ወያኔ ኢሳትን ከአየር ለማውረድ ከፍተኛ የሆነ ዘመቻ ላይ እንደሚገኝ የግንቦት 7 ምንጮች ገለጹ

ነጻ የሆነ የመረጃ ፍሰትን በመቆጣጠር የአገዛዝ ዕድሜውን ለማራዘም እየባዘነ ያለው ዘረኛው የወያኔ ሥርዓት የሰሜን አፍሪካ ህዝባዊ አብዮት በአገራችን ውስጥ የፈጠረውን ህዝባዊ መነሳሳት በመፍራት ኢሳትን ከአየር ለማውረድ  ይቻለው ዘንድ የገንዘብ ፤ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሃይል ሊያስገኝ በሚችለው አቅም ሁሉ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ለወያኔ ቅርበት ያላቸው የግንቦት 7 ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ።

በከፍተኛ ብሶትና ጭንቀት ውስጥ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደብቸኛ የመረጃ ምንጭ እያገለገለ ያለው ኢሳት ወያኔ የተዘፈቀበትን ሙስና ፤የሃብት ዘረፋና  የሥልጣን ብልግና እየተከታተለ በማጋለጥ ሥራ ላይ ከመጠመዱም በላይ  የመለስ ዜናዊ ሚስት የሆነቺው አዜብ መስፍን በዱባይ እና የፓሪስ ውድ ሸቀጣሸቀጥ መደብሮች እየበተነች ያለቺውን የአገሪቱን ሃብት ለህዝብ አይንና ጆሮ በማድረሱ መለስ እና ግብረአበሮቹ ሊወጡ በማይችሉት ቅለት ውስጥ እንደከተታቸው ይህም አገዛዙን ክፉኛ እንዳስቆጣ የመረጃ ምንጮቻችን ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ “በቀላሉ ልንመክተው የማንችለው ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሚያስከፍለው ዋጋ ሁሉ ተከፍሎ ኢሳት በአስቸኳይ ከአየር መውረድ አለበት የሚል ትዕዛዝ በቀጥታ ከመለስ ዜናዊ መሰጠቱንና ተግባራዊ እንቅስቃሴም እንደተጀመረ አክለው አጋልጠዋል።

ከአሁን ቀደም ኢሳትን ከአየር ለማውረድ ከአረብሳት ጋር የጥቅም መመሳጠር ተፈጥሮ ነበር ያሉት ምንጮቻችን ለሶስት ወራት ያህል የኢሳትን ስርጪት ያስተላልፍ የነበረው ታይኮም የተባለው የሳታላይት ካምፓኒም በተደረገበት ክፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫናና ይህ ነው ተብሎ በትክክል ለመግለጽ በሚያዳግት የተለያየ መደለያ የስርጭት አገልግሎቱን እዳቋረጠ ማወቃቸውን ገልጸዋል። የዝግጅት ክፍላችን የደረሰውን መረጃ አስመልክቶ የኢሳት ማነጅመንት አስተያየት እንዲሰጥ ተጠይቆ “ወያኔ እያደረገው ያለው ኢሳትን በተቻለ ፍጥነት ከአየር የማጥፋት ጥረት አሁን የተጀመረ አዲስ ክስተት እንዳልሆነ እናውቃለን; ።

ቀደም ሲል በአረብ ሳት እናስተላልፍ በነበርንበት ወቅት በውድ ዋጋ ከቻይና ተገዝቶ ሰሜን ኢትዮጵያ  በተተከለ የሳተላይት መጥለፊያ መሳሪያ ይመቱት እንደነበረ መረጃ ነበረን ከዚያም ቦኋላ ታይኮም ላይ የነበረንን ስርጭት በዚያ መሳሪያ ለመምታት ተሞክሮ ባለመሳካቱ የቻይና ኤክስፔርቶች ጭምር ያሉበት አንድ ኮሚቴ በመለስ ዜናዊ ት ዕዛዝ ተቋቁሞ መፍትሄ ስላላስገኘ በሌላ መንገድ ካምፓኒው አግልግሎት መስጠቱን እንዲያቋርጥ አስደርገውታል ። ከዚያ ልምድ ባገኘነው ልምድ በማንኛውም ጊዜ ተመሳሳይ የሆነ ጥቃት ሊፈጸምብን ይችላል በሚል የተለያዩ አማራጮችን ታሳቢ በማድረግ እየተንቀሳቀስን ነው፤ ገንዘባችንን ይጭነቀው እንጂ እስከመጨረሻዋ የነጻነት ቀን ድረስ ገንዘብ የሚለግሱን እውነተኛ ኢትዮጵያዊያን እስካሉ ድረስ ጥቃቱን በመመከት በአጭር ጊዜ ወደ አየር ልንመለስ የምንችልበትን አቅም እያጎለበትን ነው” ብለዋል። በአገር ቤት ያሉ አድማጮቻችንም ይህንን አውቀው እንዲዘጋጁ መል ዕክት ማስተላለፍ ጀምረናል በማለት በወያኔ ግፊት ኢንቴል ሳት አገልግሎት ካቋረጠ በሌላ መንገድ ወደ አየር የመመለሱን እድል መኖር ገልጾልናል። አድማጮቻችን የግንቦት 7 ድምጽ በኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት እንዲኖር የሚንናፍቅ ሁሉ ኢሳትን በገንዘብ የመርዳት ጊዜው አሁን መሆኑን ያሳስባል።