የደቡብ አፍሪቃው «ዑቡንቱ» ፣
በሥነ ቴክኒክ የመገናኛ አውታሮች መስፋፋት ረገድ፣ ከሁሉም ክፍላተ ዓለም በአዝጋሚነት የሚጠቀሰው የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ነው።
በሥነ ቴክኒክ የመገናኛ አውታሮች መስፋፋት ረገድ፣ ከሁሉም ክፍላተ ዓለም በአዝጋሚነት የሚጠቀሰው የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ነው።
የኒውዮርክና የፍራንክፉርት የፊናንስ ገበዮች ትናንት ታሪካዊ ግምት የሚሰጠው ውሕደት ለማስፈን ተስማምተዋል።
ህዝባዊ አመጽ በግብፅና ቱኒዚያ ከተቀጣጠለበት ጊዜ አንስቶ ሁኔታዎች በቻይናም ሊገነፍሉ የደረሱ ይመስላል። አንድ ቻይናዊ ፖለቲከኛ ነገሮች በኛም ሀገር በቋፍ ላይ ነው ያሉት ሲሉ ገልፀዋል። በእርግጥ በግብፅና ቱኒዚያ የተከናወነው አይነት ህዝባዊ አመፅ በቻይናም ቢቀጣጠል ምን ይከሰት ይሆን?
(መሀመድ ሰልማን) አዲግራት ነው ያለሁት፡፡ 35 ኪሎ ሜትሮችን ወደ ሰሜን ፈቀቅ ብል ኤርትራ ገባሁ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱ በማይገባኝ መልኩ ጥሎብኝ አሥመራን እናፍቃታለሁ፡፡ አይቻት ግን አላውቅም፡፡ “የማያውቁት አገር እንዴት ይናፍቃል?!” አትበሉኝ፡፡ ተረቱ የማይሰራበት ጊዜ ካለስ? ናፍቆቴን በከፊል ለማስታገስ ወደ ድንበር መጠጋት …
በሊቢያ የቤንጋዚ ወደብ ከተማ መንግስትን በመቃወም ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች፡ በፖሊስ እና በመንግስት ደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አስራ አራት ሰዎች ቆሰሉ።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መንግስት በንግዱ ዘርፍ ላይ የጠበቀ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላም ንግግር በሰፊው ያተኮረው በኑሮ ውድነት ላይ ነው። በተጨባጭ የአንዳንድ ሸቀጦቹን ዋጋ ጣራ መንግስት ያወጣ ሲሆን፤ በመንግስቱ መመሪያ ገበያው …
የጅምላ አስመጭዎች አሰራራቸውን ካላሻሻሉ መንግስት በቀጥታ አስመጥቶ ሊያከፋፍል ተዘጋጅቷል Read more »
የምርምር ጋዜጠኞችን በመጨቆን አፍሪቃ ቀዳሚዉን ስፍራ እንደያዘች ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ CPJ አስታወቀ።
በኤርምያስ ህሩይ የግሪጎሪያኑ አዲስ ዓመት 2011 ከገባ ገና ሁለተኛ ወር ባይገባደድም አመቱን ልዩና ታሪካዊ ሊያሰኙ የሚይስችሉት በርካታ አስገራሚ ክስተቶች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በመከናወን ላይ ናቸው። ከታሪካዊ ክስተቶቹ መካከል በከፍተኛ ደረጃ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት የሳበውና ፈርጀ ብዙ አንድምታ ያለው ሕዝቦች …
– ስለ አደጋው መንስዔ አይናገርም በቃለየሱስ በቀለ በቤይሩት አቅራቢያ ባለፈው ዓመት ጥር 17 ቀን 2002 ዓ.ም. ድንገተኛ አደጋ የደረሰበት የኢትዮጰያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን የአደጋ መንስዔ ለማወቅ የሚደረገው የአደጋ ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ባለፈው ቅዳሜ በሊባኖስ ትራንስፖርትና ሥራ ሚኒስቴር …
“የቀጣና ስምሪትና የመለዋወጫ ዋጋ መናር ለኪሳራ ይደርገናል” የሚኒ ባስ ባለንብረቶች“ኀብረተሰቡ ትክክለኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት አለበት” የትራንስፖርት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት በታደሰ ገብረ ማርያም
‹‹የተለየ እጥረት የተከሰተው በሰው ሠራሽ ችግር ምክንያት ነው›› የሐረሪ ክልል ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት‹‹የክልሉ የውኃ ችግር ከመጋቢት ወር ጀምሮ ሊፈታ ይችላል›› የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በታምሩ ጽጌ
በጋዜጣው ሪፖርተር የምዕራብ ሶማሌ ነፃነት ግንባር በመባል የሚታወቀው አማፂ ቡድን ከፍተኛ አመራር ባለፈው እሑድ ሌሊት ተገደሉ፡፡
በታምሩ ፅጌ ግንባታውን ጨርሶ በቅርቡ ማምረት እንደሚጀምር እየተገለጸ ያለው በአል-ሀበሻ ስኳር ፋብሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በሚስተር ሞሲን ሙጂድ አብዲል መጂድ ሞት በተጠረጠሩ ግለሰብ ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሠረተ፡፡
በውድነህ ዘነበ ወ/ሮ ሕልምአየሁ በሪሁን ከሰባት ልጆቻቸው ጋር ለ11 ዓመታት ከኖሩበት ቤት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በኃይል ሲፈናቀሉ ጎረቤቶቻቸው በዕንባ ነበር የሸኟቸው፡፡
የብፁዕ አባታችንን የአቡነ ዜና ማርቆስን እረፍት ምክንያት በማድረግ በነጸብራቅ መጽሔት ልዩ እትም ላይ ባለፈው ዓመት ከወጡ ጽሑፎች የቅዱሳን ጻድቃን ሕይወት በፍጹም ሃይማኖት ተመሥርቶ በቅድስና ለእግዚአብሔር የተሰጠ በመሆኑ አምላካቸው እግዚአብሔርም ልዩ ሥራውን የሠራበት፣ ኃይሉን ያሳየበት፣ በረከቱን ያስተላለፈበትና ክብሩንም የገለጠበት ታላቅ ሕይወት …
“አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ፤ እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ።” (መዝ. 4፥3) Read more »
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ላይ ባወጣው መግለጫ ባለፈው የአውሮፓዊያን 2010 ዓመተ ምህረት በ1.25 ቢሊዮን ዶላር 32 ሚሊዮን ኩንታል እንደሸመተ ገልጿል። መጠኑ ከቀደመው የአውሮፓዊያን 2009 በ22 በመቶ በዋጋ ደግሞ በ30 በመቶ እንደጨመረና ሰማኒያ በመቶው ከታዳጊ አገሮች …
ዓመት እንደ ዋዛ የቅዱስ ሲኖዶስ ክብር ግርማ ሞገስ ጻድቅ ዜና ማርቆስ ባርኩን በአጸደ ነፍስ። ቀን ሲቆጠር ጊዜየመሮጡ አባዜግባ መሬት ምሡአፈርን ሳይቀምሱ። ሳምንት ሁለት ሳምንት ወራት እየበዛ ያሉ እየመሰለን ዓመት እንደ ዋዛ። ከእኛ ጋራ ሆነው ዘውትር ስናያቸው አብረን ውለን አድረን ከቶ …
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን ትናት ሰኞ (08. 06.2003 ዓ.ም.) አደባባይ መውጣታቸው ተዘገበ። ሰልፈኞቹ የኢራን መንግስትን ሲቃወሙ በአንፃሩ ለግብፅና ቱኒዚያ የዲሞክራሲ ንቅናቄ ድጋፋቸውን አሳይተውበታል። የኢራን የፀጥታ ሀይላት በሰልፈኛው ላይ ምህረት አልባ ርምጃ መውሰዳቸውም ተጠቅሷል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን በግብፅና ቱኒዚያ የተከናወኑ …
የአየር ንብረት ለዉጥ ከእለታዊ የአየር ሁኔታ መለዋወጥ ጋ የሚያገናኘዉ መሠረታዊ መገለጫ ቢኖርም አንድ ናቸዉ ማለት ግን አይደፈርም።
በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በዛሬው ዕለት 1485 ኛውን የነቢዩ መሀመድ የልደት በዓልን በማክበር ላይ ይገኛሉ።
ካላፉት 3 ቀናት አንስቶ የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ በቱኒዝያ ስደተኞች ተጥለቅልቃለች ። እነዚህ ቁጥራቸው ከነዋሪዎቿ በላይ የሆነው በጀልባ ወደ ደሴቲቱ የጎረፉና የሚጎርፉ ስደተኞች ኢጣልያን በእጅጉ አስጨንቀዋል ።
ማሳሰቢያ የዶቸ ቬለ የፕሮግራም ሥርጭቶች ሆን ተብሎ መታወክ ደረሰባቸው፣ መታወክ የደረሰባቸው የሞገድ መስመሮች፤ Hotbird 8 ሳተላይት በኩል የሚሰራጩት ናቸው ። ሞገዶቹ ሆን ተብሎ በአዋኪ ድምፅ መሰናክል ገጥሟቸዋል ። ቀደም ባለው ጊዜ ይህ ዓይነቱ የሚያውክ ድምፅ ያጋጥም የነበረው ከኢራን በኩል ነው …
በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጀመርያ በቱኒዝያ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ለሃያ ሶስት ዓመታት በህዝብ ጫንቃ ላይ ተነሰራፍቶ የሀገሪቱን ሀብት ሲመዘብር የኖረውን መሪ ቤን አሊን ከሀገር እንዲወጣ አድርጎታል: ከሰሞኑም የግብጽ ህዝብ ከአስራ ስምንት ቀናት ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ ለሰላሳ ዓመታት ግብጽን በብረት ጡጫ …
ቱኒዚውያን መሪያቸውን ካባረሩ በኋላ እስከአሁን አልተረጋጉም። ወጣቱ በጀልባ ውደ አውሮፓ ስደትን ጀመረ። ላምፔዱሳ ሰሞኑን የሰሜን አፍሪካው አብዮት መዓት ይዞባት መጥቷል።
ለአስራ ስምንት ቀናት ከካይሮ እስከ አሌክሳንድሪያና በመላው ግብጽ የተቀጣጠለው ፀረ-መንግሥት ዓመፅ ዓርብ ዕለት ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ ስልጣናቸውን ለሀገሪቱ ጦር ሠራዊት እንዲያስረክቡ አስገድዷቸዋል። በሰሜን አፍሪካዊቱ ሀገር በወጣቶች አንቀሳቃሽነት የተጀመረው ህዝባዊ አመፅ ለሰላሣ ዓመት የገዛውን የፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክን አስተዳደር ነው ከስልጣን ያስወገደው። …
አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ በኢትዮጵያ ያለውን ሰላማዊ የዴሞክራሲ ትግል ፍሬያማ የሚያደርግ የአምስት ዓመት ስትራቴጂአዊና እቅድ መንደፉን ይፋ አደረገ። ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬም የአንድነት መሪ መሆናቸውን የፓርቲው አመራር አስታውቋል። ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡
(ሙሉ ገ.) • አንድ ሹመኛ በከተማው ያሠሩት ሕንጻ “ሰርቆ ማሳያ” ተብሏል • ግለሰቡ ከክልሉና ከኦሕዴድ ባለሥልጣናት ጋራ የሪልስቴቶች ባለቤት ሆነዋል • መሐንዲሱ የ4 ሚልዮን ብር ቤት ሲገነቡ በኦሮሚያ ክልል የሰበታ- ሐዋስ ከተማ ከመሬት ሽያጭ ሙስና ጋር በተያያዘ በአስተዳደር ሥራ ላይ …
በሰበታ ከተማ ከመሬት ሽያጭ ሙስና የተመዘበረው ገንዘብ ለፖለቲካ ሲባል እየተደበሰበሰ ነው Read more »
የጎንቻው በፈጠረህ ምድር አፍታ ስትድህ፤ ከርሰ-ምድር ገባህ ፏፏቴ አጢሰህ፤ ሰርገህ በቤታችን ምሽግ ቆፍረህ፤ አንጋዳ ገደሉ ማቆራረጫህ፤ መመላሻህ፤ ያጠላልፈናል ወልጋዳ እትብትህ፤ ስንት ድልድይ ናደ አፍለኛው ጐርፍህ፤ የራሳችን ምታት ሆዳችን፤ ቆርጠህ፤ ጊዮን ዙሪያ ጥምጥም መቀመቅ ወርደህ፤ አባይ አጥፊያችንም መዳኛችን ነህ። የአገር አከርካሪ …
በዘካሪያስ ስንታየሁ | ሪፖርተር በሸራተን አዲስ ሆቴል የተፈጠረው ውዝግብ ባለፈው ረቡዕ እልባት ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም፣ እስካሁን መፍትሔ ማግኘት አልቻለም፡፡ ሆኖም ችግሩን ለመፍታት በሆቴሉ ማኔጅመንትና በሠራተኛ ማኅበሩ መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠሉን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የሆቴሉ ማኔጅመንት ባለፈው ማክሰኞ የሆቴሉን ሠራተኞች በሙሉ …
የቱኒዝያ ስደተኞች በባህር በኩል ወደ ኢጣልያ ጠረፍ መጉረፋቸዉ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። በዚህም ጣልያን የአስቸኳይ ጊዜ ደምብ አስፍሮአል። በኢጣልያ ጠረፍ ጥበቃ ሃይል መግለጫ መሰረት ባለፈዉ ሌሊት ብቻ አንድ ሺህ ገደማ የሚጠጉ ስደተኞች ላፓዱዛ ደሴት ደርሰዋል። ቀደም ባሉት ቀናት ቢያንስ ሶስት ሹህ …
እሳት ነው ወጣቱ። ከአቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወ-መንፈሳዊ እሳት ነው ወጣቱ። እየለበለበ፤ እያንገበገበ፤ ጠላት ያነደደ፤ ባንዳዎች ያጨደ:: ሐቅ ነው ከጥንቱ፤ አያውቅም ብላችሁ እንዳትጫወቱ፤ ይፋጃል በደሙ እሳት ነው ወጣቱ:: እንኳን ላገራችን፤ ለነፃነታችን፤ ይረ-ሳል መገ ደል? ይበልጥ በወቸገል?? ስንቱ ጀግና ወድቋል፤ በአጋዚ ሕዝብ …
ከአገሬ አዲስ ሰሞኑን በሰሜን አፍሪካ የአረብ አገሮች የተካሄደውን ሕዝባዊ ትግልና ያስገኘውን መለስተኛ ድል በሚመለከት “እኛስ መቼ” የሚለው ጥያቄና የትግል ጥሪ ሲንሸራሸር ከርሟል፣ አሁንም እየተንሸራሸረ በመሄድ ላይ ነው። በብዙ ግለሰቦችና ቡድኖች ለአንድነት ትግል የሚደረገው ጥሪ እየጎላ መጥቷል። ሆኖም ግን የየራሳቸውን ጎጆ …
ማንተጋፍቶት ስለሺ የግብፅ ጦር በቀድሞ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሞባረክ 20 ታማኞች ላይ የጉዞ እገዳ አስቀመጠ። የጎዞ እገዳውን ያስተላለፈው የግብፅ ጦር ሲሆን፤ ባለስልጣናቱ ሀገር ለቀው እንዳይሸሹ በሚል ያስተላለፈው ውሳኔ እንደሆነም ተጠቅሷል። ባለስልጣናቱ መጓዝ ከፈለጉም ከጦሩ ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ተጠቁሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለ …
ዛሬ በየመን ያልታሰበ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ። 18 ቀን ያስቆጠረው የግብጽ አመጽ ትላንት እልባት ካገኘ በኋላ በየመን ውስጥ እንቅስቃሴ እየታየ ነው። ዛሬ በቁጥር በርከት ያሉ ተቃዋሚዎች በተለያየ አቅጣጫ ተሰልፈው ታይተዋል። የተቃውሞ ስልፍ የወጡት ስልፈኞች “…በቃ …ይብቃ!!” የሚሉ ድምጾች ጎልተው ይደመጡ ነበር። …
በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ በትልቅ ጉጉት የጠበቀው እና ፕሬዚደንት ሙባራክ ከስልጣን እንደሚወርዱ ያስታውቁበታል ያለው ዲስኩራቸው ህዝቡ የጠበቀውን ውጤት አላስገኘለትም ነበር፤ ግን የህዝብ ተቃውሞ ተጠናክሮ በመቀጠሉ ፕሬዚደንት ሙባራክ ትናንት ስልጣናቸውን መልቀቅ ተገደዋል። ይህም በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ደስታና ፈንጠዝያ ፈጥሮዋል።
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የታህሪር አደባባይን መናኃሪያው አድርጎ ለአስራ ስምንት ቀናት የዘለቀው ኅዝባዊ የተቃውሞ ድምፅ ዛሬ በአሸናፊነት ተጠናቋል። ከሁለት ሳምንታት በላይ ለሆነ ጊዜ ያለማቋረጥ በየቀኑ አደባባይ እአወጣ ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን ይለቁ ዘንድ ይጠይቅ የነበረው የኅዝብ ቁጣ በመጨረሻው በሙባረክ ከስልጣን መውረድ ቢጠናቀቅም፤ የአሪቱን ቀጣይ ዕጣ አስመልክቶ …
ሲባል ስምታችኋል? * ሲሞቅ አትሙቁ ፤ሲበርድ አትብረዱ ኢትዮጵያን ወደፊት፤ አርገው ይራመዱ። እንደዱሮ መስሎሽ ደርሶ መመለስ፤ ትግሉ ያስምጥሻል አንገትሽ ድረስ። * አለ ያገሬ ሰው ! አበው ሲተርቱ እንዲህ ይሉ ነበር አሉ። በገጠማቸው ነገር ሲገርሙ፤ “ጉድ እስከ እሁድ” ብለው ሲሉ ሌላኝው “ብርጉድ፤ …
ሞሐመድ ጃማሊ የሚባል አንድ ቱኒዝያዊ ዴይሊኤምራልድ ለተሰኘ ዌብሣይት አዘጋጅ እንዲህ ሲል ፃፈ፡፡ “እነሆ ቱኒዝያ እገኛለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ቱኒዚያ የት እንደምትገኝ ማብራራት ነበረብኝ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከእንዲህ ዓይነቱ ማብራሪያ አረፍኩ፡፡ ሃገሬ አምባገነኖቿን አሽቀንጥራ ጥላ የአብዮት ሰደድ ግብፅን ጨምሮ በድፍን የዐረብ ዓለም ይቀጣጠል …
የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ትላንት ጠዋት በአምባሳደር ሲኒማ ካልተመደቡ የቴሌ ሰራተኞች ጋር ያደረጉት ስብሰባ ያለ ውጤት ተበተነ። በዕለቱ በተደረገው ስብሰባ ላይ ከተጠበቀው በላይ ሰራተኞች በመገኘታቸው የአዳራሹ ወንበሮች ሞልተው ስብሰባውን ቆመው ለመከታተል የተገደዱ ሰዎች ቁጥር ከተቀመጡት እንደማይተናነስ የሰርካዲስ ምንጮች …
ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ከህዳር 23 2003 ዓም ጀምሮ ላለፉት ሁለት ወራት ስርጭቱን በታይኮም 5 ሲያስተላለፍ መቆየቱ ይታወሳል። በስልጣን ላይ ያለው ገዢ ፓርቲ ይህን የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማፈን ያለፉትን ሁለት ወራት ላይ ታች በማለት አሳልፎአል። …
ከኦባም የምርጫ ፉክክር ወዲህ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት የሳበ የውጭ ክስተት ካለ የግብጹ አብዮት የመጀመሪያ ይመስለኛል። ሁለቱንም በጉጉት ከተከታተልንባቸው ብዙ የግልና የጋራ ምክንያቶች አንዱ ሁለቱም በአገራችን እንዲሆኑልን ስለምንፈልግ መሆኑ አያከራክርም። ቢቻል ሁለቱንም ባይቻል አንዱን ማግኘት ትልቅ ነገር ነው፤ ሁለቱንም አለማግኘት ደግሞ …
የኢትዮጵያ መንግሥት ቀደም ሲል 1.8 ሚልዮን ሄክታር መሬት፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም (የዚያኑ እጥፍ) 3.6 ሚልዮን ሄክታር ለም መሬት ፣ ለውጭ ሀገር ኩባንያዎች ከ 40-99 ዓመት ገደማ በኪራይ ይሁን በሽያጭ እንዲቀራመቱ ፈቅዷል። ቻይናውያን ፣ ህንዳውያን፣ ዐረቦችና ኮሪያውያን በሽሚያ ላይ ናቸው። አውሮፓውያንም …
የግብፅ ፕሬዝደት ሆስኒ ሙባረክ ከ18ቀናት ዉዝግብ በኋላ ስልጣን ለቀቁ። ለቀናት አደባባይ ወጥቶ ስንብታቸዉን ሲጠይቅ የከመዉ ህዝብ ደስታዉን እየገለፀ ነዉ። ሙባረክ፤ ትናንት ማታ በተስፋ ሲጠብቃቸዉ ለነበረዉ ህዝብ ከፊል ሥልጣናቸውን ለምክትል ፕሪዚዳንትነት ለመረጧቸው ዖማር ሱሌይማን ማስተላለፋቸውን ከመጠቆም በስተቀር ከሥልጣን እንደሚወርዱ ሳይገልጹ ነበረ …
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በፒያሳ ከሚገኝ፡የኢንተርኔት ካፌ ሲወጡ ብዛት ባላቸዉ የፌደራል ፖሊሲ ታጣቂዎች መያዛቸዉን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል። የፌደራል ፖሊስ ታጣቂዎች ምንም አይነት የፍርድ ቤት መጥሪያም ሆነ ፍቃድ በእጃቸዉ ያልነበረ ሲሆን አቶ እስክንድርን በቀጥታ በፌደራል ፖሊሲ ጽ/ቤት ነበር የወሰዷቸዉ። በፌዴራል …
የዛሬው የዲሞክራሲ በተግባር እንግዳችን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነው ከአዲስ አበባ። በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ አብዮት መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ሚዲያውና ሕዝቡ ምን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተል አወያይተነዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች “ተዳክመዋል” በሚባልበት ወቅት እንደ ቱኒዝያና ግብፅ “ሕዝባዊ እንቅስቃሴውን …
አቶ አየለ ጫሚሶ በጠና ታመዋል ከ1997 አወዛጋቢ ምርጫ በኃላ የአዲሱ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አየለ ጫሚሶ የአልጋ ቁራኛ ሆነዋል፡፡ ሳምንታዊው ሰንደቅ ጋዜጣ በረቡእ እትሙ እንደዘገበው ሊቀመንበሩ በቤተዛታ ሆስፒታል ሲረዱ ቆይተው አሁን ከፍተኛ የውጭ ህክምና እንደሚያሻቸው ተነግሯቸው …
(ግንቦት ሰባት) — በሌሎች መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ እቃዎች ላይ የሚጨመረው ዋጋ ንረት ከዕለት ወደ ዕለት ህዝባችንን የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ሲያደርሰው “የኢኮኖሚያችን ማደግን አመልካች ነው” እያለ ሲያላግጥ የኖረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በቱንዚያ ፈንድቶ አምባገነኖች ያሉበትን አገራት እያዳረሰ ያለውን …
– ገንዘብ በመንግስት ባንኮች ውስጥ አለማስቀመጥ። – በቃ! መለስ ይውረድ! የሚሉና ሌሎችምንም መፈክሮችን በየግድግዳው ላይ መጻፍ – የተሳሳተ መረጃ ለፖሊስ መስጠትና ማወናበድ – መንገዶችን እና የባቡር ሃዲዶችን በመዝጋት የወያኔን ኢኮኖሚ መስበር – የመንግስት ተሽከርካሪዎችን ጎማና ባትሪ በመንቀል በጊዜያዊነት ከጥቅም ውጭ …