በ5 አመቱ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያልተካተተው የአባይ ግንባታ

ከዝግጅት ክፍላችን

የአባይ ግድብ ጉዳይ መለስ ዜናዊ እንደፈለገው በሚመዘውረው ፓርላማ ውስጥ ለህዝብ ጆሮ ይፋ ከሆነበት ካለፈው ወር ጀምሮ በውጥረት ላይ ያለውን የአገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት ዘልቆ እንደዋንኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ እየናኘ ይገኛል።

የአገራችንን ለም አፈር በማጠብ ለዘመናት ለሱዳንና ግብጽ በረከት ሆኖ የኖረ አባይን የመሰለ የአገሪቷን የጉስቁልና ገጽታ ለመቀየር ትልቅ ድርሻ የሚኖረው ሃብት ለማልማት ሲታሰብ እንዴት ትኩረት አይስብ ? ሆነና ነገሩ ዜናው ከአገር ተሻግሮ ከባህር ማዶ ባለው ዲያስፖራ ዘንድም ዋና የመወያያ ርዕስ ሆኖአል። ለመሆኑ ይህ የሚላኒዬም ግድብ ግንባታ ዕቅድ በምን ያህል ምስጥር ቢጠበቅ ነው እስከዛሬ በዘርፉ እውቀትና ችሎታ ካላቸው ሙያተኞች እንስቶ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የመንግሥት መሥሪያቤቶች ጭምር ሳያውቁት ተደብቆ ለመኖር የቻለው? በምርጫ 2002 በነቅስ ወጥቶ 99.6 በመቶ የሆነውን ድምጹን ለልማታዊው መንግሥታችን በምርጫ ለሰጠው ህዝባችን እድገት ለማምጣት ታስቦ በተዘረጋው የ5አመቱ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥስ ይህንን የመሰለ የልማቶች ሁሉ ልማት፤ የፕሮጀክቶች ሁሉ አውራ የሆነ ባለ 80 ቢሊዮን ግድብ እንዴትስ ሳይካተት ቀረ? ወይስ ለ5 አመት በፓርላማው ውስጥ መሽገው የኖሩ የኦነግ ሃይሎች ያንን ረቂቅ አዘጋጁትና የመንግሥታችንን ገጽታ ለማበላሸት አሻጠሩ? የመሳሰሉትን ከሚጠይቁ ጀምሮ “ አባይ ከመገደቡ በፊት ዘረኝነት ይገደብ!! አባይን አምባገነኖች ሊገድቡት አይችሉም!! ስለ አባይ ግንባት ከማውራት በፊት ዳቦ ለተራቡት ይድረስ!! ለምርጫ ያልታመነ ለአባይ ግንባታ አይታመንም !! ወዘተ የሚሉ የተቃውሞ መፈክሮች በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ መስተጋባት ጀምረዋል። በየመሥሪያቤቱ በግዴታ በመደረግ ላይ ባለው የድጋፍ ስብሰባ ላይ ካድሬዎች ድምጽ ማጉያ ጨብጠው “የወር ደምወዝ ከመስጠት ጀምሮ አስከ አንድ ሺ ብር በሚደርስ ገንዘብ ቦንድ ለመግዛት ዝግጁ ነን ” ማለታቸውን በወያኔ ቁጥጥር ሥራ ያለው ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሚያሳየን የድጋፍ ምስል ያውም እንኳን የወር ደመውዛቸውን ለቀው የአመት ደመወዝ ብጨመርላቸውም ደስተኛ አለመሆናቸውን በፊታቸው ገጽታ ላይ የሚነበበው ጉስቁልና ከሚያሳየን ብዙዎች የመንግሥት ሰራተኞች እና የወያኔ ድርጅቶች ተቀጣሪዎች ሌላ የማንንም ትኩረት አለመሳቡ ግልጽ እየሆነ መጥቶአል። ወያኔዎች ቀደም ብለው ስለአባይ ግድብ አስበውበት ቢሆን ኖሮ በ5 አመት መሪ እቅዳቸው ውስጥ ያስቀመጡዋቸው መለስተኛ ግድቦች ላይ የተመሠረተ የሃይል አቅርቦት ዕቅድ ላይ ጊዜያቸውን ባላባከኑ ነበር ብቻ ሳይሆን ከአባይ በላይ ብሄራዊ ስሜት የሚቀሰቅስ የለምና ገና ከጅምሩ ፕሮጀክቱ መቼ እና በማን እንደተጠና፤ ፕሮጀክቱን ለመገንባት የሚያስፈልግ የሰው ሃይል፤ መሳሪያ እና ገንዘብ ለማግኘት የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች፤ የግንባታውን ሥራ ለመሥራት በቂ እውቀትና ልምድ ያለው የየት አገር ኩባኒያ ለጨረታ እንደቀረበና ማን በምን መስፈርት እንዳሸነፈ ወዘተ የመሳሰሉት ወሬዎች በተለመደው የፕሮፖጋንዳ ማሰራጫዎቻቸው ጆሮአቸን እስኪዶነቁር በደስኮሩብን ነበር። ስለግልገል ግቤ 2 እና 3፤ ስለተከዜ፤ ስለፍንጮሃ ፤ የመሳሰሉት ላይ ያባከኑትን አየር ጊዜ ልብ ይሏል። ለዚህ ይመስላል የአውራ አምባው አምደኛ አቤ ቶኪቾ “የአባይ ግድብ ዜና ምንጩ “ብልጬ” ነው በማለት ሰው በየቤቱ የሚያወራውን በተረባ መልክ ያቀረበው። “ብልጬ” እነመለስ ቤተመንግሥት ውስጥ የሚቅሙት አይነት ምርጥ ጫት ስም ነው አሉ። ይህም ሆኖ ግን በዲያስፖራ ከሚኖረው ወገናችን መካከል እነመለስ ህዝቡን ለማዘናጋት “የሚላኒየም ግንባታ ያሉትን” የአባይ ግድብ ዜና ያመነና ተስፋ የሰነቀ፤ “አሁንስ ልብ ሊገዙ ሳይሆን አይቀርም” በሚለው የራሱ የዋህ ግምት እራሱን አሞኝቶ ለምስራች ነጋሪነት ወደውጪ የተሰማራውን ቡድን የስብሰባ ቀን ሲጠባበቅ የነበረ የዋህ እንዳልጠፋ በሰሜን አሜሪካው እና በአውሮፓው ስብሰባዎች ታይቶአል። እነዚህ አይነቶቹ በቁጥር ባይበዙም በመለስ ሃያ አመት ሥላጣን ቆይታ በዘረፋ ከተገኘው የአገር ሃብት ተቋዳሽ መሆናቸው የሚሰማቸው ፤ የሰሜን አፍሪካው ጸረ አምባገነን ፍልሚያ በአገር ቤት የፈጠረው መነሳሳት ያስደነገጣቸው ሰዎች ጋር ተዳምረው የስብሰባውን ቦታ ለማዳመቅ በር ላይ የአይናቸውን ቀለም እየለዩ እንዲያስገቡ ከተመደቡት የህወሃት ካድሬዎች ጋር ተጋፍተውበታል። መለስ ከወደቀ “የኛ ናት ብለው እየኮሩባት ያለው የዘረኞች ስረው መንግሥት አብራ ትናዳለችና ሚቾት ደህና ሰንቢች መምጣቱ ሊያስደነግጣቸው ይገባል። ከራስ በላይ ለአሳር ብልህ አራማጆች ምን ገዶአቸው?

ለመሆኑ ህዝባችን ምን ነክቶት ነው 99. 6 በመቶ የሆነ ድምጹን ሰጥቶ የመረጠው ሃይል “አባይን ልገድብልህና ከችጋር ላላቂቅህ ነው” ሲለው “ኤረ ወጊድልኝ መቼ አድርገሄው የሚታውቀው ነውና” በማለት ጀርባውን እያዞረ ያለው? ምክንያቱ ግልጽ ነው። በመለስ ዜናዊ የሚመራው የትግራይ ገዚ ጉጂሌ የማይታመንባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉት። ከነዚህም ጥቂቶቹ፤

  1. ጉጂለው ገና ትግል ሲጀምር የሚከተለውን እምነት እና ራ ዕይ ሰንጎ ነበር ። ጥቅስ “የትግራይ ህዝብ አጸ ዮሃንስ ከሞቱ ቦኋላ በዳግማዊ ሚኒሊኪ በሚመራው የአማራ ማዕከላዊ አገዛዝ ሥር በሃይል እንዲወድቅ ተደርጎ፤ ለከፋ ማህይምነት ፤ድህነት፤ ጉስቁልናና ስደት የተዳረገ ጭቁን ብሄር ነው፤ የህወሃት አላማም ትግራይን ከአማራ ጭቆና ነጻ በማውጣት የራሷን ሪፖብሊክ መሥርታ በሰላም መኖር እንድትችል ማድረግ ነው” የጥቅሱ መጨረሻ |የካቲት 1968 ለህትመት ከበቃው የህወሃት መጀመሪያው መግለጫ ላይ የተወሰደ| ። በማለት ትግል የጀመረ ሃይል በመሆኑ ኢትዮጵያዊ ራ ዕይና አጀንዳ የለውም። ይህ ጠባብ አላማውና አጀንዳው ኢትዮጵያን የግጦሽ ማሳ አድርጎ ከሚመለከተው እንስሳ ጋር ያመሳስለዋል።
  2. በ1990 ዎቹ በምስራቅ አውሮጳ የፈነዳው የለውጥ ማዕበል በኮሚኒዚም ሥርዓት ግንባታ ሥም ተቃዋሚን በመመንጠር የአንድ ፓርቲ አገዛዝ በአገራቸው ያሰፈኑትን የደርግ አይነቶቹን አገዛዝ እያስወገደ መምጣቱ ስኔና ስኞ የተገጣጠመለት ህወሃት ልክ በትረ ሥልጣኑን እንደተቆጣጠረ ህዝባችን ለዘመናት ግንብቶት የቆየውን የብሄራዊ አንድነት ስሜት እና እሴቶቹን በመናድ “የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነው ከሚለው ቲዎሪ ጀምሮ ፋሽስት ጣሊያን በ5 አመቱ ወረራ ወቅት ከፈጸመቺው በማይተናነስ ወንጀል ዜጎች የአንድነታቸውና የአርበኝነታቸው መግለጫ አድርገው የሚኮሩባትን አረንጓደ ቢጫ ቀይ ባንድራችንን “ተራ ጨርቅ” በማለት ያንቋሸሸ ሃይል ስለሆነ አባይን የመሰለ ብሄራዊ መግባባት የሚሻ ትልቅ የልማት መሠረት ለመጣል ተፈጥሮው አይፈቅድለትም ከሚል እምነት።
  3. ጣሊያን በህዝባችን ላይ ለፈጸመቺው ጭፍጨፋ የደም ካሳ በስንት ድርድርና ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ብርታት በደርግ ጊዜ ጣና በለስ ላይ የገነባቺውን ትልቅ ፕሮጀከት ንብረት በመዝረፍ ወደ ትግራይ ያጓጓዘ ድርጅት ነው የትግራይ ነጻነት ግንባር በትግሪኛ አጠራሩ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ። ከጣና በለስ ፕሮጄክት በተጨማሪ የፓዌ መስኖ ልማት ፤ ጋሚበላ ተገንብቶ የነበረው ባለብዙ መቶ ሺ ሄክታር የባሮ አኮቦ መስኖ ፕሮጄክት፤ የመካከለኛው እና የታቺኛው አዋሽ መስኖ ልማቶች፤ በዋቢ ሼቤሌ ወንዚ ላይ ጂጂጋ አካባቢ የነበረ ብዙ መቶ ሺ ሄክታር ወዘተ በወያኔ እንደጠላት አገር ሃብት የተዘመተበት ፤ ፕሮጀክቶቹ ላይ የነበሩ ትላልቅ ማሺነሪዎች ቡልዶዜሮች፤ ጊረደሮች እና ሌሎች ቢዙ ሚሊዮን ዶላር ግምት ያላቸው ንብረት በወቅቱ በአሸናፊው የህወሃት ጦር ታጅበው ወደ ትግራይ አቅጣጫ መጓጓዛቸውን እንጂ አገር ውስጥ ይኑሩ ከአገር ውጪ ወደሱዳን ተሻግረው ይቸብቸቡ የሚያቁት ስብሃት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ፤ በረክት ስም ዖን፤ ስዩም መስፍን፤ ብርሃኔ ገብረክርስቶስ የመሳሰሉ የአንድ ቡድን አባላት ብቻ ናቸው።
  4. የአገሪቱን ዜጎች እትብታቸው ከተቀበረቺባቸው የአያት ቅም አያቶቹ መሬት ይዞታ በማፈናቀል ከ 3 ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት ነጻ ሊባል በሚችል ዋጋ ለኤሽያና ለአረብ ከበርተዎች እየቸበቸበ ያለው ይህ ጸረ አገር ሃይል በገዛ አገራቸው ዜጎችን ለባዕዳን ባርነት አሳልፎ መስጠት በመጪው ትውልድ እና በአገሪቱ መጻይ እድል ላይ ሊኖረው የሚችለው ጉዳይ አያሳስበውም። ይህንና ይህንን የመሳሰሉ በአገሪቱ ሉአላዊነትና በዜጎቿ ነጻነት ላይ ከቀን አንድ ጀምሮ እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል በዚህች አጭር ትንታኔ አሳይቶ መጨረሽ አይቻለም።

እነኚህ ከላይ ለመግለጽ የተሞከሩት ወያኔ በህዝባችን እና በአገራችን ላይ የፈጸማቸው ደባዎች የተፈጸሙት ሆን ተብሎ እና ታቅዶ እንደሆነ መጠርጠር አንችልም። የወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ከተገለጸባቸው በርካታ ማስረጃዎች እነኚህ ጥቂቶች ናቸውና። መለስ ዜናዊ በጸረ ደርግ ትግል ወቅት ከግብጽ ከፍተኛ የገንዘብና መሳሪያ ድጋፍ ያገኝ እንደነበር በዚህም ውለታ ምክንያት አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ በመጀመሪያ እንዲፈርሱ ከተደረጉት መንግሥት መስሪያቤቶች አንዱ ውሃ ልማት እንደሆነና በተለይ በራሱ በአባይ እና በተፋሰሶቹ ላይ ለአመታት የተደረጉትን የጥናት ስራዎች በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስቴር በነበረው ታምራት ላይኔ ትዕዛዝ ከውሃ ልማት መዝገብ ቤት በወታደራዊ የጭነት መኪናዎች ተጭነው እንደወጡና የት እንደደረሱ አንደማይታወቅ የአይን አማኞች አሉ። ከአንድ ሺ በላይ ከተባረሩት እነዚያ የውሃ ልማት ሰራተኞች ውስጥ ለረጅም ጊዜ በአባይ ተፋሰስ ላይ የሰሩ መሃንዲሶች፤ ሃይዲሮሎጂስቶች፤ የመስኖ ልማት ባለሙያዎች ሲገኙ ከፊሎቹ ዛሬ በስደት አለም ይገኛሉ።ከአገር የመውጣቱ ዕድል ያልገጠማቸው ከፊሎቹ ደግሞ ከሙያው ርቀው እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር በተለያየ የሥራ መስክ ተሰማርተው ይገኛሉ። ይህንን የመሰለ ወንጀል በአገሪቱ ላይ የፈጸሙት መለስ እና ጋሻ ጃግሬዎቹ የህዝብ ብሶት ተጠራቅሞ ከስልጣን ሊጠራርጋቸው ሲቃረብ ዘዴ ዘየዱና ከማንም የውጪ ሃይል ብድር ወይም እርዳታ ሳይገኝ አባይን የሚያክል ግዙፍ ግድብ እንገድባለንና ለ5 አመት ታገሰን ብቻ ሳይሆን ገንዘብ አዋጣ ማለትም ጀምረዋል። ከአመታዊ የአገሪቱ በጄት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ከውጪ በሚገኘው እርዳታና ብድር የሚሸፍን አገዛዝ እንዴት አድርጎ ነው 80 ቢሊዮን የሚያወጣ ግዙፍ ፕሮጄክት በራሱ የሚሰራው ? አይነጋ መስሎአት አሉ?

አባይን መገደብ መቻል ወያኔ ለማጨናበር እንደሚያወራው የኤለክትሪክ ፍጆታችንን ለመርካት ብቻ ሳይሆን በየአመቱ በረሃብ አለንጋ እንደቅጠል የሚረግፈውንም ህዝባችንን በመስኖ ልማት ለመታደግ ብሎም የአገራችንን ጉስቁልና ለመቀየር ትልቅ ትርጉም ያለው የልማት ሥራ ነው። በአገር ፍቅር ስሜት እና በአርበኝነታቸው የማይታሙት የቀደሙት መንግሥታት ሳይቀሩ ይህንን ሲያልሙ ኖረው እንዳለፉ እናውቃለን። በ19ውና 20ኛ ክፍለዘመን አገራችንን ለመቀራመት ያሰፍስፉ ከነበሩት የአውሮጳ ቅኝ ገዢዎች አገራቸውን ሲከላከሉ ለኖሩ አያት ቅድም አያቶቻችንና በነርሱ ዘመን ለነበሩት መንግሥታት ያልተቻለው አባይን የመገደብ ዕቅድ ወላጆቻቸው በጣሊያን ዘመን ለፋሽስቶች ዕንቁላል ሲያቀብሉ በኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጸረ አገር ስሜት ምክንያት ዛሬም ብሄራዊ መግባባት በአገራችን እንዳይፈጠርና የተፈጥሮ ሃብታችን ተጠቃሚ እንዳንሆን ወንጀል እየተሰራብን ነው።

ባንዳው መለስ ዜናዊና በዙሪያው የተሽኮለኮሉት የወያኔ ቁንጮዎች ወደ አስራ አራት በሚጠጋ የሰሜን አሜሪካ እና የአውሮፓ ከተሞች ያሰማሩዋቸው የአባይ ግድብ ዕቅድ ዜና ምስራች አብሳሪዎች ተልዕኮ የከሸፈውና ለአባይ ግድብ ቦንድ ሺያጭ ዘመቻ የተደናቀፈው በለላ ምክንያት ሳይሆን ወያኔን ለማመን የማይቻል በመሆኑ ብቻ ነው። ይህንን ግዙፍ የልማት ግንባታ ስብሰባ ለማካሄድ በህዝብ ገንዘብ በተከራዩ አውቶብሶች ከያሉበት ተለቅመው የስብሰባውን አዳራሽ ለማድመቅ የተገኙ የትግራይ ወንድሞቻችንም ሆኑ ለወያኔ አጎንብሰው ባገኙት የከተማ ቦታ ከ124 ካሬ ሜትር ባልበለጠ ቦታ ላይ ለሰሩት ቤት የንበረት ባለቤትነት ያስጠበቁ መስሎአቸው ወያኔ በየአገሩ ባሉት ኤምባሲዎቹ አማካይነት ለሚያደርገው ስብሰባ የሚያጅቡ የሌሎች ብሄረሰቦች ወንድሞቻችን ማወቅ የሚኖርባቸው ሃቅ የ ኢትዮጵያዊነት ስሜት ዘልቆ ያልገባቸው ይልቁንም ኢትዮጵያን ለማፍረስ “የአክሱም ሃውልት ለወላይታ ምኑ ነው” ሲሉን የነበሩት መለስ ዜናዊና ጄሌዎቹ ከስልጣን እስካልወረዱ ድረስ መልካም እቅዶች ሁሉ የተስፋ እንጀራዎች ከመሆን የዘለሉ አለመሆናቸውን ነው። ስለዚህ አገራችንን ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ለማውጣትና እርስ በርሳችን በዘር ተከፋፍለን እንድንተላለቅ መለስ ዜናዊ ካዘጋጀልን ወጥመድ ለማምለጥ ከሁሉም አስቀድመን የርሱን ዘረኛ አገዛዝ በተባበረ ትግል ለመጣል በህብረት መነሳት ይኖርብናል። ይህ አባይን በአስተማማኝነት ለመገንባት የሚያስችለውንም ሃይል ይፈጥራል።

ጆሮ ያለው ሁሉ ይስማ !!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ