“ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የምንሸጋገርበት ትግል ላይ ነን” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር

የሰማያዊና ኦፌኮ ፓርቲ አባላትና አመራሮች መታሰራቸውን ሰማያዊ ፓርቲ ያወገዘ ሲሆን፤ “አሁን የፓርቲ ፖለቲካ የምናደርግበት ጊዜ ላይ አይደለንም፤ ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የምንሸጋገርበት ትግል ላይ ነን” ብለዋል የፓርቲው ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፡፡

“ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የምንሸጋገርበት ትግል ላይ ነን”                 ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር
የሰማያዊ አመራሮች ባለፈው ረቡዕ በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፤ በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች መገደላቸውንና በርካቶች መታሰራቸውን በመጥቀስ “መንግስት ፋና ወጊ የሆኑትን ተራ በተራ እየለቀመ የእሳት እራት እያደረጋቸው ነው” ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ የፓርቲው ልሳን የሆነው የ“ነገረ ኢትዮጵያ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፣ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው፣ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው ዮናታን ተስፋዬ፣ የፓርቲው አባላት፡- ቴዎድሮስ አስፋው፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬና ፍሬው ተክሌ መታሰራቸውን የጠቆመው ሰማያዊ፤ የታሰሩት አባላት ፍ/ቤት ቀርበው፣ ፖሊስ በሽብር ወንጀል እንደጠረጠራቸው በመግለፅ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል ብሏል፡፡
በቅርቡ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ዙሪያ ለፓርላማ ያደረጉትን ንግግር የተቹት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል፤ “ጠ/ሚኒስትሩ  ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያውያን የሱዳንን ድንበር የደፈሩ አስመስለው ዜጎችን “ሽፍቶች” በማለት የማይረሳ ታሪካዊ የክህደት ምስክርነት ሰጥተዋል” ሲል ብለዋል፡፡

4 Comments on ““ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የምንሸጋገርበት ትግል ላይ ነን” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር”

  1. ende !!! ye Hizb GENZEB MEZEBERACHU EYETEBALE NEW EKO

    KKKK

    ENDET NEW NEGERU ??

    MINUN NETSA WETYANEW ß

    rasachun netsa awtu abo !!!

  2. Ambulans kemakatel belay min shibir ale rasachihun wusitachihun merimiru ethiopia netsa kewotach 27 amet honat selamachinin atawukubin

  3. Is this guy really normal ?
    what a deformed face ! Most of
    the time people with ugly faces or
    appearance have an inferior complex take
    Reiyot Alemu she has the same
    complex problem. I think its their inner complex
    that makes them anger .

  4. First he has to be loyal to his party first. Shame on him because of he steals money from his party money deposit. That is why ethiopian people always vote EPRDF. Ethiopian people is the magic people no one can cheat this magic people.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*