የህዳሴ ግድብ የተባለው የወያኔ መፎከሪያ ለመስኖ አገልግሎት እንደማይውል ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጸ

የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በምክትል ጠቅላይ ምንስትርነትና የውጪ ጉዳይ ምንስትርነት ለይስሙላ የሾመው ሃይለማሪያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የህዳሴ ግድብ በፍጹም ለመስኖ አገልግሎት አይውልም ፣ በዚህም ምክንያት ግብጽ ምንም አይነት ጥርጣሬ ሊገባት አይገባም ማለቱ ብዙዎችን የሥርዓቱን ደጋፊዎች ማሳዘኑን ለማወቅ ተችሎአል።

በአንድ ወር ሁለት ስም የተሰጠው የአባይ ግድብ ግንባታ ከውጥኑ ጀምሮ ምንም አይነት ጥናት እና ዝግጅት ያልተደረገበት ሌላው ቀርቶ በራሱ የወያኔ የአምስት አመት የልማትና የእድገት ትራንስፎርመሽን እቅድ ውስጥ ያልተካተተ በመሆኑ ቀድሞውኑ በርካቶች ትክክለኝነቱን ሲጠራጠሩት የቆዩ ቢሆንም በአገዛዙ ቁንጮዋች በየእለቱ የሚሰጡ እርስ በርሳቸው የተምታቱ ገለጻዎች በየዋህነት ስለግድቡ አምነው የነበሩትን እያስከፋ መምጣቱን ለወያኔ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።

 ሃይለማሪያም ደሳለኝ ይሰራል በተባለው የአባይ ግድብ ላይ ምንም መስኖ የመጠቀም እቅድ እንደሌለ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡን ስማቸው እንደይገለጽ የጠየቁ አንድ የአካባቢ ሳይንስ ምሁር፣ እንደገለጹት የአባይ ታላቅ ግድብ ተብሎ ተሰይሞና፣ የግድቡ የውሃ ክምቺትም የጣና ሃይቅን እጥፍ ይሆናል እየተባለ የተወራለት ግድብ፣ በምንም አይነት መልኩ ለመስኖ አገልግሎት አይውልም መባሉ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በየአመቱ በረሃብ አለንጋ ለሚቀጠፈው ኢትዮጵያዊያ ህይወትና አገራችን ለምትታወቅበት ረሃብተኝነት ምንም ቅንጣት እንደሌለው የሚያሳይ ፣ እውነት አባይን መገደብ ብንችል ስለግድብ ሙያዊ እውቀት ላላቸው ምሁራን ያለውን ከፍተኛ የሆነ ንቀት የሚያሳይ ነው ብለዋል።፡ በመቀጠልም በመሰረቱ ኢትዮጵያ ከድህነትና ረህብ አረንቁአ እንድትወጣ ከተፈለገ ሃገሪቱ ያላትን የውሃ ሃብት ለኤሌክትሪክ ሃይል እየተጠቀምች ጎን ለጎን ለመስኖ ልማት መጠቀም የማትችልበት ምክንያት ፈጽሞ ሊኖር አይችልም ብለዋል። ዳሩ ግን ወያኔ የአገር ጥቅም ያስጠብቃል ተብሎ ስለማይታሰብ ፤ ያለፈው የ20 አመት ታሪኩም የሚያሳየው ለም የአገሪቱን መሬት ለባ ዕድ አገር ባለሃብቶች አሳልፎ ሲሸጥ፤ በድንበር አካባቢ ያለውን ወሰን መሬት እንደገና ዳቦ ለጠየቀው ሁሉ የሚሰጥ ሃይል ስለሆነ ከአሁን ቦኋላ ተሃዲሶ አድርጎ ይለወጣል የሚል ተስፋ ማናችንም የለንም ብለዋል።

 ይህ በ እንዲህ እንዳለ በደቡብና በደቡብ ምሥራቅ የአገራችን አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ሣቢያ የምግብ እርዳታ ፈላጊው 3 ነጥብ 2 ሚሊየን እንደደረሰ ፤ ቀደም ሲል የዓለም የምግብ ፕሮግራም እርዳታ እያደረገላቸው ያለውን ተረጂዎች ስጨምር በዚህ ዓመት አጠቃላዩ ተረጂ ቁጥር 4 ነጥብ 3 ሚሊየን መሆኑን የዓለም የምግብ ፕሮግራም ማስታወቁን ቪ ኦ ኤ ከትናንት በስቲያ ባወጣው ዘገባ ላይ ገልጾአል፡፡ እንደ ቪ ኦ ኤ ዘገባ የዘንድሮው ድርቅ መንስዔ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆየው የክረምት ዝናብ አንድም አነስተኛ መሆኑ፣ አልያም አሁንም በድርቅ በተጠቁት አካባቢዎች ከመደበኛው በታች የዓለም የምግብ ፕሮግራም ቃል አቀባይ መግለጻቸውና በዘንድሮው ድርቅ የተጠቁት አካባቢዎች ፈጥነው ያገግማሉ ብለው እንደማይጠብቁና ከዚህም ጋር ተያይዞ ሰብዓዊ እርዳታና የምግብ አቅርቦት የሚፈልገው ሰው ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ታውቁአል፡፡

ህዝብ በየአመቱ ለእንዲህ አይነት አስከፊ ረሃብ አደጋ በሚጋለጥበት አገር ስልጣን ላይ ያለው መለስ ዜናዊና ጥቂት ግብረአበሮቹ ከ8 ነጥብ 5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ዘርፈው በህገ ወጥ መንገድ ከአገር እንዳሸሹ ዩ ኤን ዲፒ የተባለው የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት አስታውቆአል።