በየመን የተቃውሞ ሰልፉ ቀጥሏል

ዛሬ በየመን ያልታሰበ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ። 18 ቀን ያስቆጠረው የግብጽ አመጽ ትላንት እልባት ካገኘ በኋላ በየመን ውስጥ እንቅስቃሴ እየታየ ነው። ዛሬ በቁጥር በርከት ያሉ ተቃዋሚዎች በተለያየ አቅጣጫ ተሰልፈው ታይተዋል። የተቃውሞ ስልፍ የወጡት ስልፈኞች “…በቃ …ይብቃ!!” የሚሉ ድምጾች ጎልተው ይደመጡ ነበር።

የመን ውስጥ ታህሪር አደባባይ የሚባል ከገብጹ ካይሮ ካለው ታሀሪር አደባባይ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቦታ አለ። ትላንትና ከዚሁ አደባባይ በቅርብ ያለ ሻራ ጀማል የሚባል ቦታ መጠነኛ ብጥበጣ የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት ግን ሁኔታው ተረጋግቶ በሰላማዊ መንግድ ነው ሰልፍ የወጡት። እዚሁ ታሀሪር የሚባለው አደባባይ ላይ ቀጣይነት ያለው ተቃውሞ ለማደረግ የታስብ ይመስላል::በቁመታቸው እና እርዝመታቸው በጣም ትላልቅ እና እንዲሁም መጠነኛ ይዘት ያላቸው ከ50 በላይ በጣም በርካታ ድንኳኖች እየተተከሉ ነው። ሰዉ ያለው ስሜት የተረጋጋ አይነት ነው።