ኢትዮጵያዊያን በለንደንና ጀርመን ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

ወያኔ ወደ ለንደን ሊመጣ ነው ተብሎ ወሬው ከተሰማበት ጊዜ ጀምረው በመጣበት መንገድ አሳፍረው ለመመለስ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ የሰነበቱት በለንደንና ጀርመን የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የዘረኛውን አገዛዝ መልእክተኞች አሳፍረው፣ አዋርደውና አሸማቀው፣ ስብሰባው በታቀደው መልኩ እንዳይካሄድ ማድረጋቸውን ዘጋቢዎቻችን ከለንደንና ጀርመን ከላኩልን ሪፖርቶች ለማወቅ ተቺሉአል::

 ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዝያ 8 ቀን 2003 ዓም ወያኔ የተለመደውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳውን በስደት ወጪ አገር ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለማሰራጨት በለንደንና ጀርመን ጠርቶት የነበረው ህዝባዊ ስብሰባ በየአዳራሾቹ ዘልቀው በገቡ ተቃዋሚዎች እና ከስብሰባው አዳራሽ መግቢያ ላይ ቁመው የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ በነበሩ እጂግ በርካታ ሰልፈኞች መጨናገፉን የግንቦት 7 ዘጋቢዎች ከየሥፍራው ለዝግጅት ክፍላችን በላኩት ዘገባ ገለጹ።

ቀደም ብሎ በተደጋጋሚ የወያኔ መለክተኞችን እያሳፈሩ በመመለሳቸው የሚታወቁት በለንደን የሚገኙ እጂግ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ካገር ቤት የተላኩትን የመለስ ዜናዊ ባለሟሎችን የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት መግቢያና መውጫ ቀዳዳ አሳጥተዋቸው እንደነበር ታውቋል፣ ፣ ሰልፈኞቹ ሲያሰሟቸው ከነበሯቸው መፈክሮች ውስጥ መለስ ነፍሰ ገዳይ ነው፣መለስ እና ጀሌዎቹ ለፍርድ ይቅረቡ !! የተጠማነው ፍትህና ዴሞክራሲን ነው፣ ነጻነታችንን ዛሬዉኑ እንፈልጋለን፣ መለስ ዛሬውኑ ከስልጣን ይውረድ፣ የሚሉ እንደሚገኙበት ዘጋቢያችን አክሎ ገልጹአል::

ዘረኛውና አምባገነኑ የትግራይ ገዢ ጉጂሌ በተለይም በሰሜን አፍሪቃ ሃገራት ውስጥ ህዝባዊ አመጾች በመፋፋማቸውና ለራሱም እንደማይቀርለት በመረዳቱ የተለያዩ አጀንዳዎችን ለኢትዮጵያዊያን በመስጠት እንደለመደው በህዝብ ትከሻ ላይ ተፈናጥጦ የመቆየት መፈራገጥ እያደረገ መሆኑን በርካታ የዜና አውታሮች ሲዘግቡት እንደቆዩ አይዘነጋም፣ ፣ አንዴ ከኤርትራ ጋር በሌላ በኩል ደግሞ ከግብጽ ጋር ጦርነት ልገጥም እቺላለሁ በማለት የህዝብን ስሜት ለማደብዘዝ ቆርጦ የተነሳው ወያኔ፣ እቅዱ አልሳካለት ሲል፣ አሁን ደግሞ አባይን እገድባለሁ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከኔ በላይ ለልማት ተቆርቋሪ ላሳር ነው በማለት የማወናበድ ዘመቻውን በሰሜን አሜሪካ ሃገራትም ሙከራ አድርጎ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት መሆኑም ታውቋል::