በዚህ ሳምንት ከወደ ሰሜን ሸዋ ባጭሩ እንዲህ የሚል መልካም ዜና ተሰምቷል። በሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳ የኢህአዴግን ስብሰባ አንሳተፍም ያሉ የኢህአዴግ አባላት የነበሩ መምህራን የ8 ቀናት ደመወዛቸው መቀጣታቸውና ከሐምሌ ወር ደመወዛቸው ተቀናሽ እንደሚሆን የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሳቸው። መምህራኑ ለደብዳቤው በቃል …

የወያኔ የአባልነት ደብተርን በመቅደድ ነፃነትን ማወጅ፤ ዛሬ!!! Read more »

ከዝግጅት ክፍላችን፤ በቅርቡ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ርሃብ አለ እንዴ ተብሎ ተጠይቆ ሳያንገራግር የሚከተለውን መልስ ሰጠ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ርሃብ ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ነው”።  አለ ሌባ ጣቱን ወደላይ ቀስሮ። መለስ ዜናዊ ይህን መልስ በሰጠበት ወቅት ኦጋዴን ውስጥ ህጻናት፤ ጎልማሶችና …

መለስ ዜናዊ የወለደው ርሃብ!!! Read more »

የህዝባችንን መረጃ የማግኘት መብት በማፈን የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም እየተወራጨ ያለው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ፤በቅርቡ ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ለተመለሰው የአሜሪካ ድምጽ የአሰተዳደር ቦርድ ያቀረበው ባለ 42 ገጽ አቤቱታ ለህዝብ ይፋ መሆኑን የግንቦት 7 ዜና ዘጋቢ ገለጸ። በወጣቱ የዲሞክራሲ አክቲቪስትና ጋዜጤኛ አበበ ገላው …

የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ከተቃዋሚዎች ይወግናል በማለት የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ለአሜሪካ መንግሥት በማስረጃነት ያቀረበው ባለ 42 ገጽ አቤቱታ አፈትልኮ ለህዝብ ይፋ ሆነ Read more »

የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በውዴታ ግዴታ ገንዘብ እንዲለግሱ ከጠየቀ ወዲህ ፣ ተቋማቱም የተጣለባቸውን እዳ የከፈሉ ቢሆንም ዘራፊው የወያኔ አገዛዝ የከፈላቺሁት መጠኑ አነስተኛ ነው በሚል በድጋሚ እንዲያዋጡ ማዘዙን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ ገለጸ። …

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በአባይ ግድብ ግንባታ ሽፋን ዜጎችን መዝረፉን ቀጥሉአል፣ የግል ትመህርት ተቋማት በግዴታ የተጣለባቸውን ገንዘብ መክፈል አንችልም እያሉ ነው Read more »

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተደራጁ ሃይሎች የጦር መሳሪያን በመጠቀም ሰፊ የሆነ ዘረፋ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየፈጸሙ መሆኑ ተደጋግሞ የተዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ባወጣው ዘገባው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ክፍል ሥር የሚገኘው ሲስኮ ላብራቶሪ …

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለው ዝርፊያ ተስፋፍቶ ቀጥሉአል፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አምስት ኪሎ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሁለት ቤተ ሙከራዎች ባልታወቁ ሰዎች ተዘረፉ Read more »

ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን መስሪያ ቤት ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ከተቀየረ በኋላ በርካታ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ከስራቸው እንዲሰናበቱ የተደረጉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን እነኝህ ከስራ የተባረሩ ሰራተኖች ከነቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የጥቃቱ ሰለባ ሰራተኞች ገልጸዋል። አንዲት ለገሃር በሚገኘው …

ከስራ የተባረሩ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሰራተኖች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸው ታወቀ Read more »

በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ አንድና ስምንት ውስጥ ከ450 በላይ የንግድ ቤቶች ያለንግድ ፈቃድ ሰርታችሁዋል በሚል ምክንያት መታሸጋቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዝን ኢሳት የውስጥ ምንጮቹን በመጥቀስ የዘገበ ሲሆን ዘረኛውና ጨካኙ የወያኔ አገዛዝ የወሰደው ርምጃ ነጋዴዎቹን እጂግ ማበሳጨቱን ተያይዞ የደረሰው ዜና አመልክቷል። ከዚሁ …

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የንግዱ ማህበረሰብ ማዋከቡን ቀጥሏል፣ መርካቶ ውስጥ ከ450 በላይ ንግድ ቤቶች ታሸጉ Read more »

በፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለገሰ ዓለሙ ከሁለት ሣምንታት በፊት ለስብሰባ ከፍትሕ ሚኒስትሩ ብርሃን ኃይሉ ጋር ለስራ በሚል አሜሪካ ሄዶ የነበረ ሲሆን ወደ ሃገር ሳይመለስ በዚያው መቅረቱን ለአገዛዙ ቅርበት እንዳለው የሚታወቀው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ። እንደ ሪፖርተር ዘገባ …

የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት ሃገርን እየጣሉ መኮብለላቸውን ቀጠሉ Read more »

ዘረኛው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በምርጫ 97 በህዝብ መተፋቱን ከተገነዘበ ወዲህ በመላው አገሪቱ የሚገኙትን አብዛኛውን የመንግሥት ሠራተኞች በሥራ ዋስትና እና የደረጃ ዕድገት ሥም እያስፈራራ አባል ያደረገ ቢሆንም አባልነታቸው ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ከመጣው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች የሚታደጋቸው ሆኖ ባለመገኘቱ በርካቶች የአባልነት ግዴታቸውን …

ወያኔ በሥራ ዋስትና አስገድዶ የኢህ አደግ አባል ያደረጋቸው የመንግሥት ሠራተኞች ድርጅቱ የሚጠብቅባቸውን የአባልነት ግዴታ ላለመወጣት እያንገራገሩ ነው ተባለ Read more »

የአሜሪካንን ጥቅም እስካስጠበቀ ድረስ በየትኛውም አለም ክፍል ካሉት አፋኝና ጨቋኝ የአምባገነን መንግሥታት ጋር ተባብሮ መሥራት የውጪ ፖሊሲው አካል የነበረው የአሜሪካ መንግሥት፤ ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ ወዲህ በአለማችን ላይ እያየለ የመጣውን የነጻነት ትግል ለመደገፍ በሚያስችል ሁኔታ እንዲሻሻል እርምጃዎች እየተወሰዱ …

የፕሬዝዳንት ኦባማ የዉጭ ርዳታ የማሻሻያ ፕሮግራም አካል የሆነ አለም አቀፍ የጋራ ትብብር ድርጅት ተቋቋመ Read more »

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቀደም ሲል የጫካ ትግል ያካሂድ በነበረበት ወቅት አብረውት የነበሩትንና የድርጅቱን ጸረ አገርና ጸረ ህዝብ አቋም በሚገባ ከተረዱ ቦኋላ ለቀው በመውጣት ከተቃውሞው ጎራ የተሰለፉትን የቀድሞ ታጋዮች ማሳደዱን በመቀጠል አቶ አስገደ ገብረስላሴ በተከታታይ ለንባብ ባበቁአቸው መጻህፍት ምክንያት የቁም እስረኛ …

ህወሃት በትግራይ ህዝብና በመላው አገራችን ላይ የፈጸመውን ክህደት ለህዝብ ንባብ ያበቁ የቀድሞ ታጋይ እና አመራር አባል አቶ አስገደ ገብረስላሴ ትግራይ ውስጥ የቁም እስረኛ ሆኑ Read more »

በወገኖቻችን ላይ አስከፊ ችጋር መጥቷል። ምሥራቅና ደቡብ ኢትዮጵያን በአስከፊ ሁኔታ እያጠቃ ያለው ጥልቅ መሠረት ያለው ችጋር እንጂ የአንድ ወቅት ረሃብ አይደለም:: ከአሁኑ ሰው በረሃብ መሞት መጀመሩ ከሁለትና ሶስት ወራት በኋላ የሚመጣውን አደጋ ከባድነት መገመት ይሰቀጥጣል። “ከ10% በላይ ተከታታይ እድገት አሳይተናል” …

ችጋር በቃን!!! ረሃብ በቃን!!! መለስ በቃን!!! Read more »

ከዛሬ ነገ ከስልጣን ወምበሬ እፈናቀላለሁ በሚል እንቅልፍ አጥቶ እየባነነ ያለው ወያኔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጂምላ የሆኑ እስራቶችን በዜጎች ላይ መፈጸም የጀመረ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች የሆኑ 40 ሰዎችን አፍሶ ማሰሩን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ አባስተላለፈው ሪኦፖርት ገለጸ። እንደ …

ዘረኛው ወያኔ ኢትዮጵያዊያንን አሁንም እያሳደደና እያሰረ ነው፣ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ አርባ የሚሆኑ መምህራንና ሰራተኞች ታሰሩ Read more »

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ባለፈው ሰኞ ሰኔ 20 ቀን ባወጣው መግለጫ ከወር በላይ በክልሉ ታግተው የሰነበቱትን ሁለት የአለም አቀፍ ድርጅቱን ሠራተኞች ማስረከቡንና የወያኔ ወታደሮች ርክክቡን ለማደናቀፍ አድርገውት የነበረውን ተከታታይ ጥቃት ማክሸፉን አስታወቀ። የወያኔ አገዛዝ የኦብነግን የድጋፍ መሠረት ለማድረቅ በተከተለው …

ኦብነግ በኦጋዴን ክልል ተጠልፈው የነበሩትን ሁለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዕርዳታ ሠራተኞችን እንዳስረከበ አስታወቀ Read more »

ከህወሃት የንግድ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ሳባ ኢንጂነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ወያኔ በመንግሥት ይዞታ ሥር የነበሩትን ንብረቶች ወደ ግል ለማዛወር ባወጣው ደንብ ከአራት አመታት በፊት ከመንግሥት በርካሽ ዋጋ የገዛውን የአዲስ ጡብ ማምረቻ ፋብሪካ ክፊያ ዋጋ እስከዛሬ ባለመፈጸሙ ክስ የቀረበበት መሆኑን …

የኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው ሳባ ኢንጂነሪንግ የአስራ አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር እዳ ያለበት መሆኑ ታወቀ Read more »

የመለስ ዜናዊ አሻንጉሊት ፓርላማ ሰኔ 7 ቀን 2003 ዓ.ም. ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄን (ግንቦት 7)፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን (ኦነግ) እና የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባርን (ኦብነግ) በሽብተኝነት መፈረጁ ተሰምቷል። ለመሆኑ ፓርላማው በምን ሥልጣኑ ነው ድርጅቶችን የሚፈርጀው? እሱ ራሱ ማን …

መደናበር ያመጣው “የሽብርተኝነት” ፍረጃ Read more »

በአህጽሮተ ቃሉ ሲፒጄ በመባል የሚጠራው አለም አቀፉ የጋዜጠኛች መብት ተንከባካቢ ድርጅት በትናንትናው እለት ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንደገለጸው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከ2001 እስከ 2011 ባለው ጊዜ ውስጥ በዓለማችን አገራቸውን ጥለው ወደ ሌሎች አገሮች በሚሰደዱ ጋዜጠኛች ቁጥር ኢትዮጵያ አንደኛ መሆኗን አስታወቀ። ስፒጄ …

ሃገራቸውን ጥለው በሚሰደዱ ጋዜጠኞች ቁጥር ኢትዮጵያ የቀዳሚነቱን ስፍራ ያዘች Read more »

ህዝባዊ አብዮት ከተቀጣጠለባቸው የአረብ አገራት ሁሉ በመልክዓ ምድር አቀማመጥ የየመንን ያህል የሚቀርበን የለም። የኢትዮጵያና የየመን መመሳሰል በመልክዓ ምድር አቀማመጥ ብቻ አይደለም፤ መመሳሰላችን በብዙ ጉዳዮች ነው። የመን የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የነገሰባት አገር ናት፤ ወይም ነበረች። አሊ አብደላ ሳልህ ለሰላሳ …

ከየመን ህዝባዊ አብዮት ምን እንማራለን? Read more »

ወያኔ የሚያከብረውን 20ኛ የድል አመት አስመልክቶ ከግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ ሃያ የክህደት፣ የውርደት፣ የዘረኛነትና  የዘራፊነት አመታት                                                ግንቦት 18 2003 ዓ.ም  በደርግና በመንግስቱ ሃይለማሪያም ቦታ ወያኔና መለስ ዜናዊ ከተተኩ 20 አመት ሆነው። ሰሞኑን መለስ ዜናዊ ሃያኛውን የንግስና በአል ለማክበር ከፍተኛ  …

ሃያ የክህደት፣ የውርደት፣ የዘረኛነትና የዘራፊነት አመታት Read more »

የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በምክትል ጠቅላይ ምንስትርነትና የውጪ ጉዳይ ምንስትርነት ለይስሙላ የሾመው ሃይለማሪያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የህዳሴ ግድብ በፍጹም ለመስኖ አገልግሎት አይውልም ፣ በዚህም ምክንያት ግብጽ ምንም አይነት ጥርጣሬ ሊገባት አይገባም ማለቱ ብዙዎችን የሥርዓቱን ደጋፊዎች ማሳዘኑን ለማወቅ …

የህዳሴ ግድብ የተባለው የወያኔ መፎከሪያ ለመስኖ አገልግሎት እንደማይውል ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጸ Read more »

የብሪቲሽ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቢቢሲ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ባለፈው አርብ ግንቦት 21 ቀን ታዋቂ ጋዜጠኞችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ የእንግሊዝ መንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት የጠረቤዛ ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱ ወቅት የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ዉስጡና ዉጩ በሙስና የተጨማለቀ አገዛዝ መሆኑ እየታወቀ ብሪታኒያም …

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ እጂግ በሙስና የተጨማለቀ መሆኑ በግልጽ እየታየ ርዳታ ለጋሽ ሃገራት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸው አሳፋሪ ነው ተባለ Read more »

በያዝነው ሳምንት የግንቦት 7 1997 ዓ.ም. ምርጫን ስድስተኛ ዓመትና የንቅናቄዓችንን ሶስተኛ የምሥረታ ዓመትን ዘከርን። ከግንቦት 7 1997 ዓ.ም. ወዲህ ስድስት የቁጭት ዓመታትን አክብረናል። ከእነዚህ ውስጥ ሶስቱ ዓመታት ያለፉት ግን ካጣናቸው መልካም ነገሮች በላይ የማስመለስ እልህ በቁጭታችን ላይ ጨምረንበት ነው። ከግንቦት …

በግንቦት 1997 ካጣነው በላይ ማግኛችን ደርሷል! Read more »

የአዲስ አበባ ከተማ ታክሲ ሾፌሮች ባለፈዉ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ በመጀመራቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪና በስራና በተለያዩ ምክንያቶች ከተማዋን የሚጎበኘዉ ህዝብ ከፍተኛ የመጓጓዣ ችግር እንደገጠመዉ የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከስፍራው ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ። እንደዘጋቢያችን አባባል የዘረኛው አገዛዝ የጸጥታ ኃይሎች የታክሲ ሾፌሮች …

በአዲስ አበባ የታክሲ ሾፌሮች አደሙ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በታክሲ እጦት እየታመሰ ነው Read more »

በቀደሙት ሁለት መንግሥታትና አሁን በስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ የመሬት ፖሊሲ መካከል ያለው ልዩነት እንዲገለጽለት የምጣኔ ሐብት አስተማሪዉን በትምህረት ክፍለ ጊዜ የጠየቀው ተማሪ ተማሪዎችን ለአመጽ የሚያነሳሳ የፖለቲካ ጥያቄ ጠይቀሃል ተብሎ ለእስር የተዳረገው ተማሪ አስቻለው ቢራቱ በታሰረበት እስር ቤት ውስጥ ለከፍተኛ የምግብ …

በወያኔ አገዛዝ ዘመንና በቀደምቶቹ 2 መንግሥታት መካከል ስላለው የመሬት ፖሊሲ ልዩነት እንዲብራራለት አስተማሪውን በመጠየቁ ለእስር የበቃው ተማሪ አስቻለው ቢራቱ በከፍተኛ ስቃይ ላይ መሆኑ ተዘገበ Read more »

ከዛሬ ነገ መጡብኝ በሚል ፍርሀት የተዋጠዉ የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ንጹህ ዜጎችን ማሰር ስልጣኑን የሚያራዝምለት ይመስል በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሆነ የእስር ዘመቻ መጀመሩን መድረክ የተባለው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ከሰሞኑ ከወደ አዲስ አበባ ባሰራጨው ዜና ገለጸ። መድረክ ባሰራጨዉ በዚሁ ዜና አያይዞ …

ወያኔ ህዝባዊ አመጽ ሊቀሰቅሱብኝ ነው የሚላቸውን ማሰር ቀጥሎአል። በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በርካታ ተማሪዎች ታስረዋል Read more »

የግንቦት20 በአል አከባባርን ለማደናቀፍና ብሎም ህዝባዊ አመጽ ለመቀስቀስ አንዳንድ ወገኖች እያሴሩ ስለሆነ አስፈላጊው ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል ሲል የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ በአገሪቱ ላሉ ወረዳዎች ሁሉ ሰርኩላር ማስተላለፉን ኢሳት የተባለው የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን ዘገበ። ኢሳት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከተለያዩ ወረዳ ባለስልጣኖች አገኘሁት …

ዘረኛው የመለስ ዜናዊ አገዝዝ የጽጥታ ሀይሎቹ ማንኛውንም ክትትል እንዲያድረጉ አዘዘ Read more »

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በአገር ውስጥ የሚገኙ የመረጃ መረቦችን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር፤ ከውጭ አገራት የሚተላለፉ የሬድዮና የቴሌቪዥን ሞገዶችን በይፋ በማፈን ኢትዮጵያ አገራችን በመረጃ ከዓለም የተነጠለች ደሴት ለማድረግ ተግቶ ይሠራል፤ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብም ያወጣል። በሌላ በኩል ደግሞ ለሙያቸው ክብር ያላቸው ጋዜጠኞችን …

የመለስ ዜናዊን የመረጃ አፈናን በህዝባዊ ኃይል እንበጣጥሳለን! Read more »

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በአትላንታ በደደረገ ህዝባዊ ስብሰባ ያደረጉት ንግግር አፕሬል 23 2011 1. መግቢያ ከዚህ በፊት በሂውስተን ከዚያም በኖርዌይ ባደረግኳቸው ንግግሮች ከሰሜን አፍሪቃና መካከለኛው ምሥራቅ አብዮቶች ልንማራቸው ስለሚገቡ ኣራት ነገሮች አንስቼ ነበር። በነኛ ንግግሮቼ ያነሳኋቸው ነጥቦች በአጭሩ የሚከተሉት ነበሩ። የነፃነትና …

የዴሞክራሲ ትግሉ በኢትዮጵያ: የማጥቃት ስልቶቻችን Read more »

በግልገል ጊቤ ቁጥር ሁለትና ሶስት እንዲሁም የሚሊየኒየሙ ፕሮጀክት እየተባለ ለሚዘፈንለት ግድብ ግንባታ የስራ ሂደት ዉስጥ የዘረኛውና የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ባለቤት የአዜብ መስፍን ቀጥተኛ የሙስና እጅ እንዳለበት ላለፉት 6 ወራት ከፍተኛ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ምንጮች ማረጋገጣቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዝን ኢሳት ዘገበ። …

የዘረኛው መለስ ዜናዊ ባሌቤት አዘብ መስፍን በእህቷ ልጅ ስም በአገሪቱ ለሚሰሩ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ብቸኛ ስምንቶ አቅራቢ በመሆን ብዙ ሚሊዮን ብር ትርፍ እያጋበሰች መሆኑ ተጋለጠ Read more »

ላለፉት ሰባት አመታት የሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት እንዳስመዘገበ፣ በአምስት አመቱ የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተብየው ደግሞ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ እያሰለፋት እንደሆነ፣ በቅርቡ ደግሞ የሚለኒየም ግድብ የተሠኘ የውሸት ፕሮጀክት ነጠላ ዜማ ይፋ ያደረገው የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በየጊዜው እየጨመረ …

በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት 32 በመቶ ደረሰ፣ ዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ የሁለት አሃዝ እድገት ውሸትነት በድጋሚ ተረጋገጠ Read more »

በአዲስ አበባ ከተማ ሚኒባስ ታክሲዎች በሚያስከፍሉት ታሪፍ ላይ ጭማሪ እንዲደረግና ትናንሽ ታክሲዎች ደግሞ በርቀት መለኪያ እየተጠቀሙ ክፍያ የሚጠይቁበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መታቀዱን፣ የአገዛዙ ሹመኞች መግለጻቸውን ተከትሎ፣ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የታክሲና አውቶብስ ፌርማታዎች ነዋሪዎች እጂግ ሲጨናነቁ መታየታቸውን ዘጋቢያችን …

አዲስ አበባ ከተማ በትራንስፖርት እጥረት እየተጨናነቀች ነው፣ ነዋሪዎች ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ አዲስ የሃሳብ አቅጣጫ ማስቀየሪያ ስልቱ ነው አሉ Read more »

በተፈጥሮ ደን ክምችታቸው በከፍተኛ ደረጃ የሚታወቁትና በኢንቨስትመንት ስም ለባለሃብቶች የተቸበቸቡት ሰፋፊ ቦታዎች፣ በባለሃብቶቹ እየተጨፈጨፉና ከሰል ለማምረትም እየተቃጠሉ እንደሆነ የቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ምንጮቹን በመጥቀስ የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ገለጸ። በክልሉ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደን ቃጠሎ እንደሚካሄድ፣ ለእርሻ ስራ ብለው የሄዱ ባለሀብቶችም …

በኢንቨስትሜንት ስም የሚካሄደው የደን ጭፍጨፋ እጂግ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱ ተዘገበ Read more »

ባለፈዉ ቅዳሜ ሚያዚያ 29 ቀን 2003 ዓም ካናዳ ቶሮንቶ ዉስጥ ከተለያዩ ማህበረሰብ የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን አወያዮችና ተሳታፊዎች የተገኙበትበት የተሳካ የ“በቃ” ንቅናቄ ስብሰባ መካሄዱንና የስብሰባዉ ተሳታፊዎችና እንግዶቹ አብሮ መስራትንና ለአንድ ዓለማ በጋራ መታገልን የሚያሳይ የአቋም መግለጫ ማውጣታቸውን ቶሮንቶ ዉስጥ የሚገኘዉ የግንቦት 7 …

በውጪ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በቶሮንቶ የተሳካ ስብሰባ አካሄዱ Read more »

ሰሞኑን ከወደ ኢትዮጵያ የሚሰማዉ ዜና “ወያኔ መሬት ቀማ” ወይም “ወያኔ ቤት አፈረሰ” የሚል ብቻ ሆኗል፡፡ መቀሌ ዉስጥ የህዝብ ቤት ካላፈረስኩ ብሎ ከከተማዉ ነዋሪዎች ጋር ግብግብ ዉስጥ ገብቶ የከረመዉ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ፊቱን ወደ ጎንደር አዙሮ ሰሜን ጎንደር ዉስጥ በደባርቅ ወራዳ የምንቃር …

የዘረኛውን መለስ ዜናዊ አገዛዝ የመሬት ቅሚያ ፖሊሲ በመቃወም የሰሜን ጎንደር የደባርቅ ወረዳ ህዝብ ተቃውሞ አስነሳ በወረዳ የተነሳው ቅዋሜ እስካሁን አልበረደም Read more »

የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ካራቱሪ ለሚባለው የህንድ ኩባንያ በገፍ ከሰጠው መሬት ላይ ከ147 ሺ ሄክታር በላይ መልሶ እንደወሰደ ብሉምበርግ የተባለው ድህረ ገጽ ዘገበ። የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ይህንን መሬት መልሶ ለመውሰድ የተገደደዉ ከአለማቀፍ ማህበረሰብ በደረሰበት ጫናና በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ የሚገኙ …

ወያኔ ለካራቱሪ ኩባንያ ሰጥቶት የነበረውን ሰፊ መሬት የተወሰነውን ክፍል መልሶ መውሰዱ ታወቀ Read more »

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን በተደጋጋሚ እንደዘገበው በአማራ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች አምና በ900 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኩንታል ማዳባሪያ በአንድ ጊዜ አንድ ሺ 200 ብር በመግባቱ ዋጋው እስካልተስተካከለ ድረስ ምንም አይነት ማዳበሪያ ላለመግዛት መወሰናቸውንና ይህንን ውሳኔ የሚጥስ እንዳይኖር በየቤተክርስቲያኑ መማማላቸው ታውቋል። …

በአማራ ክልል የሚገኙ ገበሬዎች የማዳበሪያ ዋጋ ስለተወደደባቸው ላለመግዛት መማማላቸው ታወቀ Read more »

ከዝግጅት ክፍላችን የአባይ ግድብ ጉዳይ መለስ ዜናዊ እንደፈለገው በሚመዘውረው ፓርላማ ውስጥ ለህዝብ ጆሮ ይፋ ከሆነበት ካለፈው ወር ጀምሮ በውጥረት ላይ ያለውን የአገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት ዘልቆ እንደዋንኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ እየናኘ ይገኛል። የአገራችንን ለም አፈር በማጠብ ለዘመናት ለሱዳንና ግብጽ በረከት ሆኖ የኖረ …

በ5 አመቱ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያልተካተተው የአባይ ግንባታ Read more »

አገራችንን በማፍረስ ተልዕኮ እና በሃብት ምዝበራው ወንጀል የተጠመደው ዘረኛው እና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች በትናንሽ ጥቅማ ጥቅሞች እና መደለያ በዙሪያው ያሰባሰባቸውን አንዳንድ ግለሰቦች በተለያየ ውንጀላ የማስወገድ ተግባሩን እየገፋበት እንደሆነ በዚህም ምክንያት አባዱላ ገመዳ የወቅቱ ተረኛ …

አባዱላ ገመዳ ባለአራት ፎቅ ቤቱን ተነጠቀ Read more »

ደንብና መመሪያን ያልተከተለ የሂሳብ አያያዝ ችግር በዋነኛነት ከታየባቸዉ መ/ቤቶች መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ዘርፍ ፡ የመከላከያ ሚኒስቴርና የኢምግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ዋና መመሪያ እንደሆኑ የዋናው ኦዲተር ቢሮ አስታወቀ።  የፌዴራል ዋናዉ ኦዲተር ይህን የገለፀዉ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለመንግስት ወጪ አስተዳዳርና …

በ3 የመንግስት መ/ቤቶች ዉስጥ መመሪያን ያልተከተለ የሂሳብ አያያዝ እንዳለ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ገለፀ Read more »

ወያኔ ወደ ለንደን ሊመጣ ነው ተብሎ ወሬው ከተሰማበት ጊዜ ጀምረው በመጣበት መንገድ አሳፍረው ለመመለስ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ የሰነበቱት በለንደንና ጀርመን የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የዘረኛውን አገዛዝ መልእክተኞች አሳፍረው፣ አዋርደውና አሸማቀው፣ ስብሰባው በታቀደው መልኩ እንዳይካሄድ ማድረጋቸውን ዘጋቢዎቻችን ከለንደንና ጀርመን ከላኩልን ሪፖርቶች …

ኢትዮጵያዊያን በለንደንና ጀርመን ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ Read more »

የዘረኛውና አምባገነኑ ወያኔ የጭቆናና አፈና አገዛዝ ያንገሸገሻቸው ኢትዮጵያዊያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘረኛው አገዛዝ ባለስልጣናት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃን መውሰድ መጀመራቸው የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን  የሐረሪ ክልል የመሬት አስተዳደርና የካሳ ክፍያ ኃላፊ የነበረው  ሐሺም ኢድሪስ በጥይት ተደብድቦ  መገደሉን የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከስፍራው …

ህዝብ ሲያስመርር የነበረው የሐረሪ ክልል የመሬት አስተዳደር ሹም ተገደለ Read more »

በአዋሳ ከተማ በተለያዩ የንግድ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ በርካታ ነጋዴዎች በዘረኛውና አምባገነኑ ባለስልጣናት ትእዛዝ ወደ እስር ቤት እየታጎሩ መሆኑን የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ዘገባ ገለጸ፣ ፣ ነጋዴዎቹ በገፍ ወደ ማጎሪያ እስር ቤት እየተላኩ ያሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ) አልከፈላቺሁም …

በአዋሳ በርካታ ታዋቂ ባለሃብቶች ታሰሩ Read more »

በዘረኛውና አፋኙ የወያኔ አገዛዝ ተደጋጋሚ አፈና እየተካሄደበት ያለው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ኢሳት ለ4ኛ ጊዜ የሳታላይት ጣቢያ ለመቀየር የተገደደ ቢሆንም በአዲሱ የሳታላይት በአዲሱ ሳታላይት ላይ የተጀመረው ስርጭት ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ ከፍተኛ ጉልበት ባለው የሳታላይት ሞገድ መጥለፊያ መመታቱን ኢሳት አስታወቀ።  የመለስ …

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ለ4ኛ ጊዜ የተከራየው ሳታላይት ጃም ተደረገ Read more »

የመለስ ዜናዊ አገዛዝን ለማስወገድ የሚደረገው የተባበረ የማጥቃት ዘመቻ ሚያዝያ 1 ቀን 2003 ዓም በሰሜን አሜሪካ ተጀመረ። የመለስ ዜናዊ ምስለኔዎች ሚያዝያ 1 እና 2 በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች ስለ አምስት ዓመቱ “የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ለመስበክ እንዲሁም “በአባይ ግድብ” እንቁልልጭ ኢትዮጵያዊያንን በማማለል …

የማጥቃት ዘመቻው ተጀምሯል፤ ሁሉም ለፍልሚያ ይታጠቅ!!! Read more »

በኢትዮጵያ ላይ የተጫነው ግፈኛና ዘረኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያዊያን ትከሻ ላይ ተሽቀንጥሮ ይውድቅ ዘንድ ግፊቱና ህዝብንም ለዚሁ ትግል የማያነሳሳ ጥሪ መቅረቡ ተጡዋጡፎ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ባወጣው ዘገባ ገለጸ:: እንደ ኢሳት ዘገባ በአዲስ አበባ ከተማ ከተበተኑት ጽሁፎች ውስጥ አባይ …

በተለያዩ ከተሞች የ«ተነሱ» ጥሪ ወረቀቶች መበተናቸው ቀጥሉአል Read more »

በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “አምባገነኖችን እየናጠ ያለው ህዝባዊ ማዕበል ወደ አገራችን መቼ ይደርሳል?” በሚል ጉጉት ውስጥ ናቸው። ይህ ጉጉት ተገቢም፤ የሚጠበቅም ነገር ነው። በዚህ ጉጉት መነሻነትም ከየአቅጣጫው የተለያዩ  መልእክቶችንና ጥሪዎችን እንሰማለን። ህዝባዊው አመጽ አገራችን ውስጥ የሚጀመርበት ሁኔታ በአብዛኛው አገር ውስጥ …

በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የማጥቃት ዘመቻ አሁኑኑ ይጀምሩ!!! Read more »

ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 3 ቀን በወያኔ ቁጥጥር ሥር ላሉት የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው የወያኔ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በህዝብ ምርጫ ሥልጣን ላይ ከወጣን ገና 10 ወራችን ስለሆነ ህዝቡ በአመጽ ከሥልጣን ሊያስነሳን ምንም ምክንያት የለውም ሲል የቱንዚያው አይነት ህዝባዊ አመጽ በአገራችን …

ዘረኛው መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ ከወጣን ገና 10 ወራችን ነው ስለዚህ የቱኒዚያው አይነት አብዮት በአገራችን ሊከሰት አይችልም አለ Read more »

ነጻ የሆነ የመረጃ ፍሰትን በመቆጣጠር የአገዛዝ ዕድሜውን ለማራዘም እየባዘነ ያለው ዘረኛው የወያኔ ሥርዓት የሰሜን አፍሪካ ህዝባዊ አብዮት በአገራችን ውስጥ የፈጠረውን ህዝባዊ መነሳሳት በመፍራት ኢሳትን ከአየር ለማውረድ  ይቻለው ዘንድ የገንዘብ ፤ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሃይል ሊያስገኝ በሚችለው አቅም ሁሉ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ …

ወያኔ ኢሳትን ከአየር ለማውረድ ከፍተኛ የሆነ ዘመቻ ላይ እንደሚገኝ የግንቦት 7 ምንጮች ገለጹ Read more »

የወያኔ አገዛዝ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሰሜን አፍሪካው አይነት ህዝባዊ አመጽ ሊነሳብኝ ይችላል  ከሚል ፍርሃት በርካታ ወጣቶችን በሰበብ አስባብ እያሰረ እንደሚገኝ የግንቦት 7 ዘጋቢ ከአዲስ አበባ  በላከልን ሪፖርት ገለጸ። እንደዘጋቢያችን ሪፖርት አዲስ አበባን ጨምሮ ባሉት ትላልቅ ከተሞች ብዛት ያላቸው የደህነንትና የፈደራል …

የኦሮሞ ፈዴራሊስት ዋና ጸሃፊ ከ40 በላይ አባላቶቻቸው መታሰራቸውን ገለጹ Read more »

ከቱኒዚያ ተነስቶ በተለይም የሰሜን አፍሪቃ ሃገራትን የለበለበው ህዝባዊ ማእበል የበርካታ ሃገራትን በር ማንኳኳት ከጀመረ ወዲህ ዓለማቺን ለአምባገነኖች የነበራት ትእግስት አልቆ እንጥፍጣፊ ብቻ እንደቀራት የግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ ር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፣ ፣ ዶ ር ብርሃኑ ነጋ …

ዶ|ር ብርሃኑ ነጋ ዓለም ለአምባገነኖች የነበረው ትእግስት መሙዋጠጡን ገለጹ Read more »