በነገራችን ላይ- ኢህአዴግና ሀያ ሚሊየኖቹ ! Wazema Radio

Photo FILEበሀገሪቱ አሁን የተከሰተው የረሀብ አደጋ በህዝብ ቁጥርና ስፋት በታሪክ ተወዳዳሪ የለውም። አሁን የተረጂዎች ቁጥር 20 ሚሊየን ደርሷል። ለመሆኑ ረሀቡን በተመለከተ የመንግስት ምላሽ፣ የለጋሾች አቋምና በአጠቃላይ ለችግሩ የተሰጠው ትኩረት አደጋውን የሚመጥን አይመስልም። በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን አሰባስበን ውይይት አድርገንባቸዋል። አድምጡት ተወያዩበት አጋሩት ::

በድርቅ ሳቢያ ዕርዳታ የሚፈልገው ህዝብ ቁጥር 20 ሚሊየን ደርሷል፣ ከሰሞኑ ይፋ ይደረጋል

(ዋዜማ ራዲዮ)- ድርቅ ባስከተለው ችግር የተጎዱ ኢትዮጵያውያን ተረጂዎች ቁጥር ከ10.2 ሚሊዮን ወደ 20 ሚሊዮን መድረሱን የዋዜማ ምንጮች ገለጹ።

ከሁለት ሳምንት በኋላ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የእርዳታ ሰነድ ላይ በሚካተተው የተረጂዎች ቁጥር ላይ የኢትዮጵያ መንግስትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድርድር ይዘዋል። ከድርድሮቹ አንደኛው  ረቡዕ መጋቢት 14 እንደተካሄደ ምንጮች ይገልጻሉ።

በሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር የታቀፉ እና የምግብ እጥረት ያለባቸው 8 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንዳሉ የሚያስታውሱት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድርቁ ባስከተለባቸው ችግር እነዚህኞቹም ከዋነኞቹ ተረጂዎች ጋር መደመር ይገባቸዋል የሚል ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል። ከችግሩ ስፋት እና ጥልቀት አንጻር ሁለት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በተጨማሪነት በተረጂዎች ቁጥር ሊካተቱ እንደሚገባም ይከራከራሉ።

“የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ነገሮችን ያጋንናሉ” ብሎ የሚ ያምነው የኢትዮጵያ መንግስት በሰነድ ከመፅደቁ በፊት በቁጥሮች ላይ በብርቱ ሲሟገት ይስተዋላል። የሚመጣውን እርዳታ ቢፈልግም የቁጥሮቹ መናር የሚያስከትልበትን ፖለቲካዊ ጫና ለመሸሽ በኦፊሴል የሚወጡ የተረጂዎች እና የእርዳታ ቁጥሮች አነስተኛ እንዲሆኑ ይጥራል። በአሁኑ ድርድርም የሚስተዋለው ይህ እንደሆነ የዋዜማ ምንጮች ያስረዳሉ።

“መንግስት በተቻለ መጠን ቁጥሮቹን ዝቅተኛ ለማድረግ ይጥራል። በዚህም ምክንያት በርካታ ድርድሮች እንድናደርግ እንገዳደለን” ይላሉ በግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ ምዕራባዊ የዋዜማ ምንጭ። “በአሁኑ ግን 20 ሚሊዮን የሚለውን ቁጥር ከመቀበል ውጭ ምርጫ ያለው አይመስለኝም” ሲሉ መንግስት የገባበትን አጣብቂኝ ያስረዳሉ።

ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጠረጴዛ ድርድር ላይ ያሉት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በጎን የ90 ቀናት የአስቸኳይ እርዳታ ዘመቻ ጀምረዋል። ረቡዕ ይፋ የተደረገው ዘመቻ አሁን ሀገሪቱ እጅ በገባው እና በሚፈለገው እርዳታ መካከል ያለውን ክፍተት ለመድፈን ያለመ ነው። ኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ያጋጠማትን ችግር ለመመከት 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብትጠይቅም እስካሁን ያገኘችው ግማሽ ያህሉን ብቻ ነው።

[በጉዳዩ ላይ በስፋት ያደረግነውን ውይይት እዚህ ያድምጡት]-http://wazemaradio.com/?p=1948 

9 Comments on “በነገራችን ላይ- ኢህአዴግና ሀያ ሚሊየኖቹ ! Wazema Radio”

  1. እስት መረጃ ይስጡኝ።
    በአዋሳ ከተማ ለተካሄደው ለመላው የኢትዮጵያ ጨወታ የተያዘውን ባጄት እስክ ያሳውቁኝ። አመሰግናለሁኝ።

  2. Le 41 amet le and afta
    sayaqom Telatachn yetgrai
    woyanie eñan eyegedele
    ena agerachn eyaTefat
    ygeñal.
    Lemedan and bcha mrcha
    alen.
    Esum: woyanien megdel
    new.
    Jegnoch, beyalenbet
    beyegiziew wedaj meslen
    bemeqreb, lemanm
    sanasawq bedbq yetgrai
    woyanien engdel.
    woyaniewochn sngelachew
    yeterefut sisheshu weym
    siyalqu bcha neTanet ygeñal.
    Megdeya mesariyana
    sltoch:
    Tyit, bomb, slu mesariya
    (goradie, seyf, meTrebiya,
    bilawa, Tor, ankasie),
    bebox, qomeT, dngay, merz,
    maqaTel, maneq, mafen,
    wede gedel, gudguad
    megefter, kewha masmeT,
    bebeshta maslekef, etc new.
    Zm blen mawelawel lemaleq
    new.
    Saichersun qedmen megdel
    alebn..

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*