“ለሕጋዊ” ሕግ አልባ ምላሽ !
“ለሕጋዊ” ሕግ አልባ ምላሽ ! Yidnekachew Kebede
……………………
“ ማንኛውም ዜጋ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን መግለጽ ይችላል ፤ሕጋዊ መብቱ ነው፡፡በእኛ አገር ግን ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ ሕግ-አልባ የሆነ፤በገዢው መንግሥት ፍላጎትና ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ሕገ-ወጥ አፈና ነው፡፡”
———————————
ተቃውሞ የዴሞክራሲ መገላጫ ነው! የመንግሥት አስተዳደር ጤናማነት መለኪያ ጭምር ነው፡፡ዴሞክራሲ በራሱ እጅ እግር ኖሮት የሚንቀሳቃስ ፍጡር አይደለም፤ዴሞክራሲ በሐሳብና በተግባራ በሰዎች የሚከወን መሠረታዊ መብት ነው፡፡ከመብቶች መካከል ደግሞ “መቃወም !” አንዱ ነው፡፡
ተቃውሞ በግለሰብ፣በቡድን እና በተቋም ደረጃ ሊከናወን ይችላል፤የሚቻለውን ነገር ለማደረግ የአመለካከት ነፃነት በቅድሚያ መኖር አለበት፡፡የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 29 ንዑስ-አንቀፅ 1 ይህንኑ ይደግፋል፤ “ማንኛውም ሰው ያለምንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል፡፡”
ድንጋጌው ግን ለውህሓት/ኢህአዴግ የመንግሥት አስተዳደር፣አቀበት እንደመውጣት ነው፡፡ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሠራተኛ ግምገማ መመዘኛ ከሆኑት ውስጥ አንዱ “አመለካከት” ነው፡፡ከሥራ አፈፃፀም በላይ የፖለቲካ አመለካከት የደሞዝ እና የደረጃ እድገት ያስገኛል/ያሳጣል፡፡የትኛውም ሰራተኛ በተመደበበት ሙያ የቱንም ያህል ችሎታ እና የአፈጻጸም ብቃት ቢኖረውም “አመለካከቱ”በምዘናው መሠረት ዝቅተኛ ከሆነ ዋጋ የለውም፡፡ ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት የመያዝ መብቱ በውህሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የሚደፈጠጠው ከዚህ ጀምሮ ነው፡፡ሌሎች ቡዙ ማሳያዎች ያሉ ቢሆንም ይሄን እንደ-ምሣሌ መውሰድ ይቻላል፡፡
የመንግሥት ጫና ተቋቁሞ፣ የአመለካከት ነጻነት በግለሰበ ጥረት እሁን ለማድረግ ቢፈለግ፣ ቀጥሎ የሚመጣው ሃሳብን መግለፅ ነው፡፡ለዴሞክራሲ እድገት እና ሞት ንጽጽሩ ፣ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ማክበር ወይም አለማክበር ነው፤ ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም፡፡ ተግባራዊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 2 “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው” ይላል፡፡ ይህ ነጻነት የግዛት ወሰን የለውም፣በማንኛውም ዘዴ ሐሳብን ማሰራጨት በሕግ የተቀመጠ መብት ነው፡፡
ሐሳብን ከመግለጽ ጋር በተያያዘ የሰማሁት አንድ ነገር ትዝ ይለኛል፤ነገሩ የተከሰተው በአንድ የመንግሥት መስሪያ ቤት ውስጥነው ፡፡ እና በመሥሪያ ቤቱ በተደረገ ግምገማ ላይ-ነው አሉ-አንዱ ሠረታኛ ተራው ይደርስና “አመለካከቱን” ይገልጻል፤በኋላ በእርሱና በገምጋሚዎቹ መካከል ሰፊ ክርክር ተደረግ፤ክርክሩ፣ተገምጋሚው ያልገለጸውን አመለካከት፣ለመግለጽ አስበኻል በሚል የተነሣ ክርክር ነበር አል፤ይህቺ ቁም-ነገር ያዘለች ቀልድ/ጨዋታ፤ህውሓት/ኢህአዴግ አይደለም ሐሳብ ተገልጾ ፣ያልተገለጸ ሐሳብ እንኳ ምንኛ እንደሚያሸብረው የምትጠቁም ነች፡፡(“አዎ፣ሐሳቡን አስቤአለሁ፤”የሚለው የቀልዷ ማሰረጊያ ነች፤ “ተጸጽቻለው፤ግለ-ሒሴን አውርጃለው” ነው እንግዲህ፡፡)
ሐሳብ መግለጽ ይቅርና ፣ሐሳብን ማሰብ በራሱ ሐሳብ የሆነብን እኛው ነን !በእኛ አገር ሐሳብን በነፃነት መግለፅ ለእስራት፣ሞት፣አገር ጥሎ ለመሰደድ በቂ ምክንያት ነው፡፡ ለዜጎች የሚሆንን ነገር በግድ የሚመርጥልን፣ ማሰብ ያለብንን ሐስቦ “እንዲህ እንዲህ ”መሆን አለበት የሚለን መንግሥት ለእኛ ምናችን ነው ? ምንም ! ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ የሐሳብ ማሰራጫ ተቋማት በእጁ ናቸው! ለመረጣቸው ‹ጋዜጠኞች› ‹ይሄን አድርጉ!እንዲህ በሉ!› እያለ እንዳሻው የመዘወር ‹ሥልጣን› ብእጁ ነው!‹እነዚህ፣እነዚህ ሚዲያዎች ‹ፀረ-ምናምን….ናቸው እያለ የመፈረጅ ‹ሥልጣን›የእርሱ!‹አንተ አሸባሪ! እሱ አሸባሪ!› የማለት ‹ሥልጣን› ያለው በእጁ!
በአንድ ጤናማ የዴሚክራሲ ሒደት ውስጥ፣ ማንኛውም ሰው በራሱ አመለካከቱ ለደረሰበት ድምዳሜ መሠረት ሕጋዊ ተቃውሞውን ሆነ ደጋፉን ፣ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመግለፅ መብቱ በእኛ አገር ሕግ ላይ ብቻ ሳይሆን፤በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ዴሞክራሲያዊ መብት ነው፡፡ይህ መብት በሕግ ከፍተኛ ከለላ የተሰጠው ጭምር ነው፡፡በእኛ አገር ሕገ-መንግሥት የመሰብሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት የተጠበቀ ነው፡፡በዚህም መሠረት መቃወም የተቃወሙትን ነገር በሰልፍም ሆነ በስብሰባ መግለፅ የሕግ ከለላ አለው፡፡
መንግሥት የሕዝብ መብት ለመጠበቅ የቆመ የሕዝብ አገልጋይ ነው !ሕዝብ በመንግሥት ቅር ከተሰኘ የምርጫን ዘመን ጠብቆ ፣ኃላፊነት ከመስጠትና ከመንፈግ ባላፈ ፣በማንኛውም ጊዜና ቦታ ፣በመንግሥት ላይ ያለውን ተቃወሞ እና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ይሁን እንጂ የውህሓት/ኢህአዴግ የመንግሥት አስተዳደር ለአቅመ ትችት እና ተቃውሞ ያልደረስ ነው ፣ እንደሚባለው፤ የእውነትም “ድንክዬ ”መንግሥት ነው፡፡
የአገዛዙን ሥርዓት ለመደገፍ የሕዝብ ሀብት ከሆኑ ንብረቶች ጀምሮ፣እስከ ግለሰብ ደረጃ የውዴታ ግዴት እንዲገቡ በማድረግ ፣በሚያስፈልጋቸው ቦታና በወደዱት ሰዓት፣ ካለከልካይ የተፈለገው ነገር ሁሉ ይደረጋል፡፡ ደስ ካላቸውም በመገናኛ ብዙኃን የቀጥታ ስርጭት ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡የሚገርመው ነገር የአገዛዙን ሥርዓት በመቃወም የተጠራ ሰልፍ ወይም ሰብሰባ ከላ፣ በሕዝብ ሀብት በሚተዳደሩ የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ‹ሰልፍ/ስብሰባ እውቅና ያልተሰጠው ስለሆነ ማንም እንዳይሳተፍ ፤ለመሳተፍ ቢሚሞክሩት ላይ ፖሊስ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል›በማለት ያስፈራራል፡፡
ማንኛውም ዜጋ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን መግለጽ ይችላል፤ሕጋዊ መብት ነው፡፡ በእኛ አገር ግን ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ ሕግ-አልባ የሆነ፣በገዢው መንግሥት ፍላጎትና ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ሕገ-ወጥ አፈና ነው፡፡የዚህ ዓይነቱ ሥርዓት መንሰሄ የአስተዳደር አቅም ማነሰን ያሳያል፡፡ በሕዝብ ትከሻ ላይ ተቀምጦ የሕዝብ ቅሬታን ለመቀበል ፍቃደኛ የአለመሆን ውጤት “የለሁበትም!…….የለሁበትም !….” እንዳይሆን!
“ዲሞክራሲ ማለት ምን ማላት ነው ?” ከሚለው መጽሐፍ የቀነጨብኩት አስፍሬ ጽሑፌን አበቃለው፡፡ “በመራጩ ሕዝብ ስምምነት ላይ የተመሰረተ መንግሥት በሙሉ ልቦና የመናገር እና የመወሰን ሥልጣንና ኃይል ይኖረዋል፡፡ይህ ልበሙልነት በወታደራዊ ኃይል ለተጨበጠ ሥልጣንና በሕዝብ ላልተመረጠ መንግሥት በቀላሉ የሚገኝ አይደለም፡፡”
ኢትዮጵያ አልታደለችም ሁሉም ማለት ባልችልም አብዛሀኛው ለህሊናው ሳይሆን ለሆዱ ያደረ …እሱ ከጠገበ በወንድሙ ርሀብ የሚስቅ(የሚደሰት) ማፈሪያ ትውልድ እኔማ ተቃጠልኩ…በምን አትሉኝም…ከ19-97አ/ም…ጀምሮ አንድም ለህዝብ የሚያስብ ተቃዋሚ ፓርቲ አለመኖሩ አዝናለሁ……ብቻ ተቃዋሚ ፓርቲ አለ እንዳትሉኝ ……ወያኔ በዘር የከፋፈለን አለበቃ ብሎ ……53 ፓርቲ ተመስርቶ …53 ጠቅላይ ሚንስትርነት ይገኝ ይመስል ሁሉም ለስልጣን ሽሚያ ሆነ…ያሳዝናል…አንዱን ሳልይዘው ጡቴ ወደቀ አለች አሉ…………አንድ ስራ ሳይሰሩ መነታረክ ብቻ…ለዚች ሀገር ውድቀት አንደኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ተብየዎች ናቸው:: እኔ በወያኔ አልፈርድም …ምክንያቱም አልሞት ባይ ተጋዳይ ስለሆነ………………………ተቃዋሚወች ቢመከሩም ውሀ ቢወቅጡት ……………ነው ነገሩ አይረቡም:: እኛ ካሰብነው እግዚአብሄር ይህችን ጭቁን ሀገር ወያኔ የሚባል ተምች ያጥፋላት…አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጭምር……………………………እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይባርክ……!
በጣም እኔም ተቃጠልኩ ወንድማለም ! ! ! ምን ታረገዋልህ ? ? እድገቴ ከወሎ ክ/ሃገር ውጭ ቢሆንም ኃይቅን በደምብ አውቅልሃለሁ።በጀልባ ተንሳፍፌ ያችን የምታምር ደሴትና በውስጧም የነበረውን ሕይወት የሚያድስ ጨፌና የቡና ተክሎች አልረሳቸውም። እውነትም እንደተባይ ያለምንም ራዕይ ለሆዱ ብቻ የሚርመሰመሰውን ሽባ የሆነ የተቃዋሚ መንጋ ከወያኔ ጋር ያውድመው ሰማያዊን ጨምሮ።በመጨረሻም ተስፋ እንዳትቆርጥ ወንድሜ።እግዚአብሔር/አላህ ዝም አይልም።
ለበጉም ለተኩላውም መልካም የገና በአል ይሁን!!!
” የደቡብ ወሎ ልጅ(ሀይቅ) says:January 4, 2016 at 4:34 pm
ኢትዮጵያ አልታደለችም ሁሉም ማለት ባልችልም አብዛሀኛው ለህሊናው ሳይሆን ለሆዱ ያደረ …እሱ ከጠገበ በወንድሙ ርሀብ የሚስቅ(የሚደሰት) ማፈሪያ ትውልድ እኔማ ተቃጠልኩ…በምን አትሉኝም…ከ19-97አ/ም…ጀምሮ አንድም ለህዝብ የሚያስብ ተቃዋሚ ፓርቲ አለመኖሩ አዝናለሁ……ብቻ ተቃዋሚ ፓርቲ አለ እንዳትሉኝ ……ወያኔ በዘር የከፋፈለን አለበቃ ብሎ ……53 ፓርቲ ተመስርቶ …53 ጠቅላይ ሚንስትርነት ይገኝ ይመስል ሁሉም ለስልጣን ሽሚያ ሆነ…ያሳዝናል…አንዱን ሳልይዘው ጡቴ ወደቀ አለች አሉ…………አንድ ስራ ሳይሰሩ መነታረክ ብቻ…ለዚች ሀገር ውድቀት አንደኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ተብየዎች ናቸው:: እኔ በወያኔ አልፈርድም …ምክንያቱም አልሞት ባይ ተጋዳይ ስለሆነ………………………ተቃዋሚወች ቢመከሩም ውሀ ቢወቅጡት ……………ነው ነገሩ አይረቡም:: እኛ ካሰብነው እግዚአብሄር ይህችን ጭቁን ሀገር ወያኔ የሚባል ተምች ያጥፋላት…አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጭምር……………………………እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይባርክ……! ”
A shallow analysis by a shallow person.
The world is more complicated than that. And we appreciate the many sacrifices paid by the opposition, such as Qinijit, Meiad, Andinet and Semayawi.
That they are not yet successful only means that they are confronting and being sabotaged by the most evil power in the history of the world, USA.
TPLF is being protected by USA.
These so-called Ethiopians in USA dont alert Ethiopians of the grave danger USA poses to Ethiopia, and also to all blacks.
USA policy towards Ethiopia since 1945 was that of containment, that means:
1. to prevent industrialization
2. to prevent investments (that it allowed in Japan, South Korea, Taiwan etc)
3. to distabilize
4. to impose hostile economic policies through IMF and world bank
5. to block the possibility to borrow money from the international market etc
The containment policy of USA against Ethiopia is racially motivated and its intention is to keep all black countries unindustrialized, poor and weak.
So far the USA is successful.
USA for example excluded Ethiopia as the only allied country from reconstruction programs after the end of world war 2, but included foes like Germany and Italy.
Now for decades the USA prevents the return of skilled and educated Ethiopians from the West back to their country of origin. USA is letting them get old in the West to prevent them from using their skills and knowledge (also capital) for the benefit of the Ethiopian society, like the Indian and Chinese returnees did for their countries.
Ex-CIA agent: every conflict in the world begins in the USA congress.
Listen at 39:21
https://www.youtube.com/watch?v=CBdKLHtpk5A
Nazi USA / CIA were behind:
1. the so-called Ethiopian Students Movement
2. overthrow of Haile Selassie
3. overthrow of Derg
4. separation of Eritrea
5. landlocking of Ethiopia
6. introduction of tribalism and killils in Ethiopia as initial steps to dismantle Ethiopia
7. the failure of the Qinijit revolution in relation to the 2005 elections.
ኢትዮጵያዊ ሣይሆን ኢትዮጵያ የገዛ መለስ ዜናዎ
ወያኔ ዘረኞና ጠባብ መሆኑ ቀድመን እናውቃለን
ኢትዮጵያ ሃገሬ ሳይል የሞተው የነጭ ሽብር ጠንሳሽ መጨርሻ ስልጣን የያዘው ትውልድ ቀይሽብርን አስወግዶ የጎሳ መርዙኑ እረጭቶ አሁን ኢትዮጵያን የግዛት አንደቶን አፍርሶ በአሜረካና ከእንግለዚ የሥለላ ድርጅት በመታገዝ ኢትዮጵያን ድሃና ለማኝ አደረጎት
ሳተናው አሊ