ዘረኛው ወያኔ ኢትዮጵያዊያንን አሁንም እያሳደደና እያሰረ ነው፣ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ አርባ የሚሆኑ መምህራንና ሰራተኞች ታሰሩ

ከዛሬ ነገ ከስልጣን ወምበሬ እፈናቀላለሁ በሚል እንቅልፍ አጥቶ እየባነነ ያለው ወያኔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጂምላ የሆኑ እስራቶችን በዜጎች ላይ መፈጸም የጀመረ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች የሆኑ 40 ሰዎችን አፍሶ ማሰሩን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ አባስተላለፈው ሪኦፖርት ገለጸ።

እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት እነኝህ መምህራንና ሰራተኞች ለእስራት የተዳረጉት ለዘረኛው አገዛዝ ባላቸው ይፋ ተቃውሞ ሲሆን ዘረኛው ወያኔ ግን መምህራንና ሰራተኞችን ያሰርሁ ተማሪኦዎች የሚመገቡትን ምግብ በመመረዛቸው ነው ማለቱ ታውቁአል።

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በተለይም በትምህርት ተቁአማት ተማሪዎችና መምህራን ህዝባዊ አመጽን ይቀሰቅሳሉ የሚል ፍራቻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደረበት በመምጣቱ ጭፍን የሆኑና እንዲህ አይነት እንቅስቃሴ የሚያሳይትንም ሆነ ሌሎችን ኢትዮጵያዊያን ለማሸማቀቅ የእስራት፣ ድብደንባና ሌሎች እንግሎቶችን ሲፈጽም እንደቆየ በስፋት መዘግባችን ይታወሳል።

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ አርቅቂያለሁ ብሎ በአሻንጉሊቱ ፓርላማ ተብየ ካጸደቀ ወዲህ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን፣ በሽብርተኝነት የመወንጀልና የማሰቃየት ስራን ማከናወኑ ሲዘገብ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ከኢትዮጵያዊያንም አልፎ ስዊድናዊ የሆኑ ዜጎችን ሳይቀር አሸባሪዎች ናቺሁ በማለት በዝብርተኝነት ህግ መክሰሱም በቅርቡ መዘገቡ ይታወቃል።