“መፍትሄ ያጣው የቡዳ ፖለቲካችን”
“የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች” በሚል ርዕስ አንጋፋው ፖለቲከኛና የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር ዶ/ር መረራ ጉዲና ሰሞኑን ለንባብ ካበቁት ሁለተኛ መጽሐፋቸው የተቀነጨበ
… የቡዳ ጉዳይ በሀገራችን ባሕል ውስጥ የታወቀ ስለሆነ ለማስረዳት ዝርዝር ውስጥ አልገባም፡፡ ቡዳና ፖለቲካችንን ምን አገናኛቸው ለሚለው ጥያቄ ግን ተገቢ መልስ መስጠት ስለአለብኝ አንዳንድ ጭብጦችን ላስቀምጥ፡፡ ተረቱ እንደሚለው፣ አንድ ቡዶችን ለይቶ የማያውቅ ሰው፣ የቡዶች መንደር ይደርስና፣ “እዚህ አካባቢ የቡዶች መንደር አለ ይባላል፣ የትኛው ነው” ብሎ ራሱን፤ ቡዳውን ይጠይቀዋል፡፡ ቡዳው ሰው፣ “ቡዶች የምንባለው እኛው ነን” ለማለት ድፍረት ስላጣ፣ “እኛ እዛ ማዶ ያሉት ናቸው እንላለን፣ እነሱ ደግሞ እኛን ይሉናል” አለ ይባላል፡፡
ላለፉት አርባ ዓመታት ለውጥ ለመምጣት ከአንድ ትውልድ በላይ ቀላል ያልሆነ መስዋእትነት ተከፍሎዋል። የሀገራችን ፖለቲካ ባለህበት እርገጥ ከመሆን፣ አንዳንዴ ደግሞ የኋሊት ከመሄድ አላለፈም፡፡ ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ለፀረ – ቅኝ አገዛዝ ትግል ከከፈሉት በላይ ሀገራችን ውድ ዋጋ ከፍላለች፣ የታሰበው ለውጥ ግን አልመጣም፡፡ እዚህ ላይ ዋናው ጥያቄ ለሀገራችን ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞ ኃላፊነቱን የሚወስደው ማነው? የሚለው ነው። ቢያንስ አንዱ በሌላው ላይ ጣት ከመቀሰር አልፎ የየድርሻችንን እንኳ እንውሰድ ሲባል አይታይም፡፡ እንደቡዳው፤ ስህተት የሠራሁት እኔ ነኝ ከማለት ይልቅ፤ አጥፊዎች እነዛ ናቸው ማለት ይቀላል፡፡ የአንድ ትውልድ ምርጦችን ያለርህራሄ የጨፈጨፈው መንግሥቱ ኃይለማርያም እንኳ “ሰው ይቅርና ዝንብ አልገደልኩም” ነበር ያለው፡፡ ተባባሪዎቹ የነበሩ የደርግ ባለሥልጣናትም ያንን አስከፊ ግፍ የፈጸምነው “የሀገር ፍቅር ያንገበገበን ወታደሮች ነበርን” እያሉ መጽሐፍ እየጻፉ ነው፡፡ የጥፋት ኃላፊነቱንም በሌሎች ላይ እየደፈደፉ ነው፡፡ ቢያንስ ብዙዎቹ በድንቁርና ለጨፈጨፉዋቸው ዜጐች ኃላፊነቱን ለመውሰድ አልተዘጋጁም፡፡ እውነቱን ለመናገር እኔም ባለፈው ጊዜ በጻፍኩት መጽሐፌ ላይ የነገሮችን ሚዛን ለመጠበቅ በጣም አስቸግሮኝ እንደነበረ አስታውሳለሁ። ለአብነት፤ የቀድሞ የመኢሶን ጓዶቼ ከኢሕአፓ ጋር አመሳሰልከን የሚል ቅሬታ እንዳላቸው ነግረውኛል። ታሪክ ፀሐፊዎች ስለ አንድ ድርጊት እርግጠኛ ሆነው መጻፍ ያለባቸው የድርጊቱ ተሳታፊዎች ሲሞቱ ነው የሚሉት የገባኝ አሁን ነው፡፡
አንድ ቀን ከቀድሞ የሕወሓት አመራር አባል ጋር ስለዚህ ጉዳይ አንስተን ስናወራ ለተሠሩት ስህተቶች የኃላፊነት ደረጃ ለድርጅቶች ስጥ ብትለኝ ደርግ አንደኛ፣ ሕወሓት ሁለተኛ፣ ኢሕአፓ ያንተ ድርጅት ስለሆነ ነው ወንጀሉን ያስነሳከው” አለኝ፡፡ የቀልድም ይሁን፤ የምር አስተያየቱ ቢያናድደኝም፣ ገርሞኛል፡፡
በእኛ ትውልድ ስላየናቸው የአፄ ኃይለሥላሴ፣ የደርግና የኢሕአዴግ መንግሥታት የትኛውን ትመርጣለህ ቢባል፣ የየዘመኑ ተጠቃሚ ያለምንም ጭንቀት እራሱ ተጠቃሚ የነበረበትን ሊመርጥ እንደሚችል ይገመታል። በሕዝብ ደረጃ ሲታሰብ ግን፤ እንደጊዜው ሁኔታ ሊታይ እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ ከቀይ ሽብር በኋላ፣ አብዮቱ የደርግ መንግሥት ጭፍጨፋ እየመረረው ሲመጣ ብዙ ወጣቶች፤ “ተፈሪ ማረኝ፣ የደርጉ ነገር ምንም አላማረኝ” ሲሉ መስማቴን አስታውሳለሁ፡፡ ይህ ምርጫ እንደየ ማህበረሰቡም ሊለያይ ይችላል፡፡ ኦሮሚያና ደቡብ ውስጥ፣ ከዝንጀሮ ቆንጆ…ቢሆንም የደርግ መንግሥት ሊመረጥ ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ውለታ ይሁን፣ የደርግ መንግሥት፣ የመሬት አዋጅ በእነዚህ አካባቢዎች እስከ ዛሬም ድረስ እጅግ በጣም ሰፊ ድጋፍ አለው፡፡
የቡዳ ፖለቲካችንን ከሁሉም በላይ አስቸጋሪ የሚያደርገው ሁሌም ጥፋተኞች እኛ ሳንሆን እነዛ ናቸው ብለን ስለምንደርቅ ነው፡፡ እዚህ ላይ ፈረንጆች የሚበልጡን በሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ነው፡፡ አንደኛው፣ ለነሱ ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ ጥፋት መቀበልን እንደሞት አያዩትም፡፡ ሁለተኛ፤ ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት አጥፍቶ መጥፋትን ከባህላቸው አስወግደዋል ወይም የኋላቀሮች አስተሳሰብ አድርገውታል፡፡ ቢያንስ ከሂትለር ወዲህ የአብዛኞቹ ጉዞ በዚህ አቅጣጫ ነው፡፡ ሦስተኛው፣ ፖለቲካቸው ሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሁሉንም አግኝ ወይንም ሁሉንም እጣ (Zero –sum-game) የሚባለውን ፖለቲካ ከልብ እየተው መጥተዋል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ከሥልጣን በኋላ፣ ጥሩ ኑሮ መኖርም፣ ክብር ማግኘትም እንደሚቻል አውቀዋል፡፡ እንደውም ከሥልጣን በኋላ ያለጭንቀት የተደላደለ ኑሮ መኖር እንደሚቻል ያውቃሉ፡፡ ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ንግግሩ የአፍሪካ መሪዎችን ለማስተማር የሞከረው ይህንኑ ነው፡፡ ትምህርቱ ገብቶት ይሁን፤ በተለመደው የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት የማስመሰል ፖለቲካ፤ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትርም ሲያጨበጭብ አይቻለሁ፡፡ …
(“የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች” በሚል ርዕስ አንጋፋው ፖለቲከኛና የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር ዶ/ር መረራ ጉዲና ሰሞኑን ለንባብ ካበቁት ሁለተኛ መጽሐፋቸው የተቀነጨበ
ትውልዱ የሥልጣን ናፍቆት ሣይሆን በቆይታቸው ለሚመጡት መዘዞች በተለይ ዝርፊያ ዘላቂ መፍትሄ የማፈላለግን መፍትሄ ሠጭ ሥለሚጠፋ ትውልዱ ይህን ማሥወገድ ግድ ይለዋል።
እባካችሁ:-
ደቡብ ምእራብ ምሥራቅ ሠሜን እንደፖለቲካ ማማተቡ መፍትሄን አያመጣም ግን እነዚህን ዋልታዎች ሥናሠባሥብ ሀገር ትሆናለች የተናጥል ፀሎት ይብቃን።
” Buda”, hmmm…
It seems the professor likes this word, for whatever reason. For example i have more than ones heard him saying that word on G7 radio or ESAT.
“Buda” is actually a more than average or supernatural ability, so Ethiopian politics would be good if so.
I have yet to read the article, upto this point i have only read the title.
So, why do things go wrong, and for so long, in Ethiopia ?
I think to answer this question looking at Ethiopia alone is not sufficient. That sounds like the question “why is Africa poor ?” and then to try to answer the question based on the situation in Africa alone.
That would be naive.
Ferenji tricksters have often tried to answer such a question and have often said it is because Africans are dumb. The ferenji tricksters say that despite their knowledge that it is them who pull the strings in Africa.
The last few years since the economic crisis began in ferenji lands in 2008 we have learned about so many things we had no idea before.
So i would pay attention to foreign actors to explain problems in Ethiopia. Lets not forget, USA brought TPLF to power in Ethiopia, and USA very well knew about the nature and plans of TPLF before bringing it to power.
Ex-CIA agent: every conflict in the world begins in the USA congress.
Listen at 39:21
https://www.youtube.com/watch?v=CBdKLHtpk5A
https://www.youtube.com/watch?v=0CofEbxtIxI&feature=youtube_gdata_player
1. ፈረንጆች የሚበልጡን በሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ነው፡፡ አንደኛው፣ ለነሱ ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ ጥፋት መቀበልን እንደሞት አያዩትም፡፡ ሁለተኛ፤ ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት አጥፍቶ መጥፋትን ከባህላቸው አስወግደዋል ወይም የኋላቀሮች አስተሳሰብ አድርገውታል፡፡ ቢያንስ ከሂትለር ወዲህ የአብዛኞቹ ጉዞ በዚህ አቅጣጫ ነው፡፡ ሦስተኛው፣ ፖለቲካቸው ሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሁሉንም አግኝ ወይንም ሁሉንም እጣ (Zero –sum-game) የሚባለውን ፖለቲካ ከልብ እየተው መጥተዋል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ከሥልጣን በኋላ፣ ጥሩ ኑሮ መኖርም፣ ክብር ማግኘትም እንደሚቻል አውቀዋል፡፡ እንደውም ከሥልጣን በኋላ ያለጭንቀት የተደላደለ ኑሮ መኖር እንደሚቻል ያውቃሉ፡፡
It seems this prof has positive views about ferenjis, the same people who put TPLF on the shoulder of Ethiopians for 25 years. Ferenjis are hated in Africa these days, and they should be hated in Ethiopia too, maybe even more so. How come he has sympathies for a people who are the cause of so much suffering to his people ?
Another point, ferenjis have the worst history in the world, also regarding the process to create a working political system. I am not just talking about Hitler and Holocaust, in places like Sweden, Denmark, Norway and France barbarism was the rule of the day. The Spaniards, Belgians, Italians and others committed barbaric crimes against non-ferenjis such as in DR Congo and Ethiopia. So they have gone through far worse than any other people before reaching this stage. Also, though ferenjis may have now a relatively good system in their countries, they deny the same to other peoples such as for Ethiopians. It was ferenjis who imposed the TPLF apartheid system on Ethiopians. So in view of this horrible background of ferenjis to laud ferenjis is to insult their victims in Ethiopia and elsewhere.
2. ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ንግግሩ የአፍሪካ መሪዎችን ለማስተማር የሞከረው ይህንኑ ነው፡፡
Here also, it is wrong to laud hypocrite Obama for saying that while at the same time he is imposing TPLF on Ethiopians and even went as far as calling it democratic, an insult to the oppressed Ethiopians.