መች ተፅፎ ትችት መች ተወግዞ ሙግት

ሲባል ስምታችኋል?
*
ሲሞቅ አትሙቁ ፤ሲበርድ አትብረዱ
ኢትዮጵያን ወደፊት፤ አርገው ይራመዱ።
እንደዱሮ መስሎሽ ደርሶ መመለስ፤
ትግሉ ያስምጥሻል አንገትሽ ድረስ።
*
አለ ያገሬ ሰው !

አበው ሲተርቱ እንዲህ ይሉ ነበር አሉ። በገጠማቸው ነገር ሲገርሙ፤ “ጉድ እስከ እሁድ” ብለው ሲሉ ሌላኝው “ብርጉድ፤ ሲያውድ” ነው የሚባለው። በማለት አባባሉን እየቀየሩ ይገረሙም ይደነቁም ነበር ይባላል።

እኔስ ምን ይለኛል ዛሬ እንዲሁ ባደርግ? ። ምን ማለት ነው ብላችሁ እንደገና በጥያቄ እንዳትሞሉ እፈልጋለሁና እንዲህ ለማለት ነው ብዬ ላብራራ። ስሞኑን እንደው ለተጀመረው የነፃነት ትገል የታዘብኩትን፤ ይጠቅማል ይረዳል ብዬ ያመንኩበትን፤ እንደ ባለሞያ ጽሃፊ ባይሆንም እንደዜጋ፤ ለማበርከት ስጀመር ከአንባቢያን የሚጎርፈውን የስድብም የመልካም መረዳትም አስተያየት የሚዲያዎችንም ግንዛቤና ምን ያክል “ነፃ” መድረክ እንደሁኑ በመጠኑም ቢሆን ለመረዳት አስችሎኛልና ደስታዬ የላቀ እንደሆነ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።

ጉድ እስከሁድ ያልኩት። እንግዲህ “ብርጉዱም” ባገራችን ባኽል ቡና ሲፈላ እንደ እጣን የሚጨስ የ እጣን አይነት መልካም ሽታ ያለው በመሆኑ ገጠመኙን ሁሉ “እንደብርጉዱ” ወደመልካም ቀይሮ በቅን መንፈስ ወደፊት ለመሄድ ይረዳ ዘንድ ለማሳየትም ጭምር ነውና እንዲሁ የተርዳሁትን ወርወር ላድርግላችሁ።

መቼም የመጣጥፌ ዋና አላማ እንደ እኔ እምነት ለነፃነቱ ትግላችን እገዛ ለማድረግ መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም። ጥቂቶች እንደሚሉት ሳይሆን፤ ብዙዎች እንደሚረዱት መጣጥፎች ያልታዩን ጉሉህ ችግሮቻችንን ያሣያሉ ያልተተቹን ይተቻሉ በዚህ መሃልም መልካም እይታና ግንዛቤን በመፍጠር ውጤታማ የማድረግ አስተዋጾ ማበርከታቸው እሙን ነው።

በተጫማሪም፤ ግልጽና ቀጥተኝ ትችት በመሪዎችም ሆነ በሚዲያ ክፍል አዘጋጆች ላይ መስንዘሩ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም ባይ ነኝ። ለሃገር ግንባታ ነው የቆምነው ያሉ ማንኛውም ሚዲያዎች የሚመረውንም፤ የሚጣፍጠውንም እኩል በነፃ ሚዲያቸው የማቅረቡ ተግባር በሃገራችን የታፈነውን ሚዲያ ሕዝብ ልዩነቱን በግልጽ እንዲያየው ካማድረግ ባሻገር የሚያስተላለፈው መልዕክት ቀላል ግምት የሚስጠው አይደለም። ለዚህም ምስጋናዬ ይድረሳችው እላለሁ።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ታዲያ ምነው እኛ ያላመንበት አይወራም፤ አይፃፍም፤ በሚል ጠባብ አመለካከት ሚዲያን ለስርጌ አዚምልኝ ተብሎ እንደከፈሉት አቀንቃኝ ለኔ ብቻ አዚምልኝ ማለቱ አስገማች አይሆንም ትላላችሁ?። “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትስ ለድርድር ሲቀርብ” አፋችሁን ዘግታችሁ የኛን እኩይ ተግባር ብቻ እንደፊልም ተመልከቱ፤ እንደ አዶ ከበሬ ደልቁ፤ የሚለው ጩኽታችሁን ቢያንስ ሚዲያ ማለት ምን ማለት እንደሆነም ግምት ውስጥ አስገቡና ለማስተካከል ሞክሩ። ልቦናም የስጣችሁ በማለት ለባለሞያዎቹ የሚዲያ ሰዎች ሌላውን የተግባር ጉዳይ እተዋልሁ።

በመሆኑም ለዚህ ተግባራቸው ምስጋናዬ የላቀ ነው። አንዳንድ ሚዲያዎች የሚላክላቸውን ጽሁፎች ለተወስነ ቡድን ቲፎዞ በመሆን አላማውጣታቸው ደግሞ ባለሞያ ( ፕሮፌሽናል ጋዜጠኞች ) ከሆኑ የሞያ ግዴታቸውን አልፈጸሙምና ከሌሎች ባለሞያዎች ለመማር ወይም የሞያውን አላማና ግዴታ እንደገና ወደኋላ መለስ ብሎ መመርመር መልካም ነው እላለሁ ። ልቦናቸውን ይክፈቱ ከማለት ሌላ ብዙ ማለት አልፈልግምና ይሄን በዚህ ላቁም።

ባለሞያ ጋዜጠኛ መሆንና በፍላጎት ጋዜጠኛ ለመሆን መፈለግ ልዩነቱን በግልጽ ስለሚያሳየን ብዬ ነው። አይመስላችሁም ? ቅቅቅቅ. ክክክ …ቅቅቅ ምን ይለኛል ክክክ. ቅቅቅቅ ።

እንደው ለነገሩ አንድ ጥያቄ ለፖሎቲካ መሪዎች ነን ለሚሉት ላቀርብ፤ አትጥሉት “ኮሦ ሲጠጡት ቢመረም ያሸራል ይባላልና” እስቲ እንደው ከመጀመሪያው ጀምሮ ከየት እንደጀመራችሁ፤ የት ቦታ እንደቆማቸሁ፤ የሰራቸሁትን ጥፋት፤ መልካሙንም ሰራችሁን፤ ደካማ ጎናችሁንም ጠንካራ ነኝ የምትሉበትንም፤ አሁን ደግሞ የት እንዳላችሁና ምን እየሰራቸሁ እንደሆነ ሕዝብም ሊታዘብ ሊገመግማችሁ እንደሚችል ቆም ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ከሆነ መልካም ነው። ታዲያ ለምን አልተስተካከላችሁም ? የተስተካከላችሁ ከመስላችሁ ግን፤ አንደኔ ወላዲት አምላክን ብዙ ይቀራችኋል ነው የምለው አካሄዳችሁም አደገኛ ነው።

«የ አንድ አስተዋይና ጠንካራ መልካም መሪ መለኪያ ከሕዝብ የሚስነዘርውን ጭብጨባና ሙገሣ የሚከተል ሳይሆን ውግዘትን ተቀብሎ መስተካከልም ማስተካከልም የሚችል ነው።» አሉ (ያልታወቁ) ስው።

እቅጭ እቅጩን የሚናገሩ ድሮስ መች ይታወቃሉ ብላችሁ ነው?።

ስለዚህ ስለሃገር ጉዳይ ሕዝብ የሚፈጨውንም፤ የሚቦካውንም ጠንቅቆ ያውቃልና ለኢትዮጵያ የነፃነት ትግል «ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለድርድር የሚያቀርብ መሪ» አሁንም ከመወቀስም ከመወገዝም አይደንም ነው የምለው።

መልካም ስትሰሩ ደግሞ ምን ችገር አለ እንኳን ማጨብጨብ ቀርቶ አንገታችሁ ላይ እንደ እባብ ብጠመጠምስ ምን ይለኛል ብላችሁ «አዬ…» ብቻ ለዛ ያብቃን እንጂ።

በመጨረሻም ለንባብ የማበቃቸውን ጹሁፎቼን ሁልጊዜም ቢሆን ይዤ ብቅ ማለቴ አይቀርም። በተለይ በተለይ ባቋራጭ የሆነው ይሁን፤ በሚል እራስን ለስልጣን ለማብቃት፤ ኢትዮጵያን ወደኋላ ማንነትን ወደፊት በማደርግ የሚሞከር አካሄድ ሲመጣ “አይማረኝ ብመራችሁ” እንዳሉት «ማን ነበሩ» እንኳን? «ቅቅቅቅ…» ክክክክክ። ይልቅ ልቦና ገዝታችሁ ኢትዮጵያንና ባንዲራዋን ከፊት አስቀድማችሁ በማስተዋል ሂሱንም ግለ ሂሱንም እንደ ኪኒን እየዋጣችሁ የተጀመረውን የነፃነት ትግል በጋራ ፍፃሜ ላይ እናድረስው እያልኩ ጤና ይስጥልኝ እላለሁ። ሁልግዜ ግን አስታውሱ በሕዝብ መነጽር (መነጥር) ነው የሚባለው፤ እውስጥ ነው ያለነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የተቀጣጠለውን የነፃነት ትግል በቆራጥነትና ጀግንነት መንፈስ ፍፃሜ ያደርስዋል!!

በቸር ይግጠመን

ሎሚ ተራ ተራ!