የተቃዋሚዎች ትብብር የሚያንገበግባቸው የሽፍንፍን ኢህአዴጎች መፍጨርጨር ሲጋለጥ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Medrek‬ ‪#‎OFC‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ለትግሉ እንቅፋት ሆነዋል ላሉ የመድረክ አባላት የተሰጠ ምላሽ Tilahun Endeshaw ======== ታህሳስ 27 ቀን 2008 (ከበጽናቱ አሸናፊ ለመድረክ ጽ/ቤት የተላከ) ========= እ. ኤ. አ. ጃንዌሪ …

የተቃዋሚዎች ትብብር የሚያንገበግባቸው የሽፍንፍን ኢህአዴጎች መፍጨርጨር ሲጋለጥ Read more »

ጥቂት የሀገሬን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ሳስባቸው –Melkam-selam Molla እንደ ሸንበቆ ከፍ ብለው ይታዩን ተስፋ ስናደርግባቸው ፍሬያቸው ገለባ ይሆናል። ተስፋ የጣሉባቸው በበኩላቸው ለሀገራቸው የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ፡ ከስራቸው እየተፈናቀሉ ፡ እየታሰሩ ፡ እየተደበደቡ እየተሰቃዩ ፍዳቸውን ሲበሉ ጥቂቶች ስልጣን የጠማቸው ቢሮ ቁጭ ብለው መግለጫ …

ጥቂት የሀገሬን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ሳስባቸው – (መልካምሰላም ሞላ) Read more »

#‎Ethiopia‬‪#‎Oromoprotests‬ : ተቃውሞው ቀጥሏል::የአዲስ አበባ ድሬዳዋ መንገድ የተዘጋ ሲሆን – በባሌ ሮቤ ደግሞ ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ:: ‪#‎MinilikSalsawi‬‪#‎Hirna‬‪#‎BaleRobe‬   Minilik Salsawi – ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ የሚወስደው ዋናው መንገድ በሂርና ነዋሪዎች መዘጋቱ ታወቀ::በሂርና ተማሪዎች እና ገበሬዎች ያደረጉትን ተቃውሞ ተከትሎ የወያኔ …

ተቃውሞው ቀጥሏል::የአዲስ አበባ ድሬዳዋ መንገድ የተዘጋ ሲሆን – በባሌ ሮቤ ደግሞ ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ:: Read more »

የማያዛልቀው “የሐጎስ-ቶላ-እርገጤ” ጨዋታ (አፈንዲ ሙተቂ) —- ከአሁኑ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ባልተገናኘ ሁኔታ የሐጎስ፣ የቶላ እና የእርገጤ ጨዋታን ወደ ሶሻል ሚዲያ ያመጡ ሰዎች ዓላማቸው ምን እንደሆነ አልገባንም፡፡ እኛ እንደምናውቀው በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ተመችቶት የሚኖር የትኛውም ህዝብ የለም፡፡ በደሉ፣ ድህነቱ፣ ረሃቡ፣ ጭቆናው …

የማያዛልቀው “የሐጎስ-ቶላ-እርገጤ” ጨዋታ (አፈንዲ ሙተቂ) Read more »

በውቀቱ ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት ሰው መኮርኮር ይችላል። የተማረው ሳይኮሎጂ ነው። ሳይኮሎጂ የሳቅ ስስ ብልት የት እንደሆነ አስተምሮት ይሆን እላለሁ። ነገር ግን ማሳቅ የጀመረው ትምህርቱን ከመጨረሱ በፊት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሳይኮሎጂስቶች ሲያስቁ ስላልገጠመኝ በዚህ ረገድ ግንኙነት (co-relation) መፈለጌን አቋርጫለሁ።

በውቀቱን እንደ ኮሜድያን አልቆጥረውም [ነበር]። እንደዛ እንድቆጥር የተገደድኩበት አንድ ጊዜ ቢኖር ሀብቴ ከሞተ በኋላ ሀብቴን ተክቶ ሲመጣ ነው፤ ደረጄና በውቄ ነገር ሁኖ። እዚያ ላይ በውቄ ሀብቴን ተክቶ መምጣቱ ከቀልዶቹ የተሻለ ያስቅ ነበር፤ የተሻለ። በውቀቱ ያንን ሚና ደግሞ ላይመለስበት ባደባባይ ቃል ገብቷል።

በውቀቱ ፈላስፋ ነው፤ ኮሜድያን አይደለም። በነገራችን ላይ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋም በውቀቱን ፈላስፋ ነው ይላል። “ስንት ፕሮፌሰሮች ሁለት ክላስ የሚያሰተምሩበትን ሐሳብ እሱ በሁለት መሥመር ቁጭ ያረገዋል፣” በማለት፦
ሉላዊነት

“የጋራችን ዓለም፣ የጋራችን ሰማይ
የብቻችን ሕመም፣ የብቻችን ስቃይ።”

***

“አገር ድንኳን ትሁን ፣ ጠቅልዬ የማዝላት
ስገፋ እንድነቅላት፣ ስረጋ እንድተክላት።”

***

“ከተመኙ ላይቀር ወንዝነት መመኘት፣
አገርን ሳይለቁ ሰው አገር መገኘት።”

በራሪ ቅጠሎች ላይ የመጀመሪያዋ ጽሑፍ ትመስለኛለች በሕይወት ላይ የሚስቅባት ገፀ–ባሕሪይ አለ። ሕይወት ግን ዝም ብላ የምታስቅ እንዳልሆነች የልቦለዱ መጨረሻ ይተርካል። በመጨረሻው መጽሐፉ (መውጣትና መግባት) መግቢያ ላይ ደግሞ፣ ግጥም ተርጉሞ እንደመግቢያ አስቀምጧል። ታዲያ ዘነበ ወላ አዲስ አድማስ ላይ መጽሐፉን ሲተቸው (መጽሐፉ እንደበፊቶቹ ሲሪዬስ አይደለም ብሎ በማሰብ ይመስላል) “ተመልሰህ ግባ በወጣህበት በር” ብሎ ነበር ትችቱን የቋጨው (ከመግቢያ ግጥሙ ስንኝ ተውሶ)። የበውቀቱ መግቢያ ግጥም አሁን በቃሌ እንደማስታውሳት እንዲህ ትላለች፣

“በወጣኒነቴ በድሜዬ አፍላ ጀምበር፣
የሊቅ የጣዲቁን ሐተታ ቁም ነገር፣
አዘወትር ነበር፣
እና ምን ተረፈኝ?
ተመልሼ ወጣሁ፣ በገባሁበት በር።”

ወጥቶ ከሆነ እንኳን ወጣ። ውጪው በጣም ሰፊ ነው። በውቀቱ ደሞ ሲሪዬስሊ የማትወስደንን ተፈጥሮ ሲሪዬስሊ የማይወስድ፣ ለጥፊና ካልቾዋ የማያለቅስ ጸሐፊ ነው (ቢያንስ እኔ እንደተረዳሁት)። በውቀቱ ለኔ የዘመናችን ‘አይከን’ ነው። በለበጣ የሚመለከተንን ዘመን በተመጣጣኝ ለበጣ የሚመክትልን አሽሙረኛ። የኛ ማርክ ትዌይን፣ ወይም የኛ ቮልቴር ነው – በውቀቱ ስዩም!

የበውቀቱ ግጥሞች (በተለይ የኗሪ አልባ ጎጆዎቹ) የሐዘን እንጉርጉሮ ይበዛባቸዋል። ያኔ ተረከዙ የተበሳ ጫማ አድርጌ አዲስ አበባን ስዞር እነሱን በቃሌ እየወጣሁ ነበር ዕጣ ፈንታን እተች የነበረው። ሎሬት ፀጋዬ «ወንድ ልጅ ብቻውን ነው የሚያለቅስ» ሲል፣ በውቀቱ ደግሞ፣

“እምባ ታዛዥ ሆኖ የሚገደብበት፣
ያባት ቅኔና ቀን አለፈ እንደዘበት” እያለ ከውነቱ ያጋፍጠናል።

በሳት ዳር ሐሳቦች ስብስቡ “ከንፍገት እጦትን ማካፈል ይሻላል” ብሎ በፈገግታ ሲመጣ፣ እኔም ዓለምን በሽሙጥ ፈገግታ መመልከት ጀምሬ ነበር። በውቀቱ ከጉርምስና ወደጉልምስና ሳዘግም እንደ ሳውንድ ትራክ ተከትሎኛል። የኔን ትውልድ የሚወክል አይከን ነው የምለውም በዚህ መመዘኛ ነው። ዓለም ሲሪዬስ ሲሆኑላት ሲሪዬስ እንደማትሆን አሳይቶኛል። “የፀጋዬ ቤት ከፀጋዬ በፊት” ብሎ ሲል ዛቻ፣ “እግር አልባው ባለ ክንፍ” ብሎ ሲል ቡጢ ነው የገጠመው። የተሻለው ሽሙጥ ነው። የገባው ቁም ነገሩን ይጨብጣል፤ ያልገባው ስቆ ያልፋል። መሳቅ፥ መሳቀቅን ተካ።

እንደ በውቀቱ በቃላት የሚቀናጣ ባለቅኔ የለም። “ለካስ ያባቶች faith ፌዝ ብቻ ነበረ” እያለ የማይተዋወቁትን ቃላት ድንገት ማዛመድ የሚችለው እሱ ብቻ ነው። በውቀቱ የዶ/ር እጓለ ምናባዊ ሥልጣኔ ቢሰፍን የሚገኘው ውጤት ነው። የአገር በቀል ዕውቀትን ከምዕራባውያኑ ጋር ያዋሃደ ሰው። ስትፈልጉ ከቅኔ ቤት ወጎች፣ ስትፈልጉ ከአቴና ሰማይ ላይ ፊሎዞፊያን ጎትተው ባወረዱ ሰዎች ወግ ያጨዋውታችኋል።

ከቁምነገር መጽሔት እስከ ሮዝ (አዲስ ጉዳይ) መጽሔት ድረስ ያሉ ጽሑፎቹን ደጋግሜ በማንበብ «ጽሑፎችህን ካንተ የበለጠ አውቃቸዋለሁ» ወደሚል ትምክህት ደርሼ ነበር። ተነፈስኩ እንጂ። አሁን ደሞ፣ ፌስቡክ ላይ መጥቷል። እንደ ኗሪ አልባ ጎጆዎቹ ዘመን ሰዎች ጎጆዎቹን መሬት ላይ ቀልሰው መሬት ላይ ብቻ ተጋበዙልኝ ብለው ድርቅ እንደሚሉት ጸሐፍት ሆኖ አልቀረም። ትውልዱ ፌስቡክ ላይ ሲወጣ እሱም ጎጆውን እዚያው ቀልሷል። ጎጆው ውስጥ በቀልድ እያስመሰለ የዘመናችንን እውነት ይተርክልናል። ጎጆውን መቀለስ በጀመረ ጊዜ እኔም እዚሁ ሰፈር ነበርኩ። ጓዙን ጠቅልሎ ፌስቡክ በከተመ ጊዜ ግን “እረፍት” ላይ ነበርኩ። ስለዚህ አሁን “እንኳን ደህና መጣህ” ብለው ረፈደብህ አልባልም። እዚህ ሰፈር ለማይደራደሩብህ አድናቂዎችህ ታስፈልገናለህ።
———
ግጥሞቹን በቃሌ ስለወጣኋቸው ቢሳሳቱ አያገባኝም።

በማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው እና የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸውን ሊያነጋግሯቸው ወደ ማዕከላዊ አምርተው የነበሩት ጠበቆቻቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የሁለቱ ወጣቶች ጠበቆች የሆኑት ጠበቃ አምሃ መኮንን …

ዮናታን ተስፋየ እና ጌታቸው ሺፈራው ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተደረጉ Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሃገራችንን በጉልበት እና በመሳሪያ ሃይል ከሕዝብ ፍቃድ ውጪ እየገዛ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ የገዳዮች እና የዘራፊዎች አገዛዝ የደህንነት ሹሞች እና ወታደራዊ አዛዦች አሰቸኳይ ድንገተኛ ስብሰባ መቀመጣቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::በኢሕኣዴግ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ አለመተማመን እና በጥርጣሬ …

የሕወሓት የደህንነት ሹማምንት እና ወታደራዊ አዛዦች አስቸኳይ ድንገተኛ ስብሰባ ተቀምጠዋል:: Read more »

ልዩ-ትግሬ ( Tigre-exceptional ) ሄኖክ የሺጥላ የ- ነጭ ዘረኞች አውቃለሁ ። ሰዎች ዘረኝነታቸው ከንቀት እና ከጥላቻ ነው የሚመጣው ይላሉ ። እኔ ግን እንዲሁ ሳስበው ምንጩ በትክክል ይህ ነው ማለት ባልችልም ፣ ምክንያቱ ግን ፍርሃት እና ስግግብግብነት የፈጠረው ነው የሚመስለኝ ። …

ልዩ-ትግሬ ( Tigre-exceptional ) ሄኖክ የሺጥላ Read more »

Meski Ab Fits : የሃገራችን ሰሞንኛ ፖለቲካዊ ትኩሳት ንፁሃንን ለሞት፣ መንግስትን ለከፍተኛ ድንግርግሮሽ የዳረገ እንደሆነ የሚታይነው፡፡የፖለቲካው ግመት በዋናነት ከሁለቱ ሰፋፊ ክልሎች የሚነሳ ግን ደግሞ በክፉ ውጤቱ የኢትዮጵያን ህዝብ ከዳር እስከዳር እያሳዘነ እና እያሳሰበ ያለ ሁነት ነው፡፡በንፁሃን ሞት እና በወጣቶች ጅምላ …

እሳትን በጋቢ “ማዳፈን” Read more »

በአሜሪካ የመሳርያ ባለቤትነት በህግ የተከበረ በመሆኑ የመሳርያ ቁጥጥር ማድረግ እንደ ወንጀል ይቆጠራል፡፡ በመሆኑም በየዓመቱ 30 ሺህ የሚያክሉ ዜጎች ይገደላሉ፡፡ከሶስት ዓመት በፊት በኒውታውን፣ ኮነክቲከት ላይ ከ20 በላይ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በገፍ ሲገደሉ ሕጉን ለማሻሻል ወይም የመሳርያ ቁጥጥር እንዲደረግ የሚያስችል ህግ እንዲፀድቅ …

የአሜሪካ ፕረዚደንት ባራክ ኦባማ አለቀሱ Read more »

አዲስ ገጽ መጽሔት – በአንድ ከተማ ውስጥ፥ ‘ትንቢት መናገር እችላለሁ።’ ብሎ በሀሰት የጉራ ወሬ የሚነዛ አንድ ወጣት ነበረ። የነብይነቱ ነገር ተዛምቶ ንጉሱ ጆሮ ይደርስና፥ “ጥሩት እስኪ ይህን መናጢ። እውን ነብይ እንደሆን፥ ይተንብይልና!” ይላሉ። ወጣቱ ተጠርቶ ንጉሱ ፊት ይቀርባል። ጥሪው ወጣቱን …

ከዘመን እግር ስር እንዳንወድቅ፥ የዘመኑን ለዘመኑ እንተውለት! Read more »

“ተው ልጓሙን ያዘው ፡ ቀዳማ¹ ለቀህ፣ በሁዋላ እንዳይከፋ ፡ አወዳደቅህ።” የሕዝብ ግጥም የፈረንጆቹም ዓመትም ባተ ። አሮጌው በአዲስ ተቀየረ ። እኛ ግን “ወይፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ” እንደተለመደው እኛው ነን። የሚገርመው ነገር የሸሚዛችን ቅድ እንኳ አልተቀየረም። ወያኔን ከማውገዝ ያለፈ ፋይዳ ያልው …

ጉዞ ወደ ዘመነ መሳፍንት በልጅግ ዓሊ Read more »

ስለምን ፈራን፤ እንፈራለን፣እናስፈራራለን፣እንፈራራለን ? Girma Bekele የሰው ልጅ ሞትን፣ እስራትን፣ ስቃይን፣ … የምፈራው የተፈጠረበትንና የምኖርበትን የህይወት ተልዕኮ አውቆ ፣ይህን ተልዕኮው ለማስፈጸም የሚያስችል ነባራዊ፣ ወቅታዊና ቀጣይ/የወደፊት ሁኔታ ውስጥ መሆኑን ካረጋገጠ ይህ እንዳይበላሽበት፣ ተልዕኮው እንዳይሰናከልበት ሲል ሊሆን ይችላል፤ በእኔ እምነት ሊሆን ይገባል፡፡ …

ስለምን ፈራን፤ እንፈራለን፣እናስፈራራለን፣እንፈራራለን ? Read more »

Finote Democracy Ethiopian News update and Political Analysis ታኅሣሥ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. -January 04, 2016 # ጋብ ብሎ የነበረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደገና አገርሽቶ ቀጠለ # ወደ አዲስ አበባ የሚገቡት ረሃብተኞች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ታወቀ # የወያኔ ባለስልጣኖች በአዲስ አበባ …

ወደ አዲስ አበባ የሚገቡት ረሃብተኞች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ታወቀ :: የተቃውሞ እንቅስቃሴ አገርሽቶ ቀጠለ Read more »

ሐጎስ ገዢ መደብ ሲባል ለምን እንናደዳለን? ===  ‎ኤርሚያስ ቶኩማ‬ === አንዳንዴ ልንክዳቸው የማንችላቸው ጉዳዮች አሉ ከዚህም መከካል ዋነኛው የህወሀቶች በኢንቨስትመንት እና በፖለቲካው ላይ ያላቸው ሰፊ እጅ ነው። ኢህአዴግ ድርጅቱን ያዋቀረው መሠረታዊ ድርጅቶቹ እንደወከሉት የህዝብ ብዛት ቢሆን ከሱማሌው ሶህዴፓ እኩል አጋር …

ሐጎስ ገዢ መደብ ሲባል ለምን እንናደዳለን? ‎ኤርሚያስ ቶኩማ‬ Read more »

ምንሊክ ሳልሳዊ : – ከአንድ አይነት አስተሳሰብ እናስብ ከሚለው ድሃ አስተሳሰብ ወጥተን በአንድነት እንታገል ተባለ…. የለም …. ከተናጠል ትግል በጋራ ተባብረን እንስራ ተባለ … የለም … ከዚህ ሁሉ ይበልጥ የሳይበር ዘረኝነት በማህበራዊ ድረገጽ ተስፋፍቶ ይታያል::.. ብረት እንደጋል ይቀጠቀጣል እና የሕዝቡን …

የጋለውን ብረት ሳይበርድ በጋራ ከመቀጥቀጥ ይልቅ እርስበራሳችን የምንቀጣቀጥ ካለፈ መማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች ሆነናል:: Read more »

በኦሮሚያ ክልል አለምገና ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ንብረትነቱ የአቶ ገብሩ ወልደአማኑኤል የሆነ የግንባታ ቁሳቁስ ( ኮምፖርሳቶ/ችፑድ)ማምረቻ መለስተኛ ፋብሪካ በእሳት ቃጠሎ ወድሟል።

“ለሕጋዊ” ሕግ አልባ ምላሽ !   Yidnekachew Kebede …………………… “ ማንኛውም ዜጋ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን መግለጽ ይችላል ፤ሕጋዊ መብቱ ነው፡፡በእኛ አገር ግን ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ ሕግ-አልባ የሆነ፤በገዢው መንግሥት ፍላጎትና ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ሕገ-ወጥ አፈና ነው፡፡” ——————————— ተቃውሞ የዴሞክራሲ መገላጫ ነው! የመንግሥት …

“ለሕጋዊ” ሕግ አልባ ምላሽ ! Read more »

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News ፍካሬ ዜና ታኅሣሥ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. (January 03, 2016 Weekly Summary) # አጫጭር ዜናዎች # ወያኔ በርካታ ዜጎችን እያሰረ ነው፡፡ # በጤና መድን አገልግሎት ስም ወያኔ በግዴታ ከሕዝብ ገንዘብ ሊሰበስብ …

በሰሞኑ እንቅስቃሴ ምክንያት አዲስ አበባ በሚገኘው የወያኔ ማእከላዊ እስር ቤት 400 እስረኞች ታስረዋል ተባለ Read more »

የደርግ የደህንነት ሹም ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደሥላሴ ፣ስለ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ==== ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር በጣም እንተዋወቃልን ከሀይለስላሴ ጊዜ ጀምሮ፡፡ ጠንካራ ሰው ነው፡፡ ሃገር ወዳድ ነው፡፡ ለማንም መሪ አያጎበድድም፡፡ ለማንም የሚያጎነብስ አይደለም፡፡ ለውጡ ሲመጣ ፣ መስፍን እነ አጥናፉ እነ መንግስቱን በቀና …

የደርግ የደህንነት ሹም ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደሥላሴ ፣ስለ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም Read more »

News Ethiopia Wetatoch Dimts Jan 04 2016 መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም የስፖርት ዘገባዎች እና ከአቶ ጌታቸዉ ሃይለማሪያም ጋር ያደረግነውን ቃለ -መጠይቅ ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=sZEoBH4XzMA]

ሚዲያ ፣ ሽብርና እስልምና በቅርብ ዓመታት ሚዲያዎችን እና የፖለቲካ መድረኮችን ከተቆጣጠሩ ቃላት መካከል አክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዋነኞቹ ናቸው ቢባል ከእውነታው መራቅ አይሆንም። ከሶስተኛው የፈረንጆቹ ዕልፍ ዓመት መባቻ ጀምሮ የህዝብን ጆሮ ካደነቆሩ ግልብ ጽንሰ ሐሳቦች መካከል ቀዳሚዎቹም ናቸው። የሽብርተኝነት አጀንዳ ሲነሳ …

ሚዲያ ፣ ሽብርና እስልምና – ዳሩል አርቀም Read more »

ኢትዮጵያ እርሻ ኢንዱስትሪ ውስጥ ብዙ ሲነገርለትና ሲጠበቅ የቆየው የህንዱ  ካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክት ኩባንያ ባስመዘገበው ዝቅተኛ ሥራ አፈጻጸም በ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው ቢቆይም፣ ሊሻሻል ባለመቻሉ ታኅሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. መሬቱን ተነጠቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ጠቅላላ ስፋት 54 ሺሕ ሔክታር ሲሆን፣ ካሩቱሪ …

ሴራዎች የወለዱት ደባ ያጋልጣል::. – መንግሥት ከካሩቱሪ ላይ ከ98 ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት ነጠቀ Read more »

ያኔ ይደብረኝ ነበር፡፡ መሥሪያ ቤቱ ይደብረኛል፡፡ አለቆቼ ይደብሩኛል፤ የሚጠገ’ኑት አውሮጵላኖች ሽታ ይደብረኛል፡፡ አቧራ የጠገቡት የጥገና መሳሪያዎቼ ይደብሩኛል፡፡ ለምን ይህንን ስህተት ሠራሁ እያልኩኝ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ ለምን በኮሌጅ የተማርኩትን የመሀንዲስነት ሙያ ትቼ ስለምን የአውሮጵላን ጥገና ሙያ ውስጥ ገባሁኝ እያልኩኝ ራሴን እጠይቃለው፡፡ ከኮሌጅ …

የእኔና አየርመንገዳችን ክርክር – የኢ-ፍትሓዊነት ማሳያ?! በአቤል ዋበላ Read more »

ምርጫ 1997ትን ተከትሎ ፥ ኢትዮጵያን እየመራሁ ነው የሚለው ስርኣት፥ በሰላማዊ መንገድ ሊወገድ እንደማይችል ግንዛቤ በመውሰድ ፥ እኔና ወንድሜ ኣርበኞች ግንባርን ለመቀላቀል መወሰናችንን ለኣንድ እጅግ ለምናከብረው እና ምክሩን ለምንሰማው ሰው ኣማክረነው ነበር። በወቅቱ ይህ ሰው የጠየቀን ጥያቄ “ ለምንድን ነው ጫካ …

መስ’ዋትነት ምንድን ነው ( ሄኖክ የሺጥላ ) Read more »

በሰሞኑ የአደባባይ ውሎዎች ከህዝብ ለባለሥልጣናት/ካድሬዎች የተላለፉ‹‹ ምክሮች›› 1. ‹‹ በአቅምሽ አልሚ›› ‹‹ የአማራ ህዝብ ለብአዴን ከፍተና ባለስልጣናት/ ካድሬዎች ›› በአማራ ክልል ስለ አንደኛው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸምና ስለሁለተኛው ዕቅድ ህዝብን ለማወያየት በተካሄደ ስብሰባ ላይ አንድ አዛውንት የካድሬዎችን የሰበካ/የጠመቃ ኃሳብ አድምጠው ካበቁ …

በሰሞኑ የአደባባይ ውሎዎች ከህዝብ ለባለሥልጣናት/ካድሬዎች የተላለፉ‹‹ ምክሮች›› Read more »

አዎን ለለውጥ የሚደረገው ህዝባዊ ትግል ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ግን የሚያስተባብረውና የሚያቀናጀው የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የሚመጥን አመራር የሚሠጠው የፖለቲካ ድርጅት አላገኘም፡፡ ትናንት ሌሎችን እርሷቸው ብለን፣ተስፋ ጥለንባቸው የነበሩትና ህዝብ ሊደግፋቸው፣ እኛም ልንቀላቀላቸው ፣ እነርሱም ሊተባበሩ ይገባል ያልናቸውና ትዝብታችንና ምክራችንን የለገስናቸውን …

ህዝብን ማዘናጋት ያብቃ– የውይይት መድረክ ይከፈት// Girma Bekele Read more »

ወደ አለም አቀፉ የዲፕሎማሲ መንደር ቀረብ ቀረብ ማለት ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል።ከሐያላኑ አገራት ጋር የቀጥታ ሳይሆን የእጅ አዙር የዲፕሎማሲ ጉዞን ሳይጀምሩ አልቀሩም የሚሉም አሉ። በጠመዝማዛዉ መንገድ የሚጓዙት የዲፕሎማሲ ጉዞ ከሚፈልጉበት ቦታ እስኪያደርሳቸዉ ድረስ እምብዛም አትኩሮት አልሳቡም። እርሳቸዉ ግን እየተጓዙ ነዉ። ፕሬዝዳንት …

የመጨረሻዉ መጀመሪያ አሜሪካ ለምን የአርባ ምንጭ የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ጣቢያዋን መተዉ አስፈለጋት? (ከሳዲቅ አህመድ) Read more »

የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል// አሁን ላለንበት አሳሳቢ ሁኔታ– ትግሉ የነጻነት፣ የዲሞክራሲና የፍትህ ሆኖ ባለበት በተናጠል የሚደረገው ትግል ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ለጥቃት እየዳረገን ባለበት ዛሬም ትናንት ተስፋ አላቸው ብለን ስንጠራቸው የነበሩት መድረክች ሰማያዊ ፓርቲን በማሳሳት ስለትብብር በተለመደው መንገድ ለማወጅ እመከሩ …

የመድረክ መሪው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለአንድነት ትግሉ እንቅፋት ከመሆናቸውም በላይ የኦሮሞ ሕዝብን ተቃውሞ ለመሸፋፈን እየሞከሩ ሲሉ የመድረክ አባላት ወነጀሉ:: Read more »

 Written by  ደረጀ ምንላርግህ On AddisAdmass ስለ አልበሙ ትንሽ እስኪ እናውራ” እነሆ የ “ኤፍሬም ታምሩ እና ሮሃ ባንድ እንደገና – The Reunion” የሙዚቃ አልበም ማጣጣም ከጀመርን ቀናቶች ተቆጠሩ፡፡ ዘመን ያልሻረው፣ እንደውም ከሚታመነውና ከሚጠበቀው በላይ በድንቅ የአዘፋፈን ክህሎቱና ድምጸ ውበቱ እጅግ …

ኤፍሬም ታምሩ ሮሃ ባንድ- እንደገና እጹብ ድንቅ ልዕልና!!! Read more »

“የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች” በሚል ርዕስ አንጋፋው ፖለቲከኛና የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር ዶ/ር መረራ ጉዲና ሰሞኑን ለንባብ ካበቁት ሁለተኛ መጽሐፋቸው የተቀነጨበ … የቡዳ ጉዳይ በሀገራችን ባሕል ውስጥ የታወቀ ስለሆነ ለማስረዳት ዝርዝር ውስጥ አልገባም፡፡ ቡዳና ፖለቲካችንን ምን አገናኛቸው ለሚለው ጥያቄ …

“መፍትሄ ያጣው የቡዳ ፖለቲካችን” Read more »

ገንዘብ ማባከናቸውን አምነው ይቅርታ የጠየቁ አሉ  Addis Admas Newspaper Report የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት፣ በገንዘብ ምዝበራና በአሰራር ግድፈት የጠረጠራቸው አምስት ከፍተኛ አመራሮች ላይ ክስ መመስረቱን የአዲስ አድማስ ምንጮች ገለፁ፡፡ ለፓርቲው ዲሲፕሊን ኮሚቴ ክስ የቀረበባቸው የስራ አስፈፃሚ አባላት፡- የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር …

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት 5 አመራሮችን በገንዘብ ምዝበራ ከሰሰ Read more »

የሰማያዊና ኦፌኮ ፓርቲ አባላትና አመራሮች መታሰራቸውን ሰማያዊ ፓርቲ ያወገዘ ሲሆን፤ “አሁን የፓርቲ ፖለቲካ የምናደርግበት ጊዜ ላይ አይደለንም፤ ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የምንሸጋገርበት ትግል ላይ ነን” ብለዋል የፓርቲው ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፡፡ የሰማያዊ አመራሮች ባለፈው ረቡዕ በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፤ በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን …

“ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የምንሸጋገርበት ትግል ላይ ነን” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር Read more »

“በአምስት ዓመት ከ10.6 ሚ. በላይ የሥራ እድል ፈጥሬያለሁ” – የከተማ ልማት ሚ/ር • ይሄ ‘ቁጥር’፣ ፈፅሞ እውነት ሊሆን አይችልም – ከውጭ አገር፣ 9 . ሚ ሰራተኞችን ካላመጣን በቀር ። ‘ቁጥሩ’፣ ከኢትዮጵያ ከተሞች አቅም በላይ ነው ። የመስራት አቅም ያለው ከተሜ፣ …

ይሄ ‘ቁጥር’፣ ፈፅሞ እውነት ሊሆን አይችልም – “በአምስት ዓመት ከ10.6 ሚ. በላይ የሥራ እድል ፈጥሬያለሁ” – የከተማ ልማት ሚ/ር Read more »

ከኢትዮጵያ የነጻነት ትግል ስሙ የማይፋቀው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ የአመቱ ምርጥ ሰው በመባል በኢትዮጵያ ዲጄ እና አጋር ድረገጾቹ መመረጡ ታወቀ:: ለረዥም አመታቶች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነውን የጭቆና ቀንበር ለማንሳት ደፋ ቀና በማለት የነጻነት ጎህ በእትዮጵያ ምድር ላይ እንዲበራ ሲታገር ለእስር የተዳረገው …

ከኢትዮጵያ የነጻነት ትግል ስሙ የማይፋቀው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ የአመቱ ምርጥ ሰው በመባል በኢትዮጵያ ዲጄ እና አጋር ድረገጾቹ መመረጡ ታወቀ:: Read more »

አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ በዘፈን አንደኛ ሙሉቀን መለሰ (እስከመቸ ድረስ ጥላሁን ገሰሰ) የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ? Lol የህዳሴውን ግድብ ወደ “ህዳሴው ገደል” ያሸጋገረውን ስምምነት የፈረመው ሰውየ“ እጁን ለቁርጥማት፤ ደረቱን ለውጋት“ እንዲዳርገው በመመረቅ ወደ ሰላምታየ እገባለሁ፡፡ እንዴት ናችሁ፤ ያልታደላችሁ? እኔ በህይወቴ …

“በየቦታው እንምሳለን፡፡ ለመጭው ትውልድ ነዳጅ ሳይሆን ጉዱጓድ እናወርሳለን” – በዕውቀቱ ስዩም Read more »

የህወሓትን የጓዳ ወግ ማወቅ አስቸጋሪ የነበረበት ዘመን እንደዋዛ አልፎአል። ዛሬ ቀዳዳቸው በዝቶ፤ ቴክኖሎጂውም አግዞ የፈፀሙት ብቻ ሳይሆን ያሰቡትም በቀላሉ ይገኛል። ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነው። መረጃ ከሌለ ምንም ነገር የለም። ለችግሮች መፍትሄም አይገኝም። ወያኔ ዛሬ በአስር ሺዎች ኦሮሞዎችን በገፍ የሚያስረው ስለ …

ህወሓት እንዴት ሰነበተ? – ከተስፋዬ ገብረአብ Read more »

በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከጥር 6 እስከ ጥር 8 – 2008 የሚካሄድ ሕዝባዊ ተቃውሞ !! ‪ #‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎FreedomVoice‬ ‪ =========== ተቃውሞዉ የሚገለፀዉ በኡኡታና በኳኳታ ይሆናል ። ========== በተጠቀሱት ቀናቶች ሁላችንም በያለንበት ቦታ በመሆን የአገዛዝ ስርዓቱ በህዝብና በሃገር ላይ እየፈፀም …

በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከጥር 6 እስከ ጥር 8 – 2008 የሚካሄድ ሕዝባዊ ተቃውሞ !! Read more »

በሃረርጌ ክፍለሃገር የተማሪዎችና ገበሬዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterplan‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ በምስራቅ ሃረርጌ በደኖ እንዲሁም ሂርና (ለከብት ገበያ የተሳባሰበ ሕዝብ ግብር አንከፍልም በማለት)ሕዝቡ አደባባይ በመውጣት ብሶቱን ያሰማ ሲሆን የአዲስ አበባን ማስተር ፕላንንም ተቃውሟል::የወያኔ ወታደሮች አሁንም ጭፍጨፋውን እና ማሰሩን ያላቆሙ ሲሆን …

በሃረርጌ ክፍለሃገር የተማሪዎችና ገበሬዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው:: Read more »

የእርዳታ ዘይት ተዘርፎ እየተሸጠ ነው።  Amdom Gebreslasie *~*~*~*~*~*~*~ እርዳታ ዘይት ከተጫነበት መኪና በቀጥታ ወደ ነጋዴዎች መጋዘን ገብቶ እየተቸበቸበ ነው። በትግራይ ክልል መንግስት ያመነበት በድርቅ የተጠቃ የህዝብ ቁጥር 1.2 ሚልዮን መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ህዝብ የመጣው የእርዳታ ዘይት ከመኪናው እየተዘረፈ በሃብታም ነጋዴዎች …

የእርዳታ ዘይት ተዘርፎ እየተሸጠ ነው። Read more »

“ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ምንድን ነው? ማበሳጨትን ካላካተተ፣ ሕልውና የለውም፡፡” ~ ሰልማን ሩሽዲ
፩ – ማበሳጨት

‹‹በመስከረም ወር 1997፣ ዢላንድስ ፖስተን የተባለ የዴንማርክ ጋዜጣ ነብዩ መሐመድ ላይ የሚሳለቁ ካርቱኖችን ይዞ ወጣ፡፡ የዚህ ሕትመት ዜና በመላው ዓለም እንደተሰማ በየቦታው ያሉ ሙስሊሞች ቁጣቸውን በአደባባይ መግለጽ ጀመሩ፡፡ የተቃዋሚዎቹ ምክንያቶቻቸው ሁለት ናቸው፤ አንደኛ፣ ነብዩ መሐመድን በምስል መግለጽ በእስልምና ሃይማኖት አይፈቀድም የሚልና፤ ሁለተኛ፣ ካርቱኖቹ በጥቅሉ እስልምናን እና ሙስሊሞችን ከሽብር ጋር አቆራኝተው ይገልጻሉ የሚል ናቸው፡፡  ሠላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በጋዜጣው አዘጋጆች እና በዴንማርክ መንግሥት ላይ ተቀሰቀሰ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሕይወት እስከመቅጠፍ የዘለቀ አመጽ የተቀላቀለባቸው የተቃውሞ ሰልፎች ነበሩ፡፡ ካርቱኖቹ ግን በመላው ዓለም በሚገኙ በሌሎች ጋዜጦች ላይ ለዢላንድስ ፖስተን ጋዜጠኞች የሞራል አጋርነት ለማሳየት በሚል ሰበብ ድጋሚ ታትመው ይበልጥ ተሰራጩ፡፡›› (Paul Sturges, 2006)

ሌላ ምሳሌ እንውሰድ፡፡ አንድ ወንድ “‹ሴቶችን ማስተማር የአገርን ሀብት ማባከን ነው፤ ስለዚህ ሴቶችን ማስተማር ካለብን የቤት አያያዝ፣ ምግብ ማብሰል እና ልጅ አስተዳደግ እናስተምር እንጂ ሌላ ‹የነጭ ኮሌታ› ሥራ የሚያስይዝ ትምህርት ማስተማር የለብንም› የሚል አስተያየት ሲሰጥ በቴሌቪዥን ተላለፈ፡፡ ይህን ተከትሎ የከተማው ሴቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ፡፡ ወንድ አሽከርካሪዎች የሚነዷቸውን መኪኖች ሰባበሩ፡፡ ወንዶችን እያሳደዱ ደበደቡ፡፡” በዚህ የፈጠራ ታሪክ ውስጥ የአስተያየት ሰጪው ሐሳብ ሴቶቹን አበሳጭቷቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለአመጹ እነርሱን አነሳስቷቸዋል ብሎ መደምደም ከባድ ይሆናል፡፡ አማጺዎቹ ሴቶች ስሜታቸውን መቆጣጠርና ሐሳቡን በሐሳብ መመከት ካልቻሉ ድክመቱ የነርሱ የራሳቸው ይሆናል፡፡

የዴንማርክ ፍርድቤት የፈረደውም፣ እኔ በላይኛው አንቀጽ አመጸኞቹ ሴቶች ላይ የሰጠሁትን ዓይነት ብይን ነው፡፡ “እርግጥ ነው ስዕሎቹ የተወሰኑ ሙስሊሞችን ማበሳጨታቸው አይካድም፤ነገር ግን የካርቱኖቹ ዓላማ ሙስሊሞችን ማንኳሰስ አልነበረም›› ብሏል ፍ/ቤቱ፡፡ ሲያብራራውም፣ “ስዕሎቹን አመጽ ወይም ቦንብ የመወርወር ድርጊት በእስልምና ሥም እየተደረገ ነው፤” በሚል መረዳት የካርቱኖቹ ተመልካቾች ድርሻ ነበር ብሏል፡፡ የዴንማርክ ፍርድ ቤት ብይን ለካርቱኒስቶቹ ያደላ ቢመስልም ካርቱኒስቶች ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ክስተቱ አስገድዷቸዋል፡፡ ነገር ግን የአንድ ሐሳብ (expression) አንባቢ፣ ተመልካች ወይም አድማጭ የራሱን ስሜት መቆጣጠር ድርሻ የራሱ መሆን ካልቻለ ቢያንስ የሆነ ሰውን የማያበሳጭ ሐሳብ ማፍለቅ በጣም አስቸጋሪ ስለሚሆን፣ ‹በነጻ› ቀርቶ ሐሳብን መግለጽ የሚባለው ጉዳይ ራሱ አይኖርም፡፡

 አምና የፈረንሳዩ ‹ሼርሎ ሆብዶ› መጽሔት ባወጣቸው ካርቱኖች ተበሳጭተው ጋዜጠኞችን፣ ካርቱኒስቶችን እና ፖሊሶችን የገደሉ ፅንፈኛ-ሃይማኖተኞች ጉዳይም ሊታይ የሚችለው በዚሁ ዓይን ነው፡፡ ፅንፈኞቹ የእነርሱን እሴት ያላከበረ፣ በእነርሱ እሴት መሠረት መቀጣት አለበት የሚል እርምጃ ነው የወሰዱት፡፡ ክስተቱ ለሐሳብ ነጻነት አራማጆች መርዶ ነው፡፡ አጋጣሚውን ተከትሎ ተቀጣጥሎ የመጣውም ውይይት ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው ሳንሱር እንዲያደርጉ የሚያስፈራራ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አጋጣሚው የኢትዮጵያውን ጨምሮ ለአምባገነን (authoritarian) መንግሥታት ፕሮፓጋንዳ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ ሐሳብ እንዴት መገደብ እንዳለበት ክስተቱን አስታክከው ደስኩረዋል፡፡ እነዚህ መንግሥታት ሊያስተውሉት ያልፈለጉት ነገር ቢኖር ከዴንማርክ እስከ ፓሪስ የተከሰተው ነገር ጋዜጠኞች ሐሳባቸውን በነጻነት ሲገልጹ የመንግሥት ከለላ እንደሚያስፈልጋቸው እንጂ ሐሳባቸውን በበነጻነት ከመግለጽ እንዲቆጠቡ የሚመክራቸው አልነበረም፡፡
ሌሎችን ማበሳጨት የተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ ወይም ግለሰቦች ላይ ሲከሰት ከሞላ ጎደል ከላይ ባየነው ሁኔታ ሊያልፍ ይችላል፡፡ ችግሩ የተበሳጨው አምባገነን መንግሥት (የመንግሥት ባለሥልጣናት) ሲሆኑ ነው፡፡ እነ ኤልያስ ገብሩ (አምሳሉ ገ/ኪዳን ዕንቁ መጽሔት ላይ በሚያዝያ ወር 2006 የጻፈውን ጽሑፍ ተከትሎ ጅማ ዩንቨርስቲ አካባቢ በተነሳው የተቃውሞ ብጥብጥ ሳቢያ) የተከፈተባቸው የአመጽ ማነሳሳት ክስ መታየት የሚኖርበት በዚህ ዓይን ነው፡፡ መንግሥት ጸሐፊዎቹንም፣ ለጽሑፉ የጽሑፍ ምላሽ በመስጠት ፈንታ በኃይል የጸሐፊውን ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት የተቃወሙትን፣ ሁለቱንም በክስ በማስተናገድ ጉዳዩን ለመፍታት እየጣረ፣ ጉዳዩ እስካሁን በእንጥልጥል ነው፡፡ ተመስገን ደሳለኝ ሦስት ዓመት የተፈረደበት የመንግሥት ባለሥልጣናትን የማያስደስት አልፎም የሚያበሳጭ ጽሑፍ ስለጻፈ ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ክሱ ከሽብር ወደ ‹በጽሑፍ አመጽ ማነሳሳት› የተቀየረው በተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡ ተጠያቂነት የሌለባቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት በሐሳብ ሲበሳጩ ውጤቱ የከፋ ይሆናል፡፡

፪ – የጥላቻ ንግግር እና አመጽ ማነሳሳት

በ1987 ሩዋንዳ በዓለማችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ ሰቅጣጭ የሆነውን ዜና ለዓለም አርድታለች፡፡ በ100 ቀናት ውስጥ 800 ሺሕ ያህል ሰዎች ተጨፍጭፈዋል፡፡ በጭፍጨፋው 70 በመቶ ቱትሲዎች (ወይም 20 በመቶ ሩዋንዳውያን አልቀዋል)፡፡ የጭፍጨፋው መነሾ ላይ የታሪክ ባለሙያዎች ሙሉ ለሙሉ ባይስማሙም በጎሳ ስም አመጽ እንዲቀጣጠል ያደረገው ግን የሚዲያ የጥላቻ ንግግር እንደሆነ ብዙዎቹ ይስማማሉ፡፡ ከዘር ጭፍጨፋው ዓመት ቀድሞ የተቋቋመው ሬዲዮ-ቴሌቪዥን ሊብሬ ደስ ሚል ኮሊንስ (አር.ቲ.ኤል.ኤም.ሲ) ዋነኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች በዘር ጭፍጨፋው የዚህን ሚዲያ ተቋም ሚና እስከ 10 በመቶ ያደርሱታል፡፡ ሬዲዮው በጣም ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ ከዜጎቹ ጋር በአጭር ጊዜ ለመዋሃድ በቅቷል፡፡ ይህ ሬዲዮ ነበር ቱትሲዎችን “በረሮ” ብሎ መጥራት የጀመረው፡፡ “በረሮዎቹን ደግሞ ማስወገድ አስፈላጊ ነበር፡፡” አለበለዚያ ችግር ያስከትላሉ፡፡ ሬዲዮው በተጨማሪም “በረሮ” ብሎ የጠራቸውን ዜጎች ማስወገድ ስለማስፈለጉ ብቻ ሳይሆን እንዴት መወገድ እንዳለባቸው ጭምር ተንትኗል፡፡ የጭፍጨፋው ፈፃሚዎች በአንድ እጃቸው ቆንጨራ፣ በሌላኛው ሬዲዮ ይዘው እንደነበር ሪፖርት ተደርጓል፡፡

በሩዋንዳ ጭፍጨፋ የነበረው ሬዲዮ ብቻ አልነበረም፡፡ ጋዜጣም የበኩሉን ተጫውቷል፡፡ ካንጉራ የተባለ ሳምንታዊ ጋዜጣ ‹የሁቱ ዐሥርቱ ትዕዛዛት› የተሰኘ ተወዳጅ ጋዜጣ ነበረው፡፡ ጋዜጣው በይፋ ሁቱዎች ከቱትሲዎች ጋር ምንም ወዳጅነት እንደሌላቸው አውጇል፡፡ ጠላት ናቸው በሚል ሚስቶች በባሎቻቸው፣ ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ በዚህ የማንነት ጠላትነት ላይ ተመሥርተው እንዲነሱ አድርጓል፡፡

የሩዋንዳ ሚዲያዎች የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እና ዘመቻ ውጤቱ እልቂት ሆኗል፡፡ ሚዲያዎቹ ወደዘር ጭፍጨፋ የደረሱት በሦስት ደረጃዎች ነው፤ መንግሥት ሚዲያውን በተሳሳተ መንገድ ተጠቅሞበታል – በጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ለዘር ጭፍጨፋ ማዘጋጃ አድርጎታል (1)፣ በጭፍጨፋው ወቅት አመፁን አቀጣጥሏል (2)፣ ከዚያም የጥፋቱ መጠን በትክክል ለሕዝብ እንዳይደርስ አድርጓል (3)፡፡

አሁን የሩዋንዳ መንግሥት ያንን መጥፎ ጠባሳ የጣለበትን ታሪክ ለማጥፋት በማሰብ የሁለቱንም ጎሳዎች ማንነት ክዷል፡፡ በሩዋንዳ አንዱ ሌላውን የእከሌ ጎሳ አባል ነው ብሎ በይፋ መናገር አይፈቀድለትም፡፡ ይህንን የዘር ጭፍጨፋን በማፈን ፈንታ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን ያፈነ እርምጃ እንደሆነ አጥኚዎች ይከራከራሉ፡፡ (Yakaré-Oulé (Nani) Jansen, 2014) ለሩዋንዳ መንግሥት ግን ጉዳዩ ግራ አጋቢ ነው፡፡ ለሩዋንዳ መንግሥት ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ሌሎችን እስከ ማበሳጨት በሚደርሰው ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት፣ በጥላቻ ንግግር እና በአመጽ ቅስቀሳ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት አስቸጋሪ ፈተና ይሆንባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያም ጭምር የፈረመችው የሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች ዓለምዐቀፍ ቃልኪዳን እንደሚለው “ማንኛውም ዓይነት በብሔር፣ ዘር፣ ወይም ሃይማኖት ላይ የተመሠረተ የማግለል፣ ጠላትነት ወይም አመጽ የሚያነሳሳ መልዕክት በሕግ መከልከል አለበት፡፡” ሆኖም አንድ ንግግር ወይም መልዕክት የጥላቻ ሊባል የሚችለው የትኛው ደረጃ ላይ ሲደርስ እንደሆነ መግባቢያ የለም፡፡

አስቀድመን ባየናቸው ምሳሌዎች የሚዲያ እና አመጽን ግንኙነት ስንመለከት፤ አበሳጭ የተባሉ ይዘቶችን ይዘው የወጡ የሕትመት ውጤቶች፣ አመጽ አልቀሰቀሱም፡፡ ይልቁንም የተቃውሞ አመጽ ተቀስቅሶባቸዋል፡፡ የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ደግሞ በተቃራኒው አመጹ የተካሄደው በሚዲያዎቹ የጥላቻና ጥፋት ስብከት መሪነት ነው፡፡ በነዚህ ሁለት ምሳሌዎች መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ከባድ ላይሆን ይችላል፡፡ የአመጽ ቅስቀሳ ከመደረጉ በፊት ለመከላከል ያንን ዓይነት አዝማሚያ ያለውን የሚዲያ ተቋም ቀድሞ መቆጣጠር ግን ከባድ ይሆናል፡፡ የማይቻል ግን አይደለም፡፡ ይህንን የሚቻል-ከባድ የመንግሥት ሥራ ክፍተት የሚረዱ አምባገነኖች ሚዲያን (ወይም ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን) ለማፈኛ እንደምክንያት ይጠቀሙበታል፣ እየተጠቀሙበትም ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት በብሔር ላይ ያተኮሩ አንዱን የሚያጠለሹ፣ ሌላውን ተበዳይ የሚያደርጉ የቁርሾ ታሪኮችን እንዲያውም በበጎ ሲመለከታቸውና ሲታገሳቸው ይታያል፡፡ የገዢው ፓርቲ አመሠራረትም ሆነ አቋቋም የብሔር በዳይ-ተበዳይ ግንኙነትን አጠፋለሁ በሚል ሥም ስለሆነ እነዚህ ዓይነቶቹ ትረካዎች የተስማሙት ይመስላል፡፡ ነገር ግን መንግሥት ለእነዚህ አደገኛ አዝማሚያ ላላቸው ሐሳቦች/ጽሑፎች ያለውን ትዕግሥት ቅንጣት ታክል እንኳን ስርዓቱን ለሚተቹት የለውም፡፡ ይህም የሚያስገነዝበው መንግሥት ለሐሳብ ነጻነትም፣ ይሁን ሕዝቦች ላይ ለሚደርሰው አመጽ እንደማይጨነቅ፤ ይልቁንም ለሥልጣኑ ብቻ እንደሚሳሳ ነው፡፡ ሐሳብን በመግለጽ ነጻነት እና አመጽ በመቀስቀስ መካከል ያለው ልዩነት ጠርቶ በሕግና መመሪያ እንዲደነገግ የማይፈልገውም ለዚያው ነው፡፡

“ማንም ከብስጭት የመጠበቅ መብት የለውም፡፡ ይህ መብት እስከዛሬ ባነበብኳቸው ድንጋጌዎች ሁሉ ላይ የለም፡፡ ከተበሳጫችሁ፣ የራሳችሁ ችግር ነው፤ እንደእውነቱ ብዙ ነገሮች ብዙ ሰዎችን ያበሳጯቸዋል፡፡” ~ አሕመድ ሰልማን ሩሽዲ!

This article is published on Addis_Gets magazine, on Tahsas 3, 2008 issue. 

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከምድር ጦር መምሪያ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሰራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ አለመግባባቶች እየተከሰቱ ሲሆን የሰራዊቱ አባላት ከተለያዩ ቦታዎች የሚያገኟቸው መረጃዎች የተነሳ በሚፈጠሩ ችግሮች የበላይ አዛዦች እና መኮንኖች እንዲሁም ተራ ወታደሮች ቅራኔ ውስጥ እየገቡ መሆኑ ታውቋል::የሰራዊቱ አባላት …

በደቡብ ምስራቅ እዝ የረሃብ አድማ ያደረጉ ወታደሮች ሲታሰሩ በስሜን እዝ ሊደረግ የነበረው ግምገማ እንደሰረዝ ተወስኗል:: Read more »

ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) *ለጉበት ጤናማነት ቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው። *ከሳንባ ጋር ተያያዥ ችግሮችን ይከላከላል ቀይስር ቫይታሚን ሲ በውስጡ ስለያዘ የአስም ምልክቶች እንዳይነሱ ይረዳል፣ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርም ያግዛል። …

ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች Read more »

የጨጓራ ሕመምዎን ለማስታገስ የሚጠቅሙ የጤና ምክሮች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም) • ከጥጋብ በላይ አለመመገብ • ምግብን በዝግታ መመገብ • ቅባታማ ምግቦችን ማስወገድ • ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ • ሲጋራ ያለማጤስ • ቡና፤አልኮል እና የለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር • የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል …

የጨጓራ ሕመምዎን ለማስታገስ የሚጠቅሙ የጤና ምክሮች Read more »

የድድ መድማት (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) የድድ መድማት የድ ድ ላይ ችግርን እንዲሁም ከባድ ለሚባሉ የጤና እክሎች መዳረጋችንን ጠቋሚ ምልክት ሊሆን ይችላል። ✓ የድድ መድማትን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች አንዱና ዋነኛ ምክንያት የድድ መቆጣት (inflamed gums) ወይንም ጅንጂቫይተስ (Gingivitis) ነው። በድድ መካከል …

የድድ መድማት Read more »

ሰሞኑ የኦሮሞ ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት በማድረግ የኦፌኮ_መድረክ ምክትል ሊቀ መንበር ኣቶ በቀለ ገርባ የሚገኙባቸው በመቶ የሚቆጠሩ ወጣቶችና ፖለቲከኞች እያሰረ መሆኑ፣ ትናንት ደግሞ የኦፌኮ_መድረክ ዋና ፀሓፊ ኣቶ በቀለ ነጋ ድብደባና ዛቻዎች እንደ ደረሳቸው ፤ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣት …

ህወሓት ወጣቶችን ልታስር ተዘጋጅታለች። Read more »

የሰማያዊ ፓርቲ ምስረታ !  =  ይድነቃቸው ከበደ ሰማያዊ ፓርቲ ታሕሳስ 22 ቀን 2004 ዓ.ም በይፍ የተመሰረተበት ቀን ነው፡፡የፓርቲያችን የ4 ዓመት ጉዞ እና በሂደት ያጋጣሙ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ፣ለፓርቲያችን የወደፊት እንቅስቃሴ በጎ አሰተዋጾ እንደሚኖረው እምነቴ ከፍ ያለ ነው፡፡ ፓርቲችን ከተመሰረት 4 …

የሰማያዊ ፓርቲ 4ኛ አመት ምስረታ ! ይድነቃቸው ከበደ Read more »

‹‹መንገዶች ሁሉ ወደ መስጊዶች ያመራሉ!›› በሚል መሪ ቃል ነገ ጁመዓ ታህሳስ 22/ 2008 የመጀመሪያ ክፍል የሆነውን መርሀ ግብራችንን በይፋ እንጀምራለን!!! ድምፃችን ይሰማ ‪#‎1460DaysOfPeacefulStruggle‬ ‪#‎EthioMuslimPeacefulStruggle‬ ለፍትህ ስንል ለአራት አመት በጽናት የቆምንበትን ትግላችንን የምንዘክርባቸውን መርሀ ግብሮች በተጠናከረ መልኩ እንተገብራለን!የመጀመሪያ ክፍል የሆነውን መርሀ …

‹‹መንገዶች ሁሉ ወደ መስጊዶች ያመራሉ!›› በሚል መሪ ቃል ነገ ጁመዓ ታህሳስ 22/ 2008 የመጀመሪያ ክፍል የሆነውን መርሀ ግብራችንን በይፋ እንጀምራለን!!! ድምፃችን ይሰማ Read more »

#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ :በሃረርጌ ክፍለሃገር የገበሬዎች እና ተማሪዎች ተቃውሞ በድጋሚ ተቀስቅሷል::የአቶ ሙክታር ከድር አማካሪ ወንድም በአግኣዚ ወታደሮች ተረሸኑ:: ሞት የባለስልጣናቱንም በር ማንኳኳት ጀመረች:: ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በሃረርጌ ክፍለ ሃገር በመቻሬ እና አከባቢው ከገጠር እና ከከተማው የተሰባሰቡ ገበሬዎች እና …

የአቶ ሙክታር ከድር አማካሪ ወንድም በአግኣዚ ወታደሮች ተረሸኑ:: በሃረርጌ ክፍለሃገር የገበሬዎች እና ተማሪዎች ተቃውሞ በድጋሚ ተቀስቅሷል:: Read more »