትሆናላችሁ?” ይባሉ እና የተለያዩ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርስባቸው ነግረውታል። የዝዋዩ ደግሞ የባሰ ሆኖ ነው ያገኘው። ከሱ ጋር ያወራ ማታ ማታ እየተወሰደ ይደበደባል። ይህን በመፍራት ብዙ እስረኞች ከሱ ጋር መሆን ይፈራሉ። መጽሐፍ አይገባለትም። ሕክምና ለማግኘት ሲጠይቅ “ቆይ ያንተን ጉዳይ እየተነጋገርንበት ነው”  ከሚል ውጪ ያገኘው ምላሽ ስለሌለ ከጀርባ ሕመሙ ስቃይ ጋር አብሮ ይኖራል። ምንም ዓይነት መጽሐፍት አይገቡለትም። ከሌሎች እስረኞች ተውሶ ማንበብም አይችልም። እሱ ያለበት ዞን ላይብረሪ የለም። ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ እንዳይጠይቁት ይከለከላሉ። ብዙ ጓደኞቹ እና ወዳጆቹ ብዙ ርቀት ተጉዘው ከእናቱ እና ወንድሞቹ ውጪ እሱን መጠየቅ አይቻልም ተብለው ይመለሳሉ። የዛሬ ዓመት አካባቢ እናቱን እና ወንድሞቹን ጭምር ለሁለት ወር ያክል እንዳይጠይቁት ተከልክለው ነበር። በተለያዩ ጊዜያትም እነዚሁ የቅርብ ቤተሰቦቹ ገብተው እንዳይጠይቁት ተከልክለው ይመለሳሉ። በአንድ ወቅት ታናሽ ወንድሙ የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ ሊጠይቀው በሄደ ወቅት መግባት እንደማይችል ከነገሩት በኋላ በማያቀው ምክንያት በዝዋይ እስር ቤት ፓሊሶች ተደብድቧል።

ምክንያቱን ባይገባኝም ከቅርብ ቤተሰቦቹ ውጪ መጎብኘት የሚፈቀድለትን አንዳንድ ወቅቶች ተከታትለው የሚጠይቁት ጓደኞቹ ብዙ አይደሉም። ተመስገንን የምንወደው ጓደኛችን ከሆነ ከቤተሰብ ውጪ መጠየቅ አይቻልም ብሎ ቁጭ ከማለት ዝዋይ መጠየቅ ከሚፈቀድለት ቤተሰብ ጋር ሄዶ መልዕክት መላክ ወይም መጠየቅ የሚፈቀድበትን ወቅት ጠብቆ መሄድ።

ተሜ በዝዋይ ከሌሎች እስረኞች በተለየ ብዙ ማእቀቦች ተጥሎበት እየኖረ የመንፈሱ ጥንካሬ የሚገርም ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አራት ፅሁፎችን አስነብቦናል። በእስሩ ወቅት ስላገኛቸው የኢትዮጵያ ሶማሌዎች የሚተርክ በሁለት ክፍል “የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና ከዝዋይ እስር ቤት”  እንዲሁም አሁን በኦሮሚያ ስለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ የጻፈው “ሁለተኛው ምዕራፍ” የሚሉት ጽሑፎች ይገኙበታል።

ከዓመት በፊት በላከው በአንደኛው ጽሑፉ እንዲህ ይላል  “…ግና! ይህ መንግሥታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ሕዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡”

ተሜ እንደቃሉ ጉዞውን እስከቀራኒዮ ያደረገ ጋዜጠኛ ነው። አንድ ዓመት ከአምስት ወር በእስር አሳልፏል። የሚወጣበት ቀን እየቀረበ ነው እንጂ እየራቀ አይደለም የሚሄደው። በቀሪዎቹ ጊዜዎች እና ከወጣ በኋላ በብዕሩ የሚያካፍለንን የኢሕአዴግ መንግሥት ገበናዎች ለማንበብ በጣም ነው የምጓጓው። ተሜ ከዚህ በፊት በብዙ ኮፒ ታትሞ ለገበያ ያበቃው “የመለስ አምልኮ” የተሰኘው መጽሐፍ ተወዳጅነትን አትርፎለታል። በ2007 መጨረሻ አካባቢ ደግሞ ከሙያ ባልደረቦቹ እና ከጋዜጠኛ እስክንድር ጋር (ከቃሊቲ እስር ቤት) በአንድነት በተለያየ ጊዜ የተጻፉ ጽሑፎችን በመጽሐፍ መልክ ታትሟል።

ተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኝነት ሥራው በተጨማሪ ያለውን በማካፈል ይታወቃል። ለጓደኞቹ እና ለወዳጆቹ በችግራቸው ጊዜ ከጎናቸው ሆኖ ለመርዳት የሚችለውን ያደርጋል። በምስሉ ላይ ከተሜ ጋር የሚታዩት ሕፃናት ቤተሰቦቻቸው አቅመ ደካማ በመሆናቸው ወጪያቸውን በመሸፈን የሚረዳቸው ናቸው። ወጪያቸውን ከመሸፈን ባለፈም ባለው ትርፍ ሰዓት ያዝናናቸው፤ እንዲሁም በቋሚነት የሚማሩበት ት/ቤት በመሄድ የትምህርት ሁኔታቸውን ይከታተል ነበር። አሁን ጊዜው ተገልብጦ እነዚህ ህፃናት በወር አንድ ጊዜ ከእናቱ እና ወንድሙ ጋር በመሆን ዝዋይ ድረስ ሄደው ይጠይቁታል።

በነገራችን ላይ ተሜ እነዚህን ሕፃናት እና ቤተሰቡን እንደሚያስተዳድር ለፍ/ቤት ቢገልፅ የቅጣት ፍርዱ ይቀንስለት ነበር። ሆኖም ተሜ ጥፋት ስላላጠፋሁ አቅልሉልኝ ብዬ አልጠይቅም ብሎ ምንም አይነት ማቅለያ ሳያስገባ ነው 3 ዓመት የተፈረደበት።

ብርታትና ጥንካሬን ለተሜ እና ቤተሰቦቹ እየተመኘሁ ተሜን በጨረፍታዬን በዚሁ ላብቃ።

Geezedit. ግዕዝኤዲት

ዋና መሥሪያ ቤቱ ብራይተን ኮሎራዶ የሆነው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ቁጥሩ ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ኃምሳ ሰባት የሆነ የዩናይትድ ስቴትስ የባለቤትነት መታወቂያ (ፓተንት) መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. (አፕሪል 7 ቀን 2016 እ.ኤ.አ.) ማግኘቱን አስታወቀ። ፓተንቱ የተሰጠው ለፈጠራውና የኩባንያው ባለቤት ለዶ/ር አበራ ሞላ ሲሆን፤ ኩባንያው የእርሳቸውንና የባለቤታቸው የወ/ሮ ሠናይት ከተማ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደግርማ ካሳ

ማርች 26 እና ማርች 27 ቀን 2016፣ በቪዥን ኢትዮጵያ አማካኝነት አንድ ኮንፍራንስ ተካሄዶ ነበር። በዚህ ኮንፍራንስ ላይ ብዙ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች አቅርበዋል (“የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ”)። ከነዚህ መካከል ፕ/ር መሳይ ከበደ አንዱ ነበሩ። ንግግራቸውን በሦስት ነበር የከፈሉት። የመጀመሪያው ክፍል ስለዘውግ (ethnicity) አንዳንድ ጽንሰ ሃሳቦች ለማሳየት የሞከሩበት ነው። ብዙም የማያከራክር ለጠቅላላ እውቀት የሚሆን ፍልስፍናዊና ቴዎረቲካል ትንተና በመሆኑ እዚያ ላይ ብዙ ጊዜ አላጠፋም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በነዳጅ የከበረችው የናይጄሪያ ናይጄር ዴልታ የቀድሞ አገረ ገዢ፣ የሌላዋ የነዳጅ ባለጸጋ ሃገር የኣንጎላ የነዳጅ ሚኒስትር፣ የሙዋቹ የጊኒ መሪ ላንሳና ኮንቴ ባለቤት እንዲሁም የቀድሞ የተ መድ ዋና ጸሓፊ ኮፊ አናን ልጅ ስምም በፓናማው ሰነድ በተጋለጡት የባንክ ሂሳቦች ስማቸው ተነስቱዋል።

ዘውግና ብሔራዊ አንድነት እንዴት ይታረቃሉ?

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደገለታው ዘለቀ

ይህን ርዕስ የወሰድኩት በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ፕሮፌሠር መሳይ ከበደ “የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ” በሚል ርዕስ ስር ካቀረቡት መሳጭ ጥናታዊ ጽሁፋቸው ስር ካነሷቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መሃል አንዱን መዝዤ ነው። ፕሮፌሠር መሳይ ከበደ በዚህ ፕሮግራም ላይ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፋቸው በርግጥ ደረጃውን የጠበቀና በሚገባ የተደራጀ ነው። ፕሮፌሠሩ ፈላስፋም ስለሆኑ አሳባቸውን በሚገባ ገልጸዋል። አስበውበት ተፈላስፈውበት በመሆኑ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል። በእንዲህ ዓይነት ስብሰባዎች ላይም እንዲህ ዓይነት ትንተና መኖሩ መልካም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መሳይ ከበደ

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደ

ይህ ጽሁፍ በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ ያቀረብኩት ነው።

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በሠላም ወይም በኃይል ከሥልጣን ለማውረድ ቢችሉም እንኳን፤ ባለፉት 24 ዓመታት የተዘረጋውን ዘውጋዊ ክፍፍል ለማብረድና ብሔራዊ አንድነትን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ራዕይና ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚስተዋሉት ችግሮች ሁሉ ተቀዳሚና እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ዘውጋዊ ፖለቲካ በመሆኑ ያለውን መንግሥት ለመጣልና አዲስ ሥርዓት ለመመስርት ስለ ዘውግና ዘውጋዊ ፖለቲካ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘትን ይጠይቃል። ወያኔ ከተሸነፈ የዘውግ ፖለቲካ በራሱ ይጠፋል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት ነው። ይህ ጽሁፍም “የዘውግ ፖለቲካ ዋና ዓላማ ምንድን ነው? ከብሔራዊ አንድነት ጋር በምን ሁኔታ ሊጣጣም ይችላል?” የሚሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ ይዳስሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር #Ethiopia Wetatoch Dimts  መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=1FesCqrygH8]  

የኢትዮጵያ ትልቁ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጭ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሰሞኑን በቫይበር፣ በዋትስ አፕና መሰል የድምፅ ጥሪ አገልግሎቶች መስጫዎች ላይ ክፍያ ለመጠየቅ እንዳቀደ የኩባንያዉ የሥራ አመራር ለተለያዩ ሚዲያዎች መናገራቸዉ ይታወቃል።

ይህ የከተሞች አዋጅ በክልሉ ከተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል። አንቀጾቹ የተሠረዙት ጉዳት ስላላቸው ሳይሆን በሕዝቡ ጥያቄ ስለተነሳባቸው መሆኑን የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አብራርተዋል።

#‎Ethiopia‬ ቴዲ አፍሮ አዲስ አልበሙን በቅርቡ ሊለቅ ነው:: Teddy Afro   #‎MinilikSalsawi‬ ታዋቂው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በቅርቡ እያጠናቀቀ የሚገኘውን አዲስ አልበሙን እንደሚለቅ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ተናግሯል:: ቴዲ አፍሮ ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለአድናቂ ወዳጆቹ አስተላልፏል:: ውድ ወዳጆቼ አዲሱ አልበሜን በማጠናቀቅ ላይ …

ቴዲ አፍሮ አዲስ አልበሙን በቅርቡ ሊለቅ ነው:: Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : በሕወሓት ሚዲያዎች የኦሕዴዽ 26ኛ አመትን አስመልክቶ የምንሰማው ዘገባ ሁሉ የሕወሓት አገዛዝን ድድብና እና የአላዋቂ ሳሚነት እየገለጸለን ነው:;ትላንትና ለነጻነትና ለመብት በሕወሓት ጥይት የተገደሉ የኦሮሞ ልጆች ደም ሳይደርቅ አገዛዙ የመቀባጠሪያ ሚዲያዎቹ የሚለፈልፈው ዲስኩር መበስበሱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::ትግሉ …

የኦሕዴድ 26ኛ አመት በኦሮሞ ሕዝብ ሰማእታት ላይ መሳለቅ ቀጥሏል:: ትግሉ ወደ ዝምታ ተቃውሞ ተቀየረ እንጂ አልቆመም:: Read more »

ዩሱፍ ከዲ

AA traffic police. በደመነፍስ የሚነዱ ትራፊክ ፖሊሶችና የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር

የቅዳሜ ሚያዝያ 1 2008 አጭር ገጠመኝ

ከሜክሲኮ በባልቻ አድርጎ በአብነት ወደ አውቶቡስ ተራ የሚወስደውን በተለምዶ ዶልፊን የሚባለውን ታክሲ ስሳፈር፣ ሰዓቱ ገና አንድ ሰዓት ከሃያ አካባቢ ነበር። ታክሲውም አንድ ወይም ሁለት ሰው ቀርቶት ባልሞላበት ሁኔታም ነበር መንቀሳቀስ የጀመረው። ይህ ድርጊቱ የሾፌሩን “ለሰዓት/ለጊዜ እንዲሁም ለጫናቸው ተሳፋሪዎቹ ያለውን አክብሮት” ያሳየኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁና እንዳከበርከን ክበር እያልኩኝ በውስጤ መልካም እየተመኘሁለት ነው የተጓዝኩት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

Crooked forest and TPLF.

የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያቸው ድል ማግስት መቀሌ ተገኝተው በትግርኛ ባደረጉት የአደባባይ ንግግር፤ “እኛ ከሥልጣን ብንወርድ፤ ነፍጠኞች አንድ ቀን አያሳድሩዋችሁም” ማለታቸውን የዓይን እማኝነታቸውን የሰጡ ሰዎች በወቅቱ አስነብበውናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በምስራቅ ኢትዮጵያ ረሃቡ እየባሰ መጥቷል:: #BBC #VIDEO #Ethiopia ለፖለቲካ ፍጆታው የሚሯሯጥ አገዛዝ በተንሰራፋበት ኢትዮጵያ በምስራቁ ግዛት ረሃቡ እየከፋ መቷል ሲል ቢቢሲ በዜናው እወጃው ተናግሯል::ምግብ ለማግኘት ሲባል ሕዝቡ ቀየውን ጥሎ እየተሰደደ ሲሆን ሴቭ ችልድረን እንደጠቆመው በምብ እጥረት ከሚሞቱት በተጨማሪ 16 ሚሊዮን …

በምስራቅ ኢትዮጵያ ረሃቡ እየባሰ መጥቷል:: BBC VIDEO Read more »

በምስራቅ እዝ የሕወሓት ሰራዊት የጦር መሪዎች እና በበታች መኮንኖች መካከል ንትርኩ ከሯል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianArmy‬ ‪#‎Ogaden‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎Change‬ ተቃዋሚዎች ወደሰራዊቱ ዘልቀውለመግባት አለመቻላቸውናፍላጎት አለማሳየታቸው አንዱችግር ነው Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በጎዴ በሚገኘው የሕወሓት ምስራቅ እዝ ክፍለጦር የጦር መሪዎች …

በምስራቅ እዝ የሕወሓት ሰራዊት የጦር መሪዎች እና በበታች መኮንኖች መካከል ንትርኩ ከሯል:: Read more »

ለኢሻ ሰላት በሼህ ሆጀሌ መስጂድ ተገኝተው የነበሩ የተወነሱ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተደበደቡ አቡ ዳውድ ኡስማን ትላንት መጋቢት 2 /2008 ከኢሻ ሰላት በኋላ በታላቁ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ ፖሊሶች ወደ መስጂዱ በመግባት በመስጂዱ የነበሩትን የተወሰኑ ሙስሊሞች ደብድበዋቸዋል፡፡ በተደጋጋሚ በመስጂዱ ረብሻ ፈጥሮ ሙሰሊሙን በመደብደብ …

በሼህ ሆጀሌ መስጂድ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተደበደቡ Read more »

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች የክለቡ ቦርድ ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ:: በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ስታዲይም የቡና ክለብ ደጋፊዎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ተቃውሞ ሲገልጹ አምሽተዋል::በቦታው የነበረ የቡና ክለብ ደጋፊ እንዲህ በጽሁፍ አስፍሮታል:: እግር ኳሳችን ባያድግም እንደ ኢትዮጵያ ቡና የመሰለ ደጋፊ ባለቤት …

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች የክለቡ ቦርድ ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ:: Read more »

የቀድሞ የደምሕት ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስገዶም የ”ህወሓት ልማታዊ ኢንቨስተር” ሆኑ:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Eritrea‬ ‪#‎TPDM‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎Tigray‬ ‪#‎MollaAsgedom‬ ሞላ ኣስገዶም የዴምህት ሊቀ መንበር ሁኖ ለኣመታት በኣስመራ መቆየቱና በ2007 ዓ/ም መጨረሻ ወር ማለት ጳጉሜ 800 የሚያክሉ ወታደሮች ኣስከትሎ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የሚታወቅ ነው። …

የቀድሞ የደምሕት ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስገዶም የ”ህወሓት ልማታዊ ኢንቨስተር” ሆኑ:: Read more »

የተለያዩ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ሬድዮዎችና ድረ-ገጾች ግን የሞቱት ወጣቶች ብዛት ከአራት እስከ 11 ነው ይላሉ።

ገለታው ዘለቀ ይህን ርእስ የወሰድኩት በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ “የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሄ ኣሳብ” በሚል ርእስ ስር ካቀረቡት መሳጭ ጥናታዊ  ጽሁፋቸው ስር ካነሷቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መሃል ኣንዱን መዝዤ ነው።  ፕሮፌሰር መሳይ …

ዘውግና ብሄራዊ አንድነት እንዴት ይታረቃሉ? በፕሮፌሰር መሳይ ከበደ የመፍትሄ ኣሳብ ላይ ሊነሱ የሚችሉ የሰሉ ጥያቄዎች Read more »

በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በተከሰተ የጐርፍ አደጋ  የ8 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን በመጀመሪያው የጐርፍ አደጋ 23 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡ ባለፈው ሰኞ ሌሊት ከጅግጅጋ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው “ጭናቅሰን” በተባለ ስፍራ የዘነበው ከፍተኛ ዝናብ ጐርፍ …

በድጋሚ በሱማሌ ክልል በደረሰ ጐርፍ፣ የ8 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ Read more »

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በ“ቃና” ቴሌቪዥን ላይ ተቃውሞ እንደሌለው ገልፆ ከኪነጥበብ ሙያ  ማህበራቱ የሚቀርቡት ተቃውሞዎች የሳንሱር ባህሪ ያላቸው በመሆኑ አልደግፈውም ብሏል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ማህበራት የ“ቃና” ቴሌቪዥን 70 በመቶ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎሙ የውጭ ፊልሞችን አሰራጫለሁ ማለቱን በመቃወም፣ መግለጫ …

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በ“ቃና” ቴሌቪዥን ላይ ተቃውሞ እንደሌለው ገለፀ:: Read more »

መንግስት ወደ አገራቸው እንዲመልሳቸው ተማፅነዋል ከ10-20 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል ከሶስት ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ በሱዳን አቋርጠው ሊቢያ ለመግባት ሲጓዙ የነበሩ ከ20 በላይ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ጫት ሲቅሙ በፖሊስ ተይዘው በተመሰረተባቸው ክስ፣ ከ10 እስከ 20 ዓመት እስር ተፈርዶባቸው በወህኒ ቤት እንደሚማቅቁ በተለይ ለአዲስ …

በሱዳን በ“ጫት መቃም” ወንጀል እስከ 20 ዓመት የተፈረደባቸው ኢትዮጵያውያን ተማጽኖ Read more »

ምሕረቱ ዘገዬ

Merkato, Addis Ababa. መርካቶ

በተለይ ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ ዓለምን የሚያስደምም ወንጀል በሀገራችን ውስጥ እየተሠራ ይገኛል። በዓለማችን የእስካሁንም ይሁን የወደፊት ታሪክ በፍጹም ያልታየና ሊታይም የማይችል ወንጀል ወያኔዎች እንደልባቸው እየሠሩ ናቸው። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩና የዋናው ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ቡድን አባላት የሆኑ ጥቂት ወያኔዎች እየሠሩት ያለውን የከፋና የከረፋ ወንጀል ሁለቱም መሪዎቻችን በሚገባ ያውቃሉ። ነገር ግን ሁለቱም መሪዎቻችን እልህ የተጋቡና አንዳቸው በአንዳቸው ጣልቃ ላለመግባት የወሰኑ ይመስላል፤ በድርድርም ይሁን በመሸናነፍ ቅራኔያቸውን አስወግደው እኛን ሠላም ሊሰጡን አልቻሉም ወይም ምናባልት ጊዜው ገና ነው። የዝኆኖች መራገጥ ለሣር እንደማይበጅ ሁሉ እኛም በነሱ ሰበብ እየተደቆስን አለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የቢሾፍቱ መሰናዶ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች ትናንትና እና ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ማድረጋቸውንና በፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎችና ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ በከተማይቱ የሚገኙ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች ሰሞኑን በየትምሕርት ቤታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር የተናገሩት የዐይን እማኞች ከ50 በላይ …

በቢሾፍቱ ወደ 50 የሚጠጉ ተማሪዎች ታሠሩ – VOA Read more »

የህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒትን (performance-enhancing drugs) በመመርመር ረገድ አይኤኤኤፍ (IAAF) “ወሳኝ ደረጃ ላይ” ካስቀመጣቸው አምስት ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት ተብሏል። ሌሎቹ ኬንያ፣ ሞሮኮ፣ ዩክሬይንና ቤላሩስ ናቸው። ምርምራውን ካላካሄደች ያለው አማራጭ የአለም የህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒት የሚቆጣጠረው ድርጅት (World Anti-Doping Agency)እርምጃ እንደሚገጥማት ምናልባትም ከአለም-አቀፍ …

ኢትዮጵያ 200 በሚሆኑ አትሌቶች ላይ ህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒት ተጥቅመው እንደሆነ ምርመራ ትጀምራለች – VOA Read more »

Yohanes Molla – “በኢንተርኔት አማካይነት የድምፅና የምሥል ጥሪዎችና መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ አፕሊኬሽኖች፣ ኢትዮ ቴሌኮም ከውጭ ጥሪዎች ማግኘት የሚችለውን ከፍተኛ ገቢ እንዳስቀሩበት ተገልጿል።” ብሎ ተራ ንግግር ከየትም አይገኝም። አገልግሎት ሰጪ ከሚሰጠው አገልግሎት ጋር እንጂ፥ “እንዲህ ባይሆን ይሄን ያህል አገኝ ነበር” የሚል ‘opportunity …

ከዚህ ወዲያ ሽብር? “አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል!” Read more »

የወልቃይት አማሮች ወደ ሚታረዱበት ቄራ «ሂዱ» ሲባሉ ዝም ብለን ልናይ ነው? Achamyeleh Tamiru በአለም ታሪክ ውስጥ የማንነት ጥያቄ በህዝበ ውሳኔ የተፈታበት አገር ያለ አይመስለኝም። የእኔን ማንነት የሚነግረኝ ወያኔ የሚያስቆጥረው የልግጫ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ሊሆን አይችልም። እስቲ አስቡት! በህዝበ ውሳኔ እንዲፈታ …

የወልቃይት አማሮች ወደ ሚታረዱበት ቄራ «ሂዱ» ሲባሉ ዝም ብለን ልናይ ነው? Read more »

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ ላይ ቃጠሎ ደርሷል። ቃጠሎው መድረሱን ያረጋገጡት የዩኒቨርሲቲው የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊ በሕይወት ላይ ያጋጠመ ጉዳት አለመኖሩን ለቪኦኤ ገልፀዋል። ቃጠሎው ዳመራ በሚባለው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ውስጥ በሚገኘው የተማሪዎች ማደሪያ ላይ የተነሣው ትናንት፤ ማክሰኞ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ እንደነበረ …

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቃጠሎ ደረሰ – VOA Read more »

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል። በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል። በተኩሱና ተያይዘው በደረሱ ጉዳቶች የሞቱና የቆሰሉ …

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል – VOA Read more »

የጂንካ ባለስልጣን ለሀሰት ውንጀላ እየተሯሯጠ ነው፡ አቶ አወቀ አይኬ በጂንካ ከተማ እነ ዓለማየየሁ መኮንንን በሽብርተኝነት ፈርጆ የሚንቀሳቀሰው በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አይኬ የሚመራው ቡድን እስካሁን የሄደበት መንገድ ህገወጥና በምንም ማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ የፈጠራው ውንጀላ የሀሰት ምስክሮችን ለማዘጋጀት እየተሯሯጠ መሆኑ …

የጂንካ ምክትል አስተዳዳሪ ለሀሰት ውንጀላ እየተሯሯጠ ነው፡ Read more »

ሐሙስ ጠዋት ግንቦት 10፣ 1998 መንግስታዊው የቴሌኮም ድርጅት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኤጀንሲ በጊዜው አሉኝ ካላቸው አንድ መቶ አስራ ሶስት ሽህ የኢንተርኔት ደንበኞቹ መካከል ጥቂቶቹ ከምርጫ 97 ማግስት የግል ጋዜጦችና መፅሄቶች ላይ በተወሰደው አፈና ምክንያት አማራጭ እየሆኑ ከመጡት ጥቂት ጦማሮችና የዜና ድረ …

ኢትዮጵያና የአስር ዓመታት የኢንተርኔት አፈና ( በአጥናፉ ብርሃኔና በዘላለም ክብረት ) Read more »

ሀገር በታኙን ቫይረስ ለማምከን / ቢንያም ሙልጌታ ( ከኖርዌይ ) ሀገር በታኙን ቫይረስ ለማምከን ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ታሪክ ናት፡፡ይህም በዜጎችዋ አንደበት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እውቅና በመስጠት የሚናገሩት ነው። ጥንታዊና ታሪካዊነቷ ለጉብኚዎቿ አይን መስህብ የሚሆኑ ዘመናትን ያለፉት ቅርሳ ቅርሶች ብቻ …

ሀገር በታኙን ቫይረስ ለማምከን / ቢንያም ሙልጌታ ( ከኖርዌይ ) Read more »

በኦሮሚያ ክልል የተበተኑት ጆሮ ጠቢዎች ከነአለቆቻቸው ለግምገማ ተጠሩ:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎TPLFSecurityForces‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኦሮሚያ ክልል በወያኔ የደህንነት ተቋም ለስለላ የተበተኑ የወያኔ አሽከሮች ስራቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል ለግምገማ መጠራታቸውን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል::በኦሮሚያ ክልል ለሁለት አመታት ያህል የኦሕዴድ …

በኦሮሚያ ክልል የተበተኑት ጆሮ ጠቢዎች ከነአለቆቻቸው ለግምገማ ተጠሩ:: Read more »

ኢትዮ ቴሌኮም Ethio Telecom ና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት በሚጠቀሙ ቫይበርና መሰል የስልክ ጥሪ አገልግሎቶች VoIP in Ethiopia ላይ ክፍያ ለመጣል፣ ወይም ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም እየመከሩ ነው፡፡ በኢንተርኔት አማካይነት የድምፅና የምሥል ጥሪዎችና መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ አፕሊኬሽኖች፣ …

ቫይበርና መሰል የስልክ ጥሪ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ለመጣል ባለሥልጣናት እየመከሩ ነው Read more »

በደቡብ ክልል ሀድያ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የኤልኒኖ ክስተት በሆነው የአየር መዛባት ምክንያት፣ በድንገት በሚፈጠር ቃጠሎ ከ300 በላይ የሚሆኑ ቤቶች መውደማቸው ተጠቆመ፡፡በተለይ ጊቤ፣ ሰሮ፣ ገምቦራና ሸሸጐ ወረዳዎች ላይ በተደጋጋሚ ባልታሰበ ቀንና ሰዓት በተፈጠረ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ፣ የበርካታ ቤተሰቦች ቤቶች በመቃጠላቸው ለከፋ …

ከድርቅ ጋር ተያይዞ በድንገት በሚፈጠር ቃጠሎ ከ300 በላይ የሚሆኑ ቤቶች መውደማቸው ተጠቆመ፡፡ Read more »

ሰሞኑን በሦስት ክልሎች የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ፣ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ የብሔራዊ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሰሞኑን የተከሰተው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከፍተኛ …

በሦስት ክልሎች በደረሰ ጎርፍ የ18 ሰዎች ሕይወት አለፈ:: በርካታ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም Read more »

(Saxophonist  Getachew Mekuria Died ) – ጌታቸው መኩሪያንና ሳክስፎንን ነጣጥሎ ማሰብ ለብዙዎች ይከብዳል፡፡ በተለይም ጎፈር ደፍቶ፣ ካባ ለብሶ በሳክስፎኑ ሽለላውን ሲያስደምጥ የአድማጭን ቀልብ ይገዛል፡፡ ለረዥም ሰዓታት መድረክ ላይ ያለማቋረጥ ሙዚቃ በማቅረብ ዝናን ተቀዳጅቷል፡፡ ወኔውና ሙዚቃዊ ምልዐተ ኃይሉ ከወጣትነቱ አንስቶ በዕድሜ …

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ፈርጥ የሳክስፎን ንጉሡ ጌታቸው መኩሪያ በ81 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ :: Read more »

Artist Getachew Mekuria. አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. April 4, 2016):- በ1927 ዓ.ም. የተወለደው አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ ጥበብን የተቀላቀላት በመንገድ ላይ ታንቡር መቺ በመሆን ነው። ይህ የሆነው በ1940 ዓ.ም. ነበር ። በኋላም ጥበብን እየተከተላት እሷም ወዳለችበት እየጠራችው በ1948 ዓ.ም. በመዘጋጃ ቤት ተቀጥሮ በፊት ከሚያደንቃቸው በኋላም ለረጅም ዓመታት አብረውት ከሠሩት ከአርቲስት ተፈራ አቡነወልድና ከአርቲስት ወዳጄነህ ፍልፍሉ ጋር ተቀላቀለ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

Ethnic apartheid in Ethiopia. የጎሣ ዘረኝነት (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ

የጸሐፊው ማስታወሻ፡- ይህ “የጎሣ ዘረኝነት/አፓርታይድ በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ መደበኛ በሆነ መልኩ እያዘጋጀሁ የማወጣው ተከታታይ ትችት ሁለተኛው ክፍል ነው። የዚህ ተከታታይ ጽሑፍ ጥንድ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ) በአሁኑ ጊዜ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ–ህወሓት) አድራጊ ፈጣሪነት ተመስርቶ እየተቀነቀነ ያለው አውዳሚ የፖለቲካ ሥርዓት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሰፊው የጥቁሮች ህዝብ የበላይ አገዛዝ ሥርዓት ከመፈጠሩ በፊት በጥቂት ነጮች የዘረኝነት የበላይ አገዛዝ ከነበረው የአፓርታይድ ዘረኛ አገዛዝ ተሞክሮ ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን ከምንም ጥርጣሬ በላይ ለማመላከት እና

2ኛ) ጥልቀት እና ስፋት ያለው ክርክር እና ውይይት በማካሄድ ከጎሣ ዘረኝነት የጸዳች አዲሲቷን ኢትዮጵያ የመገንባቱን አስፈላጊነት ለመፍጠር እንዲቻል የኢትዮጵያን የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተስፋዬ ገብረዮሐንስ (ከጀርመን)

Ethiopian federalism map. የወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም ሲፈተሽ

የወያኔ አስተዳደር የማዕከላዊውን የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በሀገሪቱ ተግባራዊ ያደረገው የፌደራል ሥርዓት ጎሣን መሠረት ማድረጉ የሚታወቅ ነው። እንደ ወያኔ አገላለጽ ይህ የጎሣ ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ ደም መፋሰስን ያስቀረና ሀገሪቱንም ከመበታተን አደጋ የሚታደግ ነው ይላል። ይሁን እንጂ በተግባር እየተፈፀመ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ስንፈትሽ ይህ ወያኔ-ሰራሽ የሆነው የጎሣ ፌደራሊዝም ዓላማም ሆነ እያስከተለ ያለው ውጤት ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ገለታው ዘለቀ

በመጀመሪያ ደረጃ መተማመን (Trsut) ስንል የአንድ ሕብረተሰብ የጋራ ሀብት ወይም የማኅበራዊ ካፒታል ዋና አካል መሆኑን እናንሳ። በአጠቃላይ ማኅበራዊ ካፒታል ስንል ደግሞ ልክ እንደሌሎቹ የሰው ልጆች ካፒታል የሚታይ ነው። ለምሳሌ የገንዘብ ካፒታል፣ የሰው ካፒታል (Human capital) እንደምንለው ማኅበራዊ ካፒታልም ካፒታል ይባላል። ካፒታል ነው እንደንል የሚያስችለን ምክንያት አንድም ልክ እንደሌሎቹ ካፒታሎች የሚመረት (Produce የሚደረግ) መሆኑና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ልማቶች ኢንቨስት የምናደርገው ሀብት በመሆኑ ነው። እነዚህ ተፈጥሮዎቹ ከሌሎች ካፒታሎቻችን ጋር ያመሳስሉታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

“ቃና” ( Kana Tv )የሚባል የቴሌቪዥን ጣቢያ በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ለወራት ሲያስታውቅ መቆየቱ ይታወሳል። ይሄን ተንተርሶ በርካቶች ተስፋ ሲያደርጉ ሌሎች ደግሞ በስጋት ተከበዋል፡፡ ተስፋ አድራጊዎቹ ተጨማሪ የመዝናኛ አማራጭ ልናይ ነው የሚል ሲሆን ባለስጋቶቹ ደግሞ ከቀደሙት በምን ይሻል ይሆን? ከገባንበት የመደንዘዝ …

“ቃና” ወይስ ቃታ? (ይታገሱ ጌትነት ) Read more »

• ያለምንም ወጪ ሊቢያ ድረስ አስኮብልለው በእገታ ገንዘብ ይቀበላሉ • ወላጆች የታገቱ ልጆቻቸውን ለማስለቀቅ ንብረታቸውን እየሸጡ ነው ህገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪ ደላሎች፤ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በአዲስ የማታለያ ስልት ከሀገር  በማስወጣት ለእንግልት እየዳረጓቸው ሲሆን በተለይ ሊቢያ ከደረሱ በኋላ ገንዘብ ከቤተሰቦቻቸው እንዲያስልኩ እገታ …

የሊቢያ ህገ ወጥ ደላሎች በአደገኛ ስልት እየተንቀሳቀሱ ነው Read more »

በኩዌት ኢትዮጵያውያን ሴቶችን የሚሸጥ ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ – ቡድኑ 5 ኢትዮጵያውያን አባላት አሉት ተብሏል – በስደተኞች ጀልባ አደጋ ከሞቱት መካከል አንደኛው ኢትዮጵያዊ ነው ተባለ በኩዌት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከቀጣሪዎቻቸው ቤት በማስኮብለል ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሌላ ቦታ …

በኩዌት ኢትዮጵያውያን ሴቶችን የሚሸጥ ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ Read more »

በመሃል ሾልከው የገቡትን የወያኔ አሳሞችን ለማሳፈር ትልቁን ድርሻ መወጣት ያለብን እኛ የለውጥ ሃይሎች ነን:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiopianoppositionparties‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በተቀደደበት ከመፍሰስ ያውጣን::ትግል ፈተና ቢበዛውም ቀድሞ በስሎ መገኘትን ይጠይቃል::ለለውጥ እየታገንል ነው እያልን የጋራ አቋማቸውን በሆኑ የለውጥ ሃይሎች …

በመሃል ሾልከው የገቡትን የወያኔ አሳሞችን ለማሳፈር ትልቁን ድርሻ መወጣት ያለብን እኛ የለውጥ ሃይሎች ነን:: Read more »

#Ethiopia #MinilikSalsawi : –  በአሁኑ ወቅት ከየቦታው እየተወሰዱ መድረሻቸው ያልተገኙ እስረኞች ጦላይ ወታደራዊ ካምፕ እየተንገላቱ መሆኑን የገለፀው ውስጥ አዋቂ ምንጫችን ከ2800 በላይ ሰዎች እንደምገኙ ስገልፅ ከወደ ሀረር የመጡ የ7 ልጆች እናት እንደምገኙበትም አስታውቀዋል። ይህንን የህዝብ አፈና በበላይነት የሚያስፈፅሙት የኦሮሚያ አስተዳደርና …

ከየቦታው እየተወሰዱ መድረሻቸው ያልተገኙ እስረኞች ጦላይ ወታደራዊ ካምፕ እየተንገላቱ መሆኑ ተሰማ:: Read more »