ክቡር ሚኒስትሩ ኮንትሮባድ ያስገቡት እቃዎች ኬላ ላይ መያዛቸው ተሰምቷል::

 

ክቡር ሚኒስትሩ ኮንትሮባድ ያስገቡት እቃዎች ኬላ ላይ መያዛቸው ተሰምቷል::

[ክቡር ሚኒስትሩ የሚያስገቡት ዕቃ ኬላ ላይ ተይዞባቸዋል፡፡ ሚስታቸው ደወሉላቸው]
–    ሰላም ዋልሽ?
–    ምን ሰላም አለ?
–    ምን ሆንሽ ደግሞ?
–    ምን የማልሆነው ነገር አለ?
–    ጠዋት ሰላም አልነበርሽ እንዴ?
–    የዚህ አገር ሰላም እኮ እንደ ስቶክ ኤክስቼንጅ ይወጣል ይወርዳል፡፡
–    ሴትዮ አትሳሳቺ፡፡
–    እንዴት ባክህ?
–    በአሁኑ ወቅት እንደ ኢትዮጵያ ሰላም የሰፈነባት አገር የትም የለም፡፡
–    አትቀልድ ባክህ፡፡
–    እውነቴን ነው፡፡
–    አሁን የምነግርህ ዜና ሰላምህን ይነሳህ የለ እንዴ?
–    ምንድን ነው እሱ?
–    ዕቃው ተወረሰ?
–    ልጆቼ እያሉ ማን ነው የሚወርሰኝ?
–    መንግሥት ነዋ፡፡
–    መንግሥት እኮ እኔ ነኝ፡፡
–    ለማንኛውም አሁን ስልክ ተደውሎልኝ ነበር፡፡
–    ማን ነው የደወለልሽ?
–    ዕቃው ተወረሰ ብለው ነው የደወሉልኝ፡፡
–    የትኛው ዕቃ?
–    ሳሙናና ዲተርጀንት የጫኑት መኪኖች ተይዘዋል፡፡
–    ብረት የጫኑትስ?
–    እነሱ አልተያዙም፡፡
–    ሞባይል የጫኑትስ?
–    እነሱም እስካሁን አልተያዙም፡፡
–    እፎይ፡፡
–    እፎይ ትላለህ እንዴ?
–    እነዚህስ ተይዘው ቢሆን ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር ብዬ ነዋ፡፡
–    ቂሊንጦ ነበራ የሚውጥህ፡፡
[ክቡር ሚኒስትሩ የኬላው ኃላፊ ጋ ደወሉ]
–    ማን ልበል?
–    ጭራሽ ማን ልበል ትለኛለህ?
–    የደወልከው እኮ አንተ ነህ፤ ማን ልበል?
–    ተናንቀናል ማለት ነው፡፡
–    ምን አልከኝ?
–    ክቡር ሚኒስትር ነኝ፡፡
–    ውይ ውይ በሞትኩት፤ ወሳኝ ሰዓት ላይ ነው የደወሉት ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    የምን ወሳኝ ሰዓት?
–    ይኸው ሁለት አይሱዙ ዕቃ እንደያዝኩ ነው የደወሉት፡፡
–    የምን ዕቃ ነው?
–    የሌቦች ዕቃ ነዋ፡፡
–    እንዴት?
–    ይኸው ታክስ ሳይከፍሉ ሊያሳልፉ ሲሉ እኮ ነው የያዝኳቸው፡፡
–    ምንድነው የጫኑት ዕቃ?
–    ዲተርጀንትና ሳሙና ነው፡፡
–    እ…
–    ለማንኛውም ክቡር ሚኒስትር ይቅርታ ቅድም ሌላ ሰው መስሎኝ ነው፤ ይኸው ከመቀመጫዬ ተነስቼ ሰላምታ ሰጥቻለሁ፡፡
–    ገና ከወንበርህ ለዘለዓለም አነሳሃለሁ፡፡
–    ምን አሉኝ?
–    ሰምተሃል፡፡
–    እኮ ምን አደረግኩ?
–    ያደረግከውንማ ታውቃለህ፡፡
–    ዲተርጀንትና ሳሙና ስለወረስኩ?
–    ለመሆኑ ገላህን ታጥበህ አታውቅም አይደል?
–    እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
–    ይኼን ሁላ ሳሙና እወርሳለሁ ስትል አታፍርም?
–    ታክስ እኮ ስላልተከፈለ ነው፡፡
–    እኔ ለሁሉም ነገር ታክስ ከፍዬ እችለዋለሁ?
–    የእርስዎ ነው እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
–    እና የአንተ ነው?
–    ላውንደሪ ቤት ከፈቱ እንዴ?
–    እሱን ደግሞ ማን ነገረህ?
–    አሁን ምን ይሻላል?
–    የዘራሃውን ታጭደዋለህ፡፡
–    እንዴት ማለት ክቡር ሚኒስትር?
–    ዕቃዬን እንዳሰርክ …
–    እ…
–    አንተም ትታሰራለህ፡፡
[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሯቸው ገባ]
–    ምነው ክቡር ሚኒስትር የተቆጡ ይመስላሉ?
–    ምን ሰይጣን ብቻ የተሰበሰበበት አገር?
–    ምን ተፈጠረ?
–    ዕቃዬን ይዘውብኝ ነዋ፡፡
–    ማን ነው የያዘብዎት?
–    ኬላ ላይ ነዋ፡፡
–    የምን ዕቃ ነው?
–    ዲተርጀንትና ሳሙና፡፡
–    የማን ዕቃ ነው?
–    የእኔ ነዋ፡፡
–    ክቡር ሚኒስትር የድግስ ዕቃ ያከራዩ ጀመር እንዴ?
–    ምን ማለት ነው?
–    ኬላ ላይ ከተያዘብዎት በመኪና የሚገባ ነው ብዬ ነዋ፡፡ ያ ሁሉ ሳሙና ምን ያደርግልዎታል?
–    መቼም ልታጠብበት ነው አልልህም?
–    ለነገሩ እርስዎ ቢታጠቡም አይፀዱም፡፡
–    ከምን?
–    ከሙስና!
[አንድ ባለሀብት ለክቡር ሚኒስትሩ ደወለላቸው]
–    ሰላም ወዳጄ፡፡
–    እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
–    አለሁ አንተ እንዴት ነህ?
–    ኧረ ክቡር ሚኒስትር እጅግ እኮ እየተማረርኩ ነው፡፡
–    ምን አማረረህ?
–    ምን የማያማርር ነገር አለ ብለው ነው?
–    አንተ እኮ ደረጃ አንድ ግብር ከፋይ ነህ፡፡
–    ለዛውም ዋንጫ ተሸላሚ እንጂ፡፡
–    በዚህኛውም ዓመት ደግመህ ዋንጫውን ከወሰድከው እኮ ሐትሪክ ነው የምትሠራው፡፡
–    ምን ዋጋ አለው ክቡር ሚኒስትር?
–    ዋንጫውን ታስቀረዋለሃ፡፡
–    አይመስለኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    ምን ሆነሃል?
–    እኔ በቃ የመልካም አስተዳደር ችግሩን አልቻልኩትም፡፡
–    እንዴት ማለት?
–    ሠራተኞቼ አቅተውኛል፡፡
–    ምን አደረጉህ?
–    ግብር አይከፍልም ብለው ይጠቁማሉ፡፡
–    ለምን?
–    ምቀኝነት ይዟቸው ነዋ፡፡
–    እሺ፡፡
–    በዛ በኩል የእናንተ ሰዎች ኪራይ ሰብሳቢ ነህ ይሉኛል፡፡
–    ምቀኞች በላቸው፡፡
–    በጐን ሠራተኞቼ ፍርድ ቤት ሲያመላልሱኝ ነው የሚውሉት፡፡
–    ምን ሆንኩ ብለው?
–    እየተበደልን ነው ብለው ነዋ፡፡
–    ወይ ጣጣ፡፡
–    እና ክቡር ሚኒስትር እኔ በጣም ተማርሬያለሁ፡፡
–    ቆይ ተረጋጋ፡፡
–    ፍትሕ አጥቻለሁ ነው የምልዎት፡፡
–    መላ አለው ስልህ፡፡
–    እኔ ፍርድ ቤትም መመላለስ ሰልችቶኛል፡፡
–    እኔ አሪፍ መፍትሔ አለኝ፡፡
–    ምን ክቡር ሚኒስትር?
–    በራስ ለምን አታቋቁምም?
–    ምኑን ክቡር ሚኒስትር?
–    እስር ቤቱንና ፍርድ ቤቱን!
[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ ቢሯቸው ገባች]
–    ሰው ይፈልግዎታል፡፡
–    የምን ሰው?
–    አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው ይላል፡፡
–    ተራ ሰው አደረግሽኝ እንዴ መንገደኛው ሁሉ የሚያገኘኝ?
–    አይ ክቡር ሚኒስትር አጣዳፊ ጉዳይ ገጥሞዎት ነው፡፡
–    ሴትዮ ሥራ ላይ ነው ብለሽ አባሪልኝ፡፡
[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ ባለጉዳዩ መግባት እንደማይችል ብትነግረውም አልፏት ገባ]
–    ሰላም ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    ምን ፈልገህ ነው?
–    መግባት አትችልም ብላኝ ነበር፣ ግን ጉዳዬ አጣዳፊ ስለሆነብኝ ነው፡፡
–    በጥበቃ እንዳስወጣህ ፈልገህ ነው ታዲያ?
–    አይደለም ክቡር ሚኒስትር አንዴ ያድምጡኝ፡፡
–    ምንም አላዳምጥም፡፡
–    ችግር እየፈጠረ ያለው እኮ አለማዳመጥዎት ነው፡፡
–    እሺ ምንድን ነው ችግርህ?
–    እኔ ሳሙና አስመጪ ነኝ፡፡
–    አንተ ነሃ ተፎካካሪዬ፡፡
–    አንዳንድ ነጋዴዎች ታክስ ሳይከፍሉ እያስገቡ ከገበያ እያስወጡን ነው፡፡
–    እና ምን ላድርግልህ እኔ?
–    መንግሥት ጣልቃ ይግባልንና ይቆጣጠራ፡፡
–    ሰውዬ ታመሃል፡፡
–    እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
–    ይኼ እኮ ነፃ ገበያ ነው፡፡
–    እሱንማ አውቃለሁ፡፡
–    ስለዚህ መንግሥት ጣልቃ አይገባም፡፡
–    ለነገሩ እርስዎ በደንብ ጠልቀው መግባትዎን ሰምቻለሁ፡፡
–    ምን ውስጥ?
–    ኮንትሮባንዱ ውስጥ!
[የክቡር ሚኒስትሩ የእህት ልጅ ደወለላቸው]
–    ሄሎ ጋሼ፡፡
–    እንዴት ነህ ታዳጊው ባለሀብት?
–    ኧረ ጋሼ አላሠራ አሉኝ እኮ?
–    እነማን?
–    የእናንተው ሰዎች ናቸዋ፡፡
–    ምን አደረጉህ?
–    ይኸው ሱቄን አሸጉት፡፡
–    ለምን ተብሎ?
–    ሕገወጥ ነህ ብለው ነዋ፡፡
–    የሱቪኒር ዕቃ መሸጥ ማን ነው ሕገወጥ ያደረገው?
–    አይ ያው በጐን ዶላር እሸጥ አይደል?
–    ዶላር እጥረት ስላለ አይደል እንዴ የምትሸጠው? ማን ነው እሱንስ ቢሆን ሕገወጥ ያደረገው?
–    እሱማ ጋሼ ለባንክ ብቻ የተፈቀደ ሥራ ነው፡፡
–    አንተ ካደግህ እኮ ባንክ መሆን የምትችል ልጅ ነህ፡፡
–    ብቻ ጋሼ እኔን ያሳሰበኝ የልጆቼ ጉዳይ ነው፡፡
–    እነሱማ ምን ይሆናሉ?
–    እንዴት አይሆኑ?
–    በስማቸው ያስቀመጥክላቸው ገንዘብ እኮ እነሱንም ባንክ መሆን ያስችላቸዋል፡፡
–    እ…
–    እንደውም ባንኮች መዋሀድ አለባቸው እየተባለ ስለሆነ አንድ ላይ ተዋህዳችሁ ትልቅ ባንክ መመሥረት ነው፡፡
–    እዚህ አገር ግን ሠርቶ ማደግ ቀረ ማለት ነው?
–    እሱ ቀርቶ እኮ ሌላ ስትራቴጂ መጥቷል፡፡
–    ምን የሚሉት?
–    ሰብስቦ መጥፋት!

 

3 Comments on “ክቡር ሚኒስትሩ ኮንትሮባድ ያስገቡት እቃዎች ኬላ ላይ መያዛቸው ተሰምቷል::”

  1. Le 41 amet le and afta
    sayaqom Telatachn yetgrai
    woyanie eñan eyegedele
    ena agerachn eyaTefat
    ygeñal.
    Lemedan and bcha mrcha
    alen.
    Esum: woyanien megdel
    new.
    Jegnoch, beyalenbet
    beyegiziew wedaj meslen
    bemeqreb, lemanm
    sanasawq bedbq yetgrai
    woyanien engdel.
    woyaniewochn sngelachew
    yeterefut sisheshu weym
    siyalqu bcha neTanet ygeñal.
    Megdeya mesariyana
    sltoch:
    Tyit, bomb, slu mesariya
    (goradie, seyf, meTrebiya,
    bilawa, Tor, ankasie),
    bebox, qomeT, dngay, merz,
    maqaTel, maneq, mafen,
    wede gedel, gudguad
    megefter, kewha masmeT,
    bebeshta maslekef, etc new.
    Zm blen mawelawel lemaleq
    new.
    Saichersun qedmen megdel
    alebn.

  2. tplf and your agent are looters. your time getting shorter and shorter due to what you doing. we are working day and night to expose your bad work and crime. Where ever you go there is no place to hide from the people of the eye. where do you get that much money rebels? do you guys won multi million dollars lottery from US unless within a short time 15,000 wqoyans milliners rise like a mush rooms. “Yaa” you also share the same life span of mush rooms.

  3. የክብር ሚኒሥትሩ ልጅ አ.አ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በማእረግ ተመርቃ የምትፈልጊው የሥራ መሥክ ምን እንዲሆንልሽ ትመኛለሽ ሲሏት የጉምሩክ ፈታሽ መሆን ይሻለኛል ብላለች።

    አይ የወያኔ ትውልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*